ተወካይ የጥቅም ግጭት ባለበት አኳኋዋን የፈጸመውን ተግባር ለማፍረስ ወካዬ ይኸው ድርጊት መፈጸሙን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ አቤቱታውን ማቅረብ ያለበት ስለመሆኑ፣ የፍ/ሕ/ቁ 2187 XIII
No summary available.
ሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ረታ ቶልሳ ሙስጠፊ አህመድ አመልካቾች:-
ይህ የሰበር ጉዲይ የይርጋ ድንጋጌዎችን አፈፃፀም የሚመለከት ነው። ለይርጋ ድንጋጌዎች አፈፃፀም መነሻ የሆኑት የፍሬ-ነገር ክርክሮች ሁለቱም ወገኖች እንደ ክርክር አቅጣጫቸው በስር ፍ/ቤቶች አቅርበዋል።
እኛም በዚህ ረገድ ግራ ቀኙ በሥር ፍ/ቤቶች ሲከራከሩ በክርክር ሂደት በስር ፍ/ቤቶች ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች በመነሳት ለጉዲዩ አግባብነት ካለው የይርጋ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ የድንጋጌዎችን አፈፃፀም እንደሚከተለው መርምረናል።
የጉዲዩ መነሻ የሆነው ክስ በአሁን ተጠሪዎች በፋዳራል የከፍተኛ ፍ/ቤት አማካኝነት የቀረበው ሲሆን፤ ይዘቱም በድንገት ወደ ኤርትራ ስወጣ በአ/አበባ ከተማ በቀድሞ ወረዲ 17 ቀበላ 20 በቤት ቁጥር 2024 በካርታ የታወቀውን እና በ520 ሜትር ካሬ ስፊት በ175 ሜትር ካሬ ላይ ያረፈውን ባለ ቤዝመንት ባለ አንድ ፍቅ ከዕቃው ጋር ለአሁን 1ኛ አመልካች በውክልና አስረክቤ ከአገር ከወጣሁ በኋላ በግንቦት 01/2001 መንግስት ባወጣው መመሪያ መሰረት ወደ አገር ተመልሼ እንዱያስረክበኝ ብጠይቀው ንብረቱን ለመሸጥ ያስገደደው ሁኔታ ሳይኖር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2208 እና 2211 ከተደነገገው ውጭ ሚስቱ ለሆኑት ለአሁን 2ኛ አመልካች በብር 380,000.00 /ሶስት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር/ በሆነ ዋጋ በሽያጭ ስም የእራሳቸው የጋራ ያደረጉ በመሆኑና እንደገናም ሁለቱም በአንድነት ሆነው ጥር 19 ቀን 2000 ዓ.ም በብር 3,300,000.00 /ሶስት ሚሉዮን ሶስት መቶ ሺህ ብር/ በስር ፍ/ቤት ሁለተኛ ጣልቃ ገብ ለሆኑት ለወ/ሮ ደስታ ተመስገን ሸጠው የተጠቀሙ ስለሆነ ሁለቱም የሽያጭ ውልች ፈራሽ ሆነው ንብረቱ ካስገኘው የኪራይ አላባ ጋር እንዱከፍለ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
የአሁን አመልካቾችም ለቀረበባቸው ክስ በመጀመሪያ ደረጃ የመቃወሚያ ክርክርነት ካቀረቧቸው የመከራከሪያ ነጥቦች አንደ ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነው የይርጋ ክርክር ሲሆን ይዘቱም ከሀገር እንዱወጡ ባደረገው መመሪያ መሰረት ንብረቱ በወከላቸው በአሁን 1ኛ አመልካች አማካኝነት የተሰጠው ጥቅምት 01 ቀን 2003 ዓ.ም ነው። በነበረን የስልክ ግንኙነት እንዱያውቁትም ተደርጓል። የውል ይፍረስልኝ ክስ የቀረበውም ታህሳስ 12 ቀን 2003 ዓ.ም ስለሆነ ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው የሚለውን በመጥቀስ የቀረበ መሆኑን ያስረዲል።
ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም ከዚህ በላይ በተመለከተው የይርጋ ጉዲይ ላይ ተመርኩዞ 1ኛ ተከሣሽ የነበሩት የአሁን አመልካች በተሰጣቸው ልዩ የውክልና ስልጣን መሰረት ንብረቱን የሸጡት ጥቅምት 01 ቀን 1993 ዓ.ም ሆኖ እያለ ይህንኑ የሽያጭ ውል ለማስፈረስ ክስ የቀረበው ደግሞ ታህሳስ 12 ቀን 2003 ዓ.ም ስለሆነ በሁለቱ ጊዜያቶች መካከል ያለፈው ጊዜ ሲሰላ የ10 ዓመት ጊዜ አልፍታል 1ኛ ተከሣሽ የፈፀመውን የሽያጭ ድርጊት በመቃወም የሽያጭ ውለን ለማስፈረስ የሚቀርበው ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 መሰረት በ10 ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ሲገባው ይህ ጊዜ ካለፈ በኃላ የቀረበ ክስ ሆኖ ስለተገኘ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው ሲል ብይን ሰጥቶበታል።
ይህንኑ ብይን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩለ በጉዲዩ ላይ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ የሥር ፍ/ቤት ስለይርጋው ክርክር የሰጠውን ዲኝነት አግባብነት በሚመለከት ጉዲዩን መርምሮ፤
1ኛ አመልካች ስለ ቤቱ ጉዲይ ልዩ የውክልና ስልጣን የተሰጠው ለመሆኑ የተካደ ጉዲይ አይደለም ሆኖም በዚህ የውክልና ስልጣን መሰረት ተክቶ ቤቱን የሸጡ መሆኑ ከሣሽ የአሁን 1ኛ ተጠሪ ወደ ኢትዮጵያ ሐገር ከመግባታቸው በፉት ሻጩ ያሣወቋቸው ስለመሆኑ አልተረጋገጠም። 1ኛ ተጠሪ ቤቱ መሸጡን ያወቁት ኢት/ያ ውስጥ ከገቡ በኃላ መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም 1ኛ ተጠሪ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት ሰኔ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ስለመሆኑ በማሰረጃ ያልተደገፈ እና ማስተባበያ ያልቀረበበት ስለሆነ ቤቶቹን መሸጡን ካወቀበት፤ ወደ ሀገር ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ ክሱ እስከተመሰረበት እስከ ታህሣስ 12 ቀን 2004 ዓ.ም ያለው ጊዜ ሲሰላ 6 ወር ብቻ መሆኑን 10 ዓመት ይቀርና 1 ዓመት የሞላው አይደለም ስለዚህ ክሱ በይርጋ አይታገድም በማለት የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውን ብይን ሽሮ በቀሪዎች ክርክሮች ላይ አስፈላጊውን ዲኝነት ይሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341 መሰረት መዝገቡን በመመለስ ዲኝነት ሰጥቶበታል።
ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነውም ይኸው የጠ/ፍ/ቤት በይግባኝ ደረጃ በጉዲዩ ላይ የሰጠው የመጨረሻ ፍርድ ሲሆን የዚሁኑ ፍርድ አግባብነት ግራ ቀኙ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ደረጃ ባቀረቡት የጽሐፍ ክርክር እና ከላይ በየደረጃው ባለት ፍ/ቤቶች ከተሰጠው ዲኝነት ጋር በማገናዘብ ተመልክተናል።
እንደተመለከትነውም የአሁን 1ኛ ተጠሪ ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ በሆነው ክሣቸው ላይ ለክሱ መሰረት አድርገው ያቀረቡት የክስ ምክንያትና ለጠየቁት ዲኝነት እንደ ክሣቸው በማስረጃ ቢያረጋገጡ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት ያለው የሕግ ክፍል በውክልና ሕግ ሥር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ውስጥ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2187 እና 2188 የተመለከተውን ስለመሆናቸው በክሣቸው ዝርዝር የጠቀሷቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2208 እና 2211 ጠቅሰው ማቅረባቸው አስረጂ ከመሆኑም በላይ ተወካዩ ከቤቱ ትክክለኛ ዋጋ በታች ለሚስታቸው ሸጠው የጋራ ተጠቃሚ ከሆኑ በኃላ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ዋጋ መልሶ ለሶስተኛ ወገን ሸጠዋል የሚለው የፍሬ ነገር ክርክራቸውም አመላካች ነው። ስለሆነም በግራ ቀኙ መካከል ለተነሣው የይርጋ ክርክር ጉዲይ አግባብነት እና ተፈጻሚነት ያለው ድንጋጌ በውክልና ሕግ የተመለከተው የፍ/ሥ/ሕ/ቁ. 2187 እንጂ ውልች በጠቅላላው በተመለከተው የሕግ ክፍል የሚገኘው የፍ/ብ/ሕ/ቁ.1845 ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህም ለጉዲዩ አግባብነት ካለው ድንጋጌ አንፃር ጉዲዩን ስንመለከተው በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2187 ድንጋጌ መሰረት ተወካዩ የጥቅም ግጭት ባለበት አኳኃን የፈፀመውን ተግባር ለማስፈረስ ወካዩ ይኸው ድርጊት መፈፀሙን ካወቁበት ጊዜ ጀምሮ በሚታሰብ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ ተመልክቷል፤
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም የቀረበለትን የይግባኝ ጉዲይ ተመልክቶ ዲኝነት በሚሰጥበት ጊዜ በመጀመሪያ ደረጃ የክርክር ሂደት በሙግት የክርክር ደረጃ በግራ ቀኝ ተከራካሪ ወገኖች ከቀረቡት ክርክር እና ማስረጃ የተረጋገጠበትን ፍሬ ነገሮች ለይቶ ለማውጣት በተሰጠው ማስረጃን የመመዘንና የማስረጃን የማስረዲት ክብደት የመለካት ዲኝነታዊ ተግባሩ ተጠቅሞ የአሁን ተጠሪ ቤታቸው የተሸጠ መሆኑን መቼ አወቁ መቼ ተረደ? የሚለውን ለድንጋጌው አፈፃፀም መነሻ የሆነው የፍሬ ጉዲይ ያረጋገጠው መሆኑን ተረድተናል፤
በዚህ ረገድ የአሁን አመልካች በዚህ ሰበር ደረጃ እንዱታረምላቸው ያቀረቡት እና የጠየቁት ክርክር እና ዲኝነት ከላይ በተመለከተው የፍሬ ነገር እና ማስረጃ ጉዲይ ላይ ያተኮረ እንጂ ከህግ ጥያቄ ጋር የተገናኘ ሆኖ አላገኘነውም።
በዚህ ሁለ ምክንያት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ክሱ በይርጋ ሉታገድ የሚችል አይደለም በሚል የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ባለማግኘታችን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፤
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ77515 ግንቦት 30 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው የመጨረሻ ፍርድ ፀንቷል።
ስለይርጋ ጉዲይ የአሁን አመልካች ያቀረቡት ክርክር የህግ መሰረት ያለው ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም፤
የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የተደረገው ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ፤
No topics extracted.