የማማከር የስራ ውል ልዩ ፍርም የሚያስፈልገው ሥለመሆኑ፡የፍ/ሕ/ቁ 1719፣2612(1)፣1882
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 3 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- ቢውቲ ግሪን ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - ጠበቃ እንየው ለማ ቀረቡ ተጠሪ፡- ቪክስ ሰመር ፍላወር ኃ/የተ/የግ/ማህበር አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ህዲር 20 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 9 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በውል መሰረት ለተሰራ ስራ ክፍያ እንዱፈፀም ይወሰንልኝ በማለት የቀረበን ጥያቄ የሚመለከት ነው።
በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረበው ክስ ነው። ከሳሽ ከተከሻሽ ጋር ባደረገው የስራ ስምምነት መሰረት ለተከሳሽ የምክር ስራ ለመስራትና ተከሻሽም በወር 4000 ዩሮ /አራት ሺ ዩሮ/ ሉከፍለኝ ተስማምተን እንደአውሮፖዊያን አቆጣጠር 15/10/2011 እስከ 16/01/2012 አገልግልት ሰጥቻለሁ። ስለዚህ ተከሳሽ በውለ መሰረት መክፈል ያለበትን ክፍያ ከነ ተጨማሪ እሴት ታክስ በወቅቱ በነበረው ምንዛሬ ታስቦ ብር 313‚200 /ሶስት መቶ አስራ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ብር/ እንዱከፍል ውሳኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቀርቧል። አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ከከሳሽ ጋር ያደረግነው የፅሁፍ ውል የለም። ውል ነው ተብል የቀረበው ሰነድ በሁለት ምስክሮችና በተዋዋይ ወገኖች አልተፈረመም። የውለ አለመፈረም ተዋዋይ ወገኖች ያልተስማሙ መሆናቸውን የሚያመለክት በመሆኑ ክሱ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።
የስር ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ማስረጃ ይዘት ከመረመረ በኋላ በግራ ቀኙ መካከል በቃል የተደረገ የማማከር ስምምነት አለ። በዚህ ስምምነት መሰረት ከሳሽ ሰራተኞችን ቀጥሮ የተከሳሽን እርሻ የማስተዲደር ስራ የሰራ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል። ስለዚህ ከሳሽ በውለ መሰረት ለሰጠው አገልግልት ተከሳሽ መክፈል የሚገባውን ገንዘብ፣ ማለትም ከሳሽ በክሱ የገለፀውን የገንዘብ መጠን ተከሳሽ ይክፈል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ሀምላ 25 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ፣ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገ የማማከር ውል የለም። አመልካችና ተጠሪ የማማከር ውል ለመዋዋል በፅሁፍ ረቂቁን ካዘጋጀ በኋላ ባለመስማማታቸው፣ ረቂቁ ሣይፈርም ቀርቷል። የስር ፍርድ ቤት ይህንን በማለፍ በመካከላቸው በቃል የተደረገ ውል አለ በማለት የሰጠው ውሳኔ እርስ በርሱ የሚቃረን የተጠሪን ምስክሮች ቃል መሰረት በማድረግ የተሰጠ ውሳኔ በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ ህዲር 24 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካችና ተጠሪ የተስማሙት በፅሁፍ ሣይሆን በቃል መሆኑን በማስረጃ አስረድተናል። ቀደም ብለን በቃል ባደረግነው ስምምነት መሰረት ስራዎችን እየሰራን፣ ስምምነቱን ወደ ፅሁፍ ለመቀየር ረቂቅ ውል ተዘጋጅቶ የአመልካች ስራ አስኪያጅ ወደ ኢትዮጵያ ባለመምጣታቸው ረቂቁ ሣይፈረም መቅረቱ በማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን የአመልካች አቤቱታ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች ታህሳስ 23 ቀን 2007 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቀርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሁፍ ክርክር ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች ከሳሽ /ተጠሪ/ ከአመልካች ጋር በቃል ባደረገው የምክር ግልጋልት የመሰጠን የስራ ውል መሰረት ከሳሽ /ተጠሪ/ የሰራው ስራ ተከሳሽ ክፍያ ይፈፀም በማለት የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ ከአመልካች ጋር የማማከር ስራ ውል በቃል ተዋውል በጉራጌ ዞን በሚገኘው የአመልካች እርሻ ቦታ የመገኘት የማማከር ስራውን የሚሰሩ ሰራተኞች ቀጥሮ ሰራተኞች የማማከር ስራ የሰሩ መሆኑንና ለሰራተኞች የአራት ወር ደመወዝ የከፈለ መሆኑን፣ ረቂቅ የፅሁፍ ውል ተዘጋጅቶ የነበረው በቃል የነበረውን ውል በፅሁፍ አድርገው ለማስቀጠል በመስማማታቸው መሆኑንና ረቂቁ የፅሁፍ ውል ያልተፈረመው የተከሳሽ ስራ አስኪያጅ ወደ ኢትዮጵያ ባለመምጣታቸው መሆኑን በማስረጃ ያረጋገጠ መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። አመልካች ረቂቅ የውል ሰነደ አመልካችና ተጠሪ የማማከር ስራ ውል ለመዋዋል በሚያደርጉበት ወቅት፣ ባለመስማማታቸው ረቂቁ ያልተፈረመ መሆኑን የሚያስረዲ ነው በማለት ይከራከራል። ሆኖም አመልካች ከተጠሪ ጋር የማማከር ስራ ውል ለመዋዋል ድርድር ጀምሮ እንደነበር፣ በድርድሩ ሂደት ስምምነት ላይ ባለመደረሱ ረቂቁ ሣይፈረም የቀረ በመሆኑና ረቂቅ ውለ ከመዘጋጀቱ በፉት በቃል ያደረጉት የስራ ውል የላለ መሆኑንና ተጠሪም በስራ ውለ መሰረት የፈፀማቸው ተግባራት የላለ መሆኑን የሚያስረዲ በቂና አሳማኝ ማስረጃ ያላቀረበ መሆኑን የበታች ፍርድ ቤቶች አረጋግጠዋል።
አመልካችና ተጠሪ በቃል ያደረጉት የማማከር ስራ ውል መኖሩ ብቻ ሣይሆን በተጠሪ በቃል በተደረገው የማማከር ስራ ውል መሰረት ለአራት ወራት ያህል ሰራተኞች ቀጥሮ ደመወዝ እየከፈለ የአመልካችን እርሻ ያስተዲደረና ላልች የምክር አገልግልቶችን የሰጠ መሆኑ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።
አመልካች ተጠሪ በዚህ መዝገብ የሚከራከሩበትን አይነት የስራ ውል ለመዋዋል፣ የአሰሪው /የአመልካች/ ጥያቄውን ማቅረብና የተጠሪ ጥያቄውን መቀበል ብቻ በቂ እንደሚሆን ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1779፣ ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2610 እና ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2612 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌዎች ይዘት ለመረዲት ይቻላል። ከዚህ አንፃር አመልካች የማማከር የስራ ውል በፅሁፍ ካልተደረገ በስተቀር ተዋዋይ ወገኖች በቃል ባደረጉት ስምምነት ሉቋቋሙት እንደማይችለ በመግለፅ የሚያቀርበው ክርክር የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1882 ንዐስ አንቀፅ 1፣ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2610፣ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2612 ንዐስ አንቀፅ 1 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን ይዘት ያላገነዘበና የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.