ለአንድ ጉዲት ወይም አደጋ መድረስ ጉዲት የደረሰበት ሰው አስተዋፅዋኦ ካለው የጉዲት አድራሹ ኃላፉነት በከፉል ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ 2098/1/፣ 2097/2/፣2095
No summary available.
ሚያዝያ 15 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማዉ ወላ ዓሉ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ መሀመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ኢትዮጵያ ኤ.ኀ/አገልግልት መቂ ዱሰትሪክት - ነ.ፈ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የተጀመረዉ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ተከሳሽ ተጠሪዎች ከሳሽ ነበሩ።ተጠሪዎች የሟች ቱፊ ቤንቄ ቤተሰብ መሆናቸዉን በመግለጽ በመኖሪያ ቤቱ አጠገብ ባለዉ የኤላክትሪክ ሽቦ መሀከል ትልቅ ዛፍ በመኖሩ ድርጅቱ (አመልካች) በተለያዩ ጊዜ ቆርጦ እንዱያነሳለት ቢጠይቅም ባለማንሳቱ ሟች በልጆቼ ላይ ሉወድቅ እና ሉይዝብኝ ይችላል በማለት ዛፈን ሲቆርጥ ኤላክትሪኩን በመንካቱ ሉገድለዉ ችሎል። ሁለት ቀርጥ መሬት እያከራዬ ከአንደ ቀርጥ ላይ 10 ኩንታል ቦቆል ሲያገኝ ከሁለቱም ቀርጦች 20 ኩንታል የሚያገኝ ሲሆን የ1 ኩንታል በቆል ዋጋ 500 ብር ሲሆን በ1 አመት 10,000 ብር ያገኝ ነበር፣ ለወደፉቱ ሉኖር የሚችለዉ ለ36 አመት ስለሚሆን በዚህ ሂሳብ 360,000 ብር እንዱከፈለን በማለት ጠይቀዋል። አመልካችም በሰጠዉ መልስ ፤ሟች ከኤለክትሪክ ርቆ ቤቱን መስራት ሲኖርበት የአዋጅ 464/97 ድንጋጌን በመተላለፍ፤እራሱ የተከለዉን እንጨት አጥር ለመስራት ሲቆርጥ ጥንቃቄ ባለማድረጉ በመሞቱ ልንጠየቅበት አይገባም፤ይህ የኤላክትሪክ መስመር ለብዙ አመት አገልግልት ሲሰጥ የነበረ እና እስካሁን ችግር ፈጥሮ አያዉቅም፣በመሆኑም ተጠያቂ ልንሆን አይገባም በማለት ተከራክሯል።በመቀጠልም ሟች ያገኝ ነበር የተባለዉም ገቢ የተጋነነ ነዉ ፤የወንድ አማካይ እድሜም 55 አመት በመሆኑ ሟች ለወደፉት ይኖራል ተብል የቀረበዉ ትክክል አይደለም፤ ዉድቅ ላሆን ይገባል ብሎል። ጉዲዩን ያየዉ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመስማት እንዱሁም ተገቢ ነው ያለውን ማጣራትም ከአደረገ በኋላ ሀላፉነትን በተመለከተ አመልካች የኤላክትሪኩ ሽቦ ከሟች ቤት 4 ሜትር ርቆ የነበረና መቁረጥ የማያስፈልግ ነበር ቢልም፤ በተደረገዉ ማጣራት ሟችን የገደለዉ የኤላክትርክ ሽቦ 2.85 ርቆ እንዲለ በማረጋገጥ አመልካች እንጨቱን መቁረጥ ነበረበት፣ ይህን ባለማድረጉ ለደረሰዉ አደጋ ተጠያቂነት አለበት በማለት የፍ.ህ.ቁ 2095 ድንጋጌን ጠቅሶ ወስኗል።በመቀጠልም የታጣን ገቢ በተመለከተ ሟች ሁለት ቀርጥ መሬት አከራይቶ በአመት 20 ኩንታል ያገኝ ነበር ቢባልም ተጠሪዎች መሬቱ በእጃቸዉ ሰለሚገኝ ሰራተኛ ቀጥረዉ መጠቀም ስለሚቻል በርትዕ በወር 200 ብር መቅጠር ስለሚችለ፤እና የሟችም ዕድሜው 24 አመት የነበረና ለወደፉቱ 32 አመት ሉኖር ይችላል ተብል ስለሚገመት 32×12×200 = 76,800 ብር እና የሞራል 1000 ብር ጨምሮ 77,800.00 ብር ለተጠሪዎች ይከፈላቸዉ በማለት ወስኗል።በቀጣይነት ጉዲዩን ያየዉ ፍርድ ቤትም ቅሬታዉን ባለመቀበል ሰርዞታል።
የአመልካች አቤቱታም የቀረበዉ ይህንኑ ዉሳኔ ለማስቀየር ነዉ። በመሆኑም አመልካች ባቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ቅሬታዉን ሲገልጽ፡- የኤላክትሪክ መስመሩ ከ1972 ጀምሮ ለህብረተሰቡ አገልግልት ሲሰጥ የነበረ ነዉ፤ ሟች ኤላክትሪክ በእርጥብ እንጨት ከነኩት ሉገድል እንደሚችል በሚገባ ያዉቃል 4 ሜትር ርቆ ያለዉን መስመር በቸልተኝነት እንጨት በመቁረጥ በተፈጠረዉ አደጋ የሞተ በመሆኑ ሀላፉነት የለብንም ፤ሟች እንጨቱ እንድቆርጥለት ድርጅቱን በተደጋጋሚ ጠይቋል ቢባል እንኳ የሰዉን ንብረት ለመቁረጥ መብትም የለንም፤ ባጠቃላይ ተጠሪዎችም ቢሆኑ እራሳቸዉን ችለዉ ሰርተዉ መኖር የሚችለ በመሆኑ ተጠቃሹን ገንዘብ እንድንከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ጠይቋል።
በዚህም መሰረት ችልቱ ጉዲቱ የደረሰዉ ሟች በፈጸመዉ ጥፊት ነዉ ሲል አመልካች ያቀረበዉ ክርክር ታልፍ የመወሰኑን አግባብነት በጭብጥነት በመያዝ የግራ ቀኙን በጽሁፍ መልስና የመልስ መልስ በማቀባበል አከራክረዋል።
ተጠሪዎች በሰበር መልሳቸዉ የሚለት የተቆረጠዉ ዛፍ ከመስመሩ 4 ሜትር ርቆ ነዉ ያለዉ የሚለዉ ክርክር ሀሰት ነዉ በስር ፍርድ ቤት 2.85 በአጣሪዉ ኮሚቴ በመረጋገጡ ክርክሩ ውድቅ ላሆን ይገባል፤ሟች በተደጋጋሚ አመልካች ዛፈን እንዱቆርጥ አመልክቷል፤ የመቁረጥም ሀላፉነት ነበረበት፤ ይህን ባለማድረጉ ሀላፉነት አለበት ተብል መወሰኑ የሚነቀፍ አይደለም በማለት ይከራከራለ፤፤ አመልካች በበኩለ ሟች ዛፈን ሲተክልና ቤቱን ሲሰራ በኤላክትርክ መስመር አጠገብ መስራት አልነበረበትም ፤ዛፈም ቢሆን ባይቆረጥም አደጋ አያመጣም ነበር።
ያመጣል ብል ቢያስብም ለመቁረጥ ሙያ ያላቸዉን ማማከር ነበረበት ይህን ባላደረገበት ኃላፉነት አለባችዉ ልንባል አይገባም ዉሳኔዉ ሉሻር ይገባዋል በማለት ተከራክረዋል።
ባጠቃላይ የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተገለጸዉን ሲመስል፡- እኛም የግራ ቀኙን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ዉሳኔ እና አግባብነት ካለዉ የህግ ድንጋጌ አንጻር መዝገቡን መርምረናል።
በመሆኑም ከተያዘዉ ጭብጥ አኳያ አጠቃላዩን የክርክሩን ይዘት እንዲየነዉ፡- ተጠሪዎቸ የሟች ሚስትና ወላጆች በመሆናቸዉ በመተዲደሪያ ረገድ ለሚደርስባቸዉ ጉዲት ካሳ ጠይቀዋል።
እንግዱህ የተያዘዉም ጉዲይ ሟች ቤቱ አጠገብ የነበረዉ የኤላክትርክ መስመርና ዛፈ በቅርበት በመኖሩ ቢወድቅ በልጆቹ ላይ ሉያደርስ የሚችለዉን ጉዲት በማሰብ ድርጅቱ (አመልካች) ቆርጦ እንዱያነሳለት ቢጠይቁም ባለመቆረጡ በራሳቸዉ ጊዜ በመቁረጥ ላይ እያለ ኤላክትሪኩን በመንካት ሕይወታቸዉ አልፎል።ይህን ተከትል በተጠየቀዉ የካሳ ክፍያ ሟች 32 አመት ሉኖሩ ይችላል፤በርትዕ ተጠሪዎች በወር በ2ቱ ቀርጥ መሬት ሰራተኛ 200 ብር ቀጥረዉ ሉያሰሩ የሚችለ መሆናቸዉን በመጥቀስ ባጠቃላይ የሞራል ካሳን ጨምሮ ብር 77,800 የመክፈል ሀላፉነት አለበት በማለት በመወሰኑ፤ አመልካችም ሀላፉነት የለብኝም ሟች አደጋ የማያደርስና ከመስመሩ የማይገናኘዉን ዛፍ ሲቆርጥ ነዉ የሞተዉ መቁረጥ እንኴ አስፈላጊ ቢሆን እንኳ ሙያ ያለዉን ቆራጭ በማማከር በጥንቃቄ መቁረጥ ሲገባዉ ለብዙ አመት ያለችግር አገልግልት በመስጠት ላይ የሚገኘዉን የኤላክትርክ መስመር መንካቱ የራሱ ጥፊት እንጂ ሉያስጠይቀን የሚገባ አይደለም፤ ሟች ቤቱን ሲሰራም ሆነ ዛፈን ሲተክል ወደ መስመሩ መጠጋት አልነበረበትም፤በተጨማሪም ሟች የተከለዉን ዛፍ እንድንቆርጥ አልጠየቁም እንጂ ቢጠይቁም የሰዉ ንብረትን የመቁረጥ መብት የለንም በዚህ ሁለ ምክንያት ሟችን የመካስ ኃላፉነት የለብንም በማለት ተከራክረዋል።እንግዱህ የአመልካችን ኃላፉነት በተመለከተ መስመሩ 2.85 ቅርበት ላይ መኖሩ በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ጉዲይ ነዉ አመልካች እንደሚለዉ በ 4 ሜትር ላይም አይደለም፤ሉደርስ ይችላል ተብል የተገመቱትን ነገሮች ረፖርት ሲደርሰዉም ሆነ በራሱ ክትትል አደጋን የማስቀረት ወይም የመቀነስ ሙለ ኃላፉነት እና የህግ ግዳታ ያለበት መሆኑ ግልጽ ነዉ በመሆኑም የቤቱን ግንባታና የመስመሩን ቅደም ተከተል እንደዋነኛ መከራከሪያ ሉያቀርበዉ የሚገባ አይደለም፤ኃላፉነት የለኝም ሲል አመልካች የሚያቀርበዉን የስር ፍርድ ቤቶች በማስረጃ ረገድ አጣርቶ ኃላፉነት አለበት ማለታቸዉ የሚነቀፍ አይደለም ብለናል ።ይሁን እንጂ ሟችም ቢሆን በዛፈ ምክንያት ኤላክትሪክ አደጋ ሉያደርስ ይችላል በማለት ያሰበዉን ከመቁረጡ በፉት ሉያደርስ የሚችለዉን ጉዲት ማሰብና አግባብ ያለዉን ቆራጭ በመያዝ ሉቆርጥ ሲገባ በእርግጥ አደጋ ስለማድረሱ ሳያረጋግጥ ዛፈን በቸልተኝነት መቁረጡ የሟች አስተዋጽኦ የለበትም ለማለት አይቻልም በመሆኑም የፍብ.ህ/ቁ 2097(2) መሰረት ተበዲዩ በማስተዋል ቢሰራ ኖሮ የደረሰበትን ጉዲት ሉያቀለዉ ወይም ሉያግደዉ የሚችል ሲሆን በደረሰበት ጉዲት በሙለ ካሳ መጠየቅ የማይችል መሆኑን ይደነግጋል ፤በተያዘዉም ጉዲይ ጥንቃቄ በተሞላበት እና በማሰተዋል ቢሰራ ኖር አደጋዉን ይቀንስ ነበር የሚለዉን ግንዛቤ ይዘናል፡በዚህ ሁለ ምክንያት ለደረሰዉ አደጋ የሟች አስተዋጽኦ አለ፤ ካልን በፍ.ብ/ህቁ. 2098 (1)መሰረት በከፉል ሀላፉነት አለበት ማለት ነዉ፤ በመሆኑም አመልካች አለበት የተባለዉን የጉዲት ካሳ መጠን በማሻሻል 38,400 ላሆን የሚገባው ሁኖ ተገኝቷል።የሞራል ጉዲት ካሳው ግን የሚነካ ሁኖ አልተገኘም። ።
በመጨረሻም በኦሮሚያ ክልል አዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የሟችን ለጉዲቱ መድረስ የነበረዉን የቸልተኝት ከፉል አስተዋጽኦ ሳያገናዝቡ አመልካችን ሙለ በሙለ ሀላፉ በማድረግ ተጠቃሹን የገንዘብ መጠን ካሳ እንዱከፍል መወሰናቸዉ በከፉል መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ ።በመሆኑም ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
በኦሮሚያ ክልል የአዲማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ. በቀን 05/13/2006 እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚዉ ችልት በመ.ቁ.189401 በቀን 4/2/07 የሰጡት ዉሳኔዎች ተሻሽሎል።
ሟች ለደረሰበት አደጋ በከፉል ሃላፉነት ነበረበት ብለናል።በመሆኑም አመልካች ለተጠሪዎች ሉከፈል የሚገባው የጉዲት ካሳ መጠን ብር 38,400.00፣ የሞራል ካሳ ደግሞ ብር 1000.00 በድምሩ ብር 39,400.00 (ሰላሳ ዘጠኝ ሺህ አራት መቶ ብር ) ነው በማለት ወስነናል።
የግራቀኙ የወጪና ኪሳራ ይቻቻለ ብለናል።
በህዲር 08/2007 ተሰጥቶ የነበረዉ የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል።
No topics extracted.