አንድ ጋብቻ በተጋቢዎቹ ስምምነት ፈርሶአል ልባል የሚችለው የፍቺ ስምምነቱ ተደርጎአል በተባለበት ቀን ሳይሆን የፍቺ ስምምነቱ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ባገኘበት እና በጸደቀበት ጊዜ ስለመሆኑ፡የተሸሻለው የፋድራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀፅ 76(1)
No summary available.
ሐምል 1 ቀን 2007ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ ሃና አሰፊ -ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
በዚህ መዝገብ አመልካች አቤቱታ ያቀረቡት ለስረ ነገሩ ፍርድ ምክንያት የሆነው የብድር ገንዘብ ባለቤታቸው በነበሩት በአሁኑ 2ኛ ተጠሪ የተወሰደው ጋብቻቸው ከፈረሰ በኃላ በመሆኑ የአመልካቿ የግል ንብረት የሆነው የሰላዲ ቁጥር 2-38341 ተሽከርካሪ ለአፈጻጸሙ የተያዘው አላግባብ መሆኑን ገልጸው ተሽከርካሪው እንዱለቀቅላቸው በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 418 መሰረት ያቀረቡትን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ የጸናው የአፈጻጸም ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
የጉዲዩን አመጣጥ በተመለከተ፡- 2ኛ ተጠሪ በ05/13/2000 ዓ.ም. ከ1ኛ ተጠሪ የወሰደትን የብድር ገንዘብ መመለስ በነበረባቸው ጊዜ ሳይመልሱ በመቅረታቸው 1ኛ ተጠሪ በመዝገብ ክስ መስርተው 2ኛ ተጠሪ ብር 41,000 (አርባ አንድ ሺህ) ለ1ኛ ተጠሪ እንዱከፍለ በ30/05/2005 ዓ.ም ውሳኔ ማሰጠታቸውን፣ይህንን ፍርድ ለማስፈጸም 1ኛ ተጠሪ ባስከፈቱት የአፈጻጸም መዝገብ ላይ የ2ኛ ተጠሪ ባለቤት ናቸው በተባለት የአሁኗ አመልካች ስም ተመዝግቦ የሚታወቀው የሰላዲ ቁጥር 2-38341 ተሽከርካሪ ለአፈጻጸሙ እንዱውል ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ተቀብል ተሽከርካሪው በሐራጅ ተሽጦ ለዕዲው መክፈያ እንዱውል በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ተሽከርካሪ ለአፈጻጸሙ የተያዘ መሆኑን፣አመልካቿ የአፈጻጸም ትዕዛዙን ለሰጠው ፍርድ ቤት መቃወሚያ ያቀረቡትም ይህንን ትዕዛዝ በመቃወም መሆኑን፣በ24/11/2006 ዓ.ም. አዘጋጅተው ያቀረቡት መቃወሚያ ይዘትም የአመልካች እና የ2ኛ ተጠሪ ጋብቻ በመዝገብ በ08/03/2002 ዓ.ም. በተሰጠ ውሳኔ የፈረሰ በመሆኑ በማይመለከታቸው ዕዲ የተያዘው የአመልካቿ የግል ንብረት የሆነው ተሽከርካሪ እንዱለቀቅ የተጠየቀበት መሆኑን፣በመቃወሚያው ላይ 1ኛ ተጠሪ በ16/03/2007 ዓ.ም. በሰጡት መልስ የብድር ዕዲው የተገባው አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ በጋብቻ ተሳስረው በነበረበት ጊዜ መሆኑን እና የንብረት ክፍፍልም ያላደረጉ መሆኑን በመግለጽ መቃወሚያው ውድቅ ተደርጎ አፈጻጸሙ እንዱቀጥል መጠየቃቸውን፣2ኛ ተጠሪ በሞት ተለይተዋል በመባለ በእርሳቸው በኩል የቀረበ አስተያየት አለመኖሩን፣ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኃላ የብድር ዕዲው በ2ኛ ተጠሪ የተገባው በ05/13/2000 ዓ.ም. ሆኖ ጋብቻው የፈረሰው ደግሞ በመዝገብ በ08/03/2002 ዓ.ም. በተሰጠ የፍርድ ቤት ውሳኔ መሆኑን፣አመልካቿ በፍርድ የተወሰነው ገንዘብ የተጋቢዎቹ የጋራ ዕዲ አይደለም የሚል እና የፍርድ ባለዕዲው ዕዲውን ለመክፈል የሚያስችል አቅም አላቸው የሚል ዝርዝር ክርክር ያላቀረቡ መሆኑን፣ባልና ሚስት በጋብቻ ውስጥ እያለ ለጋራ ጥቅም የተበደሩት ገንዘብ ከጋራ ሀብታቸው ሉከፈል እንደሚችል፣ ከጋራ ሀብታቸው ሉከፍለ ካልቻለ ዕዲው ከአንደኛው ተጋቢ የግል ንብረት ሉከፈል እንደሚችል እንዱሁም አንደኛው ተጋቢ በግለ የተበደረውን ገንዘብ በግል መክፈል ካልቻለ ከተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት ላይ እንደሚከፈል በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 70 የተደነገገ መሆኑን እና በአጠቃላይ ተሽከርካሪው ለዕዲው መክፈያ ሉውል የማይችልበትን ሕጋዊ ምክንያት አመልካች ያላስረደ መሆኑን ገልጾ የቀረበለትን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ አፈጻጸሙ እንዱቀጥል ትዕዛዝ ሰጥቶአል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካች ከቀድሞ ባለቤታቸው 2ኛ ተጠሪ ጋር የፍቺ ስምምነት ያደረጉት በ15/08/2000 ዓ.ም. መሆኑን እና ፍርድ ቤቱም በ08/03/2002 ዓ.ም. ያጸደቀው ይህንኑ ስምምነት ከመሆኑ አንጻር እና ብድሩ በ2ኛ ተጠሪ ተወስዶል የተባለው ደግሞ የፍቺ ስምምነቱ ከተደረገ በኃላ በ05/13/2000 ዓ.ም ከመሆኑ አንጻር የብድር ውለ አመልካችንም የሚመለከት ነው ተብል አፈጻጸሙ በግል ንብረታቸው ላይ እንዱቀጥል የተሰጠውን ትዕዛዝ አግባብነት ተጠሪዎቹ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ የ2ኛ ተጠሪ መልስ የመስጠት መብት የታለፈ ሲሆን አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ ግን የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ፍርድ ቤቱ በ08/03/2002 ዓ.ም. በዋለው ችልት ያጸደቀው በ15/08/2000 ዓ.ም. የተደረገውን የፍቺ ስምምነት በመሆኑ ጋብቻው በስምምነት ፈርሷል ልባል የሚችለው ስምምነቱ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እንጂ ስምምነቱ በፍርድ ቤት ከጸቀበት ቀን ጀምሮ አይደለም፣2ኛ ተጠሪ የብድር ውለን አድርገዋል የተባለውም ጋብቻው በስምምነት ከፈረሰ በኋላ በመሆኑ ብድሩ አመልካችን የሚመለከት ላሆን አይችልም በማለት መሆኑን የክርክራቸው ይዘት ያመለክታል።አመልካች እና 2ኛ ተጠሪ ጋብቻችንን በስምምነት አፍርሰናል በሚለበት ቀን እና ስምምነታቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበው ባጸደቁበት ቀን መካከል ያለው ጊዜ አንድ ዓመት ከሰባት ወር መሆኑን ከላይ ከተመለከተው የጊዜ ቅደም ተከተል መገንዘብ ይቻላል።በመሰረቱ ጋብቻ በፍቺ እንዱፈርስ ሉወሰን ከሚችልባቸው መንገድች አንደ ባልና ሚስት በስምምነት ለመፊታት ሲወስኑ እና ለፍርድ ቤት አቅርበው ውሳኔያቸው ተቀባይነት ሲያገኝ ስለመሆኑ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 76 (1) ስር ተመልክቷል። ከዚህ ድንጋጌ አነጋገር በግልጽ መገንዘብ የሚቻለው አንድ ጋብቻ በተጋቢዎቹ ስምምነት ፈርሷል ልባል የሚችለው የፍቺ ስምምነቱ ተደርጓል በተባለበት ቀን ሳይሆን የፍቺ ስምምነቱ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ባገኘበት እና በጸደቀበት ቀን መሆኑን ነው።ብድሩ በ2ኛ ተጠሪ ተወስዶል የተባለው ደግሞ የፍቺ ስምምነቱ በፍርድ ቤት ቀርቦ ከጸደቀበት ቀን ከአንድ ዓመት ከሶስት ወራት በፉት መሆኑ አላከራከረም።በመሆኑም ጋብቻው በስምምነት ፈርሷል ልባል የሚችለው ስምምነቱ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ እንጂ ስምምነቱ ለፍርድ ቤት ቀርቦ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ አይደለም በማለት አመልካች የሚያቀርቡት ክርክር ሕጋዊ መሰረት ያለው ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩል ፍርድ ቤቱ የፍቺ ስምምነትን ሲያጸድቅ ተጋቢዎቹ ስለፍቺው ውጤት ያደረጉትንም ስምምነት አብሮ የሚያጸድቅ ስለመሆኑ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 80 (2) ስር ተመልክቷል።
አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ጋብቻ የመሰረቱት በ1994 ዓ.ም. እንደሆነ አመልካች ለስር ፍርድ ቤት በማስረጃነት ያቀረቡት የፍቺ ስምምነት የሚያመለክት ሲሆን በፍቺ ስምምነቱ ላይ ተጋቢዎቹ ልጅ እንዲላፈሩ ከመገለጹ በቀር የጋራ ንብረት ያፈሩ ወይም ያላፈሩ ስለመሆኑ የተገለጸ ነገር የለም።ይህም በፍርድ ቤት ቀርቦ ጸድቋል የተባለው የፍቺ ስምምነት የተሟላ አለመሆኑን መገንዘብ የሚያስችል ነው።አመልካች የጋራ ንብረት ያላፈራን ስለመሆኑ በፍቺ ስምምነቱ ላይ ተገልጿል በማለት በሰበር አቤቱታቸው ላይ ያቀረቡት ክርክርም የስምምነቱን ይዘት መሰረት ያደረገ አይደለም።አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ጋር የነበራቸው ጋብቻ የፈረሰበት ስምምነት በፍርድ ቤት ጸድቋል ከተባለበት ቀን ከአንድ ዓመት በኃላ 2ኛ ተጠሪ እና አመልካች ባልና ሚስት መሆናቸውን በመግለጽ ከሶስተኛ ወገን ጋር የንግድ ድርጅት ሽያጭ ውል የፈጸሙ ስለመሆኑ 1ኛ ተጠሪ በሰበር መልሳቸው ያቀረቡትን የክርክር ነጥብ በተመለከተ ባልና ሚስት ከተፊቱ በኃላ እንደገና ከመጋባትም ሆነ የጋራ ንብረት ከማፍራት የሚከለክላቸው ነገር የለም ከማለት በቀር አመልካች ግልጽ የማስተባበያ ክርክር ያላቀረቡበት መሆኑን የክርክራቸው ይዘት ያመለክታል።
የስር ፍርድ ቤት በትዕዛዙ ላይ እንደገለጸው አመልካች የብድር ዕዲው የተገባው ከ2ኛ ተጠሪ ጋር የነበረን ጋብቻ በስምምነት ከፈረሰ በኃላ በመሆኑ ዕዲው አይመለከተኝም ከማለት በቀር 2ኛ ተጠሪ የወሰደት ብድር ለትዲር ጥቅም የዋለ አይደለም በማለት አልተከራከሩም።የዚህ ዓይነት ክርክር በሰበር አቤቱታቸውም አላቀረቡም።እንዱህ ከሆነ ደግሞ በቤተሰብ ሕጉ በአንቀጽ 71 በተመለከተው መሰረት ዕዲው ለትዲር ጥቅም እንደተደረገ ግምት የሚወሰድበት ይሆናል። አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ላይ እንደገለጹት ለአፈጻጸሙ የተያዘው ተሽከርካሪ አመልካች ከጋብቻው በፉት ያፈሩት የግል ሀብታቸው መሆኑ ቢረጋገጥ እንኳ ዕዲው የመጣው ለትዲራቸው ጥቅም ነው እስከተባለ እና ለፍርደ አፈጻጸም ሉውል የሚችል የ2ኛ ተጠሪ የግል ወይም የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት መኖሩ እስካልተረጋገጠ ድረስ የአንደኛው ተጋቢ የግል ሀብትም ቢሆን ለአፈጻጸሙ ሉውል የሚችል ስለመሆኑ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 70 (2) ድንጋጌ ስር በግልጽ ተመልክቷል።
ሲጠቃለል በስሜ ተመዝግቦ የሚገኘው የሰላዲ ቁጥር 2-38341 ተሽከርካሪ ለአፈጻጸሙ ሉውል አይገባም በማለት አመልካች ያቀረቡትን መቃወሚያ ውድቅ በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ሕጉን መሰረት ያደረገ ነው ከሚባል በቀር መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ15/05/2007 ዓ.ም.
በትዕዛዝ የጸናው የአፈጻጸም ትዕዛዝ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ የተያዘው አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዚህ መዝገብ በ20/06/2007 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተነስቷል።አፈጻጸሙን ለያዘው ፍርድ ቤት እና ለፋዳራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዲይሬክቶሬት ይጻፍ።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.