በአንድ የጋራ የሆነ የውርስ ንብረት ላይ አንደኛው ወራሽ ብቻውን ያወጣው ወጪ ካለ ወጪውን ሁለም ወራሾች ሉጋሩት የሚገባ ስለመሆኑ፣ የጋራ የሆነ የውርስ ንብረትን በተመለከተ ወራሾች የሚስማሙ ከሆነ ክፍያው በስምምነታቸው መሰረት የሚፈጸም ስለመሆኑ፣ ወራሾች ንብረቱን ስለሚካፈለበት ሁኔታ ካልተስማሙና ንብረቱ በአይነት ለወራሾች ለማካፈል የማይቻል ከሆነ ንብረቱ በሀራጅ ተሸጦ ሉከፊፈለ የሚገባ ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ 1079/1/፣ 1086/1/፣1092፣1093
No summary available.
ሰኔ 17 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካችዎች፡-1. አቶ አፈወርቅ ደርጫ ቀረቡ 2. አቶ አበባው ደርጫ ወኪል አንደኛ አመልካች ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሰራዊት ደርጫ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካችዎች የአርባምንጭ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 29 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ፣ የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ታህሣሥ 1 ቀን 2006 ዓ.ም በመዝገብ የሰጠው ትዕዛዝና የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በመዝገብ ግንቦት 7 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት ስለጠየቁ ነው። በወረዲው ፍርድ ቤት አመልካችዎች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ ሆነው የተከራከሩ ሲሆን፣ ጉዲዩ የውርስ ሀብት ክፍያን የሚመለከት ነው።
የክርክሩ መነሻ አመልካችዎች ያቀረቡት የክስ ማመልከቻ ነው። አመልካችዎች ወላጅ እናታቸው ሟች ብዙነሽ በየነ በአርባ ምንጭ ከተማ ውሃ ምንጭ ቀበላ በካርታ ቁጥር 2689 የሚታወቅና የቤት ቁጥሩ 911 የሆነ ቤት ሰርታ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች መሆኑን ገልፀው፣ የቤቱ ግምት ብር 60,000 /ስልሣ ሺ ብር/ በመሆኑ ለተከሳሽ /ተጠሪ/ የሚደርሳትን ብር 20,000/ሃያ ሺ ብር/ ከፍለናት ቤቱን እንድታስረክበን ውሣኔ ይስጥልን በማለት ክስ አቅርበዋል። ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርባ እናቷ ቤት ስትሰራ በገንዘብ ያገዝኳትና ቤቱን በጋራ ተጋግዘን የሰራነው በመሆኑ የከሳሾች ክስ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት መልስ ሰጥታለች። የወረዲው ፍርድ ቤት ሟች ቤት ስትሰራ ተከሳሽ በግሎ አውጥቻለሁ የምትለው ገንዘብ ምን ያህል እንደሆነ በውርስ አጣሪ በኩል ተጣርቶ እንዱቅርብለት ትዕዛዝ ሰጥቷል። የውርስ አጣሪው ተጠሪ ብር 13,284.50 /አስራ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ሰማኒያ አራት ብር ከሃምሳ ሣንቲም/ ሟች ቤት ስትሰራ ከግል ገንዘቧ አውጥታ እናቷን የረዲች መሆኑን በማረጋገጥ መግለጫ አቅርቧል። የወረዲው ፍርድ ቤት ከሳሾች/አመልካችዎች/ ገምተው ካቀረቡት ብር 60,000 /ስልሣ ሺ ብር/ ውስጥ ተጠሪ ያወጣችው .50 /አስራ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ሰማኒያ አራት ብር ከሃምሳ ሣንቲም/ ተቀንሶ .50 /አርባ ስድስት ሺ ሰባት መቶ አስራ አምስት ብር ከሃምሳ ሣንቲም/ ለአመልካችዎችና ለተጠሪ/ሶስቱ ወራሾች እኩል ይካፈለ። ተከሳሽ /ተጠሪ/ የአመልካችዎችን ድርሻ .66 /ሰላሣ አንድ ሺ አንድ መቶ አርሳ ሶስት ብር ከስልሣ ስድስት ሣንቲም/ ከፍላ ቤቱን ታስቀር በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካችዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ በጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችዎችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። አመልካችዎች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርበዋል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በፍርም በሰጠው ውሣኔ አፅንቶታል። አመልካችዎች ሀምላ 10 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ፣ ተጠሪ ቤቱ ስትሰራ አውጥቻለሁ በማለት የጠየቀችው ገንዘብ የአባታችን ገንዘብ እንጂ የተጠሪ ገንዘብ አይደለም። ስለዚህ ተጠሪ ከግል ገንዘቧ አውጥታለች በማለት ከውርሱ ንብረት ዋጋ ላይ ተቀንሶ እንድከፈላት የተሰጠው ውሣኔ እውነታውን የማያንፀባርቅ ነው። በልላ በኩል አመልካችዎች ያቀረብነው የዲኝነት ጥያቄ እኛ ለተጠሪ ድርሻዋን ከፍለናት ቤቱን ትልቀቅልን የሚል ሆኖ እያለ፣ የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ድርሻችሁን ትክፈላችሁና ቤቱን ታስቀር በማለት የሰጡት ውሣኔ፣ እኛ ያቀረብነውን የዲኝነት ጥያቄ ያላገናዘበና የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ እንዱሻርልን በማለት አመልክተዋል ።
ተጠሪ ህዲር 5 ቀን 2007 ዓ.ም በሰጠችው መልስ ቤቱ እድሳት የተደረገበት በእኔ ገንዘብ እንደሆነ በማስረጃ ተረጋግጧል። ቤቱን እኔ ይዤ ስኖርበት ቆይቻለሁ። ተጠሪ አዱስ ቤት በገንዘቤ ሰርቻለሁ። ቤቱን በአመልካችዎች ፈቃድና ስምምነት የሰራሁ በመሆኑ ቤቱን መያዝ የሚገባኝ እኔ ነኝ። ቤቱን ብር 60,000/ስልሣ ሺ ብር/ ገምተው ያቀረቡት አመልካችዎች ናቸው። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስሀተት የላለበት በመሆኑ እንዱፀናልኝ በማለት መልስ ሰጥታለች። አመልካችዎች ታህሣሥ 4 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ እናታችን ቤቴ ውስጥ ልጆቼ ይኑሩ የሚል ኑዛዜ ትታለች። ተጠሪ አወጣሁ ያለችው ወጭ አመልካችዎች በላለንበት የወጣ ዕውነትነት የላለው ነው በማለት ተከራክረዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራቀኙ ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ተጠሪ የአመልካችዎችን ድርሻ ከፍላ የውርስ ቤቱን እንድታስቀር የተሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ በሟች ስም ያለውን የውርስ ቤት ለማደስ ጠቅላላ ዋጋው .50 /አስራ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ሰማኒያ አራት ብር ከሃምሳ ሣንቲም/ ያወጣች መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት በውርስ አጣሪ በኩል ተጣርቶ እንዱቀርብ በማድረግ አረጋግጧል። የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ የውርስ ንብረቱን ለማደስ ብር 13,284.50 /አስራ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ሰማኒያ አራት ብር ከሃምሳ ሣንቲም/ ከግል ገንዘቧ አውጥታለች በማለት የደረሰበትን መደምደሚያ፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ተስማምቶበት በትዕዛዝ አፅንቶታል። ይህም ተጠሪ የውርስ ቤቱን ለማደስ ብር 13,284.50 ከግል ገንዘቧ ማውጣቷ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ መሆኑን ያሳያል። አመልካችዎች የወረዲው ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍሬ ጉዲይ በማጣራትና ማስረጃ በመመዘን የደረሱበት መደምደሚያ ስህተት መሆኑንና ቤቱ አባታቸው በላከው ገንዘብ የታደሰ መሆኑን በመግለፅ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። ሆኖም አመልካችዎች ያቀረቡት ይህ የፍሬ ነገርና የማስረጃ ምዘና ክርክር ለዚህ ሰበር ችልት በህገ መንግስቱ አንቀፅ 80 ንዐስ አንቀፅ3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 10 የተሰጠውን መሰረታዊ የሕግ ስህተት በሰበር አይቶ የማረም ሥልጣን ያላገናዘበና የሕግ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የውርሱን ንብረት ለማደስ ከግል ገንዘቧ ያወጣችው ብር 13,284.50 የውርስ ንብረት ክፍፍል ሲደረግ ሉተካለት ይገባል በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረተዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አላገኘነውም።
በዚህ መዝገብ መታየት ያለበት አከራካሪ የሰበር ጭብጥ፣ የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የአመልካችዎችን ድርሻ ከፍላ ቤቱን እንድታስቀር የተሰጡት ውሣኔ የውርስ ሃብት ክፍያ ደንቦችን የተከተለ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው። በወረዲው ፍርድ ቤት ከሳሽ የሆኑት አመልካችዎች ለወረዲው ፍርድ ቤት ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ፣ ከእናታቸው በውርስ ያገኙት ቤት ግምቱ ብር 60,000 መሆኑን ገልፀው ለተጠሪ ድርሻዋን ብር 20,000 /ሃያ ሺ ብር/ ከፍለናት ቤቱን እንድታስረክበን ይወሰንልን የሚል ይዘት ያለው መሆኑን ከወረዲው ፍርድ ቤት ውሣኔ ተረድተናል። ይህም አመልካችዎች የውርሱን ንብረት ተጠሪ የእነርሡን ድርሻ ከፍላ እንድታስቀር የዲኝነት ጥያቄ ያላቀረቡ መሆኑንና ተጠሪ በበኩሎ ቤቱን ማስቀረት ያለብኝ እኔ ነኝ በማለት የተከራከረች መሆኑን የሚያሳይ ነው። ይህም አከራካሪውን የውርስ ንብረት አመልካችዎችና ተጠሪ ለማስቀረት ፍላጎት ያላቸው በሆነበት ሁኔታ የውርሱ ንብረት /ቤቱ/ የሟች ወራሾች እንዳትና በምን ሁኔታ ሉካፈለ ይገባል የሚለውን ነጥብ መመርመር ይጠይቃል።
የውርስ ንብረት የሚከፈለው በወራሾቹ መካከል በሚደረግ ስምምነት እንደሆነ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1089 ንዐስ አንቀፅ 1 የሚደነግግ ሲሆን ውርሱ በአይነት መከፊፈል ከሆነ ወራሾቹ የውርሱን ንብረት በአይነት የሚካፈለ መሆኑ የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1086 ንዐስ አንቀፅ 1 ይደነግጋል። የውርሱ ሀብት በአይነት ለመከፊፈል የማይችል በሆነ ጊዜና ከወራሾቹ መካከል ይህንን ሉካፈል የማይችለውን ንብረት ሉወስድ የሚገባው የትኛው እንደሆነ በስምምነት ለመወሰን ያልቻለ እንደሆነ ንብረቱ ተሽጦ ገንዘቡ ለወራሾቹ የሚከፊፈል መሆኑን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1092 በግልፅ ይደነግጋል። ከዚህ አንፃር ሲታይ የበታች ፍርድ ቤቶች ከላይ በገለፅናቸው የውርስ ንብረት ክፍያ ደንቦች ሣይከተለ፣ አመልካችዎች ተጠሪ የውርሱን ቤት እንድታስቀር ባልተስማሙበት ሁኔታ፣ ተጠሪ የአመልካችዎችን ድርሻ ከፍላ ቤቱን እንድታስቀር የሰጡት ውሣኔ ከላይ የገለፅናቸውን የሕግ ድንጋጌዎች የሚቃረንና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው፣ በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአርባ ምንጭ ወረዲ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ፣ የጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሎል።
የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የውርሱን ንብረት ለማደስ ከግል ገንዘቧ ያወጣችው ብር 13,284.50 /አስራ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ሰማኒያ አራት ብር ከሃምሳ ሣንቲም/ ከውርስ ንብረት ዋጋ ተቀንሶ ለተጠሪ እንዱተካለት የሰጡት የውሣኔ ክፍል ፀንቷል።
የውርስ ንብረት የሆነውን ቤት ክፍያ በተመለከተ፡ ተጠሪ የአመልካችዎችን ድርሻ ከፍላ ቤቱን እንድታስቀር በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የውሣኔ ክፍል ተሽሯል።
3/ሀ/ የውርስ ንብረት የሆነው ቤት የሶስቱም ወራሾች ስለሚካፈልበት ሁኔታ አመልካችዎች እና ተጠሪ የሚስማሙ ከሆነ ክፍያው በስምምነታቸው መሰረት እንድፈጽም በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1079 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት ወስነናል።
/ለ/ አመልካችዎችና ተጠሪ ቤቱ ስለሚከፈልበት ሁኔታ ካልተስማሙና ቤቱ በአይነት ለአመልካችዎችና ለተጠሪ ለመካፈል የሚችል ከሆነ፣ አመልካችዎች ተጠሪ ቤቱን የጠገነችበትን ገንዘብ ሁለት ሶስተኛውን ለተጠሪ ከፍለው ቤቱን በአይነት እንዱካፈለ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1086 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት ወስነናል።
/ሐ/ አመልካችዎና ተጠሪ ቤቱን ስለሚከፈልበት ሁኔታ ካልተስማሙና ቤቱ በአይነት ለወራሾቹ ለማካፈል የማይቻል ከሆነ ቤቱ በሀራጅ ከተሸጠ በኋላ፣ ተጠሪ የውርስ ቤቱን ለማደስ ያወጣችው ገንዘብ በመጀመሪያ ተከፍል፣ ቀሪውን የቤቱን ዋጋ አመልካችዎችና ተጠሪ ለሶስት እኩል ሉካፈለ ይገባል በማለት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1092 እና በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1093 መሰረት ወስነናል።
No topics extracted.