ተዋዋይ ወገኖች በመካከላቸው የሚፈጠርን አለመግባባት በዘመድ ዲኛ የመጨረስ ስምምነት ማድረግ የሚችለ ስለመሆኑ፡የዘመድ ዲኛ አለመግባባቶችን አይቶ የመወሰን ስልጣን የሚመነጨው ተገልጋዮቹ በግልፅ እና በማያሻማ ሁኔታ በሚሰጡት ሥምምነት ላይ ብቻ ስለመሆኑ፡የፍ/ሕ/ቁ 3325፣3326-3346
No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገብረሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- መርዕድ ታደሰ ገብረመድህን ህንጻ ስራ ተቋራጭ - ጠበቃ ጸጋዬ አሰፊ ቀረቡ ተጠሪ፡- ኦክስፍርድ አመልጌትድ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የቀረበ የለም ከተባለ በኋላ ጠበቃ ታረቀኝ ተፈራ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰቷል።
በዚህ መዝገብ አመልካች አቤቱታ ያቀረበው በፍርድ ባለመብትነት ተሰይሞ በነበረው የአሁኑ ተጠሪ እና በፍርድ ባለዕዲነት ተሰይሞ በነበረው የአሁኑ አመልካች መካከል የነበረውን የፍርድ አፈጻጸም ክርክር የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሕግ አግባብ የተሰጠብኝ እና የምፈጽመው የግልግል ዲኝነት ውሳኔ የለም በማለት በፍርድ ባለዕዲነት ተሰይሞ በነበረው የአሁኑ አመልካች ያቀረበውን ክርክር ውድቅ በማድረግ ባለዕዲው በግልግል ዲኝነት ውሳኔው መሰረት ፈጽሞ እንዱቀርብ የሰጠው እና በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የጸናው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
የጉዲዩን አመጣጥ በተመለከተ አሰሪ በሆነው የአሁኑ ተጠሪ እና የስራ ተቋራጭ በሆነው የአሁኑ አመልካች መካከል በታህሳስ ወር 2004 ዓ.ም በተደረገው የጫማ ማምረቻ ፊብሪካ ህንጻ የግንባታ ውል መሰረት በአሰሪው በአማካሪ መሀንዱስነት የተሰየሙት እና በገላጋይ ዲኝነት ጭምር እንዱያለግለ በውለ ተመርጠዋል የተባለት ግለሰብ የስራ ተቋራጩ በውለ መሰረት ባለመፈጸሙ ምክንያት አድርሶብኛል ላለው ጉዲት ተቋራጩ በድምሩ ብር 14,391,813.61 (አስራ አራት ሚሉዮን ሶስት መቶ ዘጠና አንድ ሺህ ስምንት መቶ አስራ ሶስት ከስድሳ አንድ ሳንቲም) ካሳ እንዱከፍለው ለማስወሰን አሰሪው ያቀረበውን ክስ የተከሳሽ ስራ አስኪያጅ መጥሪያ ለመቀበል ፈቃደኛ አልሆነም በሚል አማካሪ መሀንዱሱ ጉዲዩን ተቋራጩ በላለበት ከተመለከተ በኃላ
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ አመልካች ባቀረበው አቤቱታ መሰረት አማካሪ መሀንዱሱ በሁለቱ ወገኖች በገላጋይ ዲኝነት ሳይመረጥ ሰጠ በተባለው ውሳኔ መሰረት እንዱፈጸም የተሰጠው ትዕዛዝ ከሕግ እና ከውል ስምምነታችን ውጪ ነው በሚል በአመልካች የቀረበውን አቤቱታ ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር የተለዋወጡ ከመሆኑም በላይ በ20/06/2007 ዓ.ም በተለዩት ነጥቦች ላይ በ29/7/2007 ዓ.ም በዋለው ችልት በቃል እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት በሕግ የዲኝነት ስልጣን የተሰጣቸው አካላት ሉቋቋሙ እንደሚችለ በአንቀጽ 37 (1) እና 78 (4) የተመለከተው እንደተጠበቀ ሆኖ በፋዳራልም ሆነ በክልል የዲኝነት ስልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግስት በአንቀጽ 79 (1) ስር የተደነገገ ሲሆን ከዝርዝር ሕጎች መካከልም በልላ አኳኃን እንዱፈጸም በሕግ ካልተገለጸ ክስን ተቀብል ለማከራከር ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት ብቻ ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 4 ይደነግጋል።ይህ ማለት ግን በሰዎች መካከል በተለያዩ ምክንያቶች የሚነሱ አለመግባባቶች ከፍርድ ቤቶች ውጪ በልላ አግባብ ሉስተናገደ እና እልባት ሉያገኙ የሚችለበት አግባብ አይኖርም ማለት አይደለም።ይልቁንም ግልጽ የሕግ ክልከላ ካለባቸው ጉዲዪች ውጪ ሰዎች በመካከላቸው የተነሱ ወይም የሚነሱ አለመግባባቶች ከፍርድ ቤቶች ውጪ እልባት እንዱያገኙ በስምምነት ሉወስኑ ይችላለ።በዚህ አግባብ ከሚደረጉ ስምምነቶች መካከል አንደ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 3325 ስር ትርጉም የተሰጠው ክርክርን በዘመድ ዲኛ የመጨረስ ስምምነት ነው።የዚህ ዓይነቱ ስምምነት አፈጻጸምም ከቁጥር 3326 እስከ 3346 ባለት ድንጋጌዎች የተመለከተ ሲሆን በእነዚህ ድንጋጌዎች ከተመለከቱት መሰረታዊ መርሆዎች እና መብቶች አንደ እና ዋነኛው የተገላጋዮቹ የየራሳቸውን የዘመድ ዲኛ የመምረጥ መብት ነው።
በተያዘው ጉዲይ ግራ ቀኙ በመካከላቸው ካቋቋሙት የግንባታ ውል አፈጻጸም የሚመነጩ አለመግባባቶችን በዘመድ ዲኛ ለመጨረስ በግንባታ ውለ በአንቀጽ 38 ስር ስምምነት ማድረጋቸው ያልተካደ ጉዲይ ሲሆን አከራካሪ ሆኖ የቀረበው የአንቀጹ አነጋገር አተረጓጎም፣በተለይም የአንቀጹ አነጋገር በአሰሪው የተሰየመው አማካሪ መሀንዱስ በአማካሪ መሀንዱስነቱ ከሚያከናውናቸው መደበኛ የምህንድስና ሙያ ተግባራት በተጨማሪ የዘመድ ዲኛ ስልጣን ጭምር እንዱኖረው ግራ ቀኙ ስምምነት ማድረጋቸውን የሚያመለክት ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ዓቢይ ነጥብ ነው።
“አለመግባባትን በግልግል ስለመፍታት” የሚል ርዕስ የተሰጠው የውለ አንቀጽ 38 “ከውለ በመነጩ ወይም ውለን በማስተካከል ምክንያት ወይም ማንኛውንም ዓይነት አለመግባባቶች ወይም ልዩነቶች በሚከሰትበት ወቅት በስራው አፈጻጸም ሂደት ወቅት ስራው ከተጠናቀቀ በኃላ ወይም ከተቋረጠ በኃላ ወይም ውል የማፍረስ ሁኔታ በሚከሰትበት ወቅት በመሐንዱሱ አማካኝነት ከሁለቱ አካላት በአንደ የጽሁፍ ማስታወቂያ በደረሰ በ21 ቀናት ውስጥ ሁኔታውን ለመፍታት ይሞከራል።ውሳኔውንም ለቀጣሪው እና ለኮንትራክተሩ የሚያሳውቅ ይሆናል።
ይህ ውሳኔ በቀጣሪው እና በኮንትራክተሩ መሀል ያለው አለመግባባት የመጨረሻ ውሳኔ ሲሆን በውሳኔው መሰረት ከውሳኔው በኃላ ላላ የገላጋይ ሂደትን ቢፈልጉም እንኳን ኮንትራክተሩም ሆነ ቀጣሪው ስራውን ማስፈጸም መቀጠል ይኖርባቸዋል።
አማካሪው ውሳኔውን ለቀጣሪው በጽሁፍ ካሳወቀ በኃላ እና ኮንትራክተሩም ሆነ ቀጣሪው ማስታወቂያ በደረሳቸው በ30 ቀናት ውስጥ ይግባኝ ካልጠየቁ የተወሰነው ውሳኔ የመጨረሻ እና በቀጣሪና በኮንትራክተሩ መካከል የጸና ይሆናል።መሀንዱሱ ይህንን ውሳኔ በተጠየቀ በ21 ቀናት ውስጥ ያላሳወቀ እንደሆነ ወይም ኮንትራክተሩም ሆነ ቀጣሪው በውሳኔው ያልተስማሙ ከሆነ ቀጣሪው ወይም ኮንትራክተሩ የውሳኔ ማስታወቂያ በደረሳቸው ወይም የመጀመሪያው 90 ቀናት ካለፈ በኃላ ጉዲዩ ወይም ጉዲዮቹ ለሚመለከተው ኮሚቴ በመምራት መፍትሄ እንዱያገኙ ይደረጋል።ኮሚቴው አምስት አባላትን የያዘ ሲሆን እያንዲንደ ወገን ሁለት ሁለት አባላትን ያቀርባል።ሉቀመንበር ከሁለቱ ወገኖች መሀል በስምምነት የሚሾም ይሆናል።የዚህ ኮሚቴ ውሳኔ የመጨረሻ ውሳኔ የሚሆን ሲሆን ሁለቱም ወገኖች ለውሳኔው ተገዢ መሆን ይኖርባቸዋል።”በሚል የሚነበብ ሲሆን “Settlement of Disputes Arbitration” የሚል ርዕስ ያለው የአንቀጹ የእንግሉዝኛ አነጋገርም ተመሳሳይ ይዘት ያለው ነው።
እንደሚታየው የድንጋጌው አነጋገር በአንድ በኩል ግራ ቀኙ ባደረጉት ስምምነት በአማካሪ መሀንዱሱ እንዱወሰን የተስማሙት በስራው አፈጻጸም ሂደት ወይም ስራው ከተጠናቀቀ በኃላ ወይም ከተቋረጠ በኃላ ወይም ውል የማፍረስ ሁኔታ ከተከሰተ በኃላ የሚነሳ ማናቸውም ዓይነት አለመግባባት እንደሆነ የሚያመለክት ሲሆን በልላ በኩል ግን አለመግባባቶችን አይቶ የሚወስን በግራ ቀኙ በጋራ የሚመረጥ የግልግል ኮሚቴ ስለመኖሩ በውለ ተገልጾ መገኘቱ፣እንዱሁም ከአማካሪ መሀንዱሱ ውሳኔ በኃላ “…ላላ የገላጋይ ሂደትን ቢፈልጉም እንኳን ኮንትራክተሩም ሆነ ቀጣሪው ስራውን ማስፈጸም መቀጠል ይኖርባቸዋል።” በሚል የተቀመጠው የውለ ኃይለ ቃል ግራ ቀኙ የተስማሙበት የአማካሪ መሀንዱሱ ስልጣን የግንባታ ውለ አፈጻጸም በሂደት ላይ በሚገኝበት ወቅት የሚነሱ እና በዘርፈ በተለመደው አግባብ በአማካሪ መሀንዱስ የሚወሰኑ የምህንድስና ዘርፍ ውሳኔ የሚሹ አለመግባባቶችን መርምሮ በመወሰን የተገደበ መሆኑን የሚያመለክት ነው።ውለታዎች ግልጽ ባልሆኑ እና የሚያሻሙ በሆነ ጊዜ ደግሞ ለክርክሩ ውሳኔ መስጠት የሚቻለው በታወቁ እና በፍትሐብሕር ሕግ በቁጥር 1732 እስከ 1739፣እንዱሁም በላልች ድንጋጌዎች በተመለከቱት የውል አተረጓጎም መርሆዎች መሰረት ውለን ውጤት ባለው አግባብ በመተርጎም ነው።አመልካች በሰበር አቤቱታው ላይ አማካሪ መሀንዱስ የግልግል ዲኝነት ስልጣን የላለው ስለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ቀደም ሲል በተመሳሳይ ጉዲይ በመዝገብ በ16/10/2001 ዓ.ም የሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ለተያዘው ክርክር ተፈጻሚነት ሉኖረው ይገባል በማለት ተከራክሯል። በመሰረቱ አስቀድሞ በቀረበለት ጉዲይ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ቀጥለው በሚቀርቡ ጉዲዮች ላይ ተፈጻሚነት ሉኖረው የሚችለው በሁለቱ ጉዲዮች ለክርክር የቀረቡት የሕግ እና የፍሬ ነገር ነጥቦች ተመሳሳይነት ባላቸው ጊዜ መሆኑ የሚታወቅ ነው። በተጠቀሰው መዝገብ አማካሪ መሀንዱሱ የግልግል ዲኝነት ስልጣን ነበረው ወይስ አልነበረውም? የሚለው ነጥብ አከራካሪ ሆኖ የቀረበው ተዋዋዮቹ የውላቸው አካል ካደረጉት የባትኮዲ ደንቦች አንጻር ሲሆን በዚህ መዝገብ በተያዘው ጉዲይ ግን ግራ ቀኙ ስለአማካሪ መሀንዱሱ የስልጣን ወሰን የሚከራከሩት ውላቸውን መሰረት አድርገው በመሆኑ እና የባትኮዲ ደንቦችንም የውላቸው አካል ያላደረጉት በመሆኑ በመዝገብ የተሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በዚህ መዝገብ ለቀረበው ክርክር ተፈጻሚነት ያለው ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ቀደም ሲል እንደተገለጸው ግራ ቀኙ አለመግባባቶች እንዱወሰኑ የተስማሙት በአማካሪ መሀንዱሱ እና በግራ ቀኙ በጋራ በሚመረጥ ኮሚቴ ነው።በአማካሪ መሀንዱሱ የሚሰጠው ውሳኔ በግራ ቀኙ በጋራ ለሚመረጥ ኮሚቴ በይግባኝ የሚቀርብ ስለመሆኑ ስምምነቱ አያመለክትም።ይልቁንም የአንቀጹ አነጋገር የሚያስገነዝበው ኮሚቴው አለመግባባቶችን አይቶ የሚወስነው በመጀመሪያ ደረጃ ክርክር መሆኑን ነው።ይህም በአንድ በኩል በአሰሪው በተሰየመው አማካሪ መሀንዱስ እና በልላ በኩል ደግሞ በግራ ቀኙ በጋራ በሚመረጠው ኮሚቴ ታይተው እንዱወሰኑ ግራ ቀኙ የተስማሙት የተለያዩ ጉዲዮችን መሆኑን መገንዘብ የሚያስችል ነው።በልላ አነጋገር የውለ አንቀጽ 38 አቀራረጽ እና ይዘት ግራ ቀኙ የአማካሪ መሀንዱሱ ስልጣን የግንባታ ውለ አፈጻጸም በሂደት ላይ በሚገኝበት ወቅት የሚነሱ እና በዘርፈ በተለመደው አግባብ በአማካሪ መሀንዱስ የሚወሰኑ የምህንድስና ዘርፍ ውሳኔ የሚሹ አለመግባባቶች በአሰሪው በተሰየመው አማካሪ መሀንዱስ ታይተው እንዱወሰኑ እና የውል ግንኙነቱ በቀጠለበት ጊዜም ሆነ ከተቋረጠ በኃላ የሚነሱ ላልች አለመግባባቶች ግን በግራ ቀኙ በጋራ በሚመረጠው ኮሚቴ ታይተው እንዱወሰኑ መስማማታቸውን የሚያመለክት ነው።የውለን አንቀጽ 38 ይዘት በዚህ አግባብ መተርጎሙ ከአንቀጹ ዓላማ እና አነጋገር ጋር ብቻ ሳይሆን ክርክርን በዘመድ ዲኛ የመጨረስ ስምምነትን አስመልክቶ በፍትሐብሕር ሕግ ከቁጥር 3325 እስከ 3346 ካለት ድንጋጌዎች ጋርም የሚጣጣም በመሆኑ ተገቢነት ያለው ነው።
በተያዘው ጉዲይ አማካሪ መሀንዱሱ ውሳኔ የሰጠባቸው ጉዲዮች ዓይነት እና ይዘት በግራ ቀኙ ስምምነት መሰረት ለአማካሪ መሀንዱሱ ቀርበው እንዱታዩ የተወሰኑ የምህንድስና ዘርፍ ውሳኔ የሚሹ አለመግባባቶች ሳይሆኑ ይልቁንም ከዚህ ያለፈ እና ከምህንድስና ውጪ የላላ ዘርፍ ዕውቀትን የሚሹ በግራ ቀኙ በጋራ በሚመረጠው ኮሚቴ ታይተው እንዱወሰኑ ግራ ቀኙ የተስማሙባቸው አለመግባባቶች ናቸው።ቀደም ሲል እንደተገለጸው የዘመድ ዲኛ አለመግባባቶችን አይቶ የመወሰን ስልጣን የሚመነጨው ተገላጋዮቹ በግልጽ እና በማያሻማ ሁኔታ በጽሁፍ ከሚሰጡት ስምምነት ነው።በመሆኑም በውለ እንዱወስናቸው ከተመለከቱት አለመግባባቶች ዓይነት እና ወሰን በማለፍ እና የዘመድ ዲኛ አድርጎ ባልመረጠው አማካሪ መሀንዱስ ተሰጠ በተባለው ውሳኔ መሰረት እንዱፈጽም አመልካቹ ሉገደድ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም።ፍርድ ቤቶች በፍርደ መሰረት እንዱፈጸም ትዕዛዝ ከመስጠታቸው አስቀድሞ በሕግ አግባብ የተሰጠ የሚፈጸም ውሳኔ መኖሩን የማረጋገጥ ኃላፉነት አለባቸው።የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 392 (1) ድንጋጌ አነጋገርም ይህንኑ የሚደግፍ ነው።ባልተስማማበት እና ባልመረጠው የዘመድ ዲኛ ተሰጠበት የተባለውን ውሳኔ ለማስለወጥም አመልካች ይግባኝ እንዱያቀርብ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 350 ድንጋጌ ግዳታ አይጥልበትም።
ሲጠቃለል የአመልካቹን ክርክር ውድቅ አድርጎ አመልካች በግልግል ዲኝነቱ ውሳኔ መሰረት እንዱፈጽም ይገደዲል በማለት በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በትዕዛዝ የጸናው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ23/03/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ18/04/2006 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ትዕዛዝ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
በአመልካቹ ላይ በግራ ቀኙ ስምምነት እና በሕጉ የተመለከተውን ስርዓት ተከትል የተሰጠ ሉፈጸም የሚችል የግልግል ዲኝነት ውሳኔ የለም በማለት ወስነናል።
እንዱያውቁት የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.