በአንድ ተቋም /መንግስታዊም ሆነ በባለስልጣን የተፈቀደለት/ ባለቤትነት የሚያካሄደው አደገኛ ተግባራት በልላ ሰው ላይ ጉዲት ያደረሰ በሆነ ጊዜ ድርጅቱ ስራው በህግ የሚጠበቅበትን ደረጃ ያሟላ ስለመሆኑ እና በከፉልም ሆነ በሙለ የተጎጂ ጥፊት መኖሩን እስካላስረዲ ድረስ ለደረሰው የኢት/ኤላ/ኃ/ኮ እና አቶ ጣሂር ሣፊይ XV ኃላፉነት ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2069/1/ /2/ እና 2086/2/
No summary available.
ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማዉ ወላ ዓሉ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- የኢት/ኤላ/ኃ/ኮ/ ነገላ ቦረና ዱስትሪክት - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- አቶ ጣሂር ሣፊይ - የቀረበ የለም።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የተጀመረዉ በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ፣ የአሁኑ አመልካች የስር 2ኛ ተከሳሽ ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ ደግሞ የቻይና ኤም.ሲ.ሲ 17 መንገድ ስራ ድርጅት ነበር። ተጠሪ ባቀረቡት ክስ፡- በአመልካች ድርጅት እየሰራሁ ሳለ ሳፊ በሚባል ዕቃ መንገድ እያሳየሁ እያለሁ ይህ ብረት የኤላክትሪክ ሽቦ በመንካት ባደረሰብኝ ጉዲት ግራ እግሬ ተቆርጦ በልላ አካላ ላይ ጉዲት ስላደረሰብኝ ሰርቼ የመኖር አቅም ሙለ በሙለ አጥቻለሁ።
በመሆኑም የስር 1ኛ ተከሳሽ በአዋጅ ቁ 377/96 አንቀጽ 27(3) 96(3) ፣ 97(መ) ፣ የአሁኑ አመልካች ደግሞ በፍ.ብ.ህ.ቁ 2027፣ 2028 መሰረት ኃላፉነታቸው እንዱለይላቸው፣ የካሳውን መጠን በተመለከተም በቀን 35 ብር እንደሚያገኙና ዕድሜአቸዉ 20 ሲሆን እስከ 40 አመት ሉኖሩ እንደሚችለ ዘርዝረው ባጠቃላይ ብር 499,996.80 እና የሞራል ካሳ ይከፈላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የስር 1ኛ ተከሳሽ ሀላፉነት የለበትም ተብል ከክሱ ሲወጣ አመልካች በሰጠዉ መልስ:- የኤላክትሪክ መስመሩ ደረጃዉን የጠበቀ ነው፣ተጠሪ ስራዉን ሲሰራ ጥንቃቄ ባለማድረጉ እና የያዘዉን ብረት ወደ የኤላክትሪክ ከፍ በማድረግ ያስነካዉ መሆኑን አልካደም፣ በመሆኑም በፍ.ብ.ህ.ቁ 2086 (2) መሰረት አያስጠይቀኝም በማለት ተከራክሯል። በዚህም መሰረት ጉዲዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮና አመልካች የኤላክትሪክ ሽቦዉን በምን ያክል ከፍታ ላይ እንደዘረጋ እና መዘርጋት ያለበት በምን ያክል ከፍታ እንደሆነ የቅርንጫፈ ድርጅት እንዱገልጽ ከአደረገው በኋላ ፍርድ ቤቱ በጠየቀዉ መሰረት ከቀበላዉ መስተዲድር ጋር በመሆን በቦታዉ በመገኘት የከፍታዉ ስታንደርድ 5.2 ሜትር ሲሆን አደጋዉ ሲደርስ በ5 ሜትር ከፍታ ላይ እንደነበረ አጣርቶ በደብዲቤ ቁ 397/7/05 በቀን 21/6/ 05 ዓ/ም ከተገለፀለት በኋላ ጉዲዩን መርምሮ አመልካች ስታንደርደን ጠብቆ ሽቦዉን ባለመዘርጋቱ ጉዲት ያደረሰ በመሆኑ በፍ.ብ.ህ.ቁ 2069 (1) (2) መሰረት ኃላፉነት አለበት በማለት ጀምሮ የካሳውን መጠን በተመለከተ ደግሞ የጉዲት መጠኑ 45% መሆኑ በመረጋገጡ ይሄው የጉዲት መጠን ከተጠሪው የወደፉት አማካይ እድሜ 40 አመት ጋር ተነጻጽሮ ሲታይ ብር 219,373.6 እንደሚሆን፣ በዚሁ ገንዘብ የሞራል ካሳን 1000 ብር ሲጨመር ባጠቃላይ ብር 220,378.60(ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከስልሳ ሳንቲም) እንዱከፈለዉ ወስነዋል። በቀጣይነት ጉዲዩን ያየዉ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ግራ ቀኙን በማከራከር በድምጽ ብልጫ የስር ፍርድ ቤትን ዉሳኔ ባግባቡ ነዉ በማለት አጽንቶታል።
የአመልካች ቅሬታም ይህንኑ ዉሳኔ ለማስቀየር ነዉ። በመሆኑም አመልካች ባቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ቅሬታዉን ስገልጽ ፡- የኤላክትሪክ ሽቦ ከምሰሶ ወደ ምሰሶ በአግባቡ የተወጠረ ሲሆን የመጣዉ ልዩነት የ 20 ሳንቲ ሜትር ደግሞ ከመሬት አቀማመጥ ሉከሰት ይችላል፣ ፍርድ ቤቱ ይህን ከግምት ሳያስገባ መወሰኑ እና ተጠሪ በራሱ ጊዜ አቅጣጫ ማሳያ ወደ ኤላክትሪክ ሽቦ ያስጠጋዉ እና የተበጠሰ ሽቦ ሳይኖር ተጠሪ ጥፊተኛ ሆኖ ሳለ ሙለ በሙለ አመልካችን ሀላፉ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ጠይቋል።
ተጠሪ በሰበር መልሳቸዉ የሚለት፤- ሽቦ በምሰሶ ሲወጠር በዲገት ወይም በዝቅተኛ ቦታ ቢሆንም በዛዉ ልክ ከፍ ብል ስለሚወጠር የመሬት አቀማመጥ ልዩነት አያመጣም፣ ሽቦዉ አልተበጠሰም በማለት ብቻ በእኔ ጥፊት መፈጸሙን ሳያረጋግጥ አመልካች የሚያቀርበዉ ክርክር አግባብነት የለዉም፣ የቀረበዉም ሪፖርት ሽቦዉ ስታንደርደን ጠብቆ ያለመወጠሩን አረጋግጧል፣ በመሆኑም በቀን የሚገኘዉን ገቢና የደረሰብኝን የጉዲት መጠን የመስራት አቅሜ እንዱቀንስ ያደረገ መሆኑ ተረጋግጦ ካሳው መወሰኑ ተገቢ ነዉ በማለት ተከራክሯል። አመልካች በሰጠዉ የመልስ መልስ ፡-ተጠሪ ለደረሰዉ አደጋ ቸልተኝነት አለበት፣ ስራዉን እንዱያከናዉን ያዘዘዉ የለም፣ ባጠቃላይ ጉዲት ካሳ መጠየቅ አይችልም፣ ከፍ.ብ.ህ.ቁ.2086 (2) ጋር ይቃረናል፣ በፍ.ብ/ህ.ቁ 2155(3) መሰረት ላታይ ሲገባ የታለፈ በመሆኑ ዉሳኔዉ ሉሻር ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ባጠቃላይ የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተገለፀዉን ይመስላል።እኛም የግራቀኙን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ዉሳኔ እና አግባብነት ካለዉ የህግ ድንጋጌ አንጻር መዝገቡን መርምረናል።
በመሆኑም ከተያዘዉ ጭብጥ አንጻር የክርክሩን አጠቃላይ ይዘት እንዲየነዉ የጉዲዩ መነሻ የነበረዉ ተጠሪ በምሰራበት የመንገድ ስራ ድርጅት በመሰራት ላይ ባለዉ መንገድ ሳፊ(ጠቋሚ) መሳሪያ በመያዝ በማገልገል ላይ እያለ የተወጠረዉን የኤላክትርክ ሽቦ በመንካት በደረሰዉ አካል ጉዲት የግራ እግሩ መቆረጡን በማረጋገጥ እና 45% ጉዲት የደረሰበት መሆኑን ጠቅሶ የጉዲት ካሳ እና የሞራል ካሳ ይከፈለዉ ዘንድ በመጠየቁ ሲሆን አመልካችም የተዘረጋዉ የኤላክትሪክ ሽቦ ሰታንደርደን ጠብቆ የተዘረጋ በመሆኑ ኃላፉነት የለብኝም፣ ጉዲቱ በተጠሪ ጥፊት የደረሰ ነዉ በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን ያዩት የክልለ ፍርድ ቤቶች ጉዲት መድረሱን በማረጋገጥ ኃላፉነትን በተመለከተ የተወጠረዉ የኤላክትሪክ ሽቦ ስታንደርደን ጠብቆ የተዘረጋ መሆኑን ለማጣራት ሲባል የቀበላዉ መስተዲደር እና የግራ ቀኙ ባለበት የቅርንጫፍ ድርጅቱ ስለሁኔታዉ እንዱገልጽ በማድረግ በተረጋገጠዉ መሰረት መስመሩ (ምሶሶው) በ5.20 ሜትር ርቀት ሉኖረዉ ሲገባ በ5 ሜትር ርቀት ላይ የተገኘ መሆኑን በማረጋገጥ በፍ/ብ/ህ/ቁ 2069(1)(2) መሰረት በተፈለገዉ ጥራት ኃላፉነቱን ባለመወጣቱ ለደረሰዉ ጉዲት ኃላፉነት አለበት በማለት ወስነዋል። እንግዱህ አመልካች መከራከሪያዉ ያደረገዉ የተደረገዉ የመስመር መወጠር ልኬት የመሬቱን አቀማመጥ አላገናዘበ፣ የተበጠሰ ሽቦ ሳይኖር በተጠሪ ጥፊት ለደረሰ ጉዲት ኃላፉነት የለብኝም የሚለውን ነው።
ይሁን እንጂ የመስመር ዝርጋታው ስንታደርደን ያለመጠበቁ በፍሬ ነገር ደረጃ በሚገባ በተረጋገጠበት ሁኔታና ጉዲቱም በተጠሪ ጥፊት ስለመድረሱ ያቀረበዉ ማስረጃ ሳይኖር በዚህ ረገድ ለዚህ ችልት የሚያቀርበው የፍሬ ነገር ክርክር ተቀባይነት የለዉም። መስመሩ ደረጃውን ጠብቆ የተዘረጋ መሆን ያለመሆኑና በተጠሪ በኩል ጥፊት የነበረ መሆን ያለመሆኑ በማስረጃ የሚጣሩ ነጥቦች ሲሆኑ በዚህ ረገድ ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ደግሞ ፍሬ ነገሩን አጣርተውና ማስረጃዎቹን መዝነው የአመልካችን ክርክር ውድቅ አድርገዋል። ይህ ለሰበር ሰሚ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት በሕግ ተለይቶ የተሰጠው ስልጣን ፍሬ ነገሩን ማጣራት ወይም ማስረጃን መመዘን አይደለም። በመሆኑም ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ስርዓቱን ጠብቀው ያጣሩትና የደመደሙትን የፍሬ ነገር ክርክር እንደ እውነት የምንቀበለው ይሆናል። ከዚህ አንፃር ጉዲዩን ስንመለከተው አመልካች የመስመሩ ዝርጋታ ደረጃውን የጠበቀ ነው፣ በተጠሪ በኩል ጥፊት ነበር በማለት የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት የላለው የለውም በማለት አልፈነዋል።
ላላዉ ተጠሪ በቀጣሪው ስራ ላይ ሳይታዘዝ ስለመስራቱም የቀረበ ማስረጃ ስለላለ በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን ቅሬታ የምንቀበለው ሁኖ አልተገኘም። ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አግባብ በተመሰረተ የስራ ግንኙነት ስራ ላይ እያለ ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑ መረጋገጡም በተጠቃሹ አዋጅ አንቀጽ 96(2) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስን በማመሳሰል የትርጉም ደንብ ስናየው በአመልካች በተፈጸመ ጥፊት ከውል ውጪ ኃላፉነትን በሚገዙ ድንጋጌዎች አግባብ ካሳ ከመጠየቅ የማይከለክላቸው ሁኖ አግኝተናል።
በመሰረቱ አንድ ሰው የሚፈነደ ወይም መርዝ የሚሆኑ ቅመማት ሥራ ላይ ማዋል ወይም በማከማቸት ወይም ከፍተኛ ጉልበት ያለው የኤላክትሪክ መስመር በመዘርጋት ወይም መሬትን የተፈጥሮ መልክ በመለወጥ ወይም በተለይ አደገኛ የሆነ የኢንደስትሪ ሥራ በማካሄድ ይህ ሥራው በልላው ሰው ላይ አደጋ ያደረሰ እንደሆነ ለደረሰው ጉዲት ኃላፉ እንደሚሆን የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2069/1/ የሚደነግግ ሲሆን ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ ተግባራትን በመፈፀም በልላው ሰው ላይ ጉዲት ያደረሰው መንግሥትም ቢሆን ወይም ሥራውን እንዱሰራ በባለሥልጣን የተፈቀደለት መሥሪያ ቤት ቢሆንም በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2069(1) የተደነገገው ደንብ ተፈፃሚ የሚሆን መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2069(2) በግልፅ ይደነግጋል።ከዚህ ከሕጉ ይዘትና መንፈስ አንጻር ሲታይም ተጠሪ ከላይ በተገለፁት የህግ ድንጋጌዎች መሰረት ለደረሰው ጉዲት የኤላክትሪክ መስመሩ ባለሀብት በመሆኑ ብቻ ኃላፉ ተብል መወሰኑ ተገቢ አይደለም በማለት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተገቢነት አይኖረውም። አመልካች ለደረሰው ጉዲት በኃላፉት የማያስጠይቀው የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2086(2) በሚደነግገው መሰረት ጉዲቱ የደረሰው በሙለ ወይም በከፉል በተጠሪ ጥፊት መሆኑን በማስረጃ በማስረዲትና በማረጋገጥ ነው።አመልካች ለጉዲቱ ኃላፉ አለመሆኑን ለማስረዲትም በመጀመሪያ የኤላክትሪክ መሥመሩን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስለ ኤላክትሪክ ሥራዎች የወጣው ደንብ ቁጥር 49/1991 አንቀጽ 35 ስለ ኤላክትሪክ መስመሮችና መሣሪያዎች ደህንነት የደነገገውን በሚያሟላ ሁኔታ ተዘርግቶ የነበረ መሆኑን ሉያስረዲ ይገባል። ከዚህ አንፃር በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮችን መሰረት አድርገን ጉዲዩን ስንመለከተው አመልካች ለክሱ ኃላፉ ተብል መወሰኑ የሚነቀፍበትን የሕግ አግባብ አላገኘንም።
ባጠቃላይ በተጠሪ ላይ የእግር መቆረጥ ደርሶበታል፣ በዚህም የተነሳ የመስራት አቅሙ በ45% መቀነሱ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። በመሆኑም ተጠሪ ሲያገኝ የነበረዉ እና ለወደፉት የሚያገኘዉ ገቢ/ጥቅም የቀረበት በመሆኑ የጉዲት ካሳው ከደረሰዉ ጉዲት መጠን ጋር ተመዛዝኖ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2090 እና ተከታይ ድንጋጌዎች የሚደነግጉትን መሰረት ተደርጎ የሞራል ካሳን ጨምሮ ብር 220,378.60 (ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከስልሳ ሳንቲም) ሉከፈለዉ ይገባል ተብል በስር ፍርድ ቤቶች መወሰኑ ሉነቀፍ የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት የለም። የህጉንም አላማ ስናይ የተጎዲ (ጉዲት የደረሰበት) ሰዉ በጉዲት አድራሹ ሉካስ እንደሚገባ ይታመናል። በህገ መንግስታችንም አንቀጽ 14 ሥር ማንኛዉም ሰዉ ሰብዓዊ በመሆኑ የማይደፈርና የማይገሰስ በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነትና ነጻነት መብት አለዉ።
በመሆኑም መንግስትም ሆነ ማንኛዉም ሰዉ የላላዉን ሰዉ የአካል ደህንነት የመጠበቅ የህግ ግዳታ አለበት። በተመሳሳይ ጉዲይም የሰበር ችልቱ በመ. እና በላልችም መዝገቦች ዉሳኔ ሰጥቷል። ይህ ዉሳኔ በአዋጅ ቁ454/97 አንቀጽ (2) (1) መሰረት በሀገሪቱ ባለት ፍርድ ቤቶች አስገዲጅነት ያለዉ ነው። በዚህ ሁለ ምክንያት የስር ፍ/ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ የደረሰዉን ጉዲት በማረጋገጥ የተጠቀሰዉን የጉዲት ካሳ እና የሞራል ካሳ ክፍያ መወሰናቸዉ አግባብነት ያለዉ ነዉ ብለናል።
ሲጠቃለልም የጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት በተጠሪ ላይ ለደረሰዉ ጉዲት አመልካችን ኃላፉ በማድረግ የጉዲት ካሳ እና የሞራል ካሳ ብር 220,378.60(ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከስልሳ ሳንቲም) ሉከፈለዉ ይገባል በማለት የደረሱበት ድምዲሜ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት አልተቻለም። በመሆኑም ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
በኦሮሚያ ክልል የጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀን 10/10/2005 ዓ/ም እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. በቀን 25/6/2006 ዓ/ም የሰጡት ዉሳኔ በፍ/ብ/ህ/ስ/ስ ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
አመልካች በተጠሪ ላይ ለደረሰዉ የአካል ጉዲት ሀላፉ ነዉ ተብል ጉዲት ካሳ ብር 220,378.60(ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ሶስት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከስልሳ ሳንቲም) ይክፈል መባለ በአግባቡ ነዉ ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የግራ ቀኙ የወጪ ኪሳራቸዉን ይቻቻለ ብለናል።
ግንቦት 27 ቀን 2006 ዓ.ም በዚህ ችልት ተሰጥቶ የነበረዉ የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
ለሚመለከተዉ አካል ይጻፍ።
No topics extracted.