ፍ/ቤቶች የወራሽነት ማስረጃ ወይም የምስክር ወረቀት ብቻ አንዱሰጡ ማመልከቻ ሲቀርብላቸው ውርስ እንዱጣራ የሚሰጡት ትእዛዝ የማይገባና አላስፈላጊ ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሕ/ 996/1/
No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ወ/ሮ ትሻገር ምህረቴ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ አመልካች አቤቱታ ያቀረቡት የሟች እናቴ የወ/ሮ ማሚቴ ደሳለኝ ወራሽ መሆኔ ተረጋግጦ ማስረጃ ይሰጠኝ በማለት ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
ጥያቄው የቀረበለት አምቦ ወረዲ ፍርድ ቤት የአመልካችን ጥያቄ በትዕዛዝ ውድቅ ያደረገው የሚወረስ ንብረት ስለመኖሩ ተጣርቶ የቀረበ ነገር የለም በማለት ሲሆን የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልትም እንደቅደም ተከተላቸው በፍርድ እና በትዕዛዝ ያጸኑት ይህንኑ ትዕዛዝ ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካች ቀድሞ የወሰድኩት የወራሽነት ማስረጃ ስለጠፊብኝ በድጋሚ ወራሽነቴን ላረጋግጥ በማለት ያቀረቡት ጥያቄ በስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ የመደረጉን አግባብነት አጣርቶ ለመወሰን ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የአመልካች ጥያቄ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰጣቸው አመልካች ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
በዚህ መሰረት አመልካች ለወረዲው ፍርድ ቤት ጥያቄ ያቀረቡት የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰጣቸው በመጠየቅ ሲሆን ጥያቄውን ሉያቀርቡ የቻለት ደግሞ የወሰደት የወራሽነት ማስረጃ እንደማይነበብ ተደርጏ ስለተበላሸ መሆኑን በመግለፅ ያቀረቡት ክርክር የተመዘገበው በከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የቀድሞ የወራሽነት ማስረጃ የተሰጠበት መዝገብ ቁጥር 76/83 መጥፊቱ በመረጋገጡ ምክንያት ለአመልካቿ የቀድሞው የወራሽነት ማስረጃ ቅጂ እንዱሰጥ ማድረግ ያልተቻለ ስለመሆኑም ይግባኝ ሰሚው የምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በውሣኔው ላይ አመልክቷል። በመሰረቱ ወራሽ የሆነው ሰው ለሟቹ ወራሽ መሆኑ እና ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ የሚያመለክቱ የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰጡት ዳኞችን ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 996(1) ይደነግጋል ። በተያዘው ጉዲይ አመልካች እንዱሰጣቸው ጥያቄው ያቀረቡት የወራሽነት ማስረጃ ብቻ ነው። ከውርሱ ላይ የሚያገኙት ድርሻ የሚያመለክት የምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ የለም። አንድ ሰው ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ የሚያመለክት የምስክር ወረቀት ጥያቄ መስጠት የሚቻለው ውርሱ እንዱጣራ ከተደረገ በኋላ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን የወራሽነት ማስረጃ ወይም የምስክር ወረቀት ለመስጠት ግን የውርስ ማጣራት ሂደት በቅድሚያ መከናወን የሚገባው ስለመሆኑ ሕጉ የሚጥለው ግዳታ የለም። ወራሽ የሆነው ሰው ለሟቹ ወራሽ መሆኑ እና ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ የሚያመለክት የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዱሰጡት ዳኞችን ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 996/1/ የተመለከተው ድንጋጌም የሟች ወራሽ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ብቻ እንዱሰጠው ወይም ደግሞ ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ ጭምር የሚያመላክት የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰጠው የመጠየቅ አማራጭ ለጠያቂው ወገን የተተወ እንጂ ሕጉ ሁለቱም አይነት ማስረጃዎች ሉጠየቁ እና በፍርድ ቤት ሉሰጡ የሚችለት ሳይነጣጠለ በአንድነት ስለመሆኑ በአስገዲጅነት አልደነገገም። የወራሽነት የምስክር ወረቀት የማግኘት እና የውርስ ማጣራት ሂደት ሁለት የተለያዩ ሂደቶች ስለመሆናቸው እና የተጠቀሰው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 996/1/ ድንጋጌው ውርሱ ካልተጣራ በቀር የወራሽነት ማስረጃ ላሰጥ አይችልም በሚል አግባብ ሉተረጎም የሚገባው ስላለመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ በ06/02/2001 ዓ.ም የሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም በዚህ መዝገብ ለቀረበው ተፈፃሚነት ሉኖረው የሚገባ መሆኑን ተገንዝበናል።
ሲጠቃለል አቤቱታው የቀረበለት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ የሚከተለው ውሣኔ ተሰጥቷል።
ው ሣ ኔ
በአምቦ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ11/03/2007 ዓ.ም ተሰጥቶ በምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት እንደቅደም ተከተላቸው በመዝገብ በ08/05/2007 ዓ.ም በፍርድ እና በመዝገብ በ05/06/2007 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ትዕዛዝ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ውርሱ እንዱጣራ ሳይደረግ የወራሽነት የምስክር ወረቀት መስጠት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 996 (1) ድንጋጌ አይከለክልም በማለት ወስነናል።
የአመልካቿን ጥያቄ አስተናግድ ተገቢውን ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 341(1)መሰረት ለአምቦ ወረዲ ፍርድ ቤት እንዱመለስ ወስነናል።
የውሣኔ ግልባጭ ተገቢውን መፈፀም ያስችለው ዘንድ ለአምቦ ወረዲ ፍርድ ቤት እንዱያውቁት ደግሞ ለምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ይላክ።
ውሣኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.