በልላ ሰው የስራ ድካም ወይም የላላ ሰው ሃብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው አለአግባብ ጥቅም ባገኘበት መጠን ለባለሃብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ይህ አድራጎት ባደረሰበት ጉዲት መጠን ኪሳራ መክፈል የሚገባው ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.2162
No summary available.
ሐምል 2 ቀን 2007 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- አቶ ኃይለየሱስ መንግስቴ ይግዛው - ጠበቃ ውብሰራ ሹመቴ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አማኑኤል ፀጋ የከተማ ሱቅ ቤቶች ልማት አክሲዮን ማህበርጠበቃ ደረጄ ኢቲቻ ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዲዩ ከንግድ ቤት ኪራይ ውል አፈጻጸም ጋር ተያይዞ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽ በነበረው የአሁኑ ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። ከሳሽ በ01/11/2003 ዓ.ም አዘጋጅተው ያቀረቡት ክስ ይዘትም ባጭሩ፡- በአዱስ አበባ ከተማ በአዱስ ከተማ ከፍለ ከተማ በቀበላ 08/09/18 ከሚገኙት የተከሳሽ ድርጅት ሱቆች መካከል ከሳሽ በ01/11/2001 ዓ.ም በተደረገ ውል በምድር ቤት የሚገኝ 345 ካ.ሜ ስፊት ያለው አንድ የንግድ ሱቅ በካሬ ሜትር በብር 30 (ሰላሳ) ሂሳብ ለአምስት ዓመት ተከራይተው የምግብ እና መጠጥ ቤት ንግድ ፈቃድ በማውጣት እየሰሩበት እያለ ተከሳሽ ድርጅት ከ22/09/2003 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሱቁ የሚመጣውን የኤላክትሪክ እና የውሃ መስመር በማቋረጡ የኤላክትሪክ መስመሩ በፖሉስ እና በኤላክትሪክ ኃይል ባለስልጣን ትብብር እስከተከፈተበት 22/10/2003 ዓ.ም ድረስ ከሳሽ ከንግድ ቤቱ ስራ በየቀኑ ያገኙ የነበረውን የተጣራ ትርፍ ብር 10,000 (አስር ሺህ) ለ31 ቀናት በማጣታቸው የብር 310,000 (ሶስት መቶ አስር ሺህ) ጉዲት እንደደረሰባቸው፣ ተከሳሽ የውሃ መስመሩን በኋላም ቢሆን እንዲልከፈተው፣ ከ22/10/2003 ዓም ጀምሮ እስከ 30/12/2003 ዓ.ም ድረስ ባለት 68 ቀናት ደግሞ ገቢው በግማሽ የቀነሰ እና ከሳሽ በየቀኑ የብር 5000 (አምስት ሺህ) ገቢ እንዲጡ፣በእነዚህ 68 ቀናት ከሳሽ ያጡት ገቢ ብር 340,000 (ሶስት መቶ አርባ ሺህ) እንደሆነ የሚገልጽ ሆኖ ተከሳሽ ድርጅት በከሳሽ ላይ ላደረሰው ጉዲት በድምሩ ብር 650,000 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ለከሳሽ እንዱከፍል ዲኝነት የተጠየቀበት ነው።
ተከሳሽ ድርጅት በበኩለ በ26/11/2003 ዓ.ም በሰጠው መልስ ተከሳሽ የንግድ ሱቁን ያከራየው አኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ለተባለ ተከራይ እንጂ ለከሳሽ አለመሆኑን፣ ከሳሽ በተከሳሽ ድርጅት ንብረት የተገለገለት የኪራይ ውል እና መብት ሳይኖራቸው መሆኑን፣ ከሳሽ ከተከሳሽ ማህበር ጋር በራሳቸው ስም ያደረጉት የኪራይ ውል ባለመኖሩ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 33 (2) መሰረት በተከሳሽ ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችል መብት እና ጥቅም የላላቸው መሆኑን፣ተከሳሽ ማህበር የውሃም ሆነ የኤላክትሪክ መስመር ያላቋረጠባቸው መሆኑን፣የኤላክትሪክ መስመሩ አውቶማቲክ የጠፊው በራሱ ችግር መሆኑን፣ተከሳሽ ማህበር የኤላክትሪክ መስመሩን አቋርጦት ቢሆን ኖሮ እንኳ ከሳሽ ጄኔሬተር ገዝተው ጉዲቱን መቀነስ ሲችለ የብር 650,000 ጉዲት ደርሶብኛል በማለት ክስ ማቅረባቸው ተገቢነት የላለው መሆኑን በዝርዝር በመግለጽ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክሯል።
በልላ በኩል ከሳሽ ከተከሳሽ ማህበር ጋር ያደረጉት ውል ሳይኖር በስራ አስኪያጅነት በሚመሩት አኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስም በተከራዩት የተከሳሽ የንግድ ቤት ውስጥ የንግድ ፈቃደን በራሳቸው ስም አውጥተው የንግድ ስራ በማከናወን በተከሳሽ ማህበር ንብረት አላግባብ የበለጸጉ መሆኑን ገልጾ በአኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስም የንግድ ቤቱን ከያዙበት በ01/11/2001 ዓ.ም ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት 26/11/2003 ዓ.ም ድረስ በካሬ ሜትር በአነስተኛ ዋጋ በብር 50 (ሂሳብ) የ345 ካ.ሜ ስፊት ያለው የንግድ ቤት ኪራይ ብር 638,250 (ስድስት መቶ ሰላሳ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ) ከነወለደ እንዱከፍለ፤ክሱ ከቀረበበት ቀን በኃላ ቤቱን እስኪያስረክቡ ድረስ ያለውን ኪራይም በተመሳሳይ ስላት መሰረት ከነወለደ እንዱከፍለ እና ቤቱን እንዱያስረክቡ ይወሰንለት ዘንድ በ26/11/2003 ዓ.ም የተዘጋጀ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አቅርቧል። ለዚህ ክስ ከሳሹ በ08/03/2004 ዓ.ም በፍሬ ጉዲዩ ረገድ በሰጡት መልስ በካሬ ሜትር ብር 50 ሂሳብ ለመክፈል ከሳሽ ከተከሳሽ ጋር ያደረጉት ስምምነት አለመኖሩን፣ከአኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር ውለ የተደረገው በካሬ ሜትር በብር 30 ሂሳብ መሆኑን፣ አስቀድሞ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ሳይኖር ኪራዩ ተከፍልት ቤቱን ለማስለቀቅ ተከሳሽ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት ሉኖረው የማይገባ መሆኑን በዝርዝር በመግለጽ የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም ከሳሽ የንግድ ቤቱን ከተከሳሽ ማህበር ስለመከራየታቸው ያቀረቡት ማስረጃ አለመኖሩን እና ከተከሳሽ ማህበር የንግድ ቤቱን የተከራየው አኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንደሆነ በማስረጃ መረጋገጡን ገልጾ ከሳሽ ከተከሳሽ ማህበር ጋር ያደረጉት ውል ባለመኖሩ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 33 መሰረት በተከሳሹ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት የላቸውም በማለት ዋናውን ክስ በ24/09/2004 ዓ.ም. በትዕዛዝ ውድቅ አድርጓል። ቀጥልም የተከሳሽ ከሳሽነት ክሱን በተመለከተ ክሱን ከሰማ በኃላ የመጀመሪያ ደረጃ የመቃወሚያ ነጥቦቹን በ03/03/2005 ዓ.ም በዋለው ችልት ውድቅ አድርጎ በማለፍ በ02/05/2005 ዓ.ም የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኃላ የግራ ቀኙን አጠቃላይ ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ የከሳሽ ተከሳሽ ከተከሳሽ ከሳሽ ጋር በራሳቸው ስም ያደረጉት የኪራይ ውል ሳይኖር በማህበር ስራ አስኪያጅነታቸው የኪራይ ውለን በአኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስም ከተዋዋለ በኃላ በራሳቸው ስም የንግድ ፈቃድ አውጥተው የንግድ ስራ ሲያከናውኑ መቆየታቸው መረጋገጡን፣ይህም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2162 ስር እንደተመለከተው በተከሳሽ ከሳሽ ንብረት አላግባብ መበልጸጋቸውን የሚያመለክት መሆኑን፣የግራ ቀኙ ምስክሮች በተሰሙበት ጊዜ አካባቢ በ3ኛ ፍቅ ላይ የሚገኙት የንግድ ቤቶች በወር በካሬ ሜትር በብር 120 ሂሳብ እንደሚከራዩ በተከሳሽ ከሳሽ ምስክሮች የተገለጸ መሆኑን፣የከሳሽ ተከሳሽ የያዙት የንግድ ቤት የሚገኘው በምድር ቤት ላይ በመሆኑ ኪራዩ በፍቅ ላይ ከሚገኙት የንግድ ቤቶች በላይ እንደሆነ ግምት የሚወሰድበት መሆኑን እና በዚህም ምክንያት በተከሳሽ ከሳሽ የተጠየቀው በካሬ ሜትር በወር ብር 50 የኪራይ ስላት ተቀባይነት ያለው እና ምክንያታዊ መሆኑን በዝርዝር ገልጾ የከሳሽ ተከሳሽ ይዘውት የሚገኙትን የንግድ ቤት ለተከሳሽ ከሳሽ እንዱያስረክቡ፣ በአኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስም የንግድ ቤቱን ከያዙበት በ01/11/2001 ዓ.ም ጀምሮ ውሳኔው እስከተሰጠበት 19/06/2005 ዓ.ም. ድረስ ላለው የ43 ወራት ከ19 ቀናት ጊዜ ኪራዩን በካሬ ሜትር በብር 50 እና በየወሩ በብር 17,250 (አስራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ) ሂሳብ በድምሩ ብር 752,675 (ሰባት መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ሰባ አምስት) ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ለተከሳሽ ከሳሽ እንዱከፍለ፤ውሳኔው ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ቤቱን እስኪያስረክቡ ድረስ ያለውን ኪራይም በተመሳሳይ ስላት በወር ብር 17,250 (አስራ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ) ሂሳብ ከነወለደ እንዱከፍለ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ይግባኝ ዘግቶ በማሰናበቱ ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካች በአከራካሪው ቤት የምግብና የመጠጥ የንግድ ፈቃድ አውጥተው ሲሰሩበት የነበረው በስራ አስኪያጅነት ሲመሩት በነበረው አኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስምም ቢሆን ለተጠሪ ሉከፈል የሚገባውን የአንድ ዓመት ከሶስት ወር ቅድሚያ ኪራይ ከፍለው መሆኑ ባላከራከረበት እና በስሙ ኪራዩ የተከፈለበትን ቤት አመልካች ለግላቸው አላግባብ እየሰሩበት ነው በማለት አኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሳይቃወም አመልካችን ሕገወጥ ብልጽግና አግኝተሃል በሚል በግራ ቀኙ መካከል ጭቅጭቅ ከተፈጠረ እና የአመልካች የንግድ እንቅስቃሴ ከቆመ በኃላ ያለውን የቤት ኪራይ ከነወለደ እንዱከፍለ የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ያላግባብ ስለመበልጸግ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2162 ከተመለከተው ድንጋጌ አንጻር ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዲዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው፡-
አመልካቹን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
አመልካቹ ኃላፉ የተደረጉበት የኪራይ ገንዘብ መጠን ተገቢነት ያለው ነው ወይስ አይደለም?
የሚለ ነጥቦች መሆናቸውን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዚሁ ነጥቦች አንጻር መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ ከተጠሪ ጋር የንግድ ቤት ኪራይ ውል የገባው አመልካች ሳይሆኑ አኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መሆኑ፣አመልካች የአኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ መሆናቸው፣አኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በውል ከተጠሪው በተከራየው የንግድ ቤት ውስጥ የምግብ እና የመጠጥ አገልግልት ንግድ ፈቃድ አውጥተው የንግድ ስራ ሲያከናውኑ የነበሩት አመልካች መሆናቸው፣አመልካች የንግድ ፈቃድ አውጥተው የንግድ ስራ ሲያከናውኑበት ለነበረው የተጠሪ ቤት ከተጠሪው ጋር የገቡት የኪራይ ውል አለመኖሩ በአመልካቹ ያልተካደ እና በስር ፍርድ ቤትም የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች ናቸው።በመሰረቱ አኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ከአመልካቹ የተለየ የራሱ ሕጋዊ ሰውነት ያለው በመሆኑ አመልካቹ የማህበሩ ስራ አስኪያጅ መሆናቸው በንግድ ቤቱ የንግድ ስራ ሲያከናውን የነበረው አመልካች በስራ አስኪያጅነት የሚመሩት ማህበር ነው ልባል የሚችልበት የሕግ አግባብ አይኖርም።በልላ ሰው የስራ ድካም ወይም የላላ ሰው ሀብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው አላግባብ ጥቅም ባገኘበት መጠን ለባለሀብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ይህ አድራጎት ባደረሰበት ጉዲት መጠን ኪሳራ መክፈል የሚገባው ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2162 ይደነግጋል።አመልካች በተጠሪው ሀብት መገልገላቸው የተረጋገጠ ሲሆን በተጠሪው ሀብት ለመገልገል ያስቻላቸው ሕጋዊ ምክንያት ስለመኖሩ ማስረዲት እንዲልቻለ የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል። እንዱህ ከሆነ ደግሞ ከላይ በተጠቀሰው ድንጋጌ መሰረት በተጠሪው ሀብት አላግባብ በመገልገል ባገኙት የማይገባ ብልጽግና መጠን ለተጠሪው ኃላፉ የማይደረጉበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም። በመሆኑም አመልካቹን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የውሳኔ ክፍል የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ የላላ ሰው ሀብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው ለባለሀብቱ ኪሳራ ለመክፈል የሚገደደው ከዚሁ ተግባሩ ባገኘው ጥቅም መጠን እና በአንጻሩ በባለሀብቱ ላይ ባደረሰው ጉዲት መጠን ስለመሆኑ ከላይ የተጠቀሰው ድንጋጌ ያመለክታል። ተጠሪው ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን የንግድ ቤት ለአኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያከራየው ከ01/11/2001 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ዓመታት በካሬ ሜትር በብር 30 (ሰላሳ) ሂሳብ ስለመሆኑ ተጠሪው ራሱ በስር ፍርድ ቤት በማስረጃነት ያቀረበው የኪራይ ውል ያመለክታል። የኪራይ ተመኑን በመካከል ተጠሪ የመጨመር መብት ያለው ስለመሆኑም የኪራይ ውለ አያመለክትም። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው በኪራይ ውለ መሰረት አኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የንግድ ቤቱን ይዞ ለአምስት ዓመታት ተገልግልበት ቢሆን ኖሮ ተጠሪው ሉያገኝ ይችል የነበረው ገቢ በወር በካሬ ሜትር 30 ሂሳብ ተሰልቶ የሚገኘውን ጥቅም መጠን ነው። አመልካች የንግድ ቤቱን አላግባብ ይዘው በመገልገል ተጠሪውን ላሳጡት ጥቅምም ለተጠሪው ኪሳራ መክፈል የሚገባቸው ተጠሪው ባጣው ገቢ መጠን በመሆኑ አመልካች ኪሳራውን በካሬ ሜትር በብር 50 (ሃምሳ) ሂሳብ ለመክፈል የሚገደደበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም። አመልካቹ በስራ አስኪያጅነት በሚመሩት አኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስምም ቢሆን የአንድ ዓመት ከሶስት ወር ኪራይ የከፈለ በመሆኑ ይኸው የኪራይ ገንዘብ ተጠሪው ከአመልካች ከሚፈልገው ገንዘብ ተቀናሽ መደረግ ይገባው ነበር በማለት አመልካች ያቀረቡትን እና በአጣሪው ችልትም በጭብጥነት የተያዘውን የአቤቱታ ነጥብ በተመለከተ አመልካቹ በዚህ ረገድ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክርክር እና ጥያቄ ስለመኖሩ የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም። ይህ የክርክር ነጥብ የቀረበው አሁን በሰበር ደረጃ በመሆኑ ተቀባይነት ሉሰጠው እንደማይገባ ገልጾ ተጠሪው በሰበር መልሱ ያቀረበውን ክርክርም አመልካች በመልስ መልሳቸው አላስተባበለም።በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳ የክርክር ነጥብ ደግሞ በበላይ ፍርድ ቤቶች ሉስተናገድ እንደማይገባው የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 329 (1) ድንጋጌ ያመለክታል።ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስምም ቢሆን የአንድ ዓመት ከሶስት ወሩ የኪራይ ገንዘብ ተከፍሎል ወይስ አልተከፈለም? የሚለው ጥያቄ አሁንም ድረስ አከራካሪ ሆኖ የቀጠለ ሲሆን ገንዘቡ ተከፍሎል የሚባል ቢሆን እንኳ በዚህ ገንዘብ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ማቅረብ የሚችለው ገንዘቡን ከፍያለሁ የሚለው ማህበር እንጂ አመልካቹ አይደለም።በመሆኑም በአኃጌ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስም የተከፈለው ገንዘብ ከተወሰነብኝ የገንዘብ መጠን ላይ ተቀናሽ ላደረግልኝ ይገባ ነበር በማለት አመልካች ያቀረቡት ክርክር ሕጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩል አመልካች በንግድ ቤቱ መገልገል የጀመሩት በ01/11/2001 ዓ.ም መሆኑ ያልተካደ ሲሆን በፋዳራል የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት አማካይነት ለተጠሪው ያስረከቡት ደግሞ በ11/10/2005 ዓ.ም ስለመሆኑ ተጠሪው በሰበር መልሱ ላይ ገልጿል።አመልካችም በመልስ መልሳቸው ይህንን አላስተባበለም። ተጠሪው የኤላክትሪክ እና የመብራት መስመሮችን በማቋረጡ ምክንያት አመልካች ከግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በንግድ ቤቱ መገልገል እንዲልቻለ እና ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ከቤቱ ያገኙት ጥቅም አለመኖሩን በሰበር አቤቱታቸው ላይ የገለጹ ሲሆን ተጠሪው በሰጠው መልስ አመልካቹ በንግድ ቤቱ መገልገል ያልቻለት የኤላክትሪክ እና የመብራት መስመሮች ስለተቋረጡባቸው ሳይሆን በአዱሱ የንግድ ምዝገባ አዋጅ አግባብ እንደገና ለመመዝገብ እና ፈቃዲቸውን ለማሳደስ የኪራይ ውል ማቅረብ ስለነበረባቸው እና ማቅረብ ስላልቻለ መሆኑን ገልጾ ከመከራከር በቀር አመልካች በንግድ ቤቱ መገልገል ያቆሙት ከግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ስላለመሆኑ የማስተባበያ ክርክር አላቀረበም።በመሆኑም አመልካች በካሬ ሜትር በብር 30 ሂሳብ ኪሳራውን ለመክፈል የሚገደደት ከ01/11/2001 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 22/09/2003 ዓ.ም ድረስ ላለው ጊዜ ነው።
ከ22/09/2003 ዓ.ም ጀምሮ ቤቱን ለተጠሪው እስካስረከቡበት 11/10/2005 ዓ.ም ድረስ ላለው ጊዜ አመልካች ለተጠሪው ኪሳራ የመክፈል ግዳታ አለባቸው ወይስ የለባቸውም? የሚለውን ነጥብ በተመለከተ በዚህ ነጥብ ላይ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት አመልካች ከግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በንግድ ቤቱ መገልገል ያልቻለት በምን ምክንያት እንደሆነ በቅድሚያ ተገቢው ማጣራት ላደረግ ይገባል።በከፍተኛ ፍርድ ቤት በነበረው ክርክር አመልካች በቤቱ መገልገል ያቆሙት ተጠሪው የኤላክትሪክ እና የመብራት መስመሮችን ስላቋረጠባቸው እንደሆነ በመግለጽ የተከራከሩ ሲሆን ተጠሪው ይህንን አድራጎት እንዲልፈጸመ ክድ ተከራክሯል። በመሰረቱ አንድ ሰው ለባለንብረቱ ኪሳራ ሉከፍል የሚገደደው በልላ ሰው የስራ ድካም ወይም የላላ ሰው ሀብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ቀደም ሲል በተጠቀሰው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2162 ላይ ተመልክቷል። አመልካች ከግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በንግድ ቤቱ መገልገል ያልቻለት በተጠሪው ጥፊት መሆኑ የሚረጋገጥ ከሆነ ጥቅም ባላገኙበት እና ጥቅሙን ሳያገኙ የቀሩትም በተጠሪው ጥፊት በሆነበት ሁኔታ ለተጠሪው ኪሳራ እንዱከፍለ ሉገደደ የሚችለበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም።አመልካች ከግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በንግድ ቤቱ መገልገል ያልቻለት ተጠሪው እንደሚከራከረው የተጠሪው ባልሆነ እና ይልቁንም የራሳቸው የአመልካቹ በሆነ ምክንያት ከሆነ ደግሞ ቤቱን በወቅቱ ለተጠሪው ማስረከብ ሲገባቸው አላግባብ ይዘው በመቆየት ተጠሪውን ላሳጡት ጥቅም አመልካች ኪሳራ የማይከፍለበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም። አመልካች ከግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ በንግድ ቤቱ መገልገል ያልቻለት በማን ጥፊት ወይም የትኛው ወገን ኃላፉ ለሚሆንበት ድርጊት ነው? የሚለውን ነጥብ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጭብጥነት ይዞ ያጣራው ስለመሆኑ የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም። በመሆኑም በዚህ የክርክር ነጥብ ላይ ተገቢውን ውሳኔ ለመስጠት ያስችል ዘንድ ጉዲዩ ወደ ስር ፍርድ ቤት ተመልሶ ተገቢው ማጣራት ላደረግ የሚገባው መሆኑን ተገንዝበናል።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በከፉል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት እና ሉሻሻል የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ30/08/2005 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሻሽሎል።
በተጠሪው ንብረት አላግባብ ለበለጸጉበት አመልካቹን ኃላፉ በማድረግ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
አመልካች የኪሳራ ገንዘቡን መክፈል የሚገባቸው በካሬ ሜትር በብር 50 (ሃምሳ) ሂሳብ ነው በሚል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
አመልካች የኪሳራ ገንዘቡን መክፈል የሚገባቸው በካሬ ሜትር በብር 30 (ሰላሳ) ሂሳብ ነው በማለት ወስነናል።
በንግድ ቤቱ መገልገል ከጀመሩበት ከ01/11/2001 ዓ.ም. ጀምሮ በቤቱ መገልገል እስካቆሙበት 22/09/2003 ዓ.ም. ድረስ ላለው የ22 ወራት ከ21 ቀናት ጊዜ በካሬ ሜትር በብር 30 (ሰላሳ) እና በወር በብር 10,350 ሂሳብ ተሰልቶ የሚገኘውን ውጤት ብር 234,945 (ሁለት መቶ ሰላሳ አራት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ አምስት) አመልካቹ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከሰጠበት ከ19/06/2005 ዓ.ም. ጀምሮ ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር ለተጠሪው እንዱከፍለ ወስነናል።
ከላይ በውሳኔው ክፍል ውስጥ በተመለከተው መሰረት አመልካች ከግንቦት 22 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ በንግድ ቤቱ መገልገል ያልቻለት በምን ምክንያት ወይም ከግራ ቀኙ መካከል የትኛው ወገን ኃላፉ በሚሆንበት አድራጎት ምክንያት እንደሆነ በግራ ቀኙ እና ተገቢ ሆኖ ባገኘው ማስረጃ ሁለ ካጣራ በኃላ አመልካች ከ22/09/2003 ዓ.ም.
ጀምሮ ቤቱን ለተጠሪው እስካስረከቡበት 11/10/2005 ዓ.ም. ድረስ ላለው ጊዜ ለተጠሪው ኪሳራ የመክፈል ግዳታ ያለባቸው መሆን አለመሆኑን በተመለከተ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዱመለስ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 343 (1) መሰረት ወስነናል።
እንዱያውቀው እና ተገቢውን መፈጸም ያስችለው ዘንድ የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይላክ።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ የተያዘው አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዚህ መዝገብ በ05/11/2005 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተነስቶአል።
ይጻፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.