በወንጀል ጉዲይ መነሻ ቅጣቱ በቅጣት መመሪያው ውስጥ በተለያዩ እርከኖች የሚወድቅ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ፍ/ቤቱ ዝቅተኛውን እርከን መምረጥ ያለበት ስለመሆኑ፣ የቅጣት መመሪያ 2/2006 አንቀጽ 19/11/
No summary available.
ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ተኸሉት ይመስል አመልካች፡- ሀብቱ ቱለ ዲዱ -ጠበቃ በቃለ ያለው ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የፍደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን - ዐ/ህግ ዋልተንጉስ ፍቅሬ ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የወንጀል ነው። ክርክሩ የጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረበው ክስ መነሻ ሲሆን የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ በመዝገብ በአመልካች ላይ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ይግባኝ ሰሚው ችልት የስር ፍርድ ቤትን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በመዝገብ ሰኔ 18 ቀን 2006 ዓ.ም አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የበታች ፍርድ ቤቶች በአምስተኛ ክስ ላይ የሰጡትን የጥፊተኝነት ውሳኔ እና በሁለም ክሶች ላይ ደግሞ የቅጣት አሰላልን በተመለከተ ተፈፃሚነት ያለውን መመሪያ ለይቶ ለማሳረም ነው።
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች ከላልች አምስት ሰዎች ጋር ክስ የቀረበባቸው ሲሆን በአሁኑ አመልካች ላይ የቀረበው ክስ በአራት ምድብ የተከፈለ ነው።
ተጠሪ ያቀረበው 1ኛ ክስ ይዘት፡- አመልካችን ጨምሮ የስር 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1(ሀ)((ለ)) እና አንቀፅ 379 ንዐስ አንቀፅ 1/ሀ/ የተደነገገውን በመተላለፍ የመንግስት ሰነድ አሰመስል የማዘጋጀትና መገልገል የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል የሚል ነው። 2ኛው ክስ ደግሞ አመልካችና የስር 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1(ሀ)(ለ)) እና 696(ሀ) ስር የተደገገውን በመተላለፍ የከባድ አታላይነት ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው። 3ኛው ክስ ደግሞ የአሁኑን አመልካች ጨምሮ የስር 1ኛ፣4ኛ፣5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1(ሀ) (ለ)) እና 379(1(ሀ)) ስር የተደገገውን በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት አስበው ሐሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀትና መገልገል የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው። 4ኛ ክስ ደግሞ አመልካች ከስር 1ኛ፣4ኛ፣5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ጋር ሁነው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1(ሀ)(ለ) እና 696(ሀ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከባድ የአታላይነት ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው። በአመልካች ላይ ብቻ የቀረበውና የመጨረሻው ክስ በተራ ቁጥር አምስት የተጠቀሰው ሲሆን ይዘቱም፡- አመልካቹ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1(ሀ)(ለ)) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት እና ለላላ ሰው ለማስገኘት አስቦ በአዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እ.ኤ.አ ኦገስት 23 ቀን 2005 በፏርሶኔል ማኔጅመንት በመጀመሪያ ዱግሪ መመረቁን የሚገልፅ ሀሰተኛ ጊዜያዊ ዱፕልማ እና ደጀኔ ተሉላ አሉ የተባለ ግለሰብ በአዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖልጂ ፊኩሉቲ በመካኒካል ኢንጂነሪንግ እ.ኤ.አ ጁላይ 24 ቀን 2004 ዓ/ም በአድቫንስድ ዱፕልማ መመረቁን የሚገልፅ ሀሰተኛ ጊዜያዊ የምረቃ የምስክር ወረቀት ተመሳስል የተሰራ ሐሰተኛ የዩኒቨርሲቲውን ማህተም በመጠቀምና የኃላፉዎችን ፊርማ አስመስል በመፈረም አዘጋጅቶ ካስቀመጠበት በቦላ ክፍለ ከተማ ወረዲ 08 ውስጥ በሚገኘው የተከሳሽ መኖሪያ ቤት በ2/06/2003 ዓ/ም በተደረገው ብርበራ የተገኘ መሆኑን በመዘርዝር አመልካቹ ሐሰተኛ ሰነድ የማዘጋጀት የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው።
የሥር ፍርድ ቤትም አመልካች የቀረበባቸውን ክስ እንዱረደት ከአደረገ በኋላ በስርዓቱ መሰረት በቅድመ ክስ ሂደት ግራ ቀኙ እንዱከራከሩ አድርጎ በቅድመ ክስ ጊዜ አመልካች ያቀረቧቸውን መቃወሚያዎችን ውድቅ አድርጎ ጉዲዩን ወደ መደበኛው የክርክር ሂደት በመግባት ክርክሩን መርቷል። ተጠሪ ክሱን ለማስረዲት አለኝ ያላቸውን የሰውና የፅሁፍ ማስረጃዎችን አቅርቧል።
ከዚህም በኋላ አመልካች መከላከያ እንዱያቀርቡ ተደርጎ ማስረጃዎቻቸው ተሰምተዋል። የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማና ከመረመረ በኋላ አመልካች በተጠሪ የክስ ዝርዝር የተገለፁትን ተግባራት መፈጸማቸው በተጠሪ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች የተረጋገጠና በመከላከያ ማስረጃዎችም ያላስተባበለ ናቸው በማለት አመልካች በቀረበቡባቸው አምስት ክሶች ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን በመተላለፍ የሙስና ወንጀል የፈፀመ ጥፊተኛ ናቸው በማለት የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል። ከዚህም በመቀጠል የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብልና በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተሻሽል የወጣውን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት አድርጎ ለወንጀልቹ ደረጃ በመለየትና ለእያንዲንደ የወንጀል ድርጊት የሁለት አመት እስራት መነሻ ቅጣት በማስቀመጥ ለአምስቱም ክሶች ይህንኑ የሁለት አመት እስር ጊዜ ደምሮ መነሻ ቅጣቱን አስር አመት እንደሚሆን ጠቅሶ ይኼው የቅጣት መጠን የሚወድቅበትን የእስራት ቅጣት እና የገንዘብ መቀጮውን እንደየድንጋጌዎቹ ይዘት በመለየት የእስራት ቅጣቱ በእርከን 29፣ የገንዘብ መቀጮው ደግሞ በእርከን 8 ስር እንደሚወድቅ ወስኗል። ከዚህም በኃላ በግራ ቀኙ የቀረቡትን የቅጣት አስተያየቶችን በመመርመር በአመልካች ላይ የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች በተጠሪ በኩል ያለመቅረባቸውን ጠቅሶ በአመልካች በኩል ግን ከዚህ በፉት በወንጀል ተክሰው ተቀጥተው የማያውቁ መሆኑን አመልካች የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆናቸውን የሚያሳዩ ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች መቅረባቸውን ገልጾ በመመሪያ ቁጥር 2/2006 አንቀጽ 23(4) መሰረት እያንዲንደ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ሁለት ሁለት እርከን ሲያስቀንስ የእስራት ቅጣቱ ከእርከን 29 ወደ እርከን 27 እንደሚወርድ፣ የገንዘብ መቀጮው ደግሞ ከእርከን 8 ወደ እርከን 6 እንደሚወርድ ገልፆ በእነዚህ እርከኖች ለፍርድ ቤቱ በተተወው ፍቅድ ስልጣን መሰረት አመልካች በስምንት አመት ከአምስት ወር ፅኑ እስራትና በብር 10,000.00 (አስር ሺህ) የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጡ ወስኗል። አመልካች ይህንን ፍርድ በመቃወም ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም።
አመልካች ሐምል 24 ቀን 2006 ዓ/ም በተፃፈ ሰባት ገፅ የሰበር አቤቱታ በ5ኛ ክስ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 379(1(ሀ)) ተጠቅሶ ጥፊተኛ የተባለት ድንጋጌው ከአድራጎታቸው ጋር ባልተጣጣመበት ሁኔታ መሆኑን፣ የቅጣት ውሳኔውም መመሪያ ቁጥር 1/2002 መሰረት መሰላት ሲገባው የተሻሻለውን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት መደረጉ ያላግባብ መሆኑን፣ በዚህም ምክንያት በእያንዲንደ ሕጋዊ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት መቀነስ የነበረበት የሶስት እርከን ቅጣት ሳይቀነስ የታለፈና በሕግ ፉት እኩል ሁኖ የመታየት መብታቸው የተነካ መሆኑን፣ ለእያንዲንደ ክስ መነሻ ቅጣት ከተለየ በኋላ ድምሩ የሚወድቅባቸው እርከኖችም ሶስት ሁነው እያለ በመመሪያው መሰረት ዝቅተኛው እርከን መያዝ ሲገባው ያላግባብ የታለፈ መሆኑን ዘርዝረው 5ኛ ክስ ስር የተጠቀሰው ድንጋጌ እንዱቀየርና ቅጣቱም አመልካችን በሚጠቅመው የቅጣት አወሳሰን መመሪያና ድንጋጌዎቹ ተሰልቶ እንዱወሰን ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርቦም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም በአመልካች ላይ የተጣለው ቅጣት ተገቢውን የቅጣት አወሳሰን መርሆዎችን መሰረት በማድረግ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
የበታች ፍርድ ቤቶች በአመልካች ላይ የሰጡትን የቅጣት ውሳኔ ተገቢነት ለመመርመር በመሰረታዊ ጭብነት መታየት ያለባቸው ሁነው ያገኘናቸው ነጥቦች፡-
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ፡- የበታች ፍርድ ቤቶች ቅጣቱን የወሰኑት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በማድረግ ነው።
አመልካች ጥፊተኛ ተብል የተቀጣበት የወንጀል ድርጊት የተፈፀመው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ወጥቶ ሥራ ላይ ከመዋለ በፉት መሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሳያል። ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ ያቀረበውም ይህ መመሪያ ስራ ላይ ከመዋለ በፉት ነው። አመልካች ጥፊተኛ ተብል የተቀጣበት ወንጀል ክስ ሲቀርብ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 ወጥቶ ሥራ ላይ ውሎል። በመሆኑም ለወንጀለ ቅርበት ያለውና ተፈፃሚነት የነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 ነበር። በአመልካች ላይ የቅጣት ውሣኔ ሲወሰን ተፈፃሚ የነበረው የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሆኑ አከራካሪ አይደለም። ይህም በአመልካች ላይ የቅጣት ውሳኔ ሉወሰን የሚገባው አመልካች ወንጀለን በፈጸመበትና ተገቢው ክስ በቀረበበት ጊዜ ተፈጻሚነት የነበረውን መመሪያ ቁጥር 1/2002 መሰረት በማድረግ ነው? ወይስ የጥፊተኝነት ውሳኔ ሲወሰን ተፈጻሚነት ያለውን የተሻሻለውን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በማድረግ ነው? የሚለውን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ይህንኑ የሕግ ጥያቄ በተመለከተ ይህ ችልት በወንጀል ጉዲይ ገዥ መርህ ሆኖ ከተደነገገው ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 22 እና የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 6 ድንጋጌ አንጻር በመመርመር ተፈፃሚነት ሉኖረው የሚገባው ተከሳሹን የሚጠቅመው መመሪያ ነው በማለት በሰ/መ/ እና በላልች በርካታ መዛግብት በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በመሆኑም በዚህ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰረት አመልካች ወንጀለን ሲፈጽም ወይም ክስ በቀረበበት ጊዜ ያልነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 በአመልካች ላይ የቅጣት ውሳኔ ሲወስን ተፈጻሚ የሚሆነው ይህ መመሪያ አመልካችን የሚጠቅመው ሆኖ ከተገኘ ብቻ ነው።
ከዚህ አንፃር የተያዘውን ጉዲይ ስንመለከትአመልካች ጥፊተኛ የተባለበትን የወንጀል ድርጊት ሲፈጽም ያልነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 አመልካች በወንጀለ ድርጊት ሲከሰሱ ስራ ላይ ከነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 በቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች እርከን አቀናነስ ላይ ከመመሪያ ቁጥር 1/2002 በተሻለ ሁኔታ የአመልካችን መብት የሚያስከብር አይደለም። ስለዚህ የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ችልት የቅጣት ውሳኔ ውሳኔውን የተሻሻለውን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት በማድረግ መወሰናቸው ከላይ የገለጽነውን የሕገ መንግስት ድንጋጌዎች ይህ ሰበር ችልት በሰበር መዝገብ ግንቦት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠውን አስገዲጅ ትርጉም ያልተከተለ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያትም በጉዲዩ ተፈጻሚነት ሉኖረው የሚገባው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 ነው።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡- የስር ፍርድ ቤት አመልካችን በአምስት ክሶች ጥፊተኛ ከአደረጋቸው በኃላ የወንጀልቹነ ደረጃ በመለየት ለእያንዲንደ ክስ የሁለት አመት እስራት በመነሻነት ይዞ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 184(1(ለ)) መሰረት ደምሮ አስር አመትን በመነሻነት የያዘ ሲሆን ይህ የመነሻ ቅጣት የሚያፍርበት እርከን 29 መሆኑን ለይቶ አስቀምጧል። ሆኖም አስር አመት መነሻ ቅጣት በመመሪያ ቁጥር 1/2002ም ሆነ በመመሪያ ቁጥር 2/2006 በሶስት ተከታታይ እርከኖች ያለ ሲሆን እንዱህ በሆነ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ዝቅተኛ እርከንን እንደሚይዝ በመመሪ ቁጥር 1/2002 አንቀጽ 13(9)፣ በመመሪያ ቁጥር 2/2006 ደግሞ በአንቀጽ 19(11) ድንጋጌ ስር ተመልክቷል። ሁለቱም መመሪያዎች በዚህ ረገድ ልዩነት የላለባቸው በመሆኑ በአመልካች መብት አከባበር ላይ የሚያስከትለት ችግር የለም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት አመልካች ጥፈተኛ የተባለባቸው ድንጋጌዎች ድምር ቅጣት መነሻው የሚወድቅበትን እርከን ይህንኑ መሰረት አድርጎ መያዝ ሲገባው ከፍተኛ እርከን መያዙ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት የአምስቱ ክሶች ድምር የሆነው የአስር አመት ጽኑ እስራት የሚወድቅበት እርከን 27 ተደርጎ መያዝ ያለበት ሁኖ አግኝተናል።
ሶስተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡- በቅጣት ማቅለያ አያያዝ ረገድ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ስንመለከትም አመልካች ሪኮርድ የላለባቸው መሆኑ፣ የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆናቸውን የሚያሳዩትን ነጥቦች በሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያትነት ይዞላቸዋል። ከዚህ አንጻር ጉዲዩን ስንመለከተው አመልካች የቅጣት ማክበጃ ምክንያት ያልቀረበባቸው ሲሆን ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ተይዞላቸው ድርጊቱ ከተፈፀመበትና ክሱ ከቀረበበት ጊዜያት አንፃር ሲታይ በመመሪያ ቁጥር 1/2002 አንቀጽ 16(7) ድንጋጌ መሰረት እያንዲንደ የቅጣት ማቅለያ ሶስት ሶስት እርከን የሚያስቀንስ በመሆኑ በድምሩ ስድስት እርከን መቀነስ ስለአለበት ከእርከን 27 ወደ እርከን 21 መውረድንና በዚህ እርከን ውስጥ ተገቢውን ቅጣት መወሰን የሚጠይቅ ነው። በእርከን 21 ስር የፍርድ ቤቱ ፍቅድ ስልጣን ደግሞ ከአምስት አመት እስከ ስድስት አመት ነው።
ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች መሰረት ቅጣቱን ስናሰላው አመልካችን ያርማል፣ላልች መሰል አጥፉዎችን ከወዱሁ ሉያስጠነቅቅ ይችላል ብለን የገመትነው የቅጣት መጠን በእርከን 21 ስር በአምስት አመት ጽኑ እስራት ሁኖ አግኝተናል።
ሲጠቃለልም ከላይ በዝርዝር በተመለከቱት ህጋዊ ምክንያቶች የበታች ፍርድ ቤቶች የጥፊተኝነት ውሳኔ ተገቢ ቢሆንም የቅጣት ውሳኔው ግን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 01 እና መጋቢት 09 ቀን 2006 ዓ/ም የተሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ፣ ይህንኑ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በማጽናት የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሰኔ 18 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ//ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 195 (2)(ለ-2) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች በአምስቱም ክሶች ጥፊተኛ መባላቸው በአግባቡ ነው ብለናል።
ለእነዚህ ወንጀልች ቅጣቱን በተመለከተ ግን አመልካች ሉቀጡ የሚገባው በ5 (አምስት) አመት ጽኑ እስራት ነው ብለናል። የበታች ፍርድ ቤቶች ገንዘብ መቀጮ ውሳኔ አልተነካም።
በአመልካች ላይ የተሰጠው የእስራት ቅጣት ውሳኔ የተሻሻለ መሆኑን አውቆ አመልካች በጉዲዩ ላይ የታሰሩት ማናቸውም ጊዜ ታስቦላቸው በዚህ ችልት በተወሰነባቸው የቅጣት መጠን መሰረት ተከታትል እንዱያስፈፅም ለክፍለ ማረሚያ ቤት ትዕዛዝ ይድረስ ብለናል።ይጻፍ።