አንድ የሽያጭ ውል በፍርድ ፈራሽ ነው ተብል ተዋዋዮች ወደነበሩበት እንዱመለሱ ከተወሰነ ንብረት የመመለስ ግዳታ ያለበት ሰው ንብረቱን ለውጦ ወይም በዚህ ላይ ወጪ አውጥቶ ከሆነ ከዚህ መለዋወጥ ወይም ወጪ የተነሳ ያለውን መብት በተመለከተ አለአግባብ መበልጸግ በሚለው የህጉ ክፍል መሰረት የመጠየቅ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ 1818፣የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 392/1/
No summary available.
ሰኔ 1 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ተስፊዓለም አረፊ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፍደራል የመጀሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሚያዝያ 8 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው የአፈፃፀም ትእዛዝ የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 16 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው የአፈፃፀም ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።ጉዲዩ በአፈፃፀም የተሰጠን ትእዛዝ ህጋዊነት የሚመለከት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አንደኛ ተጠሪ የአፈፃፀም ከሳሽ ፣አመልካች የአፈፃፀም ተከሳሽ ሆነው ተከራክረዋል።
የፍርድ አፈፃፀም ሂደቱ ወደ ፍርድ አፈፃፀም መምሪያ ከተመራ በኃላ የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ ፍርደን ለማስፈጸም እየተከተለ ያለው ሂደት ተገቢነት የላለው ስለሆነ፣ሂደቱ እንዱለወጥ ትእዛዝ ይሰጥልን በማለት ለሥር ፍርድ ቤት አመልካች /የፍርድ ባለዕዲ/ ጥያቄ አቅርቦ የሥር ፍርድ ቤት የአመልካችን አቤቱታ ሚያዝያ 8 ቀን 2005 ዓ.ም በሰጠው ትአዛዝ ውድቅ አድርጎታል። አመልካች የሥር ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን የአፈፃፀም ትእዛዝ አፅንቶታል።
አመልካች ሚያዝያ 3 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ውለ ፈርሶ አመልካችና ተጠሪዎች ወደነበርንበት እንድንመለስ ውሣኔ ሰጥተዋል።ይህም ውሣኔ የተሰጠው እኔ ድርጅቱን ከተረከብኩበት ሚያዝያ 24 ቀን 1998 ወዱህ ልዩ ልዩ ንብረቶችን በቦታው በማስፈር ምክንያት ነው የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሚያዚያ 24 ቀን 1995 በቦታው ላይ ያሰፈርኩትን ንብረት ዘርዝሬ እንዲቀርብ ካደረገ በኃላ በቦታው ላይ አመልካች አፍርቻለሁ በማለት የጠየቅሁትን ንብረት በተመለከተ አዱስ ክሰ አቅርቤ እንድጠይቅ የሰጠው ትአዛዝ የሰበር ችልት የሰጠውን ውሣኔ ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንድታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪዎች ሀምላ 17 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ መልስ በእኛና በአመልካች መካከል ተደርጎ የነበረው የድርጅት ሽያጭ ውል ከማድረጋችን በፉት ወደ ነበርንበት ሁኔታ እንድንመለስ ውሣኔ ተሰጥቷል።አመልካች ድርጅቱን ከእኛ የተረከበው ድርጅት እንጂ ባድ ቦታ አይደለም ስለዚህ ፍርድ አፈፃፀም መምሪያ አመልካች ድርጅቱን ከእኛ ከተረከበ በኃላ ያፈራው ንብረት የላለ መሆኑን በማረጋገጥ ድርጅቱን ለእኛ እንዱያስረክብ የተሰጠው ትእዛዝ በዋናው ጉዲይ የተሰጠውን ፍርድ መሰረት ያደረገና የሕግ ስህተት የላለበት ስለሆነ የሰበር አቤቱታው ውድቅ እንዱደረግልን በማለት አመልክተዋል።አመልካች ነሐሴ 8 ቀን 2006 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ይዘት ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የአፈፃፀም ትዕዛዝ በዋናው ጉዲይ የተሰጠውን ፍርድ ይኸ ከሰበር ችልት የሰጠውን ውሣኔና አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪዎች ሻጭ አመልካች ገዥ በመሆን ሚያዚያ 24 ቀን 1998 ዓ.ም የቡልኬት ማምረቻ ድርጅት ውል ተዋውለው የነበረ መሆኑንና በአንደኛ ተጠሪ ክስ አቅራቢነት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ህዲር 12 ቀን 2003 ዓ.ም በሰጠው ፍርድና ውሣኔ የድርጅት ሽያጭ ውለ ፈራሽ ነው ተብል ተወስኗል።
ከዚህ በተጨማሪ አመልካች በሁለተኛው ተጠሪ ስም የሚገኘውን የሲሚንቶ ውጤቶች አምርቶ መሸጫ የንግድ ድርጅት ከሚያዝያ 24 ቀን 1998 ዓ.ም በፉት ከነበረበት ሁኔታ በአንደኛ ተጠሪ/ከሳሽ/ እንዱያስረክብ ከሳሽ አንደኛ ተጠሪ በቅድሚያ ክፍያ የወሰደትን ብር 10,000/አሥር ሺ ብር / እስከ ቀረበበት ሀምላ 2 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ግምት ወለድ ጋር ለተከሳሽ / አመልካች/ እንዱከፍለ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ከዚህ በኃላ አንደኛ ተጠሪ ድርጅቱን ከቦታው ላይ ካለው አጥርና ቤት ድረስ እንድረከብ ትእዛዝ ይሰጥልኝ የሚል ጥያቄ አቅርባ ውለ ፈርሶ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ይመለሱ ተባለ እንጅ ከሳሽ በተከሳሽ የተመራን ንብረት ሉረከቡ አይገባም በማለት በመዝገብ የካቲት 29 ቀን 2003 ዓ.ም የፋዳራል የመጀሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጥቷል። የሥር ፍርድ ቤት ይህንን ትእዛዝ ከመስጠቱ በፉት በተከሳሽ /በአሁን አመልካች/ ጥያቄ አቅራቢነት፣አመልካች ሚያዚያ 24 ቀን 1998 በተደረገው ውል የገዛው የድርጅት ቦታ እንጅ ንብረት የላለበት በመሆኑ ውሣኔውን በዚህ መልኩ እንዱፈፅም በማለት ታህሣሥ 22 ቀን 2003 ዓ.ም ትእዛዝ ሰጥቷል።
የሥር ፍርድ ቤት በሰጠው ትእዛዝ ቅር በመሰኘት አንደኛ ተጠሪ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው፣የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ትእዛዝ በመዝገብ ሰኔ 20 ቀን 2003 ዓ.ም በሰጠው ትእዛዝ በማፅናቱ አንደኛ ተጠሪ በዚህ ሰበር ችልት የሰበር አቤቱታ አቅርባለች።ይህ የሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር በሰበር መዝገብ ሀምላ 2 ቀን 2004 ዓ.ም ፍርድ ሰጥቷል።ይህ የሰበር ችልት በሰጠው ፍርድ የሥር ፍርድ ቤት የፍርድ ባለመብት /አንደኛ ተጠሪን/ ክርክር ሣይሰማ ታህሣሥ 18 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠውን ትእዛዝ በማረም ታህሣሥ 24 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው የአፈፃፀም ትእዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት መሆኑን የመጀመሪያ ጭብጥ አድርጎ በመያዝ ፍርድ ሰጥቶበታል። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ከሚያዝያ 24 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ የያዘውን ንብረት የማስረከብ ግዳታ ያለበት መሆኑንና ላልችን ጉዲዬች በተመለከተ የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 392/1/ መሰረት ማዘዝ እንደሚገባቸው ገልፃ የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጡትን የአፈፃፀም ትእዛዝ ሽሮታል።
ከዚህ በኃላ አፈፃፀሙን የቀጠለው የሥር ፍርድ ቤትና ፍርደን የሚያስፈፅመው የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ የካቲት 29 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠውን ትእዛዝና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 20 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠውን ትእዛዝ ሙለ በሙለ በመሻር የአሁኑ አመልካች /ተጠሪ/ ለአመልካች ለማስረከብ የሚገደደት ከሚያዝያ 24 ቀን 1998 ዓ.ም በፉት በሽያጭ ውል ምክንያት የያዙትን ንብረት ነው በማለት በመዝገብ ሀምላ 2 ቀን 2004 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ መሰረት አጣርቶ አመልካች ለተጠሪዎች ቦታ ብቻ ሣይሆን በቦታው ላይ ያለውን ንብረት እንዱያስረክብና አመልካች ሚያዝያ 24 ቀን 1998 ዓ.ም በቦታው ላይ አፍርቻለሁ የሚለውን ንብረት ውሃና መብራት ለድርጅቱ ወጭ አውጥቼ አስገብቻለሁ የሚለትን በተመለከተ በልላ መንገድ ይጠይቁ በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል ተደርጎ የነበረው የድርጅት ሽያጭ ውለ ፈራሽ ነው ተብል በፍርድ ተወስኗል።አመልካች የገዛሁት ባድ ቦታ ስለሆነ እንድመልስ የምገደደው ባድ ቦታ መሆን አለበት በማለት ጠይቆ ፣ይህንን ጥያቄውን የሥር ፍርድ ቤት ተቀብል ታህሣሥ 24 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝና አንደኛ ተጠሪ ለአመልካች በሽያጭ ያስረከብኩትን ድርጅትና ንብረት እንድረከብ ትእዛዝ ይሰጥልኝ በማለት ያቀረበችውን ጥያቄ የሥር ፍርድ ቤት ውድቅ በማድረግ የካቲት 29 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በዚህ ሰበር ችልት ተሽሮ አንደኛ ተጠሪ ለአመልካች የሸጠችውን ድርጅትና ንብረት የመረከብ መብት ያላት መሆኑ ውሣኔ ተሰጥቶበታል።ከዚህ አንፃር አመልካች በቦታው ላይ በራሱ ወጭ ያፈራሁት ንብረት አለ በማለት የሚከራከር ቢሆንም፣ይህ የአመልካች ክርክር ጥያቄ በፍርድ ባለመብቷ አንደኛ ተጠሪ የታመነ አይደለም።
አመልካች ድርጅቱን ሚያዚያ 24 ቀን 1998 ከተረከበ በኃላ ድርጅቱ ውሃ መብራት ለማስገባት ያወጣው ወጭ አለ ወይስ የለም?አመልካች ድርጅቱን ከተረከበ በኃላ በገንዘቡ የሰራው የግንባታ ሥራ አለ ወይስ የለም?አመልካች የሰራው የአጥርና የቤት ግንባታ ሥራ አለ ቢባል በአመልካች የተሰሩ ሥራዎች በወቅቱ በነበረው የግንባታ ዋጋ ምን ያህል ያወጣለ?የሚለት ጭብጦች በአፈፃፀም ሂደት በተደረገው ማጣራት ግልፅ የሆነ ምላሽ ለማግኘት የማይቻል በሆነ ጊዜና እነዚህ ጭብጦች የግራ ቀኙን ሙለ ክርክርና ማስረጃ ተሰምቶ ሉወሰኑ የሚገባቸው ሆነው አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት ቢያገኛቸው አመልካች ቦታው ላይ ካለው ንብረት ጋር ድርጅቱን ለተጠሪ እንዱያስረክብ ትእዛዝ በመስጠት የፍርድ ባለዕዲው የፍርድ ባለመብት ከተረከባቸው ንብረት ውስጥ ሚያዚያ 24 ቀን 1998 ዓ.ም በኃላ በአመልካች ወጭ ያወጣበትና የተሰራ ነው የሚለውን ራሱን የቻለ ክስ አቅርቦ እንድጠይቅ የሰጠው ትእዛዝ የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር.392 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ይዘት መሰረታዊ ዓላማ ያገናዘበ የአፈፃፀም ትእዛዝ ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች ድርጅቱን ከተረከበ በኃላ ለመብራትና ለውሃ አውጥቻለሁ ያለው ወጭ ሰርቻለሁ የሚለው ተጨማሪ ግንባታ ውለ ፈራሽ ነው ተብል የተሰጠውን ውሣኔ የማያስለውጥ ወይም የፍርደን ተፈፃሚነት የሚያስቀር ምክንያት አይደለም በአንፃሩ ውለ ከመፍረሱ ወይም ከመሰረዙ በፉት የተነሳ ንብረት የመመለስ ግዳታ ያለበት ሰው ንብረቱን ለውጦ ወይም በዚሁ ላይ ወጭ አድርጎ እንደሆነ ከዚህ መለዋወጥ ወይም ወጭ የተነሳ ያለት መብቶች ወይም ግዳታዎች በዚህ ሕግ አላግባብ በመበልፀግ በሚመለከተው ምዕራፍ ውስጥ በተወሰኑት ድንጋጌዎች መሰረት የሚመራ መሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1818 በግልፅ ተደንግጓል።የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የአፈፃፀም ትእዛዝ አመልካች ውለ ፈርሶ ተጠሪዎች ድርጅቱን በፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረት ሲረከቡ፣እሱ ድርጅቱን ሚያዝያ 24 ቀን 1998 ሲረከብ ያልነበረ ንብረት ወይም በአመልካች ወጭ መብራትና ውሃ የገባ ተጠሪዎች አላግባብ የበለፀጉ መሆኑን በዝርዝር ገልፆ መብቱን እንዱጠይቅ የሚያመላክትና ውለ ፈራሽ በመሆኑ አመልካች በሽያጭ ውል መነሻ የተረከበውን ድርጅትና ንብረት እንዱፈፅም የሚያስገደድ ትእዛዝ በመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 392 ንዐስ አንቀፅ 1 መሥፈርት የሚያሟላ ነው። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የአፈፃፀም ትእዛዝና ውሣኔ መሰታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሚያዚያ 8 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 16 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው የአፈፃፀም ውሣኔ ፀንቷል።
ይህ ውሣኔ አመልካች ተጠሪዎች በአፈፃፀም በተረከቡት ድርጅት ላይ አውጥቸዋለሁ የሚለውን ወጭና ተጠሪዎች አላግባብ በልፅገዋል የሚልበትን ምክንያት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1818 እና ለልች አግባብነት ባላቸው ድንጋጌዎች መሰረት ጥያቄ ከማቅረብ የሚገድበው አይደለም በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.