ባድ መሬትን ለማስተላለፍ የሚደረግ የሽያጭ ውል /የመሬት ግብይት ውል/ ፍሬ ነገሩ ሕገወጥ ሥለመሆኑና እና የዚህን አይነት ውል ከጅምሩ እንደላለ ወይም እንዲልተደረገ የሚቆጠር ስለመሆኑ የኢ.ፋ.ህገመንግስት አንቀፅ 40(3) የፍ/ሕ/ቁ.1716(1) XIV
No summary available.
ሐምል 30 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመስል እንደሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ሻለቃ ጌትነት ታርቆ - ቀርበዋል ተጠሪ፡- ወ/ሮ ጀሚላ አሉ - አልቀረቡም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ነው። ስለሆነም ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው የጎንደር ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ በቀን 21/10/2003 ዓ.ም የሰጠውን ውሳኔ የሰሜን ጎንደር መስተዲደር ዞር ከፍተኛ ፍርድ ቢያፀናውም የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመ/ቁ 2665 በዐ9/08/2006 ዓ.ም በመለወጥ በሰጠው ውሳኔ ላይ አመልካች መሰረታዊ ስህተት ተፈፅሞበታል በማለታቸው ነው።
ጉዲዩ የውል መፍረስን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ በጎንደር ከተማ ቀበላ 17 ክልል ውስጥ በካርታ ቁጥር 7662/03 በእኔና በባለቤቴ ወራሾች በሆኑት ህፃናት ልጆች ስም የተመዘገበ ቤትና ቦታ ላይ እኔ ቦታ ተጠሪ ደግሞ ገንዘብ ችል ባለ 3 ፍቅ ህንፃ ሰርተን እኩል ልንካፈል እና ተጠሪ ከፍቅ ጀርባ መኖሪያ ቤት ሰርቶ ሉሰጠኝ በ21/06/03 ውል አድርገን እሱባለው ሆነ ኃ/የተ/የግ/ማ በማቋቋም ተስማማን። በውለ መሰረት እንዱፈፀም በወረዲ ፍርድ ቤት ከሶኝ ውሳኔ አሰጥቶብኛል። ከዚህ በኋላ የአሁኑ አመልካች የቤትና ቦታው ካርታ ወደ ማህበሩ እንዱዞር የሽያጭ ውል መፈፀም አለብን በሚል የአሁኑን ተጠሪ አታል የልጆቼን መብት በሚጎዲ መልኩ የሽያጭ ውለ ላይ አስፈርሞኛል በመሆኑም ውለ የፈቃድ ጉድለት ያለበት በመሆኑ ይፍረስልኝ የሚል ዲኝነት ጠይቀው በአሁኑ አመልካች ላይ በጎንደር ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻነት ነው። የአሁኑ አመልካችም በተከሳሽነት ቀርቦ በሰጠው መልስ ቀደም ሲል በ21/06/03 ዓ.ም የተደረገው ውል በ2/07/03 ዓ.ም በተደረገው ውል ተተክቷል የአሁኑ ተጠሪ ጋር ውል አልፈፀምኩም በ8/07/03 ዓ.ም የተደረገውን ውል የአሁን ተጠሪ የማድረግ ስልጣን አላት ምክንያቱም የልጆቹ ሞግዚትና ብቸኛ ወኪል ነች ውለን ያደረግነው በአሁን ተጠሪ ጠያቂነት ነው ውለ ፀድቆ ተመዝግቦ ስም ተዛውሯል። በአሁኑ ተጠሪ ስም የነበረው ካርታ ቁጥር 7662/03 በአዱስና በአሁን አመልካች ስም በወጣና ቁጥር 7668/03 በሆነ ካርታ ተለውጧል። በመሆኑም ክሱ በልላ መብት የቀረበ ነው ውድቅ ላደረግ ይገባዋል በማለት ተከራክሯል። የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ የአሁን ተጠሪ በ25/06/03 ዓ.ም የመንደር ውል ካደረጉ በኋላ በ8/7/03 ዓ.ም የአሁኑ አመልካች ጋር የሽያጭ ውል በማድረግ ውለን አስመዝግበው ስም ወደ አሁኑ አመልካች እንዱዛወር አድርገዋል። ይህንን ሲያደርጉ ደግሞ ተገደው መሆኑን አላስረደም ወደውና ፈቅደው መዋዋላቸውን ምስክሮች አስረድተዋል። በመሆኑም በ8/7/03 ዓ.ም የተደረገው ውል ሉፈርስ አይገባም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሳኔ ላይ የአሁኑ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኙን በሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ይኽው ፍርድ ቤት በ8/10/04 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ ይግባኙን ውድቅ አድርጎታል። ከዚህ በኋላም የአሁኗ ተጠሪ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረሙ ይገባል በማለት የሰበር አቤቱታ አቅርባ ይኽው ችልትም በዋናነት የሽያጭ ውለ ህጋዊነት አለው ወይስ የለውም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ አከራካሪ የሆነው የሽያጭ ውል የተደረገው በ7/7/03 ዓ.ም ነው። በዚህ ቤትና ቦታ ላይ ቀደም ሲል በአሁን ተጠሪ ባለቤት ስም የነበረው ካርታ በአሁን ተጠሪና ልጆቻቸው ስም ዞሮ ቁጥር 7662/03 የሆነው ካርታ የተሰጣቸውም በዚሁ ዕለት ነው። ይህ ከሆነ ከ1 ወር ከ15 ቀናት በኋላ ይኽው የሽያጭ ውል ተደረገበት በተባለ ቦታ ላይ በግራ ቀኙ ስም ሻለቃ ጌትነት ታርቆ እና ጀሚላ ዓሉ /PIC/ በሚል ስም በ23/7/03 ቁጥር 7668/03 የሆነ ካርታ ተሰጥቷል ይህም የሆነው ግራ ቀኙ በ23/5/03 ዓ.ም በተፈራረሙበት የንግድ ድርጅት የጋራ ሕንፃ በመገንባት ውል መሰረት እና ማህበሩም እሱባለው ሆነ ኃ/የተ/የግ/ማ ተብል እንዱመዘገብ በጋራ በ24/08/03 ዓ.ም እና በ02/06/03 ዓ.ም ለሚመለከተው አካል ካመለከቱ በኋላ ነው። ይህንንም የአሁኑ አመልካች ራሱ በስር ፍ/ቤት ካቀረባቸው ሰነድች ማየት ይቻላል የአሁን አመልካችም ቦታውን በ7/7/03 ዓ.ም በተደረገ ውል ቢገዛ ኖሮ ከዚህ በኋላ ይኽው ቦታ ላይ የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት በሆነ ድርጅት ስም ካርታ ሲወጣ ዝም ይላል ተብል አይገመትም። በመሆኑም የሽያጭ ውለ በክፈ ልቦና የአሁን ተጠሪን በመደለል የተደረገ ውል ነው። የሽያጭ ውለም የተደረገው በባድ ቦታ ላይ በመሆኑ ሕገ/ወጥ ነው። የአሁን ተጠሪም ቢሆኑ የሕፃናት ልጆቻቸውን ድርሻ የሆነን ቦታ የመሸጥ ከሕግ የመነጨ መብት የላቸውም የሚለ ምክንያቶችን በማስቀመጥ ውለ ፈራሽ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ውድቅ አድርጎታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚሁ ውሳኔ ላይ ባለመስማማት መሰረታዊ ስህተት ተፈፅሞበታል በማለት ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ግንቦት 7 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሞባቸዋል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል። ይዘቱም በአጭሩ የሽያጭ ውለ በተጠሪ ፈቃድ የተደረገና በሚመለከተው አካል ተረጋግጦ የተመዘገበ መሆን ውለ የተደረገው ቤት የነበረው ቦታ ላይ እንጂ ባድ ቦታ ላይ አለመሆኑን የሽያጭ ውለ ከመደረጉ በፉት የተቋቋመ ማህበር አለመኖሩን ተጠሪ የሸጡት የራሳቸውን ድርሻ ብቻ መሆኑን ተጠሪ የሽያጭ ዋጋውን ፈርመው መቀበላቸውን ዘርዝረው ውለ ፈራሽ ነው ተብል የተሰጠው ውሳኔ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርመሮ አመልካች የሽያጭ ውል የፈፀመው በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት ሆኖ ካርታ በስሜ ዞሮ የግንባታ ፈቃድ ከተሰጠ በኋላ የስር ሰበር ችልት ውለ የተደረገው ባድ ቦታ ላይ በመሆኑ ፈራሽ ነው በማለት ያልተከራከርንበትን ነጥብ በማንሳት መወሰኑን ያለአግባብ ነው በማለት ያቀረበውን ቅሬታ ለመመርመር በሰበር ችልት ላታይ ይገባዋል ተብል የአሁን ተጠሪ የተጠሩ ሲሆን ቀርበው ሐምል 4 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ መልስ በግራ ቀኙ መካከል በ22/05/03 ዓ.ም የንግድ ድርጅት የጋራ ህንፃ ግንባታ ውል መዋዋላቸውን ይህም ውል የተመዘገበ መሆኑን ይህንን ውል ለማስፈፀም ሲባል ህንፃው የሚሰራበት ቦታ ላይ የነበረው ቤት ፈርሶ ነፃ መሆኑን ከዚህ በኋላ የአሁኑ አመልካች የቦታውን ስመ ሀብት ወደ ጋራ ማህበሩ ለማዞር የሽያጭ ውል መደረግ አስፈላጊ ነው በማለት በ7/7/03 ዓ.ም የባድ ቦታ ሽያጭ ውል እንዱፈርሙ ያደረጋቸው መሆኑን በኋላ የተሰጠው ካርታ ቁጥር 7668/03 ግን በአመልካች ስም ሳይሆን በድርጅቱ ስም መሆኑን የሽያጭ ውለን የገቡት የቦታውን ሰመ ሀብት ወደ ድርጅት ዞሮ ግንባታ ይጀመር በማለት አመልካች ስለደለላቸው እንጂ የመሸጥ ሀሳብ ኖሯቸው አለመሆኑን ዘርዝረው የስር ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው ውሳኔ ራሱ አመልካች በበታች ፍርድ ቤቶች ያቀረበውን ማስረጃዎች መርምሮ በመሆኑ የፈፀመው የሕግ ስህተት የለም ተብል ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል አመልካችም ሐምል 7 ቀን 2006 ዓ.ም የመልስ መልሳቸውን አቤቱታቸውን በማጠናከር ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርመሮታል። እንደመረመረውም የሽያጭ ውለ ፈራሽ ነው ተብል መወሰኑ በአግባቡ ነው አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
በክርክሩ ሂደት መገንዘብ እንደተቻለው በግራ ቀኙ መካከል የሽያጭ ውለ ከመደረጉ በፉት የአሁኑ ተጠሪ የሚኖሩበት ቤት ፈርሶ በቦታው ላይ የአሁኑ አመልካች ህንፃ ግንባታውን ለመጀመር ተዘጋጅተው እንደነበር በስር ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው። ይህ ማለት ደግሞ ውለ የተደረገው /የሽያጭ ውለ/ በባድ ቦታ ላይ መሆኑን ያሳያል። ባድ መሬት ደግሞ የማይሸጥ የማይለወጥ መሆኑና የኢትዮጵያ ብሓርብሓረሰቦች ሕዝቦች የጋራ ንብረት መሆኑ ሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 4ዐ/3/ የተመለከተ ነው። በመሆኑም ይህንን ድንጋጌ በመተላለፍ የተደረገ የመሬት ግብይት ውል ፍሬ ነገሩ /Object/ ሕገ ወጥ ነው። እንደዚህ አይነት ውል ደግሞ ከጅምሩ የላለ ወይም ያልተደረገ /Voide/ ውል መሆኑን የፍ/ህ/ቁ 1716/1/ ያስቀምጣል። በዚህ ሁኔታ ደግሞ ፍርድ ቤት ህግን የማስከበር ኃላፉነትም ጭምር ያለበት በመሆኑ ተከራካሪ ወገኖች ባያነሱትም እንኳን ሕገ- ወጥ ውል ሲያጋጥመው ውለ ከጅምሩ ፈራሽ መሆኑን በመግለፅ ውሳኔ መሰጠት አለበት።
በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት ግራ ቀኛችን ያልተከራከርንበትን ጉዲይ በራሱ በማንሳት ውለ ከጅምሩ ፈራሽ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ አግባብ አይደለም የሚለው የአመልካች ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በዚህም መሰረት የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ውለ ከጅምሩ ፈራሽ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ በቀን 09/08/06 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ግራ ቀኙ በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ።
No topics extracted.