አንድ ሥራ ተቋራጭ በሰራው ህንጻ ላይ የተከሰተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በላለበት ሁኔታ ወደፉት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሉኖር ይችላል በሚል ምክንያት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት መከላከል አግባብነት የላለው ስለመሆኑና የህንጻ ተቋራጩን በፍትሐብሄር ጉዲይ ማንም ሰው ኃላፉ ነው ተብል ያለመገመት /presumption of non liablity/ መሰረታዊ መርህ ስለመሆኑ፣ የፍትሐብሕር ህግቁጥር 3268፣3282/1/ የመሰረት ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በ1996 ዓ.ም አሻሽል ያወጣውን የመንግስት ግንባታ ስለ አፈጻጸም መመሪያ አንቀፅ 8 የአዱስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን እና ናሰው ኮንስትክሽን ኃ/የተ/የግ/ ማህበር
No summary available.
ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- የአዱስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ነገረ ፈጅ አርአያ ካሣ ቀረቡ ተጠሪ፡- ናሰው ኮንስትራክሽን ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር -ጠበቀ ውቡ አስነቀው - ቀረቡ መዝገቡ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሚያዚያ 2 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ ግንቦት 19 ቀን 2000 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የግንባታ ሥራ የመጨረሻ ክፍያን የሚመለከት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ከሳሽ (ተጠሪ) የተከሳሹን የምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትና የሰሜን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ህንፃ ሰርቶ ለማስረከብ ውል የተዋዋለና ከውለ በተጨማሪ የስሚንቶ የብረትና የነዲጅ ዋጋ ጭማሪ መሰረተ ልማት ባወጣው መመሪያ መሰረት ክፍያ እንደሚፈፀም መስማማቱን በደብዲቤ ቁጥር W5PP/861/08 ህዲር 23 ቀን 2001 ዓ/ም በደብዲቤ ገልፆልን ዋናውን ውል እንድንፈርም የቀረበልኝን ጥያቄ ተቀብዬ ውለን በመፈረም በውለ መሰረት የህንፃዎቹን ግንባታ አጠናቅቄ ህንፃዎቹን ለከሳሽ /አመልካች/ አስረክቤያለሁ ተከሳሽ ከሳሽ የሰራቸው ሥራዎች በተቆጣጣሪ መሀንዱስ ተረጋግጦ እየቀረበለት ክፍያ ሲፈፅም ቆይቷል። ሆኖም ተከሳሽ ሰኔ 26 ቀን 2004 ዓ/ም በአማካሪ መሀንዱስ ተረጋግጦ የቀረበለትን ብር 4,623,938.76 ( አራት ሚልዮን ስድስት መቶ ሃያ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ስምንት ብር ከሰባ ስድስት ሣንቲም) አልከፈለም። ከሳሽ ተከሳሹ ክፉያውን እንድፈፅም ማስጠንቀቂያ ብሰጠውም ያልከፈለ ስለሆነ ከሰኔ 26 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍል ውሳኔ ይሰጥልኝ የሚል ይዘት ያለው ክስ አቅርቧል።
አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ተከሳሽ በዋናው ውል ያልተፈቀደ ለነዲጅ ለሲሚንቶና ብረት የዋጋ ጭማሪ የከፈለው ብር 1,829,661.15 (አንድ ሚሉዮን ስምንት መቶ ሃያ ዘጠኝ ሺ ስድስት መቶ ስልሣ አንድ ከአሥራ አምስት ሣንቲምና) እና ለተጨማሪ ሥራዎች የከፈለው ብር 3,696,219.55 (ሶስት ሚሉዮን ስድስት መቶ ዘጠና ስድስት ሺ ሁለት መቶ አስራ ዘጠኝ ብር ከሃምሳ አምስት ሣንቲም) የፊይናንስ ደንብና መመሪያ ያልተከተለ መሆኑን የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፊይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አሳውቋል። ስለዚህ ይኽ ገንዘብ ሉቻቻልልን ይገባል። በልላ በኩል ተከሳሽና ከሳሽ የህንፃውን የመጨረሻ ርክክብ ያልፈፀመ በመሆኑ ከሳሽ የመጨረሻ ክፍያ ሉጠይቀኝ አይገባም የሚል የመከላከያ መልስ አቅርቧል።
የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቷል የሥር ፍርድ ቤት የተከሳሽ (አመልካች) አማካሪ መሃንድስ ቀርቦ የሰጠውን የምስክርነት ቃል ከሰማ በኃላ አመልካች ያቀረበውን የመቻቻል ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል። የሥር ፍርድ ቤት አመልካች የመጨረሻ ርክብክብ ሣይደረግ ክፍያ አልከፍልም በማለት ያቀረበው ክርክር የህንፃ ሥራ ውለ የሚተዲደርበት የኮንስትራክሽን ዘርፍ መመሪያ መሰረት ያላደረገ ክርክር መሆኑን ገልፆ ተከሳሽ ከሳሽ ለሰራውና ሥራው ተረጋግጦ በአማካሪ መሃንድሱ ፀድቆ የቀረበለትን ክፍያ የማይከፍልበት ህጋዊ ምክንያት የለበትም በማለት ተከሳሽ ከሳሽ በክሱ የጠየቀውን ገንዘብ ክስ በተመሰረተበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍል ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ግንቦት 28 ቀን 2006 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ አማካሪ መሃንድስ ሳይወስን የተደረገው የዋጋ ንረት ስምምነት መሰረት የተከፈለው ክፍያና ለተጨማሪ ሥራ የተከፈለው ክፍያ የፊይናንስን ደንብ ያልተከተለ በመሆኑ ተጠሪ ከቀረበው ጥያቄ ጋር ተቻችል ቀሪው ተራፉው እንዱመለስልን ያቀረብነው ጥያቄ አላግባብ ውድቅ ተደርጎብናል። ተጠሪና አመልካች የመጨረሻ ርክብክብ ሣያደርጉ የመጨራሻ ክፍያ እንድንከፍል የተወሰነው ውሳኔ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1757 ድንጋጌን የሚጥስ ነው። አመልካች ስህተቱን ማረም እንደሚችል ይኽ ሰበር ችልት የሰጠውን አስገዲጅ ትርጉም የበታች ፍርድ ቤቶች ማለፊቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ መስከረም 28 ቀን 2007 ዓ/ም በተፃፈ መልስ አመልካች ለተጠሪ ክፍያ የከፈለው ተጠሪ የሰራው ሥራ ተቆጥሮ፣ ተለክቶና ተረጋግጦ አማካሪ መሀንድሱ ባፀደቀው ክፍያ ሰነድ መሰረት ነው። አመልካች ያልተሰራ ሥራ የከፈለው ክፍያ የለም። የዋጋ ንረት ሥምምነቱም አመልካች ስምምነቱን ሰጥቶ የውል ግዳታ የገባበት ነው።
ተጠሪ ከህግ አግባብ ውጭ ከአመልካች የተከፈለው ክፍያ ላላ በመሆኑና አመልካች ያቀረበው ይቻቻልልኝ ጥያቄ የህግ ሥርዓቱን የማያሟላ ሆኖ በመገኘቱ ውድቅ መደረጉ ተገቢ ነው።
የመጨረሻ ክፍያ የሚፈፅመው የህንፃው የመጨረሻ ርክብክብ ሲደርግ ነው በማለት ተጠሪ ያቀረበው መከረከሪያ የህግ መሰረት የለውም አመልካች ህንፃዎቹን ተረክቦ እየተጠቀመ ይገኛል። በህንፃ ላይ ለሚከሰት ጉድለት ማስተካከያ የሚሆን የመያዥያ ክፍያ ይዟል። ከዚህ ውጭ የመጨረሻ ክፍያ የመጨረሻ ርክብክብ እስኪደረግ አልከፍልም በማለት ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት የላለው ስለሆነ ውድቅ ይደረግልኝ። አመልካች ጥቅምት 17 ቀን 2007 ዓ/ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ለዚህ ሰበር ችልት ከግራ ቀኙ የቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን የመቻቻልና የመጨረሻ ርክብክብ ካልተፈፀመ የመጨረሻ ክፍያ እንድከፍል አልገደድም የሚል መከራከሪያ ውድቅ በማድረግ ለተጠሪ በክሱ የጠየቀውን ገንዘብ እንድከፍል የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ ከአመልካች ጋር ህዲር 30 ቀን 2001 ዓ/ም የግንባታ ሥራ ውል ከመዋዋለ በፉት የግንባታ ዕቃ ላይ በሚፈጠር የዋጋ ግሽበት ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮች አሰሪው (አመልካች) የሚሸፍንበት ድንጋጌ በዋናው ውል እንዱካተት ህዲር 19 ቀን 2001 ዓ/ም ጥያቄ አቅርቦ፤ አመልካች ተጠሪ ባቀረበው ሀሳብ የሚስማማ መሆኑን ህዲር 23 ቀን 2001 ዓ/ም በተፃፈ ደብዲቤ በመግለፁ ህዲር 30 ቀን 2002 ዓ/ም በዋጋ ግሽበት ምክንያት በሚፈጠረው ጭማሪ ላይ ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች የጋራ መግባባት ኖሯቸው የግንባታ ሥራ ውለ የተፈረመ መሆኑን አመልካችና ተጠሪ አልተካካደም። የህንፃው አሰሪ የሆነው አመልካች በግንባታ ዋጋ ንረት የሚመጣን ጭማሪ ዋጋ ለመሸፈን ሙለ ስምምነቱን ከሰጠ በኃላ፣ ስምምነቱን ከመሰጠቱ በፉት ያላሟላው ሥርዓት ያለ መሆኑ በኦዱተር በመተቸቱና አመልካች በተጨማሪ ሥራዎች እንዱሰሩ የሥራ ትዕዛዝ ሲሰጥና ክፍያ ሲፈፅም አንድ የአሰራር ጉድለት ያለ መሆኑ በድርጅቱ የበጀት አጠቀቀምና የፊይናንስ አያያዝና አወጣጥ ሥርዓት በመጀመሩ ኦዱተሮች መተቸቱ አመልካችና ተጠሪ ዋናውን የሥራ ውል ከመዋዋላቸው በፉት ባደረጉት የደብዲቤ ልውውጥ የተስማሙበትን የዋጋ ንረት ጭማሪ ክፍያ ስምምነትና በአመልካችና በአማካሪ መሀንዱስ በተሰጠው ተጨማሪ የሥራ ትዕዛዝ መሰረት ተጠሪ ሥራው የግንባታ ሥራ መጠንና ጥራትና ዋጋ ተረጋግጦ ለሰራው ሥራ የተከፈለውን ገንዘብ ህገ ወጥ የማድረግ ውጤት የሚያስከትል አይደለም። ከዚህ አንፃር አመልካች ከተጠሪ ጋር በተዋዋለው የግንባታ ዕቃዎች የዋጋ ንረት ጭማሪ ክፍያ ስምምነትና ተጠሪ በተሰጠው ተጨማሪ የሥራ ትዕዛዝ መሰረት ለሰራው ተጨማሪ ሥራ የተከፈለው ገንዘብ እንዱመለስለት ያቀረበው የመቻቻል ጥያቄ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1731 ንፁስ አንቀፅ 1 ገዥ መርህ የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 3252 ንዐስ አንቀጽ 1 እና የፍተብሓር ህግ ቁጥር 3266 ንዐስ ድንጋጌዎች ይዘትና ህጋዊ ውጤት ያገናዘበ ሆኖ አላገኘነውም።
አመልካች ተጠሪ ግራ ቀኙ ካደረጉት ውል ውጭ በተጭበረበረ ሀሰተኛ የክፍያ ሰነድ ተጠሪ ክፍያ የወሰደ መሆኑን ወይም ተጠሪ በግንባታ ሥራ ውለና ከውለ ጋር በአባሪነት በተያያዘው የግንባታ ሥራ የጊዜ ሰላዲ መሰረት ግንባታውን በውለ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ ባለማጠናቀቁና ግንባታው በመዘግየቱ ተጠሪ ለአመልካች የሚከፍለው ኪሣራ ወይም ቅጣት ገንዘብ ያለ ስለመሆኑ ያቀረበው ክርክር የለም። አመልካች በተጠሪ ላይ ያቀረበው በቂ የህግና የክስ ምክንያት ያለው የበሰለ የመብት ጥያቄ ሳይኖር ከተጠሪ ጋር በተደረገ ስምምነት መሰረት በማድረግ ለተጠሪ የዋጋ ንረት ጭማሪ ክፍያና የተጨማሪ ሥራ ክፍያ ተጠሪ እንዱመለስ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበው ጥያቄ የፍተብሓር ስነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 236 እና በፍትሐብሕር ሥነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 238 ንዐስ አንቀፅ 2 መስፈርት የማያሟላ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች የቀረበውን የመቻቻያ ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 30 እና የፍትሐብሕር ስነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 234 ንዐስ አንቀጽ 1 በሚደነግገው መሰረት ከተጠሪ የሚጠይቀውን የገንዘብና ተጠሪ ገንዘቡን እንዱመልስ ኃላፉ የሚሆንበትን ከሕግ ወይም ከውል የመነጨ ኃላፉነት በመግለፅ የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ አላቀረበም። በመሆኑም አመልካች አለኝ የሚለውን መብት በፍርድ ለማስወሰን ሕጉ የዘረጋቸውን ሥርዓት ያሟላ ክርክርና የመብት ጥያቄ ያላቀረበ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ክርክር ውድቅ ማድረጉ በአግባቡ ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች አማካሪ መሀንድሱ ለተጠሪ ያፀደቀለትንና ተጠሪ ክስ ያቀረበበትን የመጨረሻ ክፍያ የህንፃው የመጨረሻ ርክብክብ ከመደረጉ በፉት የመክፈል ግዳታ የለብኝም በማለት ያቀረብኩት ክርክር ውድቅ መደረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው የሚል የሰበር አቤቱታና ክርክር አቅርቧል። ይህንን የአመልካችን ክርክር ህጋዊነት ለመመርመር አመልካችና ተጠሪ ያደረጉት የሥራ ውል ልዩ ሁኔታና የግንባታ ሥራው የሚመራበትን ጠቅላላ ሁኔታ እንደዚሁም ስለ መጨረሻ ርክብክብና የክፍያ አፈፃፀም የተደነገጉትን አግባብነት ያላቸው የህግ ድንጋጌዎች መመርመር ያስፈልጋል።
አመልካች ተጠሪ የገነባቸውን ህንፃዎች ተረክቦ እየተገለገለባቸው መሆኑን ግራ ቀኙ በሥር ፍርድ ቤትና ለዚህ ሰበር ችልት ያቀረቡት ክርክር ያሳያል። አመልካች ከተጠሪ ጋር ባደረገው ልዩ የግንባታ ሥራ ውል ሁኔታ፣ ለህንፃው ተቋራጭ ለተጠሪ የመጨረሻው ክፍያ የሚከፈለው የህንፃው የመጨረሻ ርክብክብ ከተፈፀመ በኃላ መሆኑን ተስማምተው ስምምነታቸውም በውለ ልዩ ሁኔታ ውስጥ የተገለፀ መሆኑን በመግለፅ የቀረበው ክርክር የለም እንደዚሁም አመልካች ህንፃውን በጊዚያዊነት ከተረከበ በኃላ በህንፃው ላይ የሚታይ ጉድለት መኖሩንና በህንፃው ላይ የሚታየውን ጉድለት ለማስተካከል በግንባታ ሥራ ውለና በግንባታ ሥራዎች ላይ ተፈፃሚነት ባላቸው ደንቦች መሰረት በየወቅቱ ተጠሪ ከሚከፈለው ክፍያ እየቀነሰ በመያዣነት የያዘው የጉድለት ማስተካከያ የመያዥያ ገንዘብ የማይበቃው መሆኑንና ጉደለቱን ለማስተካከል ለተጠሪ ከሚከፈለው የመጨረሻ ክፍያ ክፉለን ወይም ሙለን የሚጠይቅ ስለመሆኑ የቀረበው ክርክር የለም።
አመልካች ከላይ የተገለፁትን ሁለት መከራከሪያዎች ሳያቀርብ ተጠሪ ህንፃዎቹን ሥራ ለማጠናቀቅና ህንፃዎች አገልግልት ላይ እንዱውለ ለማድረግ የሥራው የማጠናቀቂያ ሥራዎች መጠንና ጥራት ዋጋ በአማካሪ መሀንድሱ ተረጋግጦ የፀደቀውን ክፍያ አልከፍልም በማለት ይዞ የሚቆይበት በቂ ምክንያት ያለው መሆኑን የማስረዲት ግዳታ አለበት። ከዚህ አንፃር ክፍያ ለመፈፀም ተጠሪ የሰራቸው ሥራዎች አመልካች በመደበው አማካሪ መሀንድስ መመርመር መለካትና በሥራው የሚከፈለው ነጠላዎች ጥቅል ዋጋ በአማካሪ መሀንድስ ፀድቆ መቅረቡ አስፈላጊ ሁኔታ መሆኑን አመልካችና ተጠሪ ከተዋዋለት የግንባታ ስራ ውል እና ግራ ቀኙ ከሚያቀርቡት ክርክር የተረዲ መሆኑን ገልፆ የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔው አስፍሮታል። ይህ ከሆነ አመልካች ተጠሪ ሥራውን ከሰራ በኃላ ክፍያ ለመፈፀም አስፈላጊ የሆነውን የምርመራና የማረጋገጡ ሥራ በውለ በተገለፀው ጊዜ ውስጥ መፈፀምና ክፍያውም የምርመራና የማረጋገጡ ውጤት እንዱታወቅ መፈፀም ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 3268 ድንጋጌዎች እና የመሰረተ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር 1996 ዓ/ም አሻሽል የወጣውን የመንግስት ግንባታ ሥራ አፈፃፀም መምሪያ አንቀጽ 8 በጣምራ በማንበብ ለመረዲት ይቻላል። ከላይ ከጠቀስናቸው የህግ ድንጋጌዎች አንፃር ሲታይ አመልካች የመጨረሻ ርክብክብ ሣይደረግ ለተጠሪ የመጨረሻ ክፍያ የመፈፀም ኃላፉነት የለብኝም በማለት የሚያቀርበው ክርክር የህግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ከላይ ከተገለፀው በተጨማሪ ተጠሪ የገነባቸውን ህንፃዎች ለተጠሪ አስረክቦ ህንፃዎቹ በተጠሪ ቁጥጥርና ይዞታ ስር ሆነው እየተገለገለባቸው እንደሚገኝ ተረጋግጧል አመልካች ከተጠሪ ጋር የመጨረሻ እርክብክብ ለማድረግ ያላስቻለው በቂ ምክንያት ያለ ስለ መሆኑ በክርክሩ አልገለፀም። የህንፃው የመጨረሻ ርክብክብ ተጠሪ ስለሚፈልገው የሚፈፀም ተግባር አይደለም። አመልካች የመጨረሻ እርክብክብ በማድረግ ሉስተካከል ይገባቸዋል የሚላቸውን ጉድለቶች ለተጠሪ የማሳወቅ እንዱስተካከለ ማድረግና ርክብክቡን በህጉ መሰረት ለመፈፀም ፍቃደኛና ዝግጁ ሆኖ መገኘት አለበት። ተጠሪ በገነባቸው ህንፃዎች ላይ ለሚከሰት የአሰራር ጉድለት አመልካች ህንፃዎቹን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አስር ዓመት መድህንና ኃላፉ እንደሚሆን በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 3282 ንዐስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል ይህም አመልካች የመጨረሻ ርክብክብ ለመፈፀም ያጋጠሙትን ችግሮች ሣያስረዲ የመጨረሻ ርክብክብ ሣይደረግ ቀሪ ክፍያ አልከፍልም የሚለው ክርክር ህጋዊ ዕውቅናና ውጤት ከተሰጠው በአራቱ የሚገኙ የሥራ ተቋራጮች ከባንክ ወይም በልላ መንገድ ያገኙትን ካፒታል በመጠቀም ለሰሩት ሥራ ወዱያውኑ ክፍያ እንዲያገኙ የማያደርግና ይህም በምላሹ በህንፃ ተቋራጩና በኮንስትራክሽን እንደስትሪ ላይ የፊይናንስና የኢንቨስትመንት እጥረት እንዱከሰት የሚያደርግ ይሆናል።
የሥራ ተቋራጩ በሰራው ህንፃ ላይ የተከሰተ እርግጠኛ የአሰራር ጉድለት በላለበት ሁኔታ ወደ ፉት የሚታይና የሚከሰት የአሰራር ጉድለት ሉኖር ይችላል በሚል መነሻና ግምት ሥራ ተቋራጮች ለሰሩት ሥራ የመጨረሻ ክፍያ የማግኘት መብት አግባብ መከልከል ገንዘቡ በህንፃ አሰሪዎች በእጅ ያለ በቂ ምክንያት ታስሮ እንዱቀመጥ የሚያደርግና የህንፃ ተቋራጩን በፍትሐብሕር ጉዲይ ማንም ሰው ኃላፉ ነው ተብል ያለመገመት /presumption of non liablity) መሰረታዊ መርህ የሚጥስ ነው። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤት አመልካች የመጨረሻ ርክብክብ ያልተፈፀመ በመሆኑ ተጠሪ የጠየቀውን ክፍያ መክፈል የለብኝም ውድቅ በማድረግ የሰጠውን ውሳኔ ይግባኝ ሰሚው ችልት በትዕዛዝ ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም ።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጡት ውሳኔ ፀንቷል።
ይህ ፍርድ ቤት ግንቦት 29 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። የዕግድ ትዕዛዙ የተነሳ መሆኑ ለሚመለከተው ክፍል ይፃፍ
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራቸው ይቻለ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.