ለክርክር ምክንያት በሆነው መሬት ወራሽ መሆኑን በማስረጃ ያረጋገጠ ሰው ከአውራሹ ተነጥል ለጊዜው ውጭ ሀገር ሄድ መመለሱ በሕጉ “ለቤተሰብ አባል” የተቀመጠውን ትርጉም አላሟላም በሚል በቤተሰብ አባልነት መሬቱን ሉወርስ አይገባም ማለት ተገቢነት የላለው ስለመሆኑ፣ የአ/ብ/ክ/መ አዋጅ ቁጥር 133/98 ፣ደንብ ቁጥር 51/99 አንቀጽ 11/7/ሀ/ XII
No summary available.
ቀን 30/11/2007 ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃም መሰለ አመልካች፡- ዘሙ አስፊው አልቀረቡም ተጠሪ፡- መሀመድ አስፊው ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የእርሻ መሬት ይዞታን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው አማራ ክልል ሰሜን ወል ዞን ሀብሩ ወረዲ ፍ/ቤት ነው። የአሁኗ አመልካች በተጠሪ ላይ አቅርበውት የነበረው ክስ ይዘት አያቶቼ ከሆኑት ሟቾች አቶ አስፊው ሽኩር እና እናት ሰይድ ጋር በ1983 ዓ.ም መሬት በተሰጣቸው ወቅት በቤተሰብ አባልነት ተመዝግቤ እኖር ነበር። ለአያቶቼ በተሰጣቸው የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ላይ ስሜ በቤተሰብነት ተመዝግቧል። የቤተሰብ አባል ስለሆንኩ ወራሽነቴን አረጋግጫለሁ ተጠሪ /ተከሳሽ/ ድርሻ ይዞታ መሬት ያካፍልኝ የሚል ነው።
ተጠሪ በበኩላቸው አመልካች መሬት የተተመነችው ከአያቶቿ ከእኔ ወላጆች ሳይሆን ከወላጆቿ ጋር ነው። የወላጆቼ ወራሽ በመሆኔ ይዞታው በስሜ ተዛውሯል አመልካች ለክስ ምክንያት ከሆነው መሬት ድርሻ የላትም በማለት ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱም የግራቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መርምሮ አመልካች ለክርክር ምክንያት በሆነው ይዞታ ደብተር ላይ በቤተሰብ አባልነት የተመዘገበች በመሆኑ እና የወራሽነት ማስረጃ ያቀረበች በመሆኑ ከተጠሪ ጋር መሬቱን የመካፊል መብት አላት ብል ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ የአሁኑ ተጠሪ ያለውን ቅሬታ ለሰሜን ወል ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በይግባኝ አቅርቦ ግራቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ስር ፍ/ቤት ከሳሽ /የአሁኑ አመልካች/ የሟቾቹን ገቢ በቋሚነት እየተጋራች የምትኖር መሆኑን የራሷ ገቢ ያልነበራት መሆኑን ማጣራት ሲገባ ክክርክሩ መሬት እንደተቻለው መልስ ሰጭ በራሳቸው የሚተዲደሩ እና የራሳቸውን ገቢ ለማግኘት ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ ከሟቾች በመለየት ሣውዱ አረቢያ የኖሩ መሆኑ ራሳቸው ያመኑት ፍሬ ነገር በመሆኑ በአ.ቁ.133/98 ለቤተሰብ አባል የተሰጠውን ትርጉም የማያሟለ በመሆናቸው የሟቾችን መሬት በቤተሰብ አባልነት ስም ሉወርሱ አይገባም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሯል።
በዚህ ውሳኔ የአሁኗ አመልካች ቅሬታቸውን ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም በማለት ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
አመልካች ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን ጉዲዩ ለሰበር ችልት አያስቀርብም በማለት ተዘግቶባቸዋል።
አመልካቿ በስር ፍ/ቤቶች ተፈፀመ ያለትን መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመጥቀስ በዚህ ሰበር ችልት እንዱታረምላቸው አቤቱታ አቅርበዋል።
አቤቱታቸው ለሰበር ችልት ያስቀርባል የተባለው አመልካች በቤተሰብ አባልነት መመዝገቡ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ግንዛቤ ከተወሰደ በኋላ ወደ ሣውዱ አረቢያ መሄዶን ብቻ ምክንያት በማድረግ ቋሚ ስራ እንዲላት አድርጏ መወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ተብል ነው።
ግራቀኙ የፅሐፍ ክርክራቸውን አድርገዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር ከስር ፍ/ቤት ውሳኔ እና ጉዲዩ ለዚህ ችልት ያስቀርባል ተብል ከተያዘው ጭብጥ ጋር መርምረናል። እንደመረመርነውም አመልካች ስለክርክር ምክንያት በሆናቸው ይዞታ መሬት የይዞታ ደብተር ላይ በቤተሰብ አባልነት የተመዘገበች መሆኑ እና አረብ ሐገር እስከሄደችበት 1996 ዓ.ም ድረስ ከሟች አያቶቿ ጋር ትኖር የነበረ መሆኑ አረብ ሐገር እንዲለች አያቶቿ የሞቱ መሆኑ እና ከአረብ ሀገር ተመልሳ ለክርክር ምክንያት በሆነው መሬት ወራሽ መሆኗን በአዋጅ ቁጥር 133/98 እና ደንብ ቁጥር 51/99 አንቀፅ 11/7//ሀ/ መሰረት በማረጋገጥ ማስረጃ ያቀረበች መሆኑ ደርሶናል ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ተመልክቷል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አመልካች በ1996 ዓ.ም ከአያቶቿ ተለይታ ሣውዱ አረቢያ የኖረች መሆኑ ላላ ማስረጃ ሳያስፈልገው አመልካች በአዋጅ ቁ.133/98 ለቤተሰብ አባል የተሰጠውን ትርጉም አታሟላም በማለት መደምደሚያ ላይ መድረሱ ከአዋጁ ትርጉምና ዓላማ የራቀ ነው።
አመልካች ለጊዜው ወደ አረብ ሐገር መሄዶ በአዋጁ አንቀፅ 133/98 ለቤተሰብ ከተሰጠው ትርጉም ውጭ የሚያደርጉት አይሆንም ከአረብ ሐገር ከተመለሰች በኋላ ቀደም ሲል ስትኖርበት በነበረው ይዞታ መሬት ድርሻዋን ወስዲ በግብርና ለመተዲደር መብቷን ለማስከበር ያቀረበችው አቤቱታ አረብ ሐገር ሄዲ በመመለሷ ብቻ የራሷ መተዲደሪያ እንዲላት እና ለክርክር ምክንያቶች ከሆነው መሬት መጠቀሟ ተቋርጧል የቤተሰብ አባል አይደለችም። ለክርክር ምክንያት በሆነው መሬት ድርሻ የላትም ተብል መወሰኑ የክልለን አዋጅ ቁ.133/98 ዓላማን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ በስር ከፍ/ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ እንዱሁም ይህን ተከትል በይግባኝ እና በሰበር ችልቱ የተሰጡ ውሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመባቸው ናቸው ብለናል።
የሰሜን ወል ዞን ከፍ/ፍ/ቤት በመ/ቁ.11603 በቀን 19-11-03 ዓ.ም በዋለ ችልት የሰጠው ውሳኔ፣ የክልለ ጠ/ፍ/ቤት በ/ይ/መ/ቁጥር 03-09093 በቀን 1/03/07 ዓ.ም እና ጠ/ፍ/ቤት በጠ/ፍ/ሰ/ይ/መ/መ/ቁ. 03-09714 በቀን 24/4/2007 ዓ.ም በዋለ ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ቁ.348/1/ መሰረት ተሽሯል። ብለናል።
የወረዲው ፍ/ቤት በመ/ቁ.11-902 በቀን 7/08/2006 ዓ.ም በዋለ ችልት የሰጠው ውሳኔ --- ቁ.348/1/ መሰረት ፀንቷል ብለናል።
ግራቀኙ በዚህ ሰበር ችልት ያወጡትን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የውሳኔው ትክክለኛ ቅጅ ለስር ፍ/ቤቶች ይላክ።
No topics extracted.