አንድ ሰው የወንጀል ድርጊቱን የፈፀመው ከላላ ሰው ስምምነት በማድረግ ከሆነ እንደማክበጃ የሚወሰድ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁ.2/2006 ከመውጣቱ በፉት በተፈፀመ ወንጀል ቅጣትን ለመወሰን ለተከሳሹ የሚጠቅመውን የቅጣት መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ የሚገባ ስለመሆኑ ወ.ሕ/ቁ. 38(1) እና 84(1)(መ)
No summary available.
መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- አቶ ተፈሪ ንጉሴ ጥላሁን - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የፋዳራል ዐቃቤ ህግ /ዐ/ህግ በላይ ወርቅነህ ቀረቡ/ የመዝገብ ከዚህ መዝገብ ጎን ለጎን ተመርምሮ ተጣምሮ ተወስነኗል።
መዝገቦቹ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ነው። አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች መሰረታዊ የህግ ስህተት የፈጸሙ በመሆኑ በሰበር ይታረምልኝ የሚል አቤቱታ በማቅረቡ አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ነው። ጉዲዩ የማታለል ወንጀል የሚመለከት ነው። ተጠሪ በአመልካች ላይ በመ/ቁ. 136720 ሁለት ክሶች አቅርቧል። አንደኛው ክስ የወ/ህ/ቁ 692(1) የተመለተከውን በመተላለፍ ከግበረ አበሩ በመመሳጠር ባልሽ ጥር 2005 ይሞታል ከመሞቱ በፉት ገንዘብ አምጪ በማለት አሳሳች ነገሮችን በመናገር ከግል ተበዲይ መሰረት ስንታየሁ አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር እና ዋጋው ሀያ አምስት ሺህ ብር የሆነ ወርቅ በማታለል መወሰደ ፤ ሁለተኛው ክስ የወ/ህ/ቁ.692(1) የተመለከተውን በመተላለፍ የግል ተበዲይ ወ/ሮ አጸደ ስንታየሁ ባለቤትሽ ይህንን ሱስ የሚያቆመው ገንዘብ እና ጌጣጌጥ ስትስጪኝ ነው ፤
ገንዘቡ እና ጌጣጌጡም ተፀልዮበት ሲመልስ ነው የሚድነው በማለት ሀምሳ ሺህ ብር እና ዋጋው ዘጠና ሁለት ሺህ ብር የሆነ ወርቅ ከእነ መጫወቻው መወሰደን የሚያሳይ ነው። ላለው ክስ በመ/ቁ. 136734 የቀረበ ሲሆን አመልካች ግበረ አበሩ መላከ ገነት ሳሙኤል አስፊው የተባለ ግለሰብ የግል ተብዲይ የሆነችው ወ/ሮ ዘበናይ ከበደን የተሳሳተ እምነት በመጠቀም የሚያድንሽን ሰው አውቃለሁ ላገናኝሽ በማለት ከአሁኑ አመልካች ካገናኙዋት በኋላ ፤ ከያዘሽ በሽታ በህክምና አትድኝም እኔ ነው የሚያድነሽ ለዚህም አንድ መቶ ስልሳ ሺህ ብር እና ዋጋው ስልሳ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር የሚሆን ወርቅ ተቀብል በመሰወሩ ወ/ህ/ቁ. 692(1) የተመለከተውን ተላልፎል የሚል ነው።
አመልካች የቀረበበት ክስ ክድ በመከራከሩ ፍ/ቤቱ የዐ/ህግ ምስክሮች አዲምጧል። አመልካችም የበኩለን የመከላከያ ማስረጃ በማስቀረብ አሰምቷል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ በዐ/ህግ የቀረቡ ምስክሮች አመልካች የተለያዩ የማታለያ ዘዳዎች ተጠቅሞ በሁለቱም መዝገቦች የተጠቀሱትን የግል ተበዲዮች ገንዘብ እና ወርቅ መወሰደ ፤
የማታለል ድርጊቱ ሲፈጸም ዋና ወንጀል አድራጊ በመሆን የተሳተፈት የግል ተበዲይ አፀደ ስንታየሁ የነፍስ አባት የሆኑት መላከ ገነት የተባለትን ግለሰብ አመልካች በሽታን የመፈወስ ችልታና አቅም እንዲለው በመግለጽ የግል ተበዲዮች የተሳሳተ እምነት እና ግምት እንዱይዙ ማድረጋቸው ፤ በአመልካች በኩል የቀረበው አንድ የመከላከያ ምስክርም ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት ጊዜ እና ቦታ አመልካች ከአዱስ አበባ ውጭ የነበረ ስለመሆኑ የሰጠው የምስክርነት ቃል ተአማኒነት የላለው እና የዐ/ህግ ክስና ማስረጃ የማያስተባብል ነው በማለት በሶስቱም ክሶች ጥፊተኛ ነው በማለት ፈርደዋል። ቅጣት በተመለከተም በዓቃቤ ህግ በኩል የቀረበው አንድ የቅጣት ማክበጃ እንዱሁም በአመልካች በኩል ሁለት የቅጣት ማቅለያዎች በመቀበል በመ/ቁ.
136720 በሁለቱም ድርጊቶች በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እና ብር 6,000 እንዱሁም በመ/ በሶስት ዓመት ጽኑ እስራት እና ብር 2,000 የሁለቱም ድምር በወ/ህ/ቁ 186 መሰረት በስምንት ዓመት ጽኑ እስራት እና ብር 8,000 መቀጮ እንዱቀጣ ወሰኗል።
አመልካች በሁለቱም መዝገቦች የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ የጠየቀ ቢሆንም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ወደ ጉዲዩ ለመግባት የሚያስችል በቂ ምክንያት ባለመገኘቱ ይግባኙን በማሰናበት መዝገቡን ዘግቷል። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። ጉዲዩ ለሰበር ያስቀርባል የተባለ በመሆኑ ተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር አደርገዋል። የአመልካች ሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘት፡- የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ፤ ተፈጸመ የተባለው ድርጊት አንድ ወንጀል ከመስራት ሐሳብ የመነጨ መሆኑን ፤ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የቅጣት መመሪያ አዱስ ሳይሆን የቀደም መሆን እንዲለበት ወንጀለ ከላላ ግብረ አበር በመሆን ፈጸመዋል መባለ በአግባቡ አለመሆኑን የሚገልጽ ነው። ተጠሪ በበኩለ የሰጠው መልስ ያስቀርባል ከተበለው ነጥብ አንፃር ሆኖ ወንጀለ ከብድ መወሰኑ በህጉ አግባብ መሆኑ ፤ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የቅጣት መመሪያ ግን ለአመልካቹ የሚጠቅም የቀደሞ የቅጣት መመሪያ ከሆነ ቢወሰድለት እንደማይቃወም ገልፀል።
የመልስ መልስም ቀርበዋል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች እና ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረነውም በዚህ ችልት ዕልባት የሚሹ መሰረታዊ ነጥቦች አንደኛው የስር ፍርድ ቤቶች ወንጀለ በግብረ አበርነት የተፈጸመ ነው በማለት በወ/ህ/ቁ. 84(1)(መ) ጉዲዩን በማክበድ መወሰናቸው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? ሁለተኛ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 ነው ወይስ ቁጥር 2/2006? የሚለ ናቸው።
የመጀመሪያው ነጥብ በተመለከተ፡- አመልካች በሶስት የግል ተብዲዮች የማታለል ወንጀል በመፈጸም ጥሬ ገንዘብና ወርቅ መውሰደ የስር ፍርድ ቤቶች ፍሬ ነገር በማጣራት እና ማስረጃ በመመዘን ስልጣናቸው ከድምዲሜ ላይ ደርሰዋል። አመልካች የወንጀል ድርጊቱን ለመፈጸም ግብረ አበር ሆነዋል የተባለት መላከገነት የተባለ የቤተክርስትያን ሰው ነኝ ባይ ሲሆኑ አፀደ ስንታየሁ የተባለችው ተባዲይ የነፍስ አባት መሆናቸው የተካደ ጉዲ አይደለም። የግል ተበዲዮች አለን የሚለት የጤና ችግር ፤ ሉመጣ ከሚችለው አስደንጋጭ ችግር ለመታደግ ወይም ባለቤታቸው ከነበራቸው የባህሪ ችግር ለማስተካከል ገንዘብና ወርቅ በማስያዝ ፀልት ማድረግ እንደ ብቸኛ አማራጭ መወሰደ ከስር ፍርድ ቤት መዝገብ መረዲት ተችሎል። የግል ተብዲዮች ገንዘብና ወርቅ እንዱሰጡ የማሳመን ሚና የተጫወቱት የግል ተበዲይ አፀደ ስንታየሁ የነፍስ አባት ሲሆኑ በሶስቱም የግል ተበዲዮች ከፍተኛ የመንፈስ ተፅዕኖ የፈጠሩት እኚሁ የነፍስ አባት መላከገነት መሆናቸው ከአጠቃላይ የመዝገቡ ይዘት የምንረዲው ነው። በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው ጉዲይ ከህጉ ጋር ስናገናዝበው አንድ ሰው የወንጀል ድርጊቱ የፈጸመው ከላላ ሰው ስምምነት በማድረግ ከሆነ እንደ ማክበጃ እንደሚወሰድ በወ/ህ/ቁ. 38(1) እና 84(1)(መ) ተደንግጓል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች እና ግበረ አበር የነበሩት ግለሰብ የግል ተበዲዮች በማታለል ገንዘብና ወርቅ ለመውሰድ አስቀደመው በመስማማት ድርጊቱ ስለመፈጸማቸው ከቀረበው የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ የምንረዲው ነው። አመልካች እና ግበረ አበር የተባለትን መላከገነት የግል ተበዲዮች ሉያሳምን ይችላል ብለው ያቀደትን ስልት ወደ ተግባር በማሽጋገር የግል ተበዲዮች ማህበራዊ ችግር ፤
የጤና ችግር እንደምክንያት ተጠቅመው ሃይማኖታቸውን መሰረት በማድረግ ከፍተኛ የማታለል ድርጊት ፈጸመዋል። የግል ተበዲይ አፀደ ስንታየሁ የነፍስ አባት የሆኑትን መላከገነት የተባለትን ግለሰብ የግል ተበዲዮች በአመልካች ላይ እምነት ኖሯቸው ገንዘብና ወርቅ እንዱሰጣቸው ያላቸው ሀይማኖታዊ ግንኙነት ያለአግባብ ተጠቅመውበታል። ይህ ደግሞ በወ/ህ/ቁ. 84(1) (መ) እንደተመለከተው ወንጀለ በሁለት ሰዎች ስምምነት (prior agreement) የተፈጸመ መሆኑ የሚሳይ ስለሆነ የስር ፍርድ ቤቶች እንደ ማክበጃ መውሰዲቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸሙን አያሳይም። አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረበው ቅሬታ የህግ መሰረት የለውም።
ሁለተኛው ነጥብ በተመለከተ፡- አመልካች የተከሰሰባቸው የማታለል ወንጀልች በ 2005 ዓ/ም የተፈጸሙ ናቸው። ወንጀለ በተፈጸመበት ጊዜ ስራ ላይ የነበረው የቅጣት መመሪያ ቁጥር 1/2002 ስለመሆኑ ግራ ቀኙ ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በ
እና ላልች መዝገቦች በሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉም ለተከሳሽ የሚጠቅም የቅጣት መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ወሰኗል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ድርጊቱ ሲፈጸም በተግባር ላይ በነበረው የቅጣት መመሪያ መሰረት ለእያዲንደ የቅጣት ማቅለያ ሁለት እርከን የሚቀነስለት መሆኑ ተገንዝበናል። በመ/ በተሰጠው የቅጣት ውሳኔ የሁለቱም ድንጋጌዎች ቅጣት ተደምሮ በእርከን 22 የሚወድቅ ሲሆን በሁለተኛው መዝገብ የመ/ቁ. 136734 እርከን 17 ስር የሚወድቅ ነው። በሁለቱም መዝገቦች ቅጣት ተነጣጥል የተወሰነ ሲሆን አፈጻጸም በተመለከተ ግን ተጣምሮ እንዱፈጸም የሥር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቷል። በመሆኑም በመጀመሪያው የመዝገብ አመልካች ሁለት የማቅለያ ምክንያቶች በማቅረቡ በእያዲንደ ማቅለያ በቀድሞ የቅጣት መመሪያ አንቀጽ 17 መሰረት ሁለት እርከን ዝቅ የሚል በመሆኑ በአጠቃላይ ከመነሻ እርከኑ አራት እርከን ወደታች ዝቅ ይላል። በዚህ መሰረት በእርከን 18 ሥር የሚወድቅ ነው። ሁለተኛው የመዝገብ በእርከን 15 ሥር የሚወድቅ ነው።
ከላይ እንደተመለከተው የወንጀል ድርጊቱ በ 2005 ዓ.ም የተፈፀመ መሆኑን ፤ ይህ ሰበር ሰሚ ችልትም በሰ/መ/ የሰጠው አስገዲጅ ውሳኔ በየትኛውም ደረጃ ባለ ፍርድ ቤቶች ተፈፃሚ እንደሚሆን በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) የተደነገገ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤቶች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 6(1) እና በቀድሞ የቅጣት መመሪያ መሰረት ያቀረበው ማቅለያ የበለጠ ዝቅ የሚያደርግለት ነበሩ ፣የቅጣት መመሪያ መሆኑ እየታወቀ መታለፈ በአግባቡ ባለመሆኑ ፤
በቅጣት ረገድ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ በማሻሻል መወሰኑ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህ መሰረት አመልካች የፈጸመው የማታለል ወንጀል ያስከተለው ጉዲት በልላ በኩል አመልካች ሉያስተምር ሉያስጠነቅቅ የሚያስችል የወንጀል ሕጉ ዓላማና ግብ የሚያሳካ ቅጣት መወሰን ተገቢ ይሆናል። በዚህ መሰረት አመልካች በ መ/ የተወሰነበትን ቅጣት በማሻሻል በእርከን 18 ከተደነገገው 4 ዓመት ጽኑ እስራት በመውሰድ በመ/ በእርከን 13 ከተደነገገው ሁለት ዓመት ከ 6 ወር ጽኑ እስራት በመውሰድ በድምር በስድስት ዓመት ከ 6 ወር ጽኑ እስራት እና 8,000 ብር መቀጮ እንዱቀጣ የሚከተለው ውሳኔ ሰጥቷል።
1 የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ 08/04/2006 የሰጠው ፍርድ ፤
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ በሰኔ 30/2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 195(2)(ለ)(2) መሰረት ተሻሽሎል። ይፃፍ።
2 አመልካች በተከሰሰባቸው የወ/ሕ/ቁ 692(1) ሥር ጥፊተኛ መባለ በአግባቡ ነው በማለት ወስነናል።
3 የአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት አመልካች ከአሁኑ በፉት የታሰረበት ካለ በቅጣቱ የሚካተት ሆኖ እጁ ከተያዘበት ጀምሮ በስድስት ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጣ የተወሰነ መሆኑን አውቆ እስራቱን ተቆጣጥሮ እንዱያስፈጽም ታዟል። ይፃፍ።
4 የዚህ ፍርድ ግልባጭ በሰ/መ/ ይያያዝ ብለናል።
መዝገቡ ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.