በአንድ ንዐስ የስራ ተቋራጭ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ሰራተኛ ለሚደርስበት ጉዲት ዋናው ሥራ ተቋራጭ ከውል ውጪ በኃላፉነት የሚጠየቅበት የህግ መሰረት የላለ ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ./ቁ 2027-2136
No summary available.
ቀን ግንቦት 10 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- እሸት ኢንጅነሪንግ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ፊንታዬ ቢያድግልኝ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የአውሲረሱ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 4585 ሰኔ 25 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የአፊር ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 3033 መስከረም 5 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የጉዲት ካሣ ጥያቄን የሚመለከት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረበው ክስ ነው። ተጠሪ ባቀረበው ክስ የአመልካች ሰራተኛ የሆነ ልጃቸው አመልካች የንፅህና መጠበቂያ ውሃ ባለማቅረቡ ምክንያት፣ሥራ ውለ፣ አዋሽ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ሲታጠብ ስለመሆኑ በሥራ ላይ እያለ ጉዲት ደርሶበታል። ስለዚህ የአምስት ዓመት ደመወዝ ብር 270,000 /ሁለት መቶ ሰባ ሺ ብር/ ካሣ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። አመልካች ሟች የድርጅቱ ሰራተኛ አይደለም ሟች ከአመልካች ንዐስ የሥራ ውል ተዋውል የሚሰራው ድርጅት ሰራተኛ ነው በማለት ተከራክሯል። ተጠሪ ከንዐስ የሥራ ተቋራጭ ሰራተኞች ውሃ የማቅረብ ኃላፉነት ያለበት ተከሳሽ /አመልካች/ ነው በማለት ተከራክሯል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካችና ሟች የሥራ ውል ግንኙነት የላቸውም። ሆኖም ከንዐስ ተቋራጩ ሰራተኞች ውሃ የማቅረብ ግዳታ ያለበት አመልካች መሆኑ በውለ የተገለፀ በመሆኑ፣ ተከሳሽ ለሟች ከውል የመነጨ ካሣ የመክፈል ኃላፉነት አለበት ብል ብር 31,000 /ሰላሣ አንድ ሺ ብር/ እንዱከፍል ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ጥቅምት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ፣ ሟች የተጠሪ ሰራተኛ አለመሆኑ ተረጋግጧል። የበታች ፍርድ ቤቶች ባልተከራከርንበት እና በማስረጃ ያልተረጋገጠ ጭብጥ በማንሣት፣ አመልካች፣ ውሃ የማቅረብ ግዳታውን አልተወጣም ብለው የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል ተጠሪ የካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ አመልካች በውል የገባውን ውሃ የማቅረብ ግዳታ መሰረት ያላደረገ በመሆኑ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል። አመልካች መጋቢት 28 ቀን 2007 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም አመልካች የተጠሪ ልጅ በአዋሽ ወንዝ ገብቶ ሲታጠብ ለደረሰበት የሞት አደጋ ኃላፉ ነው ተብል ካሣ እንድከፍል የተሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ ክስ ያቀረበው ሟቹ ልጄ የአመልካች ሰራተኛ ነው። በሥራ ላይ እያለ ጉዲት ደርሶበታል በማለት ነው። የተጠሪ ልጅ የአመልካች ሰራተኛ አለመሆኑ ተረጋግጧል። የተጠሪ ልጅ የአመልካች ሰራተኛ ሣይሆን ከአመልካች ንዐስ የሥራ ውል ተዋውል የሚሰራው ንዐስ የሥራ ተቋራጭ ድርጅት ሰራተኛ መሆኑን የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ፍሬ ጉዲይ መሆኑን ውሣኔው ያሳያል። ይህ ከሆነ ተጠሪ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 110 እና ላልች አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ አመልካች ካሣ እንድከፍለው ለመጠየቅ የሚችልበት የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ ተጠሪ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ሕግ መሰረት በማድረግ የቀረበው የካሣ ጥያቄ ተቀባይነት የላለው ነው።
የተጠሪ ልጅ የንዐስ ሥራ ተቋራጭ ሰራተኛ ነው ከተባለ፣ ተጠሪ ክስ ለማቅረብ የሚችለው በንዐስ ሥራ ተቋራጩ ላይ እንጅ በአመልካች ላይ ላሆን አይችልም። አንድ ሰው በአንድ ጉዲት ኃላፉ የሚሆነው፣ ከሕግ ከውልና ከውል ውጭ ለጉዲቱ ኃላፉ የሚሆንበት ህጋዊ መሰረት ሲኖር ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች ለንዐስ ተቋራጩ ሰራተኞች ውሃ የማቅረብ ኃላፉነት ያለበት አመልካች ነው በማለት አመልካች በተጠሪ ልጅ ላይ ለደረሰው ጉዲት ከውል የመነጨ ኃላፉነት እንዲለበት በመግለፅ ወስነዋል። ሆኖም ፍርድ ቤቶቹ እዚህ መደምደሚያ ላይ የደረሱት በአመልካች በንዐስ ሥራ ተቋራጩ መካከል የተደረገውን ውል በዝርዝር ሣያዩና፣ ተጠሪ በንዐስ ሥራ ተቋራጩ ላይ የቀረበው ክስ ሣይኖር፣ ንዐስ ሥራ ተቋራጩ ክስ ቀርቦበት አመልካች ውል ጋር ያደረገውን ውል እንደመከላከያ ባላቀረበበት ሁኔታ ሆኖ አግኝተነዋል። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች በውል የገባውን ግዳታ ባለመወጣቱና በተጠሪ ልጅ ሞት መካከል፣ ቀጥተኛ የሆነ የምክንያትና የውጤት ግንኙነት ያለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በተጠሪ በኩል ስለመቅረቡ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ አያሳይም።
በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ለተጠሪ ልጅ ሞት ከውል የመነጨ ኃላፉነት አለበት በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች የተጠሪ ልጅ አዋሽ ወንዝ ገብቶ ሲታጠብ ለደረሰበት የሞት አደጋ ከውል ውጭ በኃላፉነት የሚጠየቅበት የሕግ መሰረት የላለ መሆኑን ተረድተናል።
አመልካች ከሕግ፣ ከውልና ከውል ውጪ የተጠሪ ልጅ አዋሽ ወንዝ ገብቶ ገላውን ሲታጠብ ለደረሰበት የሞት አደጋ በኃላፉነት የሚጠየቅበት ምክንያት ሣይኖር፣ የአውሲረሱ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የአፊር ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪ ካሣ የመክፈል ኃላፉነት አለበት በማለት የሰጡት ውሣኔ ከላይ የጠቀስናቸውን ድንጋጌዎች የሚጥስ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአውሲራሱ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የአፊር ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች ለተጠሪ ካሣ የመክፈል ኃላፉነት የለበትም ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ግራቀኙ ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.