የውርስ የይዞታ መሬትን እኩል መብት ካላቸው ወራሾች መካከል አንደኛው አስቀድሞ ይዞ ወደ ልጁ ስም ማዞር የወራሾችን መብት መንጠቅ ስለመሆኑ፣ የኦሮሚያ የመሬት አዋጅ ቁጥር 130/99 ደንብ ቁጥር 151/2005 XI
No summary available.
መጋቢት 28 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- አቶ አደኛ ጉደታ የቀረበ የለም ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል የሱለልታ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ተከሳሽ፤ 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ፤ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ጣልቃገብ ነበሩ። 1ኛ ተጠሪ ባቀረቡት ክስ እናቴ ወ/ሮ ኩሉ ቦኩ በ10/03/04 ዓ/ም ባደረባት ህመም ሞተዋል፤ በህይወት በነበሩበት ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች የመሬት ይዞታ የነበረ ሲሆን መሬቱ በአመልካች እጅ የሚገኝ በመሆኑ የላልች ወራሾች ድርሻ ወጥቶ ድርሻዬን ያካፍለኝ በማለት በመጠየቃቸው፤ አመልካች በሰጡት መልስ የግል እንጂ የውርስ ንብረት አይደለም። ከ1967 ጀምሮ ከእጄ ሳይወጣ ስጠቀምበት ቆይቻለሁ በማለታቸው 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች ይዞታው የቤተሰቦቻችን እንጂ የአመልካች ብቻ አይደለም በማለት ጣልቃ ገብተው ተከራክረዋል። ጉዲዩን ያየው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን በማከራከርና ምስክሮችን በመስማት ተጠቃሹ ይዞታ 6.5 ሄክታር መሆኑን እና ይዞታውም በሟቾች ስም የነበረ እና ከእናታቸው ሞት በኃላ (2004 ) መሬቱን አመልካች በልጃቸው ስም አስመዝግቦ እየተጠቀሙ እንደሚገኙ መስተዲድሩ ጭምር በመግለፁ በገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ.130/99 አንቀጽ 16 እና በደንብ ቁ.151/2005 መሰረት ከሟቾች ጋር አብረው ሲኖሩ የነበሩት አሁንም እዛው ያለት አመልካች ናቸው። ተጠሪዎች በአሁኑ ጊዜ ላላ ቦታ ወጥቶ ያለ በመሆኑ በይዞታው ላይ የቅዱሚያ መብት ያላቸው አመልካች በመሆኑ የተጠሪዎች ክስ ውድቅ ነው ሲል ወስኗል።
በቀጣይነት ጉዲዩን ያየው ፍርድ ቤትም ተጠሪዎች የቤተሰብ አባል በመሆን በይዞታው ሲጠቀሙ ያልነበሩ ሲሆን አመልካች አሁንም በይዞታው እየተጠቀሙ በመሆኑ አመልካች ተጠቃሚ ሉሆኑ ይገባል መባለ ባግባቡ ነው በማለት የስር ውሳኔን አጽንቶታል። በመጨረሻም ጉዲዩን ያየው የክልለ ሰበር ችልትም መዝገቡን በመመርመር፤ አመልካች ይዞታው የግላቸው መሆኑን እነጂ የቅድሚያ መብት እንዲላቸው አልተከራከሩም፤ ተጠቃሹም ደንብ ቢሆን ቅድሚያ የሚሰጠው አመልካች ድርሻን እንዱወስደ እንጂ ተጠሪዎችን መብት የሚከለክል አይሆንም፣በመሆኑም አመልካች ለብቻቸው 6.5 ሄክተር ተጠቃሚ መድረጉ ከአዋጁ አላማ ውጭ በመሆኑም ተጠሪዎች ወራሾች በመሆናቸው እኩል ሉካፈለ ይገባል በማለት የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ ሽሮታል።
አመልካች አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው። በመሆኑም አመልካችም ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ቅሬታቸውን ሲገልፁ፡- ይዞታው የተጠሪዎች እናት ሳይሆን በአዋጅ ቁ.31/67 መሰረት በ1967 ዓ/ም በምሪት ያገኘሁት ነው። በስሜም ተመዝግቦ በእጄ ተለክቶ የሚገኝ ነው። ይህ ሆኖ ሳለ ከተጠሪዎች ጋር ተካፈለ መባለ ባግባቡ አይደለም። በመሬቱ ብቸኛ ተጠቃሚ እና ከዚህ ገቢ የሚተዲደር መሆኔ እየታወቀ ከአዋጅ ቁ.130/99 አንቀጽ 9(2) ውጭ የተወሰነ በመሆኑ ሉታረም ይገባዋል በማለት ጠይቀዋል።
በዚህም መሰረት ችልቱ የደንብ ቁ.151/2005 አንቀፅ 10(10) መሰረት አመልካች የቅድሚያ መብት ጥያቄ በስር ፍርድ ቤት አላነሳም ተብል መታለፈን በጭብጥነት በመያዝ የግራቀኙን በጽሁፍ መልስና የመልስ መልስ በማቀባበል አከራክረዋል።
ተጠሪዎች በሰበር መልሳቸው የሚለት፡- አመልካች ያቀረቡት መልስ ይዞታው የግላቸውና በ1967 በህግ ተመርተው ሲጠቀሙበት የነበረ መሆኑን ነው። በምስክር እና በመስተዲደሩ የተረጋገጠው ግን የቤተሰባችን እና ሟች እስከ 2004 ዓ/ም ድረስ የሚጠቀሙ መሆኑን ነው አመልካች ቤት ስለቀሩ እና እኛ ባል በማግባታችን የቤተሰባችን ንብረት ልናጣ አይገባም የደንብ ቁ151/2005 አንቀፅ 10(10) ትክክለኛ ፍቺ ያለማወቅ የቀረበ ነው። በመሆኑም የክልለ ሰበር ችልት ውሳኔ የሚነቀፍ ባለመሆኑ ሉፀና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። አመልካችም የስር ክርክራቸውን በማጠናከር በደንብ ቁ.151/2005 አንቀጽ 10(10) መሰረት ብቸኛ ተጠቃሚ መሆን ሲገባኝ ከተጠሪዎች ጋር ተካፈል መባለ ሉታረም ይገባል ሲል ተከራክረዋል።
ባጠቃላይ የክርክሩ አመጣጥ ባጭሩ ይህን ይመስላል። እኛም የግራ ቀኙን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ አንፃር መዝገቡን መርምረናል።
ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ያከራከረውን የይዞታ ጉዲይ እንዲየነው የአመልካች አብይ ክርክር የነበረው ይዞታውን በ1967 በአዋጅ በእጄ አስገብቼ ስጠቀምበት የነበረና የውርስ ንብረት ሳይሆን የግላ ይዞታ ነው በሚል ምክንያት መሆኑን ከክርክር ይዘት የምንገነዘበው ነው። ይሁን እንጂ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠው ፍሬ ነገር ይዞታው የግራቀኙ ወላጅ እናታቸው እስከ እለተሞታቸው 2004 ዓ/ም ድረስ ስጠቀሙበት የነበረና አመልካች በልጁ ስም (በአስናቀ) ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑን በመስተዲደሩ የተገለጸ ነው። እንግዱህ ከጅምሩም በአመልካች የውርስ መሆኑ ባልታመነበትና በክርክር ሂደት የተጣራ መሆኑ እየታወቀ በስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ይዞት ቆይቷል ቤተሰብ ሆኖ ሲጠቀምበት ነበር በማለት የክልለን ደንብ ቁ.151/አንቀጽ 10(10) በመጥቀስ የቅድሚያ መብት ያለው አመልካች ነው በማለት ይዞታውን ጠቅልል እንዱወስድ በመወሰናቸው ምክንያት የክልለ የሰበር ችልት ጉዲዩን በማጣራት አመልካች ባላነሳው ክርክር የቅድሚያ መብት አለው ተብል 6.5 ሄክታር ለብቻው እንዱወስድ መወሰን የለበትም አከራካሪው ይዞታ የግራ ቀኙ ወላጆች መሆኑ እስከ ተረጋገጠ ድረስ ድርሻቸውን ሉነፈጉ አይገባም። ተጠቃሹ ደንብ ቁ. 151/ 10(10) ለአመልካች መብት ይሰጠዋል ቢባልም እንኳ እንዱቀር የመውሰድን እንጂ ተጠሪዎችን በማሳጣት ባጠቃላይ ይዞታውን ለአመልካች እንዱቀር የሚያደርግ ላሆን ተደርጎ ሉቶረጎም የሚገባው አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማረም ተከራካሪዎች ከአመልካች ጋር እኩል ድርሻ አላቸው ተብል መወሰኑ ይህ ችልትም የሚቀበለው ነው በአጠቃላይ አመልካች ከሟች ጋር እስከ 2004 ዓ/ም በመኖሩ ብቻ አመልካችም ሆነ ተጠሪዎች ላላ ገቢ ይኑራቸው አይኑራቸው ባልተረጋገጠበት አመልካች ቀድሞ ይዞ ወደ ልጁ ስም ማዞሩ ብቸኛ ተጠቃሚ ሉያደርገው አይገባም የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ 130/99ም ሆነ ተጠቃሹ ደንብ ቁ. 151/2005 በዚህ መልኩ ሉተረጎሙ የሚገባቸው አይደለም።
በመጨረሻም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚው ችልት የወረዲውን እና የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሻር ተጠሪዎች በአከራካሪው የውርስ መሬት እኩል ድርሻ አላቸው ሲል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም።
በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
በኦሮሚያ ክልል የሱለልታ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 32850 በቀን 1/7/06 ዓ/ም የከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 22061 በ20/8/2006 የሰጡትን ውሳኔ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ተሸሮ የተሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር እኩል ድርሻ አላቸው ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው ብለናል።
የግራ ቀኙ የወጪ ኪሳራቸውን ይቻቻለ ብለናል።