ጋብቻ ፀንቶ በነበረበት ጊዜ ባንደኛው ተጋቢ ተገዝቶ ነገር ግን ስመሀብቱ ከ3ኛ ወገን ሻጭ ሳይዛወር የቀረ መሆኑ ንብረቱ የተጋቢዎች የጋራ ሀብትነው ከመባል የሚያስቀረው አቶ ታረቀኝ ጥሩነህ እና ወ/ሮ ሰናይት ታደሰ
No summary available.
ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ታረቀኝ ጥሩነህ - የቀረበ የለም በአካልም በV.C ም ከሀዋሳ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሰናይት ታደሰ - የቀረበየለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዲዩ የፍቺ ውሳኔን ተከትል የቀረበ የጋራ ንብረት ክፍያ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን በዚህ መዝገብ አከራካሪ ሆኖ ከቀረበው ጉዲይ መካከል በጭብጥነት የተያዘው ተጋቢዎቹ በጋብቻ ውስጥ ያፈሩት ነው የተባለ የአንድ ባጃጅ ተሽከርካሪ ጉዲይ እና ተጠሪዋ በ02/07/2004 ዓ.ም.ከባንክ ውጪ አድርገው መውሰዲቸው የተረጋገጠው የብር 34,000 (ሰላሳ አራት ሺህ) ጉዲይነው።
ክርክሩ በተጀመረበት በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ብ/ክ/ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት ከሳሽ የነበሩት የአሁኗ ተጠሪ ተከሳሽ በነበሩት በአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ጋብቻቸው በተከሳሹ ጥፊት እና በካሳ ውሳኔ ጭምር የፈረሰ መሆኑን ገልጸው በጋብቻ ውስጥ የተፈሩ ናቸው ያሎቸው የማይንቀሳቀስ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ክፍያ እንዱፈጸምላቸው ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን የአሁኑ አመልካች ለክሱ መልስ ከመስጠታቸው በተጨማሪ በተጠሪዋ እጅ የሚገኝ ነው ያለት ጥሬ ገንዘብ በድርሻቸው ክፍያ እንዱፈጸምላቸው የበኩላቸውን የዲኝነት ጥያቄ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም ክሱን እና የግራ ቀኙን ምስክሮች ከሰማ በኃላ በመዝገብ በ05/09/2005 ዓ.ም. በዋለው ችልት በግራ ቀኙ የክፍያ ጥያቄ ለቀረበባቸው ንብረቶች ሁለት የተለያዩ ውሳኔዎችን ሰጥቷል። በአሁኗ ተጠሪ ጠያቂነት ውሳኔ ከተሰጠባቸው ንብረቶች መካከል ለሰበር ክርክሩ ለተያዘው ጭብጥ ምክንያት የሆነው ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ጊዜ የአሁኑ አመልካች ገዝተው ስመሀብቱን ሳያዛውሩ ሲሰሩበት ነበር የተባለው የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 1-1420 ደሕ የሆነን ባጃጅ ተሽከርካሪ ሲሆን በአሁኑ አመልካች ጠያቂነት ውሳኔ ከተሰጠባቸው ንብረቶች መካከል ለሰበር ክርክሩ ለተያዘው ጭብጥ ምክንያት የሆነው ደግሞ ተጠሪዋ በ02/07/2004ዓ.ም.ከአቢሲኒያ ባንክ ወጪ አድርገው መውሰዲቸው የተረጋገጠው የብር 34,000 (ሰላሳ አራት ሺህ) ጉዲይ ነው።
ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር የተለዋወጡ ሲሆን እኛም በጉዲዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው፡-
አመልካች ገዝተው ስመ ሀብቱን ሳያዛውሩ ሲሰሩበት ነበር የተባለው የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ1- 1420 ደሕ የሆነው ባጃጅ ተሽከርካሪ የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት ነው በሚል የተሰጠው የውሳኔ ክፍል የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
ተጠሪዋ በ02/07/2004 ዓ.ም. ከአቢሲኒያ ባንክ ወጪ አድርገው መውሰዲቸው የተረጋገጠው ብር 34,000 (ሰላሳ አራት ሺህ) ለትዲር ጥቅም እንደዋለ የሚቆጠር ነው በማለት የተሰጠው የውሳኔ ክፍል የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
የሚለ መሆናቸውን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዚሁ ነጥቦች አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ ጋብቻው ጸንቶ በነበረበት ጊዜ አመልካች አንድ ባጃጅ ተሽከርካሪ ገዝተው ነገር ግን ስም ሳያዛውሩ ሲሰሩበት የነበረ ስለመሆኑ ገልጸው ክፍያ እንዱፈጸምላቸው ተጠሪዋ ላቀረቡት ክስ አመልካች ስለተባለው ባጃጅ ተሽከርካሪ የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን እና ባጃጁ የተገዛበትን ውልም ሆነ በአመልካች ስም የተመዘገበበትን የባለቤትነት ማስረጃ ሳያቀርቡ ተጠሪ ያቀረቡት የድርሻ ክፍያ ጥያቄ ተቀባይነት የላለው መሆኑ ገልጸው በመሸሽ መልክ መልስ ከመስጠታቸው በቀር ባጃጅ ተሽከርካሪውን ያልገዙ እና ሲሰሩበትም ያልነበሩ ስለመሆኑ በግልጽ የሰጡት የማስተባበያ መልስ አለመኖሩን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል። ባጃጁን በተመለከተ ተጠሪዋ ስለራሳቸው 1ኛ ምስክር በመሆን በሰጡት ምስክርነት አመልካች አንድ ባጃጅ ተሸከርካሪ ገዝተው ነገር ግን ስም ሳያዛውሩ ሲሰሩበት የነበረ ስለመሆኑ ገልጸው መመስከራቸውን ፣የተጠሪዋ 2ኛ ምስክር አመልካች ባጃጁን ሲገዙ እንዲላዩ፣ነገርግን ያሽከረክሩ እንደ ነበረ እና ያሳድሩ የነበረውም በግቢአቸው ውስጥ እንደሆነ በመግለጽ መመስከራቸውን እና የተጠሪዋ 3ኛ ምስክር ደግሞ አመልካቹ ባጃጁን ያሽከረክሩ እና በቤታቸው ያሳድሩ የነበረ ከመሆኑ በተጨማሪ ባጃጁን የገዙት ስለመሆኑም ጭምር እንደነገሯቸው ገልጸው መመስከራቸውን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል። ቀደም ሲል እንደተገለጸው አመልካች ስለባጃጅ ተሸከርካሪው የማውቀው ነገር የለም፣በስሜም አልተመዘገበም፣የሽያጭ ውለም አልቀረበም በማለት በደፈናው ከመከራከር በቀር በተጠሪዋ ምስክሮች የተሰጠውን ምስክርነት ለማስተባበል ያቀረቡት ማስረጃ አለመኖሩን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት ባጃጅ ተሽከርካሪ የእኔ ነው በማለት የቀረበ ወገን ስለመኖሩም የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም።
እንዱህ ከሆነ ደግሞ በአመልካቹ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 235 መሰረት በመሸሽ መልክ የተሰጠውን የመከላከያ መልስ እና በተጠሪዋ ምስክሮች የተሰጠውን ምስክርነት መሰረት በማድረግ አመልካች ጋብቻው ጸንቶ በነበረበት ጊዜ ገዝተው ነገር ግን ስም ሳያዛውሩ ሲሰሩበት የነበረው ባጃጅ ተሽከርካሪ የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት ነው በሚል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ሕጉን እና የግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ መሰረት አድርጎ የተሰጠ ነው ከሚባል በቀር የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ አመልካች በወረዲው ፍርድ ቤት የዲኝነት ጥያቄ ያቀረቡት ተጠሪዋ ከአቢሲኒያ ባንክ ብር 34,000 በ02/07/2004 ዓ.ም.ወጪ አድርገው በዚያኑ ዕለት የተለያዩ ዕቃዎችን ይዘው ከቤት የወጡ በመሆኑ ከዚህ ገንዘብ ወስጥ ግማሹን ሉያካፍሎቸው የሚገባ መሆኑን በመጠየቅ ሲሆን ተጠሪዋ በበኩላቸው መልስ የሰጡት አመልካች የእናታቸውን ለቅሶ ጎንደር ደርሰው ከተመለሱ በኃላ የገንዘብ እጥረት እንዲጋጠማቸው በመግለጽ ለሚያካሄደት የበርበሬ ንግድ ስራ ለማዋል ያስችላቸው ዘንድ ገንዘቡን ወጪ አድርገው እንዱሰጧቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ተጠሪ ገንዘቡን በ02/07/2004 ዓ.ም. ወጪ አድርገው በዚያኑ ዕለት የሰጧቸው መሆኑን እና አመልካቹም ለበርበሬ ግዥ ያዋለት መሆኑን፣ገንዘቡ ከባንክ ወጪ ተደርጎ ከተሰጣቸው ከአምስት ቀናት በኃላ በ07/07/2004 ዓ.ም አመልካች ጠብ ፈጥረው ተጠሪዋን ከቤት ያባረሩ መሆኑን በመግለጽ እንደሆነ የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል። ይህንን የክርክር ነጥብ ለማስረዲት ግራ ቀኙ ካቀረቡት ማስረጃ መካከል በተጠሪዋ በኩል የቀረበው ማስረጃ የራሳቸው ምስክርነት ሲሆን በአመልካቹ በኩል የቀረበው ማስረጃ ደግሞ ከአመልካቹ ምስክርነት በተጨማሪ ተጠሪዋ ከቤት የወጡት በ05/07/2004 ዓ.ም ስለመሆኑ በላልች ሁለት ምስክሮች የተሰጠው ምስክርነት ነው። ተጠሪዋን ብረት ይዘው ከቤት የወጡት በ02/07/2004 ዓ.ም.ስለመሆኑ አመልካች በ03/07/2004 ዓ.ም.ለአካባቢው ፖሉስ ጽ/ቤት አመልክቻለሁ በማለት የተከራከሩ ቢሆንም ለፖሉስ ያመለከቱት በርግጥም በ03/07/2004 ዓ.ም.መሆኑን የሚያመለክት ማስረጃ የቀረበ ስለመሆኑ የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም። በመሰረቱ አንድ ግዳታ እንዱፈጸምለት የሚጠይቅ ሰው ለግዳታው መኖር ማስረጃ የማቅረብ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2001(1) እንዱሁም በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 258 እስከ 261 ድንጋጌዎች ስር የተመለከተ ሲሆን በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት አመልካች እንደ አቤቱታቸው አስረድተዋል ልባል የሚችለው ተጠሪዋ ከቤት የወጡት ለክሱ ምክንያት የሆነውን ገንዘብ ብር 34,000 ከባንኩ ባወጡበት በ02/07/2004 ዓ.ም. መሆኑን ማስረዲት ቢችለ ኖሮ ነው። ቀደም ሲል እንደተገለጸው ይህንን ነጥብ ደግሞ ማስረዲት አልቻለም። ይልቁንም አመልካች ያሰሟቸው 2ኛ እና 3ኛ ምስክሮች ያረጋገጡት ተጠሪዋ ከቤት የወጡት በ05/07/2004 ዓ.ም.መሆኑን ነው።
የስር ፍርድ ቤቶች ብር 34,000 አስመልክቶ አመልካች ያቀረቡትን ክርክር ሳይቀበለ የቀሩትም ከግራቀኙ ማስረጃ መካከል የተሻለ ክብደት ያለው ጋብቻው ጸንቶ ባለበት ጊዜ ገንዘቡን ለትዲር ጥቅም ያዋለ ስለመሆኑ በተጠሪዋ በኩል የቀረበው ማስረጃ መሆኑን መሰረት በማድረግ ነው።
በመሆኑም ተጠሪዋ በ02/07/2004 ዓ.ም. ከአቢሲኒያ ባንክ ውጪ አድርገው መውሰዲቸው የተረጋገጠው ብር 34,000(ሰላሳ አራት ሺህ) ለትዲር ጥቅም እንደዋለ የሚቆጠር ነው በማለት በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የውሳኔ ክፍል የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
ሲጠቃለል ከላይ በዝርዝር በተገለጹት ምክንያቶች አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ስላልተቻለ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት በመዝገብ በ05/09/2005 ዓ.ም. ተሰጥቶ በሀዋሳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ23/11/2005ዓ.ም. በፍርድ እና በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ በ15/02/2006 ዓ.ም. በፍርድ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓትሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ፀንቷል።
በሀዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት በመዝገብ የተያዘው አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዚህ መዝገብ በ05/03/2005 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
እንዱያውቁት የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.