ባል እና ሚስቶች ሲጋቡ ለጎጆ መውጫ ተብል በቤተሰባቸው ፍቃድ የተሰጣቸው መሬት ሲገለገለበት የቆዩ በሆነ ጊዜ ንብረቱ የጋራ ሀብት ሀኖ በፍቺ ጊዜ እኩል ሉካፈለት የሚገባ ስለመሆኑ፣ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ የመሬት አዋጅ ቁጥር 110/1999 አንቀጽ 5/5/,2/7/ X
No summary available.
ቀን ሐምል 28/2007 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃ መሰለ አመልካች፡- ወ/ሮ ዘምዘም ሸረፊ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የባል እና ሚስት ንብረት ክርክር መሰረት ያደረገ ነው። የአሁኑ አመልካች በወረዲ ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ 1ኛ ተጠሪ ከሳሽ 2ኛ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል ። በ1ኛ ተጠሪ የቀረበው ክስ በቀን 03/06/2006 ዓ.ም የተፃፈ ክስ ዝርዝር ይዘቱ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር የነበራቸው ጋብቻ በፍቺ የፈረሰ መሆኑን በመግለፅ የተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የመሬት ይዞታ አንድ የቆርቆሮ ቤት አንድ የሳር ክዲን ቤት እንዱሁም በጓሮ የጫት ተክል ፣ቡና ፣ሙዝ ተክል ያለበት አንድ በሬ አንድ ጊደር አንድ ጥጃ እና የውሃ ጀኔሬተር የጋራ የባል እና ሚስት ስለሆነ 2ኛ ተጠሪ ድርሻቸውን እንዱያካፍሎቸው የሚል ክስ አቅርበዋል።
በ2ኛ ተጠሪ የተሰጠ መልስ የጋራ ንብረት የለንም በክሱ የተጠቀሱት የእናታቸውን ወይም የጣልቃ ገብ መሆኑ በመግለፅ መልስ ሰጥቷል።በአሁን አመልካች ጣልቃ ገብተው ለክርክር ምክንያት ሆኑት የመሬት ይዞታ ፣ ቀንድ ከብቶች እና የውሃ ጄኔሬተር የራሳቸው መሆናቸው የከሳሽ እና የተከሳሽ ንብረት አይደለም በማለት መቃወሚያ አቅርበው የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ተሰምቶ ክርክሩ ተጠናቋል።
ፍርድ ቤትም በመ/ቁ. 08575 በቀን 25/07/06 ዓ.ም በዋለው ችልት ሁለት ጥማድ በጣልቃ ገብ ለጎጆ መውጫ የተሰጣቸው መሆኑ በማረጋገጥ እኩል ባልና ሚስት እንዱካፈለ አንድ በሬ አንድ ጊደር አንድ ጥጃና የውሃ ጀነሬተር ተጠሪዎች በእኩል እንዱካፈለ ተወሰነ።
የወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅሬታ በአመልካች በመቅረቡ፤ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙ ክርክር እንዱካሄድ በማድረግ በመ/ቁ. 10375 በቀን 19/10/2006 ዓ.ም በዋለው ችልት የስር ፍርድ ቤት በውሳኔ አፅንቶታል።
አሁንም አመልካች ለክልለ ጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታቸውን በማቅረባቸው ችልቱ በጉዲዩ ላይ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ አፅንቷል።
አመልካች በቀን 13/04/2007 ዓ.ም የተፃፈ አቤቱታ ለዚህ ችልት አቅርበዋል። ተጠሪዎች እንዱቀርቡ በማድረግ የፅሐፍ ክርክር አድርገዋል። ከአመልካች ክርክር ይዘት ተጠሪዎች እንዱከፈለ የተወሰነው የመሬት ይዞታ፣ቀንድ ከብቶችና የውሃ ጀነሬተር የግላ ንብረቶች ናቸው።
ተጠሪዎች ምንም መብት የላቸውም ሲለ የመሬት ይዞታው በስሜ ግብር ካርኒ የሚቆረጠው በላለባቸው ንብረት የተሰጠ ውሳኔ ሉሰረዝ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
በአንደኛ ተጠሪ የተሰጠ መልስ ጎጆ ስንወጣ በአካባቢው ባህል የተለመደ 4 ጥማድ ይዞታ ሰጥተውን አንድ አነስተኛ የሳር ቤት ሰርተን ቋሚ ተክልች በመትከል ለ 11 ዓመት ባልና ሚስት በጋራ ስንጠቀምበት የነበረ ነው። ይህንን በማስረዲት ነው የተወሰነው። ቀንድ ከብቶች ጀነሬተር የባልና ሚስት የጋራ ሃብቶችን በትዲር ውስጥ ያፈራናቸው መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ የተወሰነ ስለሆነ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ስለላለው በውሳኔ እንዱፀናላቸው ጠይቀዋል። በ2ኛ ተጠሪ የተሰጠ መልስ ደግሞ የጋራ የሆነ መሬትና ንብረት የለንም። አብረን ባልና ሚስት የተጠቀምንበት ሁኔታ የለም። ለጎጆ መውጫ ተብል ከአመልካች የተሰጠ ስጦታ የለም። የምንተዲደረው የነበረው ለእኩል እርሻ እያረስኩ በማገኘው ገቢ ቤተሰቤን አስተዲድር ነበር። በአመልካች የቀረበ አቤቱታ በአግባቡ ነው በማለት መልሳቸው አቅረበዋል።አመልካችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥና ይዘት ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ተጠሪዎች ለ11 አመታት በጋብቻው ቆይታው ጋብቻው በፍቺ በመፍረሱ ምክንያት በ1ኛ ተጠሪ በጋራ ያፈሩትን ሃብት ድርሻቸው እንዱሰጣቸው ያቀረቡት ክስ በ2ኛ ተጠሪ የጋራ የሚባል ሃብት እንደላላቸው ሲከራከሩ የአሁኑ አመልካች በክርክሩ ጣልቃ በመግባት ተጠሪዎች የሚከራከሩበት ንብረት የግላቸው መሆኑን ተከራከሩ በፍሬ ነገር ደረጃ ማጣራት የሚገባው በክሱ የተጠቀሱትን ንብረቶች የባልና ሚስት ናቸው ወይስ የአመልካች ናቸው የሚለውን ጭብጥ በማስረጃ ማረጋገጥ ያለበት ሆኖ በመገኘቱ የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙ ማስረጃ ያቀረበ መሆኑን ከመዝገቡ መገንዘብ ይችላል፤ አመልካች ለተጠሪዎች ጎጆ መውጫ ከይዞታቸው የሰጡ መሆናቸው ተጠሪዎችና በዚሁ የተሰጣቸው በጋራ ይጠቀሙበት እንደነበር በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ነው።
የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ብ/ክ/መ/ የመሬት አዋጅ ቁ 110/1999 አንቀፅ 5/5/ ላይ የተደነገገው ባልና ሚስት ጋብቻው ወቅት አብረው ይጠቀሙ የነበረው ይዞታ በፍቺ ጊዜ የመጠቀም መብት አይከላከልም።
በአዋጁ አንቀፅ 2/7/ በጋራ ይጠቀሙበት የነበር ይዞታ በፍቺ ወቅት እኩል የመካፈል መብት ይሰጣል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው መሬት በአመልካች ለተጠሪዎች ለጎጆ መውጫ የተሰጣቸው መሆኑን በስር ፍርድ በማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ ከመዝገቡ መገንዘብ ይቻላል። ለዚህ አመልካች በፍቃዲቸው የሰጡት ይዞታ ተጠሪዎች በጋራ 11 አመት ይጠቀሙበት የነበር ይዞታ በእኩል እንዱካፈለ እንዱሁም የቀንድ ከብቶችና የውሃ ጀነሬተር የባልና ሚስት የጋራ ሃብት ናቸው በማለት በተሰጠው ውሳኔ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አላገኘንም በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በዚህ ጉዲይ በስር ፍርድ ቤቶች ማለትም የደ/ብ/ብ/ሕ/ብ/ክ/መንግስት ጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 62532፣ የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 08575 በቀን 19/10/06ዓ.ም እና የስልጤ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 08575 በቀን 25/07/06/ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በአመልካች የቀረበው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
በዚህ ችልት ያደረጉት ወጪና ኪሳራ የራሳቸውን ይቻለ።
በቀን 27/04/2007ዓ.ም የተሰጠው እግድ ተነስተዋል። ይጻፍ።
No topics extracted.