በተደጋጋሚ በተፈፀመ የወንጀል ድርጊት የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ስለመሆኑ የወንጀል ድርጊት ለረጅም ጊዜ ሲፈፀም የቆየ ከሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀል ድርጊቱ ካቆመበት ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ ወንጀል ህግ ቁጥር 219(2) XVI
No summary available.
መጋቢት 14 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ኃይለ ወልዳ መኮንን - ጠበቃ ጳውልስ ተሰማ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ተጠሪ ያቀረበባቸውን ለእርሳቸው አገልግልት ባልታሰበ ወይም እርሳቸውን በማይመለከት ሰነድ የመገልገል የወንጀል ክስ የተመለከተው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠባቸው እና በይግባኝ ሰሚው ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የጸናው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበው ክስ ይዘት ባጭሩ፡-አመልካች ጥቅምን ወይም መሻሻልን ለማግኘት በማሰብ ትክክለኛ ስማቸው ኃይለ ወልዳ ሆኖ እያለ ሰይፈ ወልዳ እንደሆነ አድርገው በመግለጽ ለእርሳቸው አገልግልት ያልታሰበውን ወይም እርሳቸውን የማይመለከተውን እና የወንድማቸው ሰይፈ ወልዳ የሆነውን ከመድኃኒዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሰጠ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የምስክር ወረቀት (ትራንስክሪፕት) እና ከትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠ የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መልቀቂያ የምስክር ወረቀት በማቅረብ በየካቲት ወር 1977 ዓ.ም. በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተቀጠሩ በመሆኑ፣ ከተቀጠሩ በኃላ ወንጀለን ለመደበቅ በማሰብ ህዲር 30 ቀን 1979 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርበው ሰይፈ ወልዳ እና ኃይለ ወልዳ በሚለ ሁለት ስሞች ሲጠሩ እንደነበረ እና አሁን ግን ኃይለ ወልዳ በሚለው ስም ብቻ ለመጠራት እንደሚፈልጉ በመግለጽ በፍርድ ቤት በማስወሰን ይህንን የፍርድ ቤት ውሳኔ ለተቀጠሩበት መስሪያ ቤት አቅርበው ከማህደራቸው ጋር እንዱያያዝ በማድረግ እስከ ህዲር 19 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራ አስተናጋጅነት እና በመሪ የበረራ አስተናጋጅነት ሲሰሩ የቆዩ በመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. የወንጀል ሕግ በአንቀጽ 385(1)(ለ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ሀሰተኛ በምስክር ወረቀት የመገልገል ወንጀል አድርገዋል የሚል ሲሆን አመልካች ተጠይቀው በክሱ የተመለከተውን ወንጀል አላደረግሁም በማለታቸው ፍርድ ቤቱ ተጠሪ ያቀረባቸውን ሶስት ምስክሮች ምስክርነት ከሰማ እና የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኃላ ዐቃቤ ሕግ በክሱ መሰረት ያስረዲባቸው መሆኑን ገልጾ አመልካች መከላከያቸውን ማሰማት እንዱጀምሩ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 142 መሰረት ትዕዛዝ በመስጠቱ አመልካች የሰው መከላከያ የላላቸው መሆኑን ገልጸው ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ መግለጫው ላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 9 ዘርዝሮ በማስረጃነት ካቀረባቸው ሰነድች መካከል ሶስቱን በመከላከያነት ጭምር የጠቀሱ ከመሆኑም በላይ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃይለ ወልዳ በሚል ስም የተሰጠው የምስክር ወረቀቶችን፣የስራ እድገት ደብዲቤን እና በዚሁ ስም የተሞላ የጡረታ ቅጽ በመከላከያ ማስረጃነት አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱም በሁለቱ ወገኖች የቀረበውን አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ አመልካቹ በተጠሪ የቀረበባቸውን ክስ እና ማስረጃ አስተባለዋል ሉባለ የሚችለት በወንድማቸው ሰይፈ ወልዳ ስም በተሰጡ የትምህርት ማስረጃዎች ለስራ ቅጥር ስላለመገልገላቸው ወይም የትምህርት ማስረጃዎቹ የላላ ሰው ሳይሆኑ የራሳቸው ስለመሆናቸው በማስረዲት መሆኑን እና ይሁን እንጂ አመልካች ያቀረቧቸው የመከላከያ ሰነድች ከላይ ከተጠቀሱት ፍሬ ነገሮች አንደንም የማያስረደ መሆኑን ገልጾ አመልካች ባቀረቡት የሰነድ መከላከያ በዐቃቤ ሕግ ማስረጃ የተመሰረባቸውን ፍሬ ነገር ለማስተባበል አልቻለም በማለት በክሱ በተጠቀሰባቸው ድንጋጌ ስር የጥፊተኝነት ውሳኔ ከሰጠባቸው በኃላ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብል አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ድንጋጌ ደረጃ ያልወጣለት መሆኑን፣ድንጋጌው የሚያስቀጣው በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ መሆኑን፣ አመልካች ሰነደን በመገልገል ከሃያ ዓመት ላላነሰ ረጅም ጊዜ ያልተቋረጠ ጥቅም ያገኙ እና ፍርድ ቤትን ሳይቀር አሳስተው የመጀመሪያውን ወንጀል ለመሸፈን ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸው በድርጊቱ አለመፀፀታቸውን የሚያሳይ ነው በማለት የእስራት ቅጣቱን አማራጭ በመውሰድ እና ወንጀለንም በክብደቱ እና በአፈጻጸሙ በከባድ ደረጃ በመመደብ፣በድንጋጌው ስር በከባድ ደረጃ ለተመደበ ወንጀል በቅጣት አወሳሰን መመሪያው ከተቀመጠው ፍቅድ ስልጣን ውስጥ የሁለት ዓመት እስራት መነሻ አድርጎ በመያዝ፣ይህ የቅጣት መጠን በመመሪያው አባሪ አንድ በእርከን 10 ስር የሚወድቅ መሆኑን፣በዐቃቤ ሕግ በኩል የቀረበ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት አለመኖሩን፣የአመልካቹ የዘወትር ጠባይ መልካምነት እና የቤተሰብ አስተዲዲሪ መሆናቸው በሁለት የማቅለያ ምክንያትነት ሲያዙ ፍቅድ ስልጣኑን ከእርከን 10 ወደ እርከን 8 ዝቅ የሚል መሆኑን በዝርዝር ገልጾ በመጨረሻ አመልካች በእርከን 8 በተቀመጠው ፍቅድ ስልጣን መሰረት በአንድ ዓመት ከስድስት ወር ቀላል እስራት እንዱቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን ዘግቶ በማሰናበቱ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካች ወንጀለን ፈጽመዋል ከተባለበት ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ ሲቆጠር ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት አመልካች ላቀረቡት መቃወሚያ የስር ፍርድ ቤቶች የይርጋ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው ድርጊቱ ከቆመበት ህዲር ወር 2005 ዓ.ም ጀምሮ እንጂ ድርጊቱ መፈጸም ከጀመረበት ከ1977 ዓ.ም. ጀምሮ አይደለም በማለት የመወሰናቸውን አግባብነት ከወንጀል ሕግ አንቀጽ 219(2) ድንጋጌ አንጻር ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ በአብላጫ ድምጽ በተሰጠ ትዕዛዝ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም፡-
በአመልካች የቀረበው የይርጋ መቃወሚያ በስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ የተደረገው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም?
በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
የሚለትን ነጥቦች መሰረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
በዚህም መሰረት የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ አመልካች የተከሰሱበት ድንጋጌ የሚያስቀጣው በቀላል እስራት ወይም በመቀጮ ሲሆን በሕጉ በተለየ ሁኔታ በግልጽ ካልተደነገገ በቀር ቀላል እስራት ከአስር ቀን እስከ ሶስት ዓመት የሚደርስ ስለመሆኑ በወንጀል ሕጉ በአንቀጽ 106(1) ተመልክቷል።በልላ በኩል የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ጊዜን አስመልክቶ ከአንድ ዓመት በላይ በቀላል እስራት ለሚያስቀጣ ወንጀል የክስ ማቅረቢያው የይርጋ ጊዜ አምስት ዓመት ስለመሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 217(1)(ሰ) ስር ተደንግጎ ይገኛል።የክስ ማቅረቢያ የይርጋ ዘመን መቆጠር የሚጀምረው በመርህ ደረጃ ጥፊተኛው ወንጀለን ከፈጸመበት ቀን አንስቶ ስለመሆኑ እና ይሁን እንጂ የወንጀለ ድርጊት እየተደጋገመ ተፈጽሞ እንደሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የመጨረሻው የወንጀል ድርጊት ከተፈጸመበት ቀን አንስቶ ስለመሆኑ፣እንዱሁም የወንጀለ ድርጊት ለረጅም ጊዜ ሲፈጸም የቆየ ከሆነ የይርጋ ዘመኑ መቆጠር የሚጀምረው የወንጀለ ድርጊት ካቆመበት ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ በዚሁ ሕግ በአንቀጽ 219(2) ስር በዝርዝር ተመልክቷል።
አመልካች በአየር መንገደ የተቀጠሩት በወንድማቸው ሰይፈ ወልዳ ስም የተሰጠውን የትምህርት ማስረጃ በማቅረብ መሆኑ እና እስከ ህዲር ወር 2005 ዓ.ም. ድረስ በአየር መንገደ ውስጥ በስራ ላይ ሉቆዩ የቻለትም በእነዚሁ የትምህርት ማስረጃዎች አማካይነት እና መነሻ በተፈጠረ የስራ ቅጥር ግንኙነት ወይም የስራ ውል መሰረት መሆኑ በክርክሩ ተረጋግጧል። የይርጋ ጊዜው መቆጠር መጀመር የሚገባው ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ ነው በማለት አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት አመልካች ለወንድማቸው ለአቶ ሰይፈ ወልዳ የተሰጠውን የትምህርት ማስረጃ በ1977 ዓ.ም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ አቅርበው የተመዘገቡ ቢሆንም የተቀጠሩት ግን ፈተናውን አመልካች ራሳቸው ተፈትነው በመሆኑ እና የተቀጠሩበትን ስራ ለረጅም ጊዜ ሲሰሩ የነበረውም አየር መንገደ በሰጣቸው ስልጠና ባገኙት ዕውቀት እንጂ በምዝገባ ጊዜ ባቀረቡት የትምህርት ማስረጃ ባለመሆኑ ስልጠናውን አጠናቀው ስራ ከጀመሩ እና በተለይ ደግሞ ኃይለ ወልዳ በሚለው ስም ብቻ እንዱጠሩ በፍርድ ቤት ካስወሰኑበት ከ1979 ዓ.ም. ጀምሮ በሰይፈ ወልዳ ስም በተሰጠው የትምህርት ማስረጃ ተገልግለዋል ወይም ጥቅምን ወይም መሻሻልን አግኝተዋል ሉባለ አይገባም በማለት መሆኑን ተገንዝበናል።ይሁን እንጂ አመልካች ለስራው የተመዘገቡትም ሆነ ፈተናውን ወስደው ለስልጠና እና ለስራ ቅጥር የበቁት የእርሳቸው ባልሆኑ የትምህርት ማስረጃዎች በመገልገል በመሆኑ አመልካች ስልጠናውን ካጠናቀቁበት ቀንም ሆነ ስራ ላይ ከተሰማሩበት ቀን ጀምሮ የትምህርት ማስረጃዎቹ አገልግልት ተቋርጧል ልባል የሚችልበት አግባብ የለም።ለስራው የተቀጠሩት የራሳቸው ባልሆኑ የትምህርት ማስረጃዎች በመገልገል መሆኑን ስልጠናውን ባጠናቀቁበት ቀን ወይም ስራ ላይ በተሰማሩበት ቀን ለአየር መንገደ አስታውቀው የነበረ ስለመሆኑ እና በዚህም ምክንያት የእርሳቸው ባልሆኑ የትምህርት ማስረጃዎች የመገልገላቸው ሁኔታ እንዱያበቃ ወይም እንዱቋረጥ የተደረገ ስለመሆኑ አመልካች ያቀረቡት ክርክር የለም።ለረጅም ጊዜ ሲፈጸሙ የቆዩትን ወንጀልች የይርጋ ዘመን አቆጣጠር በተመለከተ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ቀደም ሲል በመዝገብ በ12/07/2005 ዓ.ም. የሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ለተያዘው ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለው መሆኑን ተገንዝበናል።በመሆኑም አመልካች ያቀረቡትን የይርጋ መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሕጉን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ በተመለከተው ፍርድ ቤት አመልካች ወንጀለን አላደረግኩም በማለት የተከራከሩ ቢሆንም የራሳቸው ያልሆኑትን እና ሰይፈ ወልዳ ለተባለ ወንድማቸው የተሰጡትን የትምህርት ማስረጃዎች የራሳቸውን ፍቶግራፍ በመለጠፍ የራሳቸው እንደሆኑ አስመስለው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በማቅረብ በ1977 ዓ.ም ለስራ ቅጥር የተገለገለበት መሆኑ እና በዚህ ሁኔታ በተቋቋመ የስራ ውል መሰረት እስከ ህዲር ወር 2005 ዓ.ም ድረስ ጥቅም ሲያገኙበት የነበረ መሆኑ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን እና አመልካች በቤተሰብ ውስጥ ሰይፈ በሚል ላላ ስም ተጠርተው የማያውቁ፣ ይልቁንም ሰይፈ ወልዳ ከኢትዮጵያ ውጭ በመኖር ላይ የሚገኙ የአመልካች ታላቅ ወንድም ስለመሆናቸው የአመልካች ወንድም መሆናቸውን በገለጹት 2ኛ የዐቃቤ ሕግ ምስክር ጭምር የተመሰከረ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።አመልካች ያቀረቧቸው የሰነድ ማስረጃዎች ቀደም ሲል እንደተገለጸው አመልካች በወንድማቸው ሰይፈ ወልዳ ስም በተሰጡ የትምህርት ማስረጃዎች ለስራ ቅጥር ስላለመገልገላቸው ወይም የትምህርት ማስረጃዎቹ የላላ ሰው ሳይሆኑ የራሳቸው ስለመሆናቸው የማያስረደ መሆኑንም መዝገቡ ያመለክታል።ወንጀለን ስለመፈጸሜ በማስረጃ አልተረጋገጠብኝም ወይም የተጠሪን ማስረጃ በመከላከያዬ አስተባብያለሁ በማለት አመልካች በሰበር አቤቱታቸው በግልጽ ያቀረቡት ክርክርም የለም።የቅጣት ውሳኔውም ቢሆን ከላይ በዝርዝር እንደተገለጸው የወንጀለን አፈጻጸም ሁኔታዎች፣ሕጉን እና የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያውን መሰረት በማድረግ በአግባቡ የተሰጠ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ16/10/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ13/12/2006 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ቁጥር 195(2)(ለ)(2) መሰረት ፀንቷል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች እንዱሁም አመልካች ለሚገኙበት ማረሚያ ተቋም ይላክ። ለአመልካቹም በዚያው በኩል ይድረስ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.