አንድ ፍርድ ቤት የጥፊተኝነት ውሳኔ ከተሰጠበት የህግ ድንጋጌ ስር ከተቀመጠው የቅጣት አማራጭ ውጪ የሚሰጠው የቅጣት ውሳኔ የሕግ መሰረት የላለው አቶ ጎሹ ዮሐንስ እና የፋ.የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዐ/ህግ
No summary available.
ቀን ሰኔ 17/2007 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ሙስጠፊ አህመድ ተኸሉት ይመሰል አመልካች፡- ጎሹ ዮሐንስ ገብሩ ጠበቃ ወንድ ይፍራው አረፈ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል የሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓ/ሕግ የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ በስልጣን አለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል የሚመለከት ሆኖ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁኑ ተጠሪ ከሳሽነት ነው። በሥር ፍርድ ቤት በዚህ ጉዲይ ተከራካሪ ያልሆኑትን ጨምሮ በሦስት ግለሰቦች ላይ የቀረበው ክስ 1ኛ ተከሳሽ አደምኑር ፣2ኛ ተከሳሽ አዲነ ይርዲው 3ኛ ተከሳሽ የአሁኑ አመልካች በመሆን ነው ። የአሁኑ አመልካች በሥር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ጉዲይ ነው።
የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች እና በዚህ ጉዲይ ተከራካሪ ያልሆኑ ግለሰቦች ሁለት ክስ ያቀረበ ሲሆን የመጀመሪያው ክስ በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በነበሩት አደም ኑር ገበያው እና አዲነ ይርዲው የቀረበ ነው ። የክሱ አጭር ይዘትም ፡- በ 1997ዓ.ም የወጣው የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) (ለ) እና 379(1)(ሀ)እና (ለ) የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ በመንግስት ንብረት ላይ ጉዲት ለማድረስ እና ለራሳቸው የማይገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ 1ኛ ተከሳሽ በግብርና ምርት ላኪነት የተሰማራ ባለሀብት /ኢንቨስተር /2ኛ ተከሳሽ ደግሞ ወኪል መስለው የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት ለመቅረብ እና ከድርጅቱ በርካታ ኩንታል ማዲበሪዎች ለመውሰድ ያመቻቸው ዘንድ በሀሰት የተዘጋጀ በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሰሉቨን ወረዲ መሬት ለማልማት የተደረገ የመሬት ኪራይ ውልና ተዛማጅ ደብዲቤ ፣በንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር እንደተሰጠ ተደረገው ተመሳስለው የተሰሩ የንግድ ፈቃድች በአማራ ክልል መንግስት እንደተሰጠ ተደርጎ ተመሳስል የተሰራ የኢንቨስትመንት ፈቃድና የውክልና ማስረጃ እንዱሁም ትክክለኛው ከባንክ ገቢ የተደረገው የገንዘብ መጠን 914.55 ሆኖ እያለ ብር 914,355.00 ያክል ገንዘብ እንዲለው የሚገልጽ ሀሰተኛ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ.እና ላልች ሰነድች በመያዝ ሰኔ 23 ቀን 2001 እና በተከታዮች ቀናት በግብርና ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት በመቅረብ ገቢ በማድረግ አላግባብ የተጠቀሙና በ2ኛ ክስ የተመለከተውን የመንግስት ንብረት ሐምል 03 ቀን 2001 ዓ.ም በመወሰዲቸው ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት በፈጸሙት በሀሰተኛ ሰነድም መገልገል የሙስና ወንጀል እንደተከሰሱ፤
ሁለተኛው ክስ በሁለም ተከሳሾች የቀረበ ሲሆን ዋና ይዘቱ ፡- በ1997 ዓ.ም የወጣው የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ) (ለ) 33 እና 407(1)(ሀ)(ለ)እና (2) የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ 3ኛ ተከሳሽ(የአሁኑ አመልካች) በ1ኛ ክስ በተመለከቱት ቀናት የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት የድርጅቱ የሽያጭና ገበያ ጥናት ዋና ክፍል ኃላፉ ሆኖ በሚሰራበት ወቅት ለራሱ እና ለላልች ተከሳሾች የማይገባ ጥቅም ለማግኘት እንዱሁም ለማስገኘት እና በመንግስት ጥቅም ላይ ጉዲት ለማድረስ በማሰብ፡ሀ. 2ኛ ተከሳሹ ከ1ኛ ተከሳሽ የሚገለገልበትን በርካታ ሰነድች ይዞ በማዲበሪያ ግዥ ሲጠየቅ በመመሪያ መሰረት 3ኛ ተከሳሽ እንደ ኃላፉነታቸው ከዋናው ጋር ማመሣከር ሲገባቸው ይህንኑ ባለማድረጋቸው የማዲበሪያ ግዥ ጥያቄውን በስሙ በቀጥታ ያቀረበው 2ኛ ተከሳሽ ሆኖ እያለ ይኸው ተከሳሽ የ1ኛ ተከሳሽ የፈጠራ ድርጀት /አደም ኑር ገበያው ኃ/የተ/የግ/ማህበር /ንብረት መስለው የቀረቡትን በ1ኛ ክስ የተመለከቱትን ሐሰተኛ ሰነድች ይዞ ሲቀርብ 3ኛ ተከሳሽ የዋጋ ማሣወቂያ ከመፍቀዲቸው በፉት የራሱ ሰነድች መሆናቸውን ሳያረጋግጡ ላላመለከተ (ግዥ ላልጠየቀ) አካል ከመመሪያው ውጭ መፍቀዲቸው ፡- 2ኛ ተከሳሽ የ1ኛ ተከሳሽ ወኪል ናቸው ቢባል እንኳ የተያዘው የውክልና ማስረጃ የወካይ ስምና ፊርማ ያልተሟላና ለዚህ በቂ አለመሆኑ እየታወቀ እንዱታረምና በመመሪያው መሰረት የውክልና ደብዲቤ እንዱቀርብና የግዥ መጠየቂያ ማመልከቻው እንዱስተካከል አለ ማድረጋቸው እንዱሁም በቀን 02/11/2000 ዓ.ም በቁጥር 89/008-12/00 ከዋናው መሥርያ ቤት ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በአድራሻ እና ለንግድ መመሪያ በግልባጭ የተፃፈው የማዲበሪያ ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ ለሰፊፉ የግል እርሻዎች የሚፈቀደው የማዲበሪያ የሽያጭ መጠን ለአንድ ሄክታር መሬት አንድ ኩንታል ዲፕና አንድ ኩንታል ዮሪያ በጠቅላላው ከ 500 ኩንታል ሣይበልጥ የሚሸጥ መሆኑ እየገለጹ ተከሳሽ ከመመሪያው ውጭ 3,000 ኩንታል ማዲበሪያ በመፍቀደ፤
ለ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾችም በመግቢያው ላይ በተጠቀሰው የወንጀል ሐሳብ በመነሳት ከ3ኛ ተከሳሽ በመመሣጠርና በመንግስትና በህዝብ ሐብት ላይ ጉዲት ለማድረስ አስበው የመንግስት የልማት ድርጅት የሽያጭ ህጋዊ አሰራሮችና መመሪያዎች እንዱጣሱ በማድረግ ባለሀብትና ወኪል በመምሰል በ1ኛ ክስ የተገለጹትን ሐሰተኛ ሰነድች ይዘው በመቅረብ ግምቱ ብር 913,440.45 የሆነ ማዲበሪያ ከተጠቃሹ የመንግስት የልማት ድርጅት ላይ ወስደዋል ።
በመሆኑም ተከሳሾቹ የሽያጭና የአሰራር መመሪያዎች በአግባብ ከማከናውን በመታቀብ እና እርስ በርስ የጥቅም ተከፊይ ለመሆን በመመሳጠር በዋና ወንጀል አድራጊነት ተሳታፉ በመሆን ድርጊቱን በመፈፀማቸው በስልጣን ያለ አግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው።
በሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች (አመልካች) ቀርበው በጉዲዩ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበው በተሰጠው ብይን እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ሁለቱም ክሶች ተነጣጥለው እነዱታዩ ትዕዛዝ ተሰጥቷል ። አንደኛ ተከሳሽ ጥሪ ተደርጎለት ባለመቅረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ታዟል ። 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች (አመልካች ) ክሱን ክደው በመከራከራቸው የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች ተሰምቷል ። 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾችም የበኩላቸው የመከላከያ ማስረጃ አቅርበዋል ። የሥር ፍርድ ቤትም የግራቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ 2ኛ ተከሳሽ የነበረው በተመለከተ የዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በሁለቱም ክሶች የተጠቀሱትን ፍሬ ነገሮች የፈፀመ ስለመሆኑ መስክሯል ። የ2ኛ ተከሳሽ የመከላከያ ማስረጃ ያስረደት ፍሬ ነገር ተከሳሹ የድለላ ሥራ የሚሰራ ስለመሆኑ እንጂ ለተከሰሰበት ጉዲይ ባስያዘው ጭብጥ መሰረት ድርጊት ያልፈጸመ ስለመሆኑ የመሰከሩት ነገር የለም ። 2ኛ ተከሳሽ በሰነድ ማስረጃነት የቆጠረው በአንደኛ ተከሳሽ ለ2ኛ ተከሳሽ ተሰጠ የተባለውን የውክልና ማስረጃ የወካይ ስምና ፊርማ የላለው ስለመሆኑ ለግብርና ምርት ማሣደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት የፃፈው ማመልከቻም በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ጉዲዩ ለማስፈጸም የተዋዋለበት ሰነድ የዓቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ የሚያጠናክሩ ናቸው ከሚያሰብል በስተቀር የዓቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ተከላክሎል የሚያስብለ አይደለም ። ስለሆነም በቀረበበት 1ኛ ክስ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ)(ለ) እና 379(1)(ሀ) በ2ኛ ክስ የወ/ሕ/ቁ.
32(1)(ሀ)(ለ)፤33 እና 407(1) (ሀ)(2)በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.113(2) መሰረት አንቀጽን በመቀየር በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1) (ሀ)(ለ) እና 407(1)(ሀ) በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.149(1)መሰረት ጥፊተኛ ነው ተብሎል።
የአሁኑ አመልካች (3ኛ ተከሳሽ) በተመለከተም የዓቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ እንዱከለከለ በተሰጠው ብይን መሰረት በድርጅቱ የሚወጡ የማዲበሪያ ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ ወሰን በተመለከተ በዓቃቤ ሕግ ክስ የተጠቀሰው መመሪያ ተፈፃሚነት ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አንጂ ለዋናው መ/ቤት ተከሳሽ ለሚሰሩበት ለሽያጭና ገበያ ጥናት ዋና ክፍል አለመሆኑን በዝርዝር ያስረደና በክሱ የተጠቀሰው የማዲበሪያ ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ በአድራሻ የተፃፈው ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በመሆኑ 3ኛ ተከሳሽ በኃላፉነት ተመድበው ለሚሰሩበት የሽያጭና የገበያ ጥናት ዋና ክፍል በዓቃቤ ሕግ የክስ ማመልከቻ የተጠቀሰውና በድርጅቱ ሐምል 02 ቀን 2000 ዓ.ም ተላለፈ የተባለው መመሪያ ከወጣ በኃላ ሚያዝያ 19 ቀን 2001 ዓ.ም ተከሳሹ በኃላፉነት ተመድበው ለሚሰሩበት ለሽያጭና ገበያ ጥናት ዋና ክፍል በአድራሻ የተላለፈው የማዲበሪያ ሽያጭ መመሪያ በተሰጣቸው ስልጣን መጠኑ እስከ 10,000 ኩንታል የሚደርስ የማዲበሪያ ሽያጭ ለግል ስፊፉ የእርሻ ልማት ባለሃብት መፍቀድ እንደሚችለ ሥልጣን የተሰጣቸው ለመሆኑ የሚያረጋግጥ የመከላከያ የሰነድ ማስረጃ የቀረበ ሲሆን ይህም ተከሳሽ በዓቃቤ ሕግ ከመመሪያ ውጭ የማዲበሪያ ግዥ ፈቅደዋል በሚል የተጠቀሰባቸው የክስ ፍሬ ነገር በተመለከተ በመከላከያ ማስረጃዎቻቸው ተከላክለዋል የሚያስብል ሆኖ ተገኝቷል ። 3ኛ ተከሳሽ በዓቃቤ ሕግ ከተጠቀሰባቸው የክስ ፍሬ ነገሮች ውስጥ 2ኛ ተከሳሽ ከ1ኛው ተከሳሽ ጋር የሚገለገለባቸው ሐሰተኛ ሰነድች ይዞ የማዲበሪያው ግዥ በቀጥታ የጠየቀው 2ኛ ተከሳሽ ሆኖ የማዲበሪያው ግዥ ከመፍቀዲቸው በፉት 2ኛ ተከሳሽ ግዥው እየጠየቀ ያለው የራሱን ሰነድች ይዞ እንደሆነ ሣያረጋግጡ ግዥው ላልጠየቀ አካል ፈቅደዋል ። 2ኛው ተከሳሽ የ1ኛው ተከሳሽ ወኪል ነው ቢባል እንኳ ተያይዞ የቀረበው የውክልና ሰነድ የወካይ ስምና ፊርማ የላለው መሆኑን እያወቁ የማዲበሪያው ግዥ እንዱፈጸም ፈቅዶል በሚል ሲሆን በዓቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች 2ኛ ተከሳሽ ሰኔ 23 ቀን 2001 ዓ.ም የማዲበሪያ ግዥ በራሱ ስም የጠየቀና የቀረቡት ሰነድች አደም ኑር ገበያው ኃ/የተ.የግ ማህበር የሚል ሆኖ እያለና የቀረበው የውክልና ሰነድ የወካይ ስምና ፊርማ የላለው ስለሆነ በግልጽ በቀላለ ችግሩን መለየትና ማጣራት የሚያስችል ሆኖ እያለ ይህንን ሳይፈጽሙ ከድርጅቱ ማዲበሪያ ግዢ እንዱፈፅም መፍቀዲቸው የተመሰከረባቸው በመከላከያ ማስረጃዎች የተከለከለ ሆነው አልተገኘም ። በዚህም መሰረት በ3ኛ ተከሳሽ (አመልካች ) ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ)(ለ) እና 33 እና 407(1)(ሀ)(ለ) (2) ተላልፎል በማለት የቀረበው ክስ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.113(2) መሰረት አንቀጹን በመቀየር በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ)(ለ) እና 33 እና 407 (1)(ሀ) ሥር በወ/መ/ሥ/ሥ/ህቁ 149(1) መሰረት ጥፊተኛ ነው በማለት ተወስኗል።
ቅጣት በተመለከተም 1ኛ ተከሳሽ በላለበት የታየ በመሆኑ የቅጣት ማቅለያዎች ግምት ውስጥ ሳይገባ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች በተመለከተም በግራ ቀኙ የቀረቡት የቅጣት ማክበጃና ማቅለያዎች ከወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 በማገናዘብ 1ኛ ተከሳሽ በ 13 ዓመት ጽኑ እስራት እና 6,000 ብር መቀጮ 2ኛ ተከሳሽ በ 8 ዓመት ጽኑ እስራት 5000 ብር መቀጮ 3ኛ ተከሳሽ (አመልካች) ደግሞ በ 4 ዓመት ከ 6 ወር ጽኑ እስራትና ብር 2500.00 እንዱቀጡ ተወስኗል።
የአሁኑ አመልካች የሥር ፍርድ ቤት የጥፊተኝነትና ቅጣት ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ይግባኝ ችልት ያቀረቡት አቤቱታው ወደ ጉዲዩ ለመግባት የሚያስችል በቂ ምክንያት የለውም በማለት ውድቅ ተደርጓል ። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
ጉዲዩ ለሰበር ይቅረብ በመባለ ግራቀኙ የጹሐፍ ክርክር አድርገዋል ። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘት ፡- የዋጋ ማሳወቂያ መስጠት መደበኛ ሥራቸው እንደሆነ ፤የቀረበላቸው የሐሰት የሰነድ ማስረጃ የተባለው ሐሰተኛ ስለሀመሆናቸው ለማረጋገጥ የሚችለበት አግባብ እንዲልነበረ ሽያጭ የፈቀደው የላላ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ነው። የዋጋ ማሳወቂያ የተሰጠው ለ 5 ቀን የሚያገለግል ስለመሆኑ ፤የዋጋ ማሳወቂያ መስጠት ለመሸጥ ሐሳብ ማቅረብ እንጂ ሽያጭ መፈጸም አይደለም ። እቃ ለመሸጥ አሳብ መቅረብ የወንጀል ድርጊት አይደለም ። በሲ.ፒ.ኦ ደረሰ የተባለው ጉዲት በቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ ትዕዛዝ የተከናወነ እንጂ አመልካች ተሳትፍ እንዲልነበራቸው በድርጊቱ ምክንያት እና ውጤት ግንኙነት የለውም የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ሉሻር ይገባል የሚል ስለመሆኑ ተረድተናል። ተጠሪ በበኩለ በአመልካች በኩል መጣራት የገባቸው የነበሩ ነገሮች ባለ መጣራታቸው ከመመሪያው ውጭ ሽያጭ ተከናውነዋል ።አመልካች በሥር ፍርድ ቤት ተከሳሾች በነበሩ ግለሰቦች የቀረበው የሰነድ ማስረጃ ሳያጣራ በማሳለፍ ምክንያት ድርጊቱ የወንጀል ውጤት ያስገኘ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እነዱጸና መጠየቁን ተመልክተናል ። አመልካች ባቀረበው የመልስ መልስ የሰበር አቤቱታው በማጠናከር ተከራክሯል።
ከሥር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በጽሐፍ ያደረጉት ክርክር ፤ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነውን ፍርድ አግባብነት ካላቸው የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎች በማዛመድ እንዱሁም ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ እንደተቻለው በአመልካች ላይ የቀረበው የወንጀል ክስ የወ/ሕ/ቁ 32(1)(ሀ)(ለ)፣33እና 407(1)(ሀ)(ለ)እና (2) የተመለከተውን በመተላለፍ በሥር ፍርድ ቤት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በነበሩ የቀረቡ ሐሰተኛ ሰነድች የዋጋ ማሳወቂያ ከመፍቀዲቸው በፉት የ2ኛ ተከሳሽ የራሱ ሰነድች መሆናቸው አላረጋገጡም ። ግዥ ላልጠየቀ ግለሰብ ከመመሪያው ውጭ ፈቅደዋል። 2ኛ ተከሳሽ በአንደኛ ተከሳሽ ወኪል ነው ቢባል እንኳ የተያዘው የውክልና ማስረጃ የወካይ ስምና ፊርማ የለም።ከዋናው መሥሪያ ቤት የተፃፈው የማዲበሪያ ሽያጭ አፈፃፀም መመሪያ ለሰፈራ እርሻዎች የሚፈቀደው የማዲበሪያ ሽያጭ መጠን በሄክታር አንድ ኩንታል ዲፕና አንድ ኩንታል ዮሪያ በጠቅላላው ከ 500 ኩንታል እንደማይበልጥ የሚሸጥ መሆኑ እየታወቀ 3000 ኩንታል መዲበሪያ እንዱሸጥ ፈቅደዋል የሚል ይዘት ያለው ሲሆን ፤የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ፍሬ ነገር በማጣራት እና ማስረጃ በመመዘን ሥልጣኑ የደረሰበት ድምዲሜ አመልካች በተሰጣቸው ሥልጣን መሰረት መጠኑ እስከ 10,000 ኩንታል ማዲበሪያ መሸጥ እንደሚችለ ይሁንና 2ኛ ተከሳሽ የ1ኛ ተከሳሽ ተወካይ እነደሆነና የቀረቡ የግዥ ሰነድች አደም ኑር ገበያው ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት የሚል ሆኖ ሳለ 2ኛ ተከሳሽ በራሱ ስም ግዥ መጠየቁ የቀረበው የውክልና ሰነድም የወካይ ስምና ፊርማ የላላው እንደሆነ ፤ይህም በቀላለ ችግሩን መለየትና ማጣራት የሚቻል እንደነበር ነው።
በመሰረቱ አንድ የመንግሥት ሰራተኛ በሥልጣኑ ያለአግባብ የተገለገለ ከሆነ በወ/ሕ/ቁ.407 ሥር ተጠያቂ እንደሚሆን ግልጽ ነው ። የዚህ ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘት የወንጀል ድርጊት የተፈጸመው የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት ወይም በልላ ሰው መብት ጥቅም ላይ ጉዲት ለማድረስ በማሰብ እንደሆነ ፤የድርጊቱ አፈፃፀምም የተሰጠው ሹመት ወይም ሥልጣን በግልጽ ተግባር ወይም ግድፈት ከተሰጠው ስልጣን አልፍ በመሥራት ወይም ሥልጣኑ በማይፈቅደለት በተለይም ሥልጣን ሳይኖረው ወይም ከሥራ ከታገደ ከተዛወረ ፤ከተሻረ ወይም ሥልጣኑን ወይም ኃላፉነቱ ከተወ በኃላ የተፈጸመ ከሆነ የወንጀል ድርጊቱ ለማቋቋም በአማራጭ የተዘረዘሩ መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች ናቸው። እንደ ወንጀለ ክብደትም ከወንጀል ፈፃሚው ኃላፉነት፤የደረሰው ጉዲት ወይም የተገኘው ጥቅም ወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመበት ዓላማ መሰረት በማድረግ ወንጀለ እንደሚከብድ የወ/ሕ/ቁ. 407(2) እና (3) ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት ዓላማና መንፈስ መረዲት ይቻላል ። የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዓቃቤ ሕግ ክስ በማሻሻል በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) (ለ) እና 407(1)(ሀ) ሥር ጥፊተኛ ያላቸው ስለመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ያሳያል ። የዚህ ድንጋጌ ሙለ ይዘት ፡ የተሰጠው ሹመት ወይም ሥልጣን በግልጽ ተግባር ወይም ግድፈት ያለአግባብ የተገለገለበት እንደሆነ “የሚል ነው ።
በተያዘው ጉዲይ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች በዚህ ድንጋጌ ሥር ጥፊተኛ ለማለት እንደመነሻ የወሰደው ግዥው የተጠየቀው ለአደም ኑር ሆኖ እያለ 2ኛ ተከሳሽ በራሱ ስም የራሱ ሰነድች ይዞ እየጠየቀ መሆን ያለመሆኑን አላጣሩም ፤2ኛ ተከሳሽ የ1ኛ ተከሳሽ ተወካይ ነው ቢባል እንኳ የውክልና ሰነደ የወካይ ስምና ፊርማ ያለው ነው በቀላለ መለየት ይቻል ነበር በሚል ነው ።
አመልካች የዋጋ ማሳወቂያ ሰነድ የሰጡ ስለመሆኑ አላከራከረም ። በዋጋ ማሳወቂያው መሰረት ሽያጭ መፍቀድና ማከናወን ደግሞ በልላ የሥራ ክፍል የሚደረግ ስለመሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ከተደረገው ክርክር መረዲት ይቻላል ። አመልካች በኃላፉነት እንዱጠየቁ በመሰረታዊነት የተያዘው ምክንያት የውክልና ሰነደ የተሟላ ባለመሆኑ ችግሩን በቀላለ መለየትና ማጣራት ይቻል ነበር በሚል ነው። በዚህ ጉዲይ መታየት ያለበት መሰረታዊ ነጥብ አመልካች በውክልና ሰነደ ላይ የወካይ ስምና ፊርማ የላለ መሆኑ እየታየ የዋጋ ማሳወቂያ ሰነድ መስጠታቸው በወ/ሕ/ቁ 407(1) (ሀ) ሥር ጥፊተኛ ሉያሰኛቸው ይችላልን ? የሚል ነው።
ከክርክር ሂደቱ መረዲት እንደተቻለው አመልካች የቀረቡ ሰነድች በጥንቃቄ ለይተው ማጣራት የማይችለበት ሁኔታ እንደነበር በግልጽ የቀረበ ክርክር ባይኖርም በወ/ሕ/ቁ.407(1)(ሀ) እንደተመለከተው ግን የተሰጣቸው ኃላፉነት ያለአግባብ የተገለገለ ስለመሆናቸው የወንጀል ሕጉ እንደ መሰረታዊ ማቋቋሚያ የዘረዘረው ፍሬ ነገር ስለመረጋገጡ ከሳሽ ወገን የማስረዲት ሸክሙ ስለመወጣቱ የሚያሳይ ነገር በሥር ፍርድ ቤት አልቀረበም ። ይህ ከሆነ ደግሞ በአመልካች የተፈጸመው ድርጊት ስልጣን አላግባብ መገልግል ሳይሆን የሥራ ኃላፉነትን ባለመወጣት የሚፈጸም ወንጀል መሆኑን መረዲት ይቻላል ። አመልካች የሥራ ግዳታቸው ሲወጡ ከእሳቸው የሚጠበቀውን ግብይት ለማካሄድ እንደቅድመ ሁኔታ የሚወሰደ የቀረቡ ሰነድች በተገቢው መንገድ ተፈረመው የቀረቡ መሆን ያለመሆናቸው ፤የውክልና ሰጪ ስምና ፊርማ መኖር ያለመኖር የድርጅቱን አሰራር በሚፈቅደው አግባብ በጥንቃቄ ባለማጣራታቸው በሥር ፍርድ ቤት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በቀረቡት ሐሰተኛ ሰነድ ተጠቅመው ከግብርና ምርት ማሳደጊያ አቅራቢ ድርጅት ማዲበሪያ ወስደዋል ። በዚህም በድርጅቱ የገንዘብ ጥቅም ላይ ጉዲት ደርሰዋል ።
በመሆኑም አመልካች የሥር ፍርድ ቤት በወ/ሕ/ቁ 407(1)(ሀ) ሥር ጥፊተኛ ማለቱ የወንጀል ድርጊቱ ይዘትና ባሕሪ ያላገናዘበ ነው። አመልካች ጥፊተኛ ሉሆኑ የሚገባው ከፈጸሙት የወንጀል ድርጊት በተጣጣመ መልኩ መሆን ይገባዋል ። በዚህም አመልካች የሥራ ኃላፉነታቸው ሲወጡ ተገቢው ጥንቃቄ ባለማድረጋቸው በሥር 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ያቀረቡት የሰነድ ማስረጃ የወካይ ስምና ፊርማ የላለው ። ንብረት እንዱገዛ የጠየቀው 1ኛ ተከሳሽ ሆኖ ሳለ 2ኛ ተከሳሽ በስሙ ግዥ መጠየቁ የቀረቡ ሰነድች አግባብነትና አስፈላጊ ፍርማልቲዎች የሟለ መሆን ያለመሆናቸው የተለመደው አሰራር ተከትለው ባለማጣራታቸው ምክንያት የሥራ ኃላፉነትን ያለመሰጠት ወንጀል ፈጽመዋል ። ስለሆነም የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በወ/ሕ/ቁ/32(1)(ሀ)(ለ)፤33እና 407(1)(ሀ)ሥር ጥፊተኛ ማለቱ እና በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት መጽናቱ በአግባቡ ባለመሆኑ አመልካች ጥፊተኛ መሆን ያለባቸው አግባብነት ባለው የወንጀል ድንጋጌ በመሆኑ የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 113(2) በሚያዘው መሰረት ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ህግ አንቀጽ 407 (1) (ሀ) ወደ ወ/ህ/ቁ.420/1/ሥር በመለወጥ ጥፊተኛ ናቸው ብለናል ።
አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ሕግ በመለወጡ በሥር ፍርድ ቤቶች የተወሰነው ቅጣት ተገቢነት መርምረናል ። የወንጀል ቅጣት የሚወሰነው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያወጣው መመሪያ ቁጥር 1/2002 ወይም ቁጥር 2/2006 መሰረት በማድረግ ነው። አመልካች ጥፊተኛ የተሰኙበት የሕግ አንቀጽ የወንጀል ደረጃ እና መነሻ የእስራት ወይም መቀጮ እርከን የወጣለት አይደለም ። አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 420(1) ከአንድ ሺህ ብር በማይበልጥ መቀጮ ወይም ከስድስት ወር በማይበልጥ ቀላል እስራት ያስቀጣል። የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው በ2001 ዓ.ም በመሆኑ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው የቅጣት መመሪያ 1/2002 ነው። የወንጀል ቅጣት ሲወሰን የወንጀል ሕጉ ዓላማና ግብ በአንድ በኩል የወንጀል ፈፃሚው ግላዊ ሁኔታዎች በልላ በኩል ግምት ውስጥ መግባት እንዲለባቸው ከወ/ሕ/ቁ 1 እና 88 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘትና ዓላማ የምንረዲ ነው ። በተያዘው ጉዲይ ፍርድ ቤቱ የእስራት አማራጭ ወስዶል ። አመልካች የፈጸሙት የወንጀል ድርጊት ክብደትና ባህሪ መሰረት በማድረግ የስድስት ወር ቀላል እስራት መነሻ ይዘናል ። መቀጮ በተመለከተ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች በ 2500 ብር እንዱቀጡ የወሰነ ቢሆንም በዚህ ድንጋጌ የቀላል እስራት አማራጭ ብቻ የተወሰደ በመሆኑ የሥር ፍ/ቤት የጣለው መቀጮ የሕግ መሰረት የላለው ስለሆነ ሉነሳ የሚገባው ነው።በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች አመልካች ሉያርምና ሉያስተምር ይችላል ፤መሰል አጥፉዎችን ያስጠነቅቃል ብለን ያመነበት አመልካች በስድስት ወር ቀላል እስራት ሉቀጡ ይገባል ። የሥር ፍርድ ቤቶች በአመልካች የተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ዓይነት በአግባቡ ሳያገናዝቡ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ)እና (ለ) 407(1)(ሀ)ሥር ጥፊተኛ ማለታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ በማረም በወ/ሕ/ቁ.32(1)(ሀ)(ለ)፤33 እና 420(1) ሥር ጥፊተኛ ናቸው በማለት ተከታዩን ወስነናል ።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ.94053 በ 2/09/2005ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እና ቅጣት ፤የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወ/ይ/መ/ቁ.92016 በ 29/02/2006ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.195(2)(ለ)መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች ጥፊተኛ መሆን ያለባቸው በሥልጣን ያለአግባብ በመገልገል የወ/ህ/ቁ 407(1)(ሀ)ሥር ሳይሆን የሥራ ኃላፉነትን ባለመወጣት ወንጀል የወ/ህ/ቁ.420(1) ሥር ነው በማለት ወስነናል ።
አመልካች ለፈጸሙት ወንጀል በስድስት ወር ቀላል እስራት ሉቀጡ ይገባል በማለት ወስነናል። አመልካች በሥር ፍ/ቤት የተወሰነባቸው /ሁለት ሺህ አምስት መቶ /መቀጮ ለመንግስት ገቢ አድርገውት ከሆነ ወጪ ሆኖ እንዱከፈላቸው ታዟል።
ይፃፍ ።
No topics extracted.