የተከሰሱ ሰዎች በህግ የተጠበቀላቸው የመሰማት መብት ቀሪ የሚሆነው ህጉ በዘረጋው ስርዓት ባለመብቱ ሳይጠቀምበት ሲቀር ብቻ ስለመሆኑ በህግ የተዘረጋ የክርክር አመራር ሳይሟላ የሚሰጥ ዲኝነት የግልፅነት መርህን የሚቃረንና በውጤቱም የተከራካሪ ወገንን መሰረታዊም ሆነ ሥነሥርዓታዊ መብት የሚጎዲ በመሆኑ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚገባ ስላለመሆኑ ፣ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 20/4/፣9/4/፣13/1/2/ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች አለም አቀፍ ቃልኪዲን አንቀፅ 14/3/ለ/
No summary available.
ሚያዚያ 12 ቀን 2007 ዓ/ ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ብርሃኑ ኑርጋ - ጠበቃ አመሃ መኮንን - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በሙስና ወንጀል የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 434/1997 አንቀጽ 29 እና 31 ድንጋጌዎች አግባብ የቀረበውን የውርስ ማመልከቻ መነሻ አድርጎ የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች እና ከእኚህ አመልካች ጋር በሙስና ወንጀል ተከሰው የጥፊተኝነት ውሳኔ ከተሰጠባቸው ላልች ስድስት ግለሰቦች ላይ ባቀረበው የንብረት ውርስ ጥያቄ ነው።
የዋናው ክስ ይዘትም ባጭሩ፡- ተከሳሾች ከ1999 ዓ/ም እስከ 2000 ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ የመንግስት ሰራተኛ፣ አስመጪና የእቃ አስተላላፉ ሁነው ሲሰሩ ሕገ ወጥ ጥቅም ለማግኘት አስበው በተለያዩ ዱክላራሲዩን ቁጥሮች ከአሳወቋቸው እቃዎች እና ከውጪ ለአስመጧቸው እቃዎች መክፈል የሚገባቸውን ብር 13,457,694.40 (አስራ ሶስት ሚሉዩን አራት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና አራት ብር ከአርባ ሳንቲም) ቀረጥና ታክስ ሳይከፈለ የከፈለ አስመስለው ከመቅረጫ ጣቢያ እቃዎቹን እንዱለቀቁ እና የፈፀሙት ወንጀል እንዲይደርስባቸው ለማድረግ እቃዎቹን የሚይዘውን መረጃ ከመስሪያ ቤቱ "አሲኩዲ" የመረጃ ሲስተም በማጥፊት የመንግስት ቀረጥ እንዲይሰበሰብ በማድረጋቸው በግብረአበርነት በስልጣን ያላግባብ ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ሲሆን የግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ተሰምቶ አመልካችና ላልች የስር ተከሳሾች ጥፊተኛ ተብለው የእስራት ቅጣት የተወሰነባቸው መሆኑን የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመ/ ነሐሴ 23 ቀን 2003 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ ያሳያል።
ከዚህም በኋላ የአሁኑ ተጠሪ በዋናው የወንጀል ጉዲይ ክስ የቀረበባቸው ሰዎች ጥሬ ገንዘብና ላልች ንብረቶች ታግደው እንዱቆዩ አድርጎ የነበረ መሆኑን ጠቅሶ በእያንዲንደ አጥፉ ስም የታገደውን የንብረት አይነትና የጥሬ ገንዘብ መጠን ዘርዝሮ በወንጀል ጉዲይ ጥፊተኛ የተባለት ግለሰቦች በድርጊታቸው በመንግስት ላይ ለደረሰው ጉዲት ማካካሻነት በአንድነትና በነጠላ ኃላፉነት ያለባቸው ናቸው በማለት ጠቅሶ በአመልካችና በላልች ግለሰቦች ስም በባንክ የሚገኝ ገንዘብ ለመንግስት በውርስ ገቢ እንዱደረግ፣ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታግድ የሚገኘው የስር 7ኛ ተጠሪ(አቶ ነብዩ በድሩ) ጅምር የመኖሪያ ቤትና መጋዝን በፍርድ አፈፃፀም መምሪያ በኩል በሐራጅ ተሸጦ ገንዘቡ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባንክ ሂሳብ ውስጥ ገቢ እንዱደረግ ትዕዛዝ እንዱሰጥለት አቤቱታ አቅርቧል። በአሁኑ አመልካች ስም በባንክ ይገኛል የተባለው የገንዘብ መጠን በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ተክለሐይማኖት ቅርንጫፍ በሑሳብ ቁጥር 179 ብር 123,738.52 (አንድ መቶ ሃያ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሃምሳ ሁለት ሳንቲም) እና በንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ተክለይሐይማኖት ቅርንጫፍ በሑሳብ ቁጥር 221 ደግሞ ብር 1,020,095.80 (አንድ ሚሉዩን ሃያ ሺህ ዘጠና አምስት ብር ከሰማንያ ሳንቲም) ስለመሆኑ በተጠሪ የውርስ ማመልከቻ ላይ ተጠቅሷል። የአሁኑ አመልካች ለተጠሪ የውርስ ጥያቄ ላይ በሰጡት መልስም በመንግስት ላይ ደርሷል በማለት በማመልከቻው ላይ የተጠቀሰው ብር 13,457,694.40 (አስራ ሶስት ሚሉዩን አራት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና አራት ብር ከአርባ ሳንቲም) በእርግጥ ለመድረሱ በሚያሳምን ሁኔታ ተጣርቶ ያለመቅረቡን፣ በማካካሻነት ንብረት ሉወረስ የሚገባው በመንግስት ላይ በእርግጥ ለደረሰው ጉዲት ተመጣጣኝ መሆን እንደአለበት በጸረ ሙስና ልዩ የሥነ ስርዓትና የማስረጃ ሕግ መደንገጉን፣አመልካቹ ጥፊተኛ የተባለት በዱክሉራሲዩን በደግፍ ይርጋ ስም ያስገቡት ሁኖ ንብረቱ በዋናው መዝገብ አራተኛ ተከሳሽ የነበሩት አቶ ነብዩ በድሩ በመሆኑ ቀረጡን መክፈል የሚገባቸው ይኼው ግለሰብ መሆናቸውን፣ እንዱወረስ የተጠየቀውና በፍርድ ቤት የታገደው በባንክ የሚገኘው ገንዘብ አመልካቹ ጥፊተኛ የተባለበት ድርጊት ከመፈጸሙ በፉት በተከፈተ ሑሳብ ውስጥ የተገኘና መጠኑም በእንቅስቃሴ ከፍ ዝቅ ሲል የቆየ በመሆኑ በስራ እንጂ በሕገ ወጥ መንገድ ያላገኙት መሆኑን፣ጥፊተኛ የተባለት የጉምሩክ ስነ ስርዓት በመጣስ እንጂ በዋናው ወንጀል ተሳትፍ ኑሯቸው ባለመሆኑና በወንጀል ቀጥተኛ ተሳትፍ አድርገዋል ተብለው ጥፊተኛ ከተባለት ተከሳሾች በመንግስት ላይ ደረሰ ለተባለው ጉዲት ለማካካስ በቂ ንብረት የተያዘ መሆኑን ዘርዝረው የተጠሪ የውርስ አቤቱታው ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ላልች የሥር ተከሳሾችም አለን የሚሎቸውን ክርክሮችን አቅርበዋል። ክርክሩ በዚህ መልክ የቀረበለት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ በተከሳሾች ላይ የውርስ ጥያቄ መቅረብ የሚገባው እያንዲንዲቸው በወንጀል ድርጊት ምክንያት ሳይከፍለ በቀሩት የታክስና ቀረጥ መጠን እንጂ በወንጀለ ድርጊት ላልተሳተፈበትና ጥቅም ላላገኙበት የገንዘብ መጠን ላሆን አይገባም የሚለውን ድምዲሜ ይዞ ተጠሪ ተከሳሾች በመንግስት ላይ የደረሰውን ብር 13,457,694.40 (አስራ ሶስት ሚሉዩን አራት መቶ ሃምሳ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ዘጠና አራት ብር ከአርባ ሳንቲም) በአንድነትና በነጠላ ሉከፍለ ይገባል በማለት ባቀረበው አቤቱታ ሁለም አጥፉዎች የሚገደደበት ምክንያት የለም፣ አመልካች አድራጎት በዱክላራሲዩን ፣21702፣23132 በገቡት እቃዎች ሳይከፈል የቀረው ግብርና ታክስ መጠኑ ብር 2,539,233.00 (ሁለት ሚሉዩን አምስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ሶስት ብር) መሆኑን፣ ይህንኑ ገንዘብ ተጠቃሚ የሆኑትም አመልካች ሳይሆኑ የስር ተከሳሽ የነበሩት አቶ ነብዩ ብድሩ መሆናቸውን፣ አመልካች በጉምሩክ አስተላላፉነታቸው ቀረጥና ታክስ የመክፈል ግዳታ ያልተጣለባቸውና ግብሩንና ታክሱን የመክፈል ኃላፉነት የአቶ ነብዩ ብድሩ ሽፊ በመሆኑ ይህንኑ ገንዘብ የመክፈል ኃላፉነት የአቶ ነብዩ በድሩ ብቻ ነው በማለት ወስኗል።በላልች ተከሳሾችም ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህ ውሳኔ አቶ ነብዩ ብድሩ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ፍርድ ቤቱ አቶ ነብዩ ብድሩንና የአሁኑን ተጠሪ በመልስ ሰጪነት ሰይሞ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ አቶ ነብዩ ብድሩ ለብቻቸው እንዱከፍለ የተወሰነው የሕግ መሰረት በላለበት አግባብ ነው በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ውሰኔ አሻሽል ብር 2,539,239.50 (ሁለት ሚሉዩን አምስ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ብር ከሃምሳ ሳንቲም) መክፈል ያለባቸው አቶ ነብዩ ብድሩ ሺፊ ብቻ ሳይሆኑ በወንጀል ድርጊቱ አብረውት ጥፊተኛ ተብለው የተቀጡት ተከሳሾችሸ ጭምር ናቸው በማለት ገንዘቡን በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ሲል ወስኗል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው የሃላፉነት አይነትና መጠን አመልካች በወንጀለ የነበራቸውን የተሳትፍ ደረጃ ያላገናዘበና የህግ መሰረት የላለው መሆኑን እንዱሁም ውሳኔው የአመልካችን መብትና ጥቅም የሚነካ ሁኖ እያለ በይግባኝ ክርክሩ ላይ አመልካች እንዱካፈለ ሳይደረግ መወሰኑ ተገቢነት የላለው መሆኑን ዘርዝረው መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪም ቀርቦ በሰጠው መልስ በይግባኝ ሰሚው ችልት በነበረው ክርክር ተጠሪ ይግባኝ ባይ ባልሆነበት ሁኔታ በሰበር ክርክሩ ተሳታፉ ላሆን የሚችልት አግባብ ያለመኖሩንና አመልካች ይነሳልን ለሚለት የእግድ ትዕዛዝም ተቃውሞ የላለው መሆኑን ጠቅሶ ከክርክሩ ውጪ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን አጠናክረው የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለሰበር ችልት ያስቀርባል ተብል ሲታዘዝ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል የተባለበት ቀዲሚው ነጥብ አመልካች የይግባኝ ክርክሩ ተሳታፉ ሳይሆኑ ገንዘቡን በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ተብል በመሆኑ ይህንኑ ጭብጥ መመርመሩ ተገቢ ሁኖ አግኝተናል።
አመልካች ከአቶ ነብዩ ብድሩ ጋር ብር 2,539,239.50 (ሁለት ሚሉዩን አምስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ብር ከሃምሳ ሳንቲም) በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ተብል በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ የተሰጠው አመልካቹ የክርክሩ ተካፊይ ሳይሆኑ መሆኑን ከይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ ተገንዝበናል። አሁን በዚህ የሰበር ክርክር ደረጃ ደግሞ አመልካች ይህ የይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ መብትና ጥቅማቸውን የሚነካ ሁኖ እያለ የክርክሩ ተሳታፉ ሳይሆኑ መወሰኑ ያላግባብ ነው በማለት ተከራክረዋል።
በመሰረቱ የተከሰሱ ሰዎች በሕግ ከተጠበቁላቸው መብቶች አንደ የመሰማት መብት ነው። ይህ መብት በመጀመሪያም ሆነ በላልች የክርክር ደረጃዎች በሕጉ የተዘረጋውን ስርዓት በመከተል ሉጠበቅ የሚገባ ነው።መብቱ ቀሪ የሚሆነው ሕጉ በዘረጋው ስርዓት ባለመብቱ ሳይጠቀምበት ሲቀር ብቻ ነው። በመሆኑም የመሰማት መብት ተከሳሾች የቀረበባቸውን ማናቸውንም ማስረጃ የመመልከት፣ የቀረቡባቸውን ምስክሮች የመጠየቅ፣ ለመከላከል የሚያስችላቸውን ማስረጃ የማቅረብ ወይም የማስቀረብ እንዱሁም ምስክሮቻቸውን ቀርበው እንዱሰሙላቸው የመጠየቅ መብት ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 20 (4) የተደነገገ ሲሆን ይህ መብት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9(4) ድንጋጌ አግባብ የአገሪቱ የሕግ አካል በሆኑት የአለም አቀፍ ስምምነቶችም ጥበቃ ያገኘ ስለመሆኑ የሲቭልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዲን 14(3(ለ)) ድንጋጌን በመመልከት የምንረዲው ጉዲይ ነው።አለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ በአንቀጽ 10 ያስቀመጠው ድንጋጌም ማንም ሰው በተከሰሰበት ወንጀል ውሳኔ ለማግኘት ሙለ የእኩልነት መብቱ ሉጠብቅለት እንደሚገባና ሚዛናዊና ይፊ የሆነ ፍርድ የማግኘት መብት እንደአለው ያሳያል። ይህ መብት የሚጠበቀው የመከራከር መብቱ በአግባቡ ሲጠበቅ መሆኑን ከድንጋጌው ይዘት የምንረዲው ነው። በእነዚህ ድንጋጌዎች ስር የተመለከተው የተከሳሽ መብት የሚያስገነዝበው አንድ ተከሳሽ ተገቢ ባልሆነ ማስረጃ ጥፊተኛ እንዲይባልና በከሳሹ ወገን ማስረጃ ቀርቦ ከሆነም በበኩለ ምንም ጥፊት ያልፈፀመና ንፁህ መሆኑን የማስረዲት ሁኔታዎችን ማመቻቸት የሚችል መሆኑንና ክርክሩ የእኩልነት መብቱ ተጠብቆ በግልጽና ተከሳሹ በይፊ በሚያውቀው አግባብ መሆን ያለበት መሆኑን ነው። በመሆኑም ለቀረበበት ክስም ሆነ ይግባኝ ተገቢውን ክርክርና ማስረጃ ለማዘጋጀት የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆን ተደርጎ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮችንና በቂ ጊዜ ማግኘት እንደሚገባው ሕጉ ያስገነዝበል። ተከሳሹ ይህንኑ በሕገ መንግስቱ ጥበቃ ያገኘውን የመሰማት መብታቸውን በመጀመሪያ ደረጃ ክርክርም ሆነ በይግባኝ ደረጃ በሚደረገው ክርክር በአግባቡ እንዱጠቀም ማድረግ የፍርድ ቤት ኃላፉነት መሆኑንም ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 13(1) እና (2) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ጉዲይ ነው።
በመሆኑም ይህ የተከሳሽ የመሰማት መብት ሉታለፍ የሚገባው ተከሳሹ መብቱን የማይጠቀምበት መሆኑን በግልፅ ለፍርድ ቤቱ ሲያረጋግጥለት ወይም በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት ክርክር መኖሩን እንዱያውቀው ተደርጎ ይህንኑ እያወቀ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ፍቃደኛ ሳይሆን መቅረቱ በእርግጥ ሲታወቅ ብቻ መሆኑን ከድንጋጌዎች መንፈስ የምንገነዘበው ነው። ተከሳሹ የመሰማት መብቱን ስለመተው ባልተረጋገጠበት አግባብ ግን የተከሳሽን መብትና ጥቅም የሚነካ ውሳኔ ፍርድ ቤት መስጠት ተገቢነት የላለው አካሄድ ነው።
ወደ ተያዘው ጉደይ ስንመለስ የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩን ያየው አመልካችንና ተጠሪን እንዱሁም በወንጀለ ጥፊተኛ የተባለትን ሁለንም ሰዎች የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆኑ አድርጎ ሲሆን አመልካች ለተጠሪ የውርስ ጥያቄ አለኝ ያለትን የፍሬ ነገርና የሕግ ክርክር አቅርበዋል።አመልካቹ ያቀረቡትን ክርክርም የስር ፍርድ ቤት ተቀብል ለአመልካች መብትና ጥቅም ላይ ጉዲት የማያደርስ ውሳኔ ሰጥቷል። በዚህ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ የአሁኑ ተጠሪ በውጤቱ ተጠቃሚ መሆኑን ተገንዝቦ ይግባኝ ያልጠየቀ ቢሆንም ገንዘቡን ለብቻቸው ለተጠሪ እንዱከፍለ የተወሰነባቸው የወንጀለ ተሳታፉ ነበር የተባለ ግለሰብ(አቶ ነብዩ በድሩ) ግን ገንዘቡን ብቻዬን ልከፍል አይገባም በማለት አመልካችንና ላልችንም ግለሰቦች ሉጨምር ይገባል በማለት ይግባኝ አቅርበው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ክርክሩን የአሁኑ አመልካች ሳይጠራ በመምራት ጉዲዩን መርምሮ የአመልካች የንብረት ጥቅምና መብት የሚነካ ውሳኔ ሰጥቷል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካችን ወደ ክርክሩ እንዱገቡ ያላደረገበት ሕጋዊ ምክንያት ስለመኖሩም በውሳኔው ላይ አልገለጸም።ይህም አመልካች የይግባኝ ክርክሩ የሚመለከታቸው መሆኑን እንዱያውቁ ተደርጎ የክርክሩ ተሳታፉ ለመሆን ፍላጎት የላላቸው መሆኑ ሳይረጋገጥ ክርክሩ መመራቱን የሚያረጋገጥ በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በክርክር አመራር መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መፈፀሙን የሚሳይ ሁኖ አግኝተናል። በሕግ የተዘረጋ የክርክር አመራር ሳይሟላ የሚሰጥ ዲኝነት የግልጽነት መርህን የሚቃረንና በውጤቱም የተከራካሪ ወገንን መሰረታዊም ሆነ ስነ ስርዓታዊ መብት የሚጎዲ በመሆኑ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚገባ አይደለም።
ከእነዚህ ሁለ ምክንያቶች አንጻር ጉዲዩን ስንመለከተው አመልካች በሕጉ የተጠበቀላቸውን የሰውነት መብት ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ያለፈው አመልካቹ በግልጽ በመብታቸው የማይጠቀሙበት መሆኑን ሳያረጋገጡ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ሕዲር 06 ቀን 2006 ዓ/ም ብር 2,539,239.50 (ሁለት ሚሉዩን አምስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ብር ከሃምሳ ሳንቲም) አመልካች ከአቶ ነብዩ በድሩ ሽፊ ጋር በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ተብል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ብቻ ተሽሯል።
አመልካች የይግባኝ ክርክሩ ተካፊይ ሁኖ የመሰማት መብት የታለፈው ያላግባብ ነው ብለናል። በመሆኑም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ክርክሩን በመ/ ቀጥል የአመልካችን የመሰማት መብት በሕጉ አግባብ ሰምቶ አቶ ነብዩ ብድሩና ላልች የክርክሩ ተካፊይ ሉሆኑ የሚገባቸው ሰዎች ካለም ወደ ክርክሩ እንዱገቡ አድርጎ በጉዲዩ ላይ ተገቢውን ዲኝነት እንዱሰጥበት ጉዲዩን መልሰን ልከንለታል።ይጻፍ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።