በወንጀለኛ ህግ አንቀፅ 692(1) መሰረት የማታለል ተግባር ተፈፅሟል ለማለት መሟላት ስላለባቸው ሁኔታዎች አንድ ሰው ለወንጀል ድርጊት ኃላፉ ተብል ቅጣት ሉወሰንበት የሚገባው ወንጀለ መሰራቱ ወይም መፈፀሙና ተሰራ ወይም ተፈፀመ የተባለው ወንጀል ደግሞ በተከሳሹ መፈፀሙ በበቂና በአሳማኝ ሁኔታ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀፅ 23(4)፣32፣40፣57 እና 58(1) የወ/መ/ሥ/ሥ/ቁ/. 141፣142 እና 149
No summary available.
መጋቢት 28 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ አበባ አረፊይኔ ጠበቃ መረሣ ፍሰሃ ቀረቡ ተጠሪ፡- የትግራይ ክልል አቃቤ ሕግ - ተልፎል **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ አመልካች በአድዋ ወረዲ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በጸናው የጥፊተኝነትና የቅጣት ዉሳኔ ባለመስማማት ቅሬታቸዉ በሰበር እንዱታይላቸው ሐምል 30 ቀን 2006 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው።
በአድዋ ወረዲ ፍርድ ቤት ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበዉ ክስ በ1996 ዓ.ም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 692/1/ ሥር የተመለከተዉን በመተላለፍ ተገቢ ያልሆነ ከፍ ያለ ጥቅምና ብልጽግና ለማግኘት ወይም ለላላ ሰዉ ለማስገኘት አስበው ከስር 1ኛ ተከሳሽ ከነበረው ከአቶ ተክለማሪያም ገ/ማርያም ጋር አባሪ ተባባሪ ሁነው ወደ ግል ተበዲይ መኖሪያ ቤት ድረስ ሐምል 21 ቀን 2002 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ሲሆን በመሄድ ከበሽታሽ የሚፈውስ ደብተራ አለ በሚል የአሁኗ አመልካች የሥር 1ኛ ተከሳሽን ወደ ግል ተበዲይ ቤት ልካባት የሥር 1ኛ ተከሳሽም ወደ ግል ተበዲይ ቤት ገብቶ ስሜ ይትባረክ ሽፈራው እባለላሁ ብል በሽታሽ በወርቅሽ ስለሆነ ወርቅሽን ሁለ አቅርቢ፣አንድ አንዲታስቀሪ ብል ልሚ፣ድሮና አረቄ አቅርቢ ብልአት ወርቁን ከአቀረበችለት በአቦጀዱ ጠቅልል መድሃኒት አድርጌበታለሁ በማለት ላላ ተመሳሳይ አቦጀድ የተጠቀለለ ቆርኪ ጠቅልል አስቀምጦ ወርቁን መድሃኒት አድርጌበት ስለሆንኩ በኃላ መጥቼ ራሴ እስከምፈታው እንዲትነኩ ብል ባለ ሃያ አራት ካራት ወርቅ ግምቱ ብር 447,000.00 የሆነ 447 ግራም የሆነ ወርቅ ይዞ መሰወሩን ዘርዝሮ አመልካችና የስር 1ኛ ተከሳሽ በግብረአበርነት የማታለል ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው። የአሁኗ አመልካች የዕምነት ክህደት ቃል እንዱሰጡ ሲጠየቁ የቀረበባቸውን ክስ አልፈጸምኩም፤ ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክረዋል። በዚሁ መሰረት ዐቃቤ ሕግ አለኝ ያላቸዉን የሰነድና የሰዉ ማስረጃ በማቅረብ አሰምቷል። አመልካች እንዱከላከለ በተሰጠዉ ብይን መሰረት አለኝ ያሎቸውን ማስረጃዎችን አቅርበው አሰምተዋል። ጉዲዩን የመረመረዉ የወረዲው ፍርድ ቤትም አመልካች በክሱ ላይ ተጠቅሶ የቀረበባቸውን የሕግ አንቀጽ በመተላለፍ ጥፊተኛ ናቸዉ በማለት ፍርድ ከሰጠ በኃላ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመቀበልና ከፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ጋር አገናዝቦ መመልከቱን ጠቅሶ አመልካችን በሶስት አመት ከአምስት ወር ቀላል እስራት እና በብር 500.00(አምስት ሺህ) እንዱቀጡ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ የአሁኗ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም፣ የሰበር አቤቱታቸውን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበውም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም ተብል አቤቱታቸው ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ጉዲዩ በወረዲው ፍርድ ቤት የታየው ከስልጣኑ ውጪ መሆኑን፣ አቃቤ ሕግ አመልካች በወንጀለ የነበራቸውን ተሳትፍ እንደ ክሱ ያለማስረዲቱን፣ በዓቃቤ ሕግ ምስክሮች የግል ተበዲይ እና የስር 1ኛ ተከሳሽ ቀደም ብለው የሚተዋወቁ መሆናቸው መነገሩም አመልካች በወንጀለ አፈፃጸም ተሳትፍ ያልነበራቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው፣ የቅጣት ውሳኔም ተገቢውን የቅጣት አወሳሰን ስርዓት ተከትል የተወሰነ አይደለም የሚል ነው።አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ መጥሪያ ደርሶት ባለመቅረቡ ምክንያት በፅሐፍ መልስ የመስጠት መብቱ ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸዉ ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን እንደሚከተለዉ መርምሯል። በዚሁ መሰረት የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልጉ አበይት ጭብጦች፡-
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡- ዐቃቤ ሕግ በአመልካች ላይ የመሰረተዉን የማታለል ወንጀል ለማስረዲት የግል ተበዲይንና ላልች ምስክሮችን በምስክርነት ያቀረባቸዉ ሲሆን ምስክሮቹም ቀጥተኛ የሆነ የምስክርነት ቃል የሰጡና የአካባቢ ምስክሮች ናቸው። የአይን ምስክር የሆኑት 1ኛ እና 2ኛ ምስክሮች ሲሆኑ አመሰካከራቸውም የስር አንደኛ ተከሳሽ በአሁኗ አመልካች አማካኝነት በክሱ በተጠቀሰው ጊዜ ወደ ግል ተበዲይ ቤት ሂድ ስሜ ይትባረክ ሽፈራው እባለላሁ ብል በሽታሽ በወርቅሽ ስለሆነ ወርቅሽን ሁለ አቅርቢ፣አንድ አንዲታስቀሪ ብል ልሚ፣ድሮና አረቄ አቅርቢ ብሎት ወርቁን ከአቀረበችለት በኋላ በአቦጀዱ ጠቅልል መድሃኒት አድርጌበታለሁ በማለት ላላ ተመሳሳይ አቦጀዳ የተጠቀለለ ቆርኪ ጠቅልል አስቀምጦ ወርቁን መድሃኒት የአድርግሁበት ስለሆነ በኃላ መጥቼ ራሴ እስከምፈታው እንዲትነኩ ብል ባለ ሃያ አራት ካራት ወርቅ ግምቱ ብር 447,000.00 የሆነ 447 ግራም የሆነ ወርቅ ይዞ መሰወሩን፣አመልካች ከስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር ወደ ግል ተበዲይ ከሄዲቸውም በተጨማሪ የስር 1ኛ ተከሳሽ በግል ተበዲይ ቤት ውስጥ እያለ አመልካች ስልክ እንደደወለለትና ለምስክሮቹ ገልጾ ከግል ተበዲይ ቤት ወጥቶ ወደ አመልካች ደርሶ መመለሱንና አመልካች ልጃቸውን እየላኩ ሁኔታውን ሲከታተለ የነበሩ መሆኑን ዘርዝረው የመሰከሩ መሆናቸውን ከውሳኔው ግልባጭ ተረድተናል። ምስክሮቹ ይትባረክ ሽፈራው የተባለውና ወርቁን የወሰደው የስር 1ኛ ተከሳሽ አመልካች የአጎቴ ልጅ ነው ብለው መሄዲቸውንም መመስከራቸውን የውሳኔው ግልባጭ ያሳያል።ላልች ምስክሮች የአከባቢው ምስክሮች ሲሆኑ የሥር 1ኛ ተከሳሽ ወደ ግል ተበዲይ ሲገባ፣ ከጊዜ በኋላ የግል ተበዲይ ግለሰቡ ሲሰወሩ የሚያውቁት መሆን ያለመሆኑን ሲጠየቋቸው እንደነበርና ወርቅ ዘርፍ የተሰወረባቸው መሆኑን 1ኛ እና 2ኛ የዓቃቤ ሕግ ምስክሮች የነገራቸው መሆኑን የገለፁ ምስክሮች ናቸው።
እንግዲህ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካችን ጥፋተኛ ለማድረግ በአቃቤ ሕግ በኩል የቀረቡትን የሰው ምስክሮች አመሰካከር ይዘት ከላይ የተጠቀሰው መሆኑን በውሳኔው ላይ የገለፁት ጉዳይ ሲሆን ፍርድ ቤቶቹ በፍርድ ሐተታው በግልጽ ያስቀመጡት ድምዳሜውም ከአቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃል አመልካች የስር 1ኛ ተከሳሽ የግል ተበዳይን ከበሽታ እፈውሳለሁ በሚል ወርቃቸውን አታልሎ ሲወስድባቸው ተሳትፎ የነበራቸው መሆኑን አየን፣ ወርቁን ይዞ የተሰወረው ሰው የአመልካች ትክክለኛ ዘመዳቸው ሳይሆን የአጎታቸውን ልጅ መሆኑንና ስሙን ሁለ ቀይሮ ከግል ተበዳይ ጋር ሲተዋወቅ አመልካች ይህንኑ ለግል ተበዳይና ለ2ኛ ምስክር ሉታመን በሚችል ሁኔታ የገለፁ መሆኑን መመልከታቸውንና ሁኔታውን እውነት መስሐቸው መቀበላቸውን መመስከራቸውን የሚያሳይ ነው።የወረዳው ፍርድ ቤትም ፍሬ ነገርን በማጣራትና ማስረጃን በመመዘን የደረሰበት ድምዳሜ በዚህ ረገድ ተመሳሳይ የሆነ ስልጣን ባለው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሙለ በሙለ ተቀባይነት አግኝቷል።በመሆኑም አመልካች በማታለል ድርጊቱ አፈጻጸም ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸው መሆኑ፣በስር 1ኛ ተከሳሽ ሲፈጸም የነበረውን ሁኔታ ልጃቸውን እየላኩ መከታተላቸው ውጤቱን በመቀበል የራሳቸው ማድረጋቸው በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ይህ ችሎት በኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብሉክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች መሰረት ከተሰጠው ስልጣን አኳያ አመልካች በወንጀል ተሳትፎ የነበራቸው መሆኑን በስር ፍርድ ቤቶቸ የተደረሰውን ድምዳሜ እንዳለ የሚቀበለው ነው።
አመልካች ከሚከራከሩባቸው ነጥቦች ውስጥ አመልካች የድርጊቱ ተሳታፊ መሆናቸው በአቃቤ ህግ ማስረጃዎች አልተገለፀም በሚል ነው፣የግል ተበዳይ የስር 1ኛ ተከሳሽን ቀደም ብለው ያውቁት ነበር በሚል ነው።
በመሰረቱ በአንድ የወንጀል ጉዳይ የሚቀርብ ማስረጃ በቂና አሣማኝ በሆነ ሁኔታ የወንጀል ድርጊቱ መፈፀሙንና የወንጀል ድርጊቱን ፈፃሚውን ማንነት በትክክል ለይቶ ማሳየት ያለበት ስለመሆኑ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 141 ድንጋጌ ይዘትንና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው።አንድ ሰው ለወንጀል ድርጊት ኃላፊ ተብሎ ቅጣት ሉወሰንበት የሚገባው ወንጀለ መስራቱ ወይም መፈፀሙና ተሰራ ወይም ተፈፀመ የተባለው ወንጀል ደግሞ በተከሳሹ መፈፀሙ በበቂና በአሳማኝ ሁኔታ ሲጋገጥ ስለመሆኑ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23(4)፣32፣40፤57፣58(1) እና ከወ/መሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 141፣142 እና 149 ድንጋጌዎች አገላለፅና መንፈስ መመልከት የምችለው ጉዳይ ነው።ማንም ሰው በዋና ወንጀል አድራጊነት ወንጀል እንዳደረገ የሚቆጠረው ወንጀለን እርሱ ራሱ በቀጥታ ቢያደርግ ወይም በቀጥታ ባያደርግም እንኳን በመላ ሀሳቡና አድራጏቱ በወንጀለ ድርጊትና በሚሰጠው ውጤት ሙለ ተከፋይ በመሆን ወንጀለን የራሱ ያደረገ ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ለ/ በግልጽ ተደንግጓል።ከሳሽ የሆነው አቃቤ ሕጉም ይህንኑ በሕጉ የተጣለበትን ግድታ መወጣት አለበት።
ከላይ እንደተገለጸው አመልካች በክሱ የተጠቀሰውን የማታለል ተግባር ከግብረ አበራቸው ጋር ሁነው በቀጥታ ተሳትፈውና ውጤቱንም የራሳቸው በማድረግ ወንጀለን የፈፀሙ መሆኑን የተነገረባቸው በጊዜውና በቦታው በነበሩት ምስክሮችና በጠንካራ የአካባቢ ምስክሮች መሆኑን የበታች ፍርድ ቤቶች አረጋግጠዋል። የአቃቤ ሕግ ምስክሮች ቃልም በመከከላከያ ማስረጃዎች ያልተስተባበለ መሆኑን ፍሬ ነገሩን አጣርተውና ማስረጃዎቹን መዝነው አረጋግጠዋል።ስለሆነም አመልካች ለወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ የነበሩ መሆኑ በበቂና አሳማኝ በሆነ ሁኔታ በአቃቤ ሕግ ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች የወንጀል ተጠያቂነት የለብኝም በማለት የሚያቀርቡት ቅሬታ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 23(2)፣32(1(ሀ)(ለ)፣58 እና ስለ ማታለል ወንጀል የተመለከተውን ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ያገናዘበ ሁኖ ሰላላገኘነው አልተቀበልነውም።
በወንጀል ሕግ አንቀጽ 692(1) ስር ማታለል ተፈጽሟል ለማለት አራት መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች መረጋገጥ አለባቸዉ። እነዚህም፡- አጥፉዉ ሆን ብል አሳሳች የሆኑ ነገሮችን በመናገር፣ የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባዉን ነገር በመደበቅ ወይም ላላዉን ሰዉ የተሳሳተ እምነት ወይም ግምት በመጠቀም፣ በማድረግም ሆነ ባለማድረግ መግለጽ ይኖርበታል፣ ተበዲዩ መታለል ይኖርበታል ወይም በአጥፉዉ የተገለጸለትን አምኖ ሉቀበል ይገባል፣ በሀሰት የተገለጸለትን በማመን የፈጸመዉ ተግባር መኖር አለበት፣ እንዱሁም የግል ተበዲይ በመታለለ ያጣዉ የገንዘብ ጥቅም ሉኖር ይገባል።
ወደ ተያዘዉ ጉዲይ ስንመለስም እነኚህ በሕጉ የተመለከቱት መመዘኛዎች የተሟለ በመሆናቸው አመልካችን ከወንጀለ ተጠያቂነት የሚድኑበትን አግባብ አላገኘንም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡- ቅጣትን በተመለከተ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ሕግ አንቀጽ 692/1/ በቅጣት አወሳሰን መመሪያዉ ደረጃ የወጣለትና እርከኑ የተለየ ነዉ።የግል ተበዲይ በተፈጸመባቸዉ የማታለል ወንጀል ምክንያት 447,000.00 ብር በጥሬ ገንዘብ አጥተዋል።
የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን እድሜና የጤና ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ በቀላል እስራት ሉቀጡ እንደሚገባ ከለየ በኋላ የቅጣት መጠኑን አሰልቷል።
ከዚህ መረዲት የሚቻለዉ አመልካች የብር 447,000.00 ያለአግባብ ብልጽግና የማግኘት ሀሳብ የነበራቸዉ መሆኑን ነዉ። ስለሆነም 447,000.00 ብር ደረጃ 6 ስር የሚወድቅ ሲሆን በእስራት እርከን 16፣ በገንዘብ መቀጮ ደግሞ እርከን 4 ላይ ያርፊል። በቅጣት ማክበጃነት በዐቃቤ ሕግ በኩል የቀረበ አንድ ማክበጃ በስር ፍርድ ቤት ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን ይህም የስር 1ኛ ተከሳሽ ጋር ቅድመ ስምምነት አድርገው ወንጀለን መፈፀማቸውን የሚገልጽ ሲሆን ከድርጊቱ አፈፃጸም እና ከማታለል የወንጀል ድርጊት ባህርይ አንጻር ሲታይ ምክንያቱ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 84(1(መ))ስር የሚወድቅ ሁኖ አግኝተናል። በመሆኑም አመልካች ላይ አንድ ማቅለያ ምክንያት መያዙ ተገቢ ሁኖ ተገኝቷል። በስር ፍርድ ቤት ለአመልካች በቅጣት ማቅለያነት ያለፈ ባህሪያቸው መልካም የነበረ መሆኑ በወ/ሕግ አንቀጽ 82/1/ሀ/ እና የቤተሰብ አስተዲዲሪነታቸው በአንቀጽ 86 መሰረት ተይዞላቸዋል። ይህ ችልትም እነዚህን ቅጣቶች እንደ ጠቅላላ የቅጣት ማቅለያዎች እንዲለ ተቀብሎቸዋል።
ይህ ችልት አመልካች በቀላል እስራት አማራጭ መቀጣት ይገባቸዋል በሚል የስር ፍርድ ቤት ማመኑን ቢገነዘብም የስር ፍርድ ቤት መነሻ ቅጣቱን የያዘበት ሁኔታ ሕጉ ስለ ቀላል እስራት የጊዜ ገደብ በአንቀጽ 106 ከአስቀመጠው ጋር አብሮ የሚሄድ ሁኖ አላገኘውም። ይልቁንም የሥር ፍርድ ቤት በግል ተበዲይ ላይ ደረሰ የተባለውን የገንዘብ ጥቅም ጉዲት መጠን መሰረት አድርገን እርከኑ ሲታይ እርከን 16 ማረፈ ተገቢ ሁኖ በእያንዲንደ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ምን ያህል እርከን ሉቀንስ ይገባዋል? የሚለውን ጥያቄ ወንጀለ የተፈፀመው ነባሩ መመሪያ ስራ ላይ በነበረበት ጊዜ መሆኑን ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 6 ይዘትና መንፈስ አንጻር ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ ቢመለከተውም ከነባሩ መመሪያ አንቀጽ 16(6) ድንጋጌ አንፃር ለውጥ የሚያመጣ ሁኖ ተገኝቷል።
የስር ፍርድ ቤት አመልካች ሁለት ማቅለያ ምክንያቶች እንዲሎቸው ከገለፀ በኃላ የቅጣት ማክበጃውን ይዞ እርከኑን ከእርከን 16 ወደ እርከን 17 ከፍ ከአደረገ በኋላ በዚሁ እርከን ለፍርድ ቤቱ በተተወው ፍቅድ ስልጣን ውስጥ(ከሶስት አመት ከሶስት ወር እስከ ሶስት አመት ከአስራ አንድ ወራት) ሶስት አመት ከአምስት ወር ቀላል እስራት ወስድ አመልካች በዚሁ የእስራት ቅጣት ጊዜ እንዱቀጡ ሲል ወስኗል። ሆኖም በመመሪያው መመሰረት የቅጣት ማክበጃ ከተወሰነ በኋላ ህጋዊ የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ሳይሰለ አጥፉው በማረሚያ ቤት ሁኖ የሚታሰረው የእስራት ጊዜ መጠን ሉወሰን እንደማይችል በአንቀጽ 19 ሰር የተመለከተው የቅጣት አሰላል ስርዓት ያሳያል። በመመሪያ መሰረት በድምሩ አራት እርከን ሲቀነስላቸዉ የእስር ቅጣቱ ከእርከን 17 ወደ እርከን 13 ስለሚወርድ በዚሁ እርከን ውስጥ የፍርድ ቤቱ ፍቅድ ስልጣን ደግሞ ከሁለት አመት ሶስት ወር እስከ ሁለት አመት ዘጠኝ ወር እስራት ነው።
ከዚህ ፍቅድ ስልጣን ውስጥ አመልካችና ያርማል፤ ለፈጸሙት አድራጎት ያስተምራታል፣ ላልችን ደግሞ ያስጠነቅቃል ባልነዉ በ2(ሁለት)አመት እንዱቀጡ መወሰኑ ተገቢ ሁኖ ተገኝቷል።
በዚሁም መሰረት የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
በአድዋ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ የካቲት 25 ቀን 2006 ዓ.ም ተሰጥቶ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዚያ 08 ቀን 2006 ዓ/ም ፣በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ/ም በአመልካች ላይ ያስተላለፈዉ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2(ለ-2) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች ለድርጊቱ ጥፊተኛ መባላቸው በአግባቡ ነው፣ ቅጣቱን በተመለከተ ግን ተገቢውን የቅጣት አወሳሰን መርህ ያልተከተለ በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሰጠውን የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በማሻሻል አመልካች በዚህ ጉዲይ የታሰሩት ጊዜ የሚታሰብላቸው ሁኖ በ2 (ሁለት) አመት ቀላል እስራት ሉቀጡ ይገባል በማለት ወስነናል።
የክፍለ ማረሚያ ቤት በዚህ ችልት በተሰጠው የቅጣት ውሳኔ መሰረት ቅጣቱን ተከታትል እንዱያስፈፅም ብለናል። ይፃፍ።
የቅጣት ውሳኔ የተሻሻለ መሆኑን እንዱያውቁት የዚህ ዉሳኔ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤት ይተላለፍ ብለናል።