አንድ በወንጀል የተከሰሰ ተከሳሽ መጥሪያ ባስመዘገበው የመኖሪያ አድራሻ እንደደረሰው ሳይደረግ ወይም በዚሁ አድራሻ ተፈልጎ ሉገኝ አለመቻለ ሳይረጋገጥ መጥሪያ በጋዜጣ እንዱወጣ አድርጎ ጉዲዩን በላለበት ማየት የስነ ስርዓት ህጉን ያልተከተለ ስለመሆኑ፣ በወንጀል ጉዲይ የተከሰሱ ሰዎች የቀረበባቸውን ማንኛውም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረበባቸውን ምስክሮች የመለየት፣ አቶ አታክልቲ አብርሃ እና የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሁመራ ቅርንጫፍ XVII የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዱሁም ምስክሮቻቸው ቀርበው እንዱሰሙላቸው የመጠየቅ መብት ያላቸው ስለመሆኑ፣ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገመንግስት አንቀፅ 20/4/ የወ/መ/ሥ/ሥነሥርዓት አንቀፅ 199 /ሀ/ ፣ 123፣202/3/፣
No summary available.
ግንቦት 10 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ አታክልቲ አብርሃ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገ/ጉ/ባለስልጣን የሁመራ ቅርንጫፍ ዐቃቤ ሕግ -የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
በዚህ መዝገብ አመልካች አቤቱታ ያቀረቡት ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ የተደረገው ክሱ እና መጥሪያው በመደበኛ መኖሪያ አድራሻቸው እንዱደርሳቸው ሳይደረግ በመሆኑ ክርክሩ በላለበት ታይቶ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 በአንቀጽ 91 (2) ስር የተሰጠባቸው የጥፊተኝነት እና የስድስት ዓመት ከአስር ወር ጽኑ እስራት እና የብር 5,500 የቅጣት ውሳኔ ተነስቶ ጉዲዩ እንደገና ባለበት እንዱታይ እንዱደረግ ያቀረቡትን ማመልከቻ እና ተጠሪው የሰጠውን መልስ ከመረመረ በኃላ የአመልካችን ጥያቄ ባለመቀበል በትግራይ ብ/ክ/መንግስት የምዕራባዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው እና በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያገኘው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል በማለት ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2001 በአንቀጽ 91 (2) ስር ክስ የቀረበበት ተከሳሽ ጉዲይ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 161 (2) መሰረት በላለበት ላታይ የሚችል መሆን አለመሆኑን እና አመልካች በላለበት የተሰጠባቸው ውሳኔ ተነስቶ ጉዲዩ ባለበት እንዱታይ ያቀረቡት ጥያቄ በስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ተጠሪ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በላለበት የተሰጠባቸው ውሳኔ ተነስቶ ጉዲዩ ባለበት እንዱታይ አመልካች ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
በዚህም መሰረት ጉዲዩን አመልካች በላለበት አይቶ የጥፊተኝነት ውሳኔውን የሰጠው የምዕራባዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሁመራ ምድብ ችልት ጉዲዩ ተከሳሹ በላለበት እንዱታይ ትዕዛዝ የሰጠው የፋዳራል ፖሉስ ተከሳሹን አላገኘኃቸውም በማለት ምላሽ ሰጥቷል፣ተከሳሹ በክልላዊ ጋዜጣ በወጣ ማስታወቂያም ተጠርተው አልቀረቡም በማለት ነው።ተከሳሽ በበኩላቸው በላለሁበት ታይቶ የተሰጠው ውሳኔ ሉነሳልኝ ይገባል በማለት የሚከራከሩት በጎንደር በሕክምና ላይ የነበሩ መሆኑን እና ከሕክምና ክትትለ በኃላም በመደበኛው መኖሪያ ቦታቸው የነበሩ ሆኖ እያለ የፍርድ ቤቱ ክስ እና መጥሪያ በአግባቡ እንዱደርሳቸው ሳይደረግ ፖሉስ አላገኘሁትም ብሎል በማለቱ እና በጋዜጣ ማስታወቂያ ተጠርተው አልቀረቡም በማለት ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ የተደረገው አላግባብ ነው በማለት መሆኑን ተገንዝበናል።አመልካቹ በጎንደር ከተማ በህክምና ክትትል ላይ ነበርኩ የሚለበት ጊዜ ፍርድ ቤት መቅረብ ነበረባቸው ከተባለበት ጊዜ በፉት እንደሆነ ከጊዜው ቅደም ተከተል መገንዘብ የተቻለ በመሆኑ አመልካች በህክምና ክትትል ላይ ነበርኩ የሚለበት ጊዜ ለጉዲዩ አወሳሰን አግባብነት ያለው አይደለም።በልላ በኩል ግን አንድ ተከሳሽ በላለበት የተሰጠበት ውሳኔ እንዱነሳለት የሚያቀርበውን ማመልከቻ ለመቀበል ከሚቻልባቸው ምክንያቶች አንደ መጥሪያው ለተከሳሹ ያልደረሰው የመሆኑ ጉዲይ ስለመሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 199 (ሀ) ስር የተመለከተ ሲሆን በተያዘው ጉዲይ የፋዳራል ፖሉስ በደፈናው ተከሳሹን አላገኘኃቸውም ብሎል ከመባለ ውጭ ተከሳሹን አላገኘኃቸውም በማለት ፖሉስ ምላሽ የሰጠው በርግጥም በምርመራ ጊዜ ከሰጡት መደበኛ የመኖሪያ አድራሻቸው ተገቢውን ፍለጋ አድርጎ ሉያገኛቸው እንዲልቻለ ተገቢውን ማረጋገጫ በመስጠቱ ስለመሆኑ የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም። የፋዳራል ፖሉስ እንዲላገኛቸው አረጋግጧል ከማለት ውጭ ጉዲዩ በላለሁበት የታየው መጥሪያው በመደበኛ የመኖሪያ አድራሻዬ እንዱደርሰኝ ሳይደረግ ነው በማለት አመልካች ባቀረቡት የክርክር ነጥብ ላይ ተጠሪው ያቀረበው ግልጽ ማስተባበያ አለመኖሩን ተገንዝበናል።
አመልካቹ በምርመራ ጊዜ ከገለጹት መደበኛ የመኖሪያ አድራሻቸው ተፈልገው የታጡ ስለመሆኑም ተጠሪው በግልጽ አልተከራከረም።ባስመዘገቡት አድራሻ መጥሪያው ለአመልካቹ የተላከ መሆኑ ወይም አመልካቹ በዚሁ አድራሻቸው ተፈልገው ያልተገኙ መሆኑ ሳይረጋገጥ ወደ ጋዜጣ ጥሪ አማራጭ የሚኬድበት አግባብ ስለማይኖር የጥሪ ማስታወቂያው በክልላዊ ጋዜጣ መነገሩ ብቻውን መጥሪያው ለአመልካች በአግባቡ እንዱደርስ ተደርጓል ለማለት የሚያስችል አይደለም።
በመሰረቱ በወንጀል ጉዲይ የተከሰሱ ሰዎች የቀረበባቸውን ማንኛውንም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ፣ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዱሁም ምስክሮቻቸው ቀርበው እንዱሰሙላቸው የመጠየቅ መብት እንዲላቸው በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግስት በአንቀጽ 20 (4) ተደንግጎ የሚገኝ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን ሕገ መንግስታዊ መብት ተግባራዊ ማድረግ የሚችለት ደግሞ ክስ የቀረበባቸው መሆኑን በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 123 በተመለከተው መሰረት በሚላክ መጥሪያ እንዱያውቁት ሲደረግ ነው።አመልካቹ መጥሪያው በሕግ አግባብ የደረሳቸው መሆኑን ደግሞ የመዝገቡ ገልባጭ አያረጋግጥም።
በልላ በኩል አንድ ተከሳሽ ጉዲዩ በላለበት ታይቶ የተሰጠበት ውሳኔ ተነስቶ ባለበት በድጋሚ እንዱታይ ያቀረበውን ማመልከቻ ባለመቀበል በሚሰጠው ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ ላይ ይግባኝ ማለት የማይቻል ስለመሆኑ እና ይግባኝ ማለት የሚቻለው በቅጣቱ መጠን ላይ ብቻ ስለመሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 202 (3) ስር በግልጽ የተመለከተ ሆኖ ሳለ እና አመልካች ለትግራይ ብ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በቅጣቱ ረገድ ያቀረቡት ቅሬታ ሳይኖር የቀድሞው ውሳኔ ሉነሳ አይገባም በሚል በተሰጠው ውሳኔ ላይ የቀረበለትን ቅሬታ ይግባኝ ሰሚ ችልቱ አስተናግድ ውሳኔው ጉድለት የለበትም በማለት የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 195 (1) ድንጋጌን ጠቅሶ የሰጠው ትዕዛዝ ሕጋዊ መሰረት ያለው ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል ጉዲዩ አመልካች በላለበት ታይቶ የጥፊተኝነት እና የስድስት ዓመት ከአስር ወር ጽኑ እስራት እና የብር 5,500 የቅጣት ውሳኔ የተሰጠባቸው መጥሪያው ባስመዘገቡት የመኖሪያ አድራሻ እንዱደርሳቸው ሳይደረግ ሆኖ እያለ እና ይህም በላለበት የተሰጠባቸውን ውሳኔ ለማንሳት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 199 (ሀ) ድንጋጌ መሰረት በቂ ምክንያት ሆኖ እያለ ውሳኔው ተነስቶ ጉዲዩ ባለበት እንደገና እንዱታይ አመልካች ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
አንድ ተከሳሽ ጉዲዩ በላለበት ታይቶ የተሰጠበት ውሳኔ ተነስቶ ባለበት በድጋሚ እንዱታይ ያቀረበውን ማመልከቻ ባለመቀበል የሚሰጥ ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ ይግባኝ የማይባልበት ስለመሆኑ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 202 (3) ስር በግልጽ የተመለከተ በመሆኑ ማመልከቻው ውድቅ መደረጉን አስመልክቶ የቀረበለትን ይግባኝ በማስተናገድ የትግራይ ብ/ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ 09/10/2006 ዓ.ም. የተሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
በላለበት ታይቶ የተሰጠባቸው የጥፊተኝነት እና የስድስት ዓመት ከአስር ወር ጽኑ እስራት እና የብር 5,500 የቅጣት ውሳኔ ተነስቶ ጉዲዩ ባለበት እንደገና እንዱታይ አመልካች ያቀረቡትን ማመልከቻ ውድቅ በማድረግ በትግራይ ብ/ክ/መንግስት የምዕራባዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁመራ ምድብ ችልት በመዝገብ በ05/09/2006 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
አመልካች በላለበት ታይቶ የጥፊተኝነት እና የስድስት ዓመት ከአስር ወር ጽኑ እስራት እና የብር 5,500 የቅጣት ውሳኔ የተሰጠባቸው መጥሪያው ባስመዘገቡት የመኖሪያ አድራሻ እንዱደርሳቸው ሳይደረግ ወይም በዚሁ አድራሻቸው ተፈልገው ሉገኙ አለመቻላቸው ሳይረጋገጥ በመሆኑ እና ይህም በላለበት የተሰጠባቸውን ውሳኔ ለማንሳት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 199 (ሀ) ድንጋጌ መሰረት በቂ ምክንያት በመሆኑ ውሳኔው ተነስቶ ጉዲዩ ባለበት እንደገና እንዱታይ አመልካች ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት ያለው ነው በማለት ወስነናል።
በትግራይ ብ/ክ/መንግስት የምዕራባዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁመራ ምድብ ችልት በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 202(1) በተደነገገው መሰረት ቀድሞ ጉዲዩን ያዩት ዳኞች በማይሰየሙበት ችልት አመልካች ባለበት ጉዲዩን እንደገና በማየት በስነ ስርዓት ሕጉ በተመለከተው መሰረት የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ሰምቶ ተገቢውን ውሳኔ ላሰጥበት ይገባል በማለት ወስነናል።
በዚሁ መሰረት መፈጸም ያስችለው ዘንድ የዚህ ውሳኔ ግልባጭ በትግራይ ብ/ክ/መንግስት የምዕራባዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁመራ ምድብ ችልት እንዱሁም በሚገኙበት የሁመራ ማረሚያ ተቋም በኩል ለአመልካቹ ይላክ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.