በተዋዋይ ወገኖች የነበረን ውል አንደ ለላላኛው የውል መለዋወጥ ጥያቄውን ማቅረቡ በፍሬ ነገር ደረጃ ሳይረጋገጥ ውለ ተራዝሟል ልባል የማያስችል ስለመሆኑ፡የውለ አጻጻፍ ፍርም ወይም ዓይነት በሕግ የታዘዘ ሆኖ እንደ ትዕዛዙ ባይፈጸም ፈራሽነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ፡የፍ/ብ/ሕ/ቁጥርየፍ/ሕ/ቁ 1684፣1722፣1678(ሐ))
No summary available.
ሐምል 01 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ስማድል ኮሙኒኬሽን ተርሚናል ፊብሪካ ኃ.የተ.የግል ማህበር ተጠሪ፡- አቶ የሺጥላ ደሳለኝ በዚህ መዝገብ የተያዘው ጉዲይ በሰ/መ/ ከቀረበው ጉዲይ ጋር ተመሳሳይነት ስላለው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 11 መሰረት መዝገቦችን አጣምረን በመመርመር ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዲዩ አንድ የውል ክርክር በፍርድ ቤት የሚታይበትን አግባብ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥር 10 ቀን 2005 ዓ/ም በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የአመልካች የክስ ይዘትም፡-አመልካች በኢትዩጵያ ውስጥ የሚገጣጥማቸውን ስማድል ተንቀሳቃሽ ስልኮችን የአሁኑ ተጠሪ ለአንድ አመት ብቸኛ ወኪል በመሆን በኢትዩጵያ ውስጥ ለማከፊፈል በ03/12/2003 ዓ/ም በተፈረመ ውል ስምምነት መደረጉን፣አመልካችም የሚያመርተውን ምርት ለተጠሪ የንግድ መደብር የሺጥላ ሞባይል ሴንተር እያስረከበ ተጠሪ እቃዎቹን እየሸጠ ክፍያውንም እየፈፀመ ቀሪ ሑሳብ ማመዛዘኛ(ባላንስ) እየተሰራ የውለ ዘመን መጨረሻ ድረስ እቃ እየወሰደ የውለ ጊዜ መጠናቀቁን፣ ተጠሪ በውለ ዘመን የተረከባቸውን እቃዎችን ዋጋ ቀስ በቀስ ለአመልካች ገቢ እያደረገ እስከ ውለ ዘመን ማብቂያ ማለትም እስከ 03/13/2004 ዓ/ም ድረስ ያለውን ሑሳብ አጠናቅቆ መከፍለን፣ተጠሪ የብቸኛ ወኪልነቱን ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ ከ05/13/2004 ዓ/ም ጀምሮ የማከፊፈል ሰራውን እስከአቋረጠበትና የመጨረሻ ክፍያ እስከተፈፀመበት ህዲር 18 ቀን 2005 ዓ/ም ድረስ የብር 4,663,730.00(አራት ሚሉዩን ስድስት መቶ ስልሳ ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሰላሳ ብር) እቃዎችን በንግድ መደብሩ ሰራተኞች መረከቡን፣ ተጠሪ ከውለ ዘመን ማብቂያ በኋላ ለወሰደው እቃ የመጨረሻ ሂሳብ ጥቅምት 03 ቀን 2005 ዓ/ም ገቢ አድርጎ በልዩነት የተገኘው ተራፉ ገንዘብ ብር 131,155.00(አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ አምስት ብር) ታሳቢ ተደርጎ እስከ ህዲር 18 ቀን 2005 ዓ/ም ድረስ ብር 2,322,815.80(ሁለት ሚሉዩን ሶስት መቶ ሃያ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ አስራ አምስት ብር ከሰማንያ ሳንቲም) ገቢ ማድረጉን፣ ይህ ገንዘብ ከብር 4,663,730.00 ላይ ተቀናሽ ሲደረግ በልዩነት ብር 2,340,914.50 (ሁለት ሚሉዩን ሶስት መቶ አርባ ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ አራት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) ተጠሪ ለአመልካች መክፈል ይጠበቅበት እንደነበር፣አመልካች በወቅት ባልተሸጡ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅነሳ ስላደረገ ያልተሸጡ እቃዎች ላይ ቆጠራ ተደርጎ እ.ኤ.አ ዱሴምበር 05 ቀን 2012 ብዛታቸው 1000 ለሆኑ ሞባይል ስልኮች ለተጠሪ የብር 52,425.00(ሃምሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ሃያ አምስት ብር) ተቀናሽ መደረጉን፣ተጠሪ ቅናሽ ከተደረገለት በኃላ ለአመልካች ብር 2,288,489.40(ሁለት ሚሉዩን ሁለት መቶ ሰማንያ ስምንት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ብር ከአርባ ሳንቲም) እንዱከፍል የሚጠበቅበት መሆኑንና የወሰዲቸውን እቃዎችን እንዱመልስ ወይም ገንዘቡን እንዱከፍል ቢጠየቅ ፈቃደኛ ያለመሆኑን ዘርዝሮ ተጠሪ የሚፈለግበትን ብር 2,288,489.40 ከ18/03/2005 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ፣ከክሱ ወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍል ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ ተጠሪ በስር ተከሳሽነቱ ቀርቦ ለአመልካች ክስ በሰጠው መልስም፡- የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚና የፍሬ ነገር ክርክሮችን አቅርቧል። ተጠሪ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረበው ነጥብ የፍርድ ቤቱን ስልጣን የሚመለከት ሲሆን ይኼውም በግራ ቀኙ መካከል በ03/12/2003 ዓ/ም በተደረገ ስምምነት በውለ አፈጸጻም ጋር በተያያዘ አለመግባባት ቢፈጠርና ይህም አለመግባባት በስልሳ ቀናት ውስጥ በስምምነት መፍትሓ ሉያገኝ ካልቻለ ጉዲዩ ሶስት ገላጋይ ዳኞች(አርቪትሬተርስ) ለሚሰየመው አለም አቀፍ የንግድ ምክር ቤት ቀርቦ መፍትሓ እንደሚሰጠው፣የግልግል ዲኝነቱ የሚደረገውም በእንግሉዝኛ ቋንቋ በሆንግ ኮንግ እንደሚሆንና ጉባኤውም የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ እንደሚሆን በውለ አንቀፅ 10 ስር ስምምነት መደረጉን፣ከዚህም በተጨማሪ አለመግባባቱ የሚታየው በኢትዩጵያ ሕግ እንዲልሆነና በ2000 ዓ/ም አለም አቀፍ የንግድ ድንጋጌዎች(ኢንተርናሽናል ኮሜርሺያል ተርምስ፤ኢንኮተርምስ) አማካኝነት እንደሆነ ተፈፃሚነት ስላለው ሕግ በሚደነግገው የውለ አንቀጽ 11 ስር ግራ ቀኙ መስማማታቸውንና ይኼው በውለ የተመለከተው የአለመግባባት አፈታት መንገድ በውለ በተመለከተበት አግባባብ ከሚታይ በቀር ጉዲዩ ወደ ፍርድ ቤት የሚወሰድበት አግባብ ያለመኖሩና በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልትም በሰ/መ/ አስገዲጅ የህግ ትርጉም የተሰጠበት መሆኑን ጠቅሰው ጉዲዩን ፍርድ ቤቱ ሉመለከተው አይችልም በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የስር ፍርድ ቤትም በዚህ የተጠሪ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ከሰማ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ ጉዲዩ በግልግል እንደሚታይ ግራ ቀኙ በውላቸው ላይ ያስቀመጡ መሆኑን በምክንያትነት ይዞ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን የማየት ስልጣን የለውም ሲል ክሱን ውድቅ አድርጎ አመልካች የከፈለውን የዲኝነት ገንዘብ በደንቡ መሰረት እንዱመለስለት፣ተጠሪ ደግሞ የወጪና ኪሳራ ዝርዝር የማቅረብ መብት አለው በማለት ብይን ሰጥቷል።ወጪና ኪሳራን በተመለከተም ግራ ቀኙን አከራክሮ አመልካች ለተጠሪ ብር 37,760.07(ሰላሳ ሰባት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ብር ከዜሮ ሰባት ሳንቲም) እንዱከፍል በማለት ጥር 14 ቀን 2006 ዓ/ም በዋለው ችልት ወስኗል።ስልጣንን አስመልክቶ በተሰጠ ብይን አመልካች፣ በወጪና ኪሳራ ላይ በተሰጠው ውሳኔ ደግሞ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በተለያዩ መዛግብት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኃላ ችልቱ ስልጣኑን አስመልክቶ የቀረበውን ክርክር መርምሮ በግራ ቀኙ መካከል ያለው ውል ተራዝሟል፣ያለመራዘሙን አመልካች አልካደም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሲያፀናው ወጪና ኪሳራን በተመለከተ የሰጠውን ውሳኔ በተመለከተ ግራ ቀኙን አከራክሮ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማሻሻል አመልካች ለተጠሪ በክሱ ገንዘብ መጠን 3% የጠበቃ አበል እንዱከፈል በማለት ወስኗል። የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ብይንና ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- በአመልካችና በተጠሪ መካከል በ03/12/2003 ዓ/ም በተደረገ ውል ያለመግባባቱ የሚፈታበት አግባብ የተቀመጠው እስከ 03/13/2004 ዓ/ም ላለው ጊዜ ተፈፃሚነት ለሚኖረው ውል ሁኖ እያለና በዚህ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ውለ አብቅቶ የግራ ቀኙ በፅሐፍ ያደረጉት ስምምነት ሳይኖር ግንኙነቱ ከ05/13/2004 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ህዲር 18 ቀን 2005 ዓ/ም በመቀጠል ለተፈፀመ የሞባይል ግብይነት የቀረበውን የክፍያ ጥያቄ የቀደመው ውል እንዱቀጥል በግራ ቀኙ መካከል በጽሐፍ የተደረገ ውል በላለበትና ቀዲሚው ውል ጊዜው ባበቃበት ሁኔታ የመጀመሪያው ውል ተፈጻሚነት እንዲለው ተደርጎ ያለመግባባቱ በፍርድ ቤት ሳይሆን በግልግል የሚታይ ነው መባለም ሆነ ወጪና ኪሳራን በተመለከተ አመልካች ለተጠሪ እንዱተካ ተብል መወሰኑም ረቺና ተረቺ ባልተለየበት ሁኔታ በመሆኑ ያላግባብ የተወሰነ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርቦም ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካለቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥም፡- በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው ውል ጳጉሜ 03 ቀን 2004 ዓ/ም ከተጠናቀቀ በኃላየተደረጉ ግብይቶችን አስመልክቶ በግራ ቀኙ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት የመዲኘት ስልጣን በፍ/ብ/ቁጥር 1684 መሰረት ውለ የተራዘመ በመሆኑ የሽምግልና ዳኞች ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለኝም ያለበትን አግባብነትና እንዱሁም በግልጽ በውለ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀ በኋላ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1684 ትርጉም ተሰጥቶ ውለ መራዘሙ በሽምግልና ዲኝነቱ ስልጣን የሚኖረውን ውጤት ለመመርመር ተብል በመሆኑ ጉዲዩን ከዚሁ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለው ተመልክተናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአመልካች የክስ ይዘት አመልካች በኢትዩጵያ ውስጥ የሚገጣጥማቸውን ስማድል ተንቀሳቃሽ ስልኮችን የአሁኑ ተጠሪ ለአንድ አመት ብቸኛ ወኪል በመሆን በኢትዩጵያ ውስጥ ለማከፊፈል በ03/12/2003 ዓ/ም በተፈረመ ውል ስምምነት የተደረገ ሲሆን የውለ ዘመን ማብቂያ እስከ 03/13/2004 ዓ/ም ድረስ ስለመሆኑ፣በመጀመሪያ ውል መሰረት መከፈል የሚገባውን ሂሳብ ተጠሪ አጠናቅቆ ለአመልካች ከፍሎል በማለት አመልካች ክሱን መመስረቱን፣ተጠሪ የብቸኛ ወኪልነቱን ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ ከ05/13/2004 ዓ/ም ጀምሮ የማከፊፈል ሰራውን እስከአቋረጠበትና የመጨረሻ ክፍያ እስከተፈፀመበት ህዲር 18 ቀን 2005 ዓ/ም ድረስ ያለው ግብይት ላይ ያልተከፈለው ሑሳብ መኖሩን ዘርዝሮ አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ መመስረቱና ተጠሪም የመጀመሪያው የውለ ጊዜ ከአበቃ በኋላ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ግንኙነት ቀድሞ በጽሐፍ በተደረገው ውል አግባብ ሉገዛ ይገባል በሚል ምክንያት ጉዲዩ በግልግል እንጂ በፍርድ ቤት የሚታይበት አግባብ የለም የሚል ክርክር አንስተው የበታች ፍርድ ቤቶችም በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለው ግንኙነት ውለ በመራዘሙ ምክንያት ቀድሞ በተደረገው የውል ግንኙነት አግባብ መገዛት አለበት በሚል ድምዲሜና የፍ/ሕ/ቁጥር 1684 እና 1731(1) ድንጋጌዎችን በዋቢነት በመጥቀስ ጉዲዩን ፍርድ ቤት ለማየት ስልጣን የለውም ሲለ የወሰኑ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ ተዋዋይ ወገኖች ሕግ ከወሰናቸውና ከከለከላቸው ነገሮች በቀር የሚዋዋለትን ጉዲይ እንደመሰላቸው የመወሰን መብት ያላቸው መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1711 በግልጽ የደነገገ ሲሆን በሕግ አግባብ የተቋቋሙ ውልች ደግሞ ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ የሕግን ያህል ኃይል ያላቸው ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1731 ስር ተቀምጧል። በመሆኑም በሕግ እስካልተከለከለ ድረስ ተዋዋይ ወገኖች አንድን ጉዲይ ከፍርድ ቤት ውጪ በልላ የሙግት መፍቻ ዘዳ ለመፍታት ስምምነት ማድረግ እንደሚችለና ስምምነቱ መኖሩና ሕጋዊ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ደግሞ ተዋዋዮቹ በስምምነታቸው መሰረት መገዛት እንደአለባቸው፣ፍርድ ቤቱም ሕጋዊ ውል መኖሩን አረጋግጦ ውለ እንዱፈጸም ማድረግ ያለበት መሆኑ የሚያከራክር አይሆንም።
ከክርክሩ ሂደት በግልፅ መገንዘብ የሚቻለው በ03/12/2003 ዓ/ም በግራ ቀኙ በጹሐፍ የተገባው ውል የተሻሻለ ስለመሆኑ አለመረጋገጡን ነው።የውል መለወጥ ሥርዓት በሕጉ የተዘረጋ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1722 ያሳያል። በዚህም መሰረት ዋናውን ውል የመለወጥ ጉዲይ በዚሁ ውል በተደነገገገው አፃጻፍ (ፍርም) መሰራት ያለበት መሆኑ በተጠቃሹ ድንጋጌ ስር በግልጽ ተደንግጓል። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ከአመልካች ጋር በጹሐፍ ያደረጉትን ውል በፁሐፍ የለወጡ መሆኑን አላስረደም። ይልቁንም ተጠሪ በዚህ ረገድ የሚከራከሩትና የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ፍሬ ነገር የቀድሞ ውል ጊዜው ከአለቀ በኋላ ሁለቱ ወገኖች በቀድሞ ውል መሰረት ግንኙነታቸውን የቀጠለ መሆኑ እንጂ አመልካች ወይም ተጠሪ ያቀረቡት የውል አቀራረብ ጥያቄ ኑሮ ላላኛው ወገን በዝምታ ግንኙነቱን የቀጠለ ስለመሆኑ አይደለም። ስለሆነም አመልካች ወይም ተጠሪ አንደ ለላላኛው የውል መለዋወጥ ጥያቄውን ማቅረቡ በፍሬ ነገር ደረጃ ያልተረጋገጠ መሆኑን የክርክሩ ሂደት የሚያሳየው ጉዲይ ከመሆኑም በላይ የውል መለወጥ ሉከተለው የሚገባውን ስርዓት በመከተል ውለ ስለመለወጡ ያልተረጋገጠ በመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበው የተጠሪ ክርክርም ሆነ የበታች ፍርድ ቤቶች ድምዲሜ የሕግ መሰረት ያለው ሁኖ አላገኘነውም።
በመሆኑም በ03/12/2003 ዓ/ም የተደረገው ውል በአመልካችና ለተጠሪ መካከል ከ05/13/2004 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 18/03/2005 ዓ/ም ድረስ ነበረ ለተባለ ግንኙነት ተፈፃሚ ላሆን የሚችልበት አግባብ የለም።
በልላ በኩል ግን በ03-12-2003 ዓ.ም የተደረገው ውል እና በውለ የተቀመጠው የተዋዋይ ወገኖች መብትና ግዳታ በሕጉ አግባብ አልተለወጠም፣ ቀዲሚው ውል ተጠናቋል ከተባለ ተጠሪ በ03-12-2003 ዓ.ም በተደረገው ውል ከገባው ግዳታ በኋላ ነበር ለተባለ የግራ ቀኙ ግንኙነት በአመልካችና በተጠሪ መካከል ውል አለ ተብል የ03/12/2003 ዓ/ም ተደረገ የተባለውን ውል ለክሱ ምክንያት ላሆን የሚችልበት አግባብ መኖር ያለመኖሩን ማየቱ ተገቢ ነው። የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለው ውል ተራዝሟል ብል ለመደምደም መነሻ ያደረገው በ03/12/2003 ዓ/ም ተደረገ የተባለውንና አመልካች ለማስረጃነት ያቀረበውን ሰነድ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት ያሳያል። እንዱሁም አመልካች ይህ ውል ከተጠሪ ጋር ከ5/13/2004 ዓ/ም በኃላ የፅሐፍ ውል የለም ብል ለመከራከር እንደማያስችለውና ውል የለም ካለ ደግሞ ክሱን የመሰረተበት አግባብ ምን እንደሆነ ጠቅሶ ያቀረበው ክርክር የለም በማለት ይግባኝ ሰሚው ችልት በውሳኔው ላይ ማስፈሩን ተመልክተናል። በእርግጥ የአንድ ግዳታ ምንጭ ውል ወይም ሕግ ሲሆን አንድ መብት አለኝ በማለት ክስ የሚያቀርብ ሰውም የመብቱን ምንጭ ማሳየት እንደሚጠበቅበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33፣80፣231 እና በላልች ድንጋጌዎች ስር የተመለከተው የክስ አመሰራረት ስርዓት ያስገነዝባል። ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካችም በተጠሪ ላይ ክስ ሲመሰርት በመካከላቸው ቀድሞ በፅሐፍ የሆነ ውል የነበረ መሆኑና በዚያ ውል ተጠሪ ያለባቸውን ግዳታ የተወጡ መሆኑን አሳይቶ ለክሱ መሰረት የሆነው ግን ከቀዲሚው ውል ጊዜ ማብቃት በኋላ በነበራቸው ግንኙነት መሰረት ተጠሪ አልተወጡም የተባለው ግዳታ ነው። በመሰረቱ በጠቅላላ ውል በሕግ ፉት የጸና ውል አለ ለማለት መሟላት ከአለባቸው ነገሮች አንደ በሕጉ ተለይቶ የተቀመጠ ፍርም ካለ ይህንኑ ማሟላት ሲሆን በአመልካችና በተጠሪ መካከል ነበር የተባለው የተንቀሳቃሽ ስልክ በወኪልነት የማከፊፈል ውል ፍርምን በተመለከተ በሕጋችን ለተዋዋይ ወገኖች ነፃነት የተተወ ነው። በፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 1719(1) በሁለቱ ወገን ተዋዋዮች በማናቸውም ሁኔታ የተደረገ ስምምነት ውል ለማድረግ በቂ ነው በማለት የተቀመጠው ድንጋጌ የሚያስገነዝበውም ሕጉ ይህን ነፃነት መጠበቁን የሚያሳይ ነው። በልላ በኩል የውለ አጻጻፍ ፍርም ወይም ዓይነት በሕግ የታዘዘ ሆኖ እንደ ትዕዛዙ ባይፈጸም ፈራሽነትን የሚያስከትል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1678(ሐ)) ድንጋጌ ያሳያል። ሆኖም የተንቀሳቃሽ ስልክ በወኪልነት የማከፊፈል ውልን በተመለከተ ግን በግልጽ የተቀመጠ የፍርም ግዳታ ባለመኖሩ ተዋዋይ ወገኖች በመሰላቸው መልኩ ሉያደርጉት ይችላለ።
ስለዚህ የተንቀሳቃሽ ስልክ በወኪልነት የማከፊፈል ውል በቃል፣ በድርጊት፣ ወይም በጽሐፍ ሉፈጸም ይችላል። ከዚህ አንጻር ጉዲዩን ስንመለከተው የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች አቀረበ የተባለውን ሰነድ ከ05/13/2004 ዓ/ም በኋላ እስከ 18/03/2005 ዓ/ም ድረስ ላለው ጊዜ የቀረበ ማስረጃ ስለመሆኑ ሳያረጋግጥና የውለ ጊዜ ያበቃ ስለመሆኑ አመልካች ጠቅሶ እየተከራከረ የግራ ቀኙ ግንኙነት በፅሐፍ ያለውን ውል መሰረት ያደረገ ነው፣ ውለ ተራዝሟል በማለት ያሰፈረው ድምዲሜ የአመልካችን የክርክር ይዘትና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1719 ድንጋጌን ያላገናዘበ ሁኖ አግኝተናል። በሰ/መ/ የተሰጠው አስገዲጅ የህግ ትርጉምም በመዝገቡ ተከራካሪ የነበሩ ወገኖች በመካከላቸው የተሻሻለ ውል መኖር ያለመኖሩ አካራካሪ ባልሆነበትና በሕግ ፉት የፀና አንድ ውል መኖሩና በዚህ ውል ደግሞ ግራ ቀኙ ያለመግባባትን በግልግል ለመፍታት የተስማሙ መሆኑ ተረጋግጦ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ በመሰረታዊ የክርክር ነጥቦች አሁን ከተያዘው ጉዲይ ጋር ተመሳሳይነት የላለው በመሆኑ በዚህ ረገድ ተጠሪ የሚያቀርቡት ክርክር ከአስገዲጅ የሕግ ትርጉም አተገባበር አንፃር ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም።ሲጠቃለልም በአመልካችና በተጠሪ የተነሳው ክርክር በ03/12/2003 ዓ/ም የተደረገው ውል ከአበቃ በኋላ ግራ ቀኙ በዚሁ ውል ለመገዛት በፍ/ሕ/ቁጥር 1684 እና 1722 ድንጋጌዎች አግባብ ያራዘሙት ውል ሳይኖር በአዱስ መልክ የተፈጠረውን ላላ ውል መሰረት ያደረገ በመሆኑ በ03/12/2003 ዓ/ም በተደረገ ውል መሰረት በግልግል እንዱታይ የሚደረግ ባለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል፤፡ በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ06/03/2006 እና 14/06/2006 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በ24/8/2003 ዓ/ም የጸናው ውሳኔ እንዱሁም በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በ24/08/2006 ዓ/ም የተሻሻለው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሸሯል።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል ከ05/13/2004 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 18/03/2005 ዓ/ም ድረስ ያለውን ግንኙነት የመዲኘት ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት ነው ብለናል። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት አመልካችን የዲኝነት ገንዘብ ተመልሶለት ከሆነ ተገቢውን እንዱፈጽም በማድረግ ክርክሩን በመ/ እንዱቀጥል አድርጎ ጉዲዩን በሕጉ አግባብ አጣርቶ ተገቢውን ሉወሰን ይገባል በማለት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።ይጻፍ።
ወጪና ኪሳራን በተመለከተ ተጠሪን ለወጪና ኪሳራ ዲርጓል የተባለና በጉዲዩ ላይ የተሰጠ ውሳኔ የተሻረ በመሆኑ አሁን ባለው የክርክር ደረጃ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል የሚገደድበት ወጪና ኪሳራ የለም ብለናል።
No topics extracted.