በስጦታ ሰጪ ላይ በተደረገ የመንፈስ መጫን የተደረገ የስጦታ ውል ይፍረስልን ጥያቄ መቅረብ ያለበት ስጦታው በተደረገ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ስለመሆኑ አጠቃለይ የሥጦታ ውልን በመቃወም የይፍረስልን ጥያቄ መቅረብ ያለበት በአስር ዓመት ጊዜ ውስጥ ስለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ.2441፣በፍ/ብ/ሕግ ቁ.1845
No summary available.
ቀን 30/11/2007ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃም መሰለ አመልካቾች፡- 1ኛ. ወ/ሮ አሰፈ ዘለቀ 2ኛ. ወ/ሮ ብርቱካን ዘለቀ 3ኛ. ወ/ሮ ሰላማዊት ዘለቀ 4ኛ. ወ/ሪት አምሳለ ዘለቀ ጠበቃ አበበ ደጉ 5ኛ. ወ/ሮ ተስፊነሽ ዘለቀ 6ኛ. ወ/ሪት ወርቁሀ ዘለቀ 7ኛ. ተማሪ ራሄል ዘለቀ ተጠሪ፡- አቶ ዲዊት በርሄ አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የይርጋ ተፈጻሚነትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው ሃዋሳ ከተማ የመጀ/ደ/ፍ/ቤት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካቾች በተጠሪ እና 2ኛ ተከሳሽ በነበሩት ወላጅ እናታቸው ላይ በመሰረቱት ክስ ነው። የአመልካቾች የክስ ይዘት፡- ሟች አባታችን አቶ ዘለቀ ባዱቦ በንግድ ስራ ተሰማርቶ እያለ በሞት ሲለይ ለአቅመ ሄዋን አልደረስንም። እናታችን ሞግዚት ሆና የካቲት ወር 1988ዓ.ም ወራሽነታችንና የሷን ሞግዚትነት በፍ/ቤት አረጋግጧል። በአባታችን የውርስ ሃብት ስታስተዲድረን ነበር ተጠሪ የእናታችን ወንድም ልጅ በመሆኑ ቤተሰብ ነው። 1ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) ከ2ኛ ተከሳሽ (የአመልካቾች እናት) ጋር በመመሳጠር የውርስ ሃብታችን እንደሆነ እያወቀ በአመልካቾች የውርስ ሀብት ላይ የመዋዋል ስልጣን ሳይኖረው ሃምላ 2ቀን 1999 ዓ.ም 2ኛ ተከሳሽ ከሆነችው እናታችን ጋር የስጦታ ውል እንደተዋዋለ ተረድተናል። የስጦታ ውለ በተደረገበት ጊዜ ሁለት አመልካቾች ለአቅመ ሄዋን አልደረስንም። 2ኛ ተከሳሽ ከንብረቱ ግማሹ የአመልካቾች የውርስ ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ስልጣን አልነበራትም በራሷም መብት ሲሆን ልጆቿን አለአግባብ ከውርስ መንቀል አትችልም። በተጠሪው እና በ2ኛ ተከሳሽ (የአመልካቾች ወላጅ እናት) መሀከል የተደረገው የስጦታ ውል ለህግና ለሞራል ተቃራኒ እና 2ኛ ተከሳሽ የግል ንብረቷ ባልሆነ ንብረት ላይ የተደረገ የስጦታ ውል በመሆኑ በህግ ፉት የማይጸና ፈራሽ ነው ተብል ይወሰንልን። በ2ኛ ተከሳሽ ስም የተዘዋወረው ንብረት ስመ ባለቤትነት ተሰርዞ ወደ አመልካቾች ይዛወርልን የሚል ነው።
ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ጉዲዩ የቀረበለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለውም የሚል እና ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ያቀረቡ ሲሆን በአማራጭ መልሳቸው ክርክር ያስነሳው ቤት በስጦታ ውል ለ1ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) በተላለፈበት ጊዜ ንብረትነቱ በ2ኛ ተከሳሽ በስማቸው የባለሃብትነት ማስረጃ አውጥተው የአመልካቾች አባት ባለቤት ናት ወደ 2ኛ ተከሳሽ ከተዛወረ በኋላ የስጦታ ውለ የተደረገ በመሆኑ የስጦታ ውለ ለህግም ሆነ ለሞራል ተቃራኒ ነው ልባል አይገባም። 2ኛ ተከሳሽ ባለሃብትነቱን በስማቸው አዛውረው ለባንክ ያስያዙትን ንብረት እዲውን ከፍዬ ስጦታውን እንድቀበል ሳደርግ አመልካቾች ሳይቃወሙ የስጦታ ውለ ተደርጎ 7ዓመት ከሆነ በኋላ ክስ ማቅረባቸው ተገቢ አይደለም የሚል ነው ፍ/ቤቱ በተጠሪ የተነሳውን መቃወሚያ በብይን አልፍ የግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማ በኋላ ለክርክር ምክንያት ከሆነው ሆቴል ግማሹን 50% 2ኛ ተከሳሽ ለተጠሪ በስጦታ ማሳለፊቸው ወይም መስጠታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የአመልካቾች የውርስ ድርሻ የሆነውን ግማሹን 50% የአመልካቾች ያልተከፊፈለ የውርስ ሃብትን ጠቅላላው ለ1ኛ ተከሳሽ (ተጠሪ) የሰጡ በመሆኑ የሥጦታ ውለ በከፉል ይፍረስ። ወደ ነበሩበት መመለስ የማይቻል ስለሆነና ንብረቱን በስምምነት መካፈል የሚችለ ከሆነ ይካፈለ ካልቻለ በሃራጅ ሸጠው እኩል ይካፈለ ከባንክ በብድር የተወሰደውን ብር 600,000 አመልካቾች 300,000 ብር ለተጠሪ ይክፈለ በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ የአሁኑ ተጠሪ ይግባኝ ቅሬታቸውን ለሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ጉድለት የለውም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 377 መሰረት ይግባኙን ሰርዞታል።
በስር ፍ/ቤቶች በተሰጡ ውሳኔዎች ላይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ይታረምልኝ በማለት ተጠሪ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የተጠሪዎች (የአሁኑ አመልካቾች) ጥያቄ ይዘት በእናታቸው የተደረገ የሥጦታ ውል እንዱሻር የሚጠይቅ ነው። ተጠሪዎች ስጦታው ከተደረገበት ቀን አንስቶ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ክስ ያላቀረቡ በመሆኑ ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2441(1) መሰረት በሁለት አመት ይርጋ ቀሪ የሚሆን ነው በማለት የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ በመሻር ወስኗል።
በዚህ በክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ላይ ተፈጸመ ያለትን መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመጥቀስ አመልካቾች አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
የአመልካቾች አቤቱታ ያስቀርባል የተባለው የአመልካቾች የስጦታ ውል ይፍረስልን ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2441 (1) ውለ ከተደረገ ጀምሮ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ አልቀረበም በይርጋ ይታገዲል የይርጋው ክርክር በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 በ10ዓመት የይርጋ ጊዜ አይታይም መባለ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ተብል ነው የግራ ቀኙን ክርክር ከስር ፍ/ቤት ውሳኔ እና ከተያዘው ጭብጥ አንጻር እንዱሁም አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ ጋር መርምረናል። እንደመረመርነውም ከስር ፍ/ቤት ውሳኔ እና በዚህ ሰበር ችልት ግራ ቀኙ ካደረጉት ክርክር የአመልካቾች የመብት ጥያቄ የሟች አባታችን የውርስ ድርሻ እና በስር ፍ/ቤት 2ኛ ተከሳሽ የሆነችው ወላጅ እናታችን የሚስትነት ድርሻ ያለበትን ንብረት የስር 2ኛ ተከሳሽ የወንድሟ ልጅ ለሆነው ተጠሪ በስጦታ ውል አሳልፊ መስጠት አትችልም የተደረገው የስጦታ ውለ ለሞራል እና ለሕግ ተቃራኒ በመሆን ይፍረስልን የሚል ነው። አንድ ሰው በስጦታ ለላላ ሰው መስጠት የሚችለው የራሱ የሆነውን ንብረት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2427 ተመልክቷል። የስር ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካቾች የስጦታ ውለ ይፍረስልን በሚል ክስ የማቅረብ መብታቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2441(1) መሰረት በሁለት አመት ይርጋ ቀሪ ይሆናል በሚል የሰጠው ውሳኔ የተጠቀሰው የፍ/ሕግ ድንጋጌ መነሻ የሚያደርገው ፍ/ብ/ሕግ አንቀጽ 2439 ስለመንፈስ መጫን የሚለውን በመሆኑ አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ በስጦታ ሰጪ ላይ በተደረገ የመንፈስ መጫን የተደረገ የስጦታ ውል ይፍረስልን የሚል ባለመሆኑ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው ይርጋ በፍ/ብ/ሕግ ቁ.1845 የተመለከተው መሆን ሲገባው የፍ/ሕ/ቁ. 2441(1) ጠቅሶ የአመልካቾች አቤቱታ በሁለት አመት ይርጋ ታግዶል (ቀሪ ሆኗል) በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል።
የደ/ብ/ብ/ከ/መ/ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ር በቀን 21/01/2007ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
በተያዘው ጉዲይ ተፈጻሚነት ያለው የይርጋ ድንጋጌ ፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2441(1) ሳይሆን በፍ/ሕ/ቁ. 1845 የተመለከተው ነው ብለናል።
የክልለ ጠ/ፍ/ቤት ከይርጋ ክርክር ውጭ ባለ በግራ ቀኙ ክርክሮች የመሰለውን ውሳኔ ይስጥበት ብለናል።
ግራ ቀኙ በዚህ ሰበር ችልት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል። የዚህ ውሳኔ ትክክለኛ ቅጂ ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ይላክ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.