አንድ ሞግዚት አካለመጠን ያልደረሰን ልጅ በማስተዲደር ስልጣኑ ክርክር የሚደረግበት ጥቅም ከ300 ብር ያነሰ ካልሆነ በቀር ያለ ቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ፈቃድ ምንም ግልግል መፈጸም የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 301
No summary available.
ሰኔ 17 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማዉ ወላ ዓሉ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካቾች፡- 1ኛ ዶ/ር ጥላሁን ኪሮስ ጠበቃ ፅጌ ሐዋስ ቀረቡ 2ኛ አቶ ሐደሽ ኪሮስ ተጠሪዎች፡- 1ኛ ህፃን ሰናይ የማነ ኪሮስ 2ኛ ህፃን ፍዩሪ የማነ ኪሮስ ሞግዚት ወ/ሮ ሄለን ያቆብ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉደዩ የውርስ ሀብት ክፍፍል ጥያቄ የተመለከተ ሲሆን የተጀመረው በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ የመንግስት የመቐለ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካቾች ተከሳሾች ተጠሪዎች ከሳሾች በመሆን ነው የተከራከሩት። አመልካቾች ባቀረቡት አቤቱታ የሥር ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን የሚለውን ክርክር አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ነው።
የአሁኑ ተጠሪዎች በሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ አጭር ይዘት ወላጅ አባታቸው አቶ የማነ ኪሮስ በ17/01/1996 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ስለተለዩ ሟች አባታቸው ከወላጅ እናታቸው ወ/ሮ ደስታ ረታን ተክተው ከእህት ወንድሞቻቸው የወረሱት ቤትና ቦታ አዋሳኙ በምስራቅ አቶ በላይ አርአያ በሰሜን ወ/ሮ ኪሮስ ታደሰና ወ/ሮ በላይነሽ ታረቀ፣ በምእራብ መንገድ፣ በደቡብ መንገድ የሚዋሰን ስፊቱ 333 ካሬ ሜትር ተከፍል እንዱሰጣቸው የማይካፈል ከሆነ በጨረታ ተሾጦ እንዱካፈለ የሚጠይቅ መሆኑን የሚያሳይ ነው።
አመልካቾች በተጠሪዎች ለቀረበው ክስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አቅርበዋል። ዋናው ፍሬ ነገሩም። የተጠሪዎች ሞግዚት በስ/ፍ/መ/ቁ. 52/97 በ30/02/97 ዓ.ም ሞግዚትነት በፍርድ ቤት አጽድቀው ቤቱና ቦታው በሽማግላ ወደ አንድ መቶ ሺህ ተገምቶ ከ1ኛ አመልካች ብር 25‚000.00 /ሃያ አምስት ሽህ ብር / ተቀብለዋል። በውልና ማስረጃ በ06/01/1997 ዓ.ም ጽድቋል። ስለዚህ ጉዲዩ በዕርቅ እልባት አግኝቶ ያደረ መሆኑን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.244/2//1/ መሰረት ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ጠይቋል። በተጠሪዎች ጠበቃ በሰጡት መልስም ዕርቁን ፈጽመዋል የተጠሪዎች ወ/ሮ ሄለን ያዕቆብ የፈፀሙት ዕርቅ በ6/01/97 ዓ.ም ነው። ሞግዚት ሆነው የተሾሙት በ30/02/97 ዓ.ም በመሆኑ ዕርቁን በፈፀመበት ወቅት ሕጋዊ ተግባር ለመፈፀም መብት አልነበራቸውም ሞግዚቱ ሳይሾም ሕጋዊ ተግባር መፈፀም ስለማይችለ እርቁ ከሕግ ውጭ ነው። ዕርቅ የመፈፀም ሥልጣን አላቸው ቢባል እንኳ አንድ ሞግዚት ከ300 ብር በላይ በሆነው የንብረት ጥቅም ላይ ስለህፃን ሆኖ መዋዋል አይችልም። የፍ/ሕ/ቁ. 301 እና 3307 ጋር የሚቃረን ነው በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኃላ አመልካቾች እና የተጠሪዎች ሞግዚት በሽማግላዎች በ6/01/97 ዓ.ም ባደረጉት ስምምነት ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት የ4 ወራሾች የነበረ በዘመድ ሽማግላ ብር 100‚000.00 ተገምቶ የከሳሾች ሞግዚት የአመልካች ድርሻ 25‚000.00 በተጠሪዎች ስም ተቀብለው ለወደፉቱ ምንም ዓይነት መብት እንደላላቸው በሽማግላዎች ፉት ተስማምተው ፉርመው በመቀላ ከተማ ውልና ማስረጃ ቀርቦ ለህግና ሞራል ሰለማይቃረን ፀድቋል የተጠሪዎች ሞግዚት ከዚህ በኃላ በ30/02/97 ዓ.ም ሞግዚትነት አረጋግጠዋል በ6/01/97 ዓ.ም የተደረገው ስምምነት ለህግና ለሞራል ይቃረናል ተብል እንዱፈርስ የቀረበ ጥያቄ የለም። የተጠሪ ልጆች እናት ባለቤታቸው እንደሞቱ በሕግ እንደ ሞግዚት ነው የምትቆጠረው በፍ/ህ/ቁ.205 በተሰጣቸው ስልጣን የአውራሻቸው የውርስ ሀብት እንደምትቀበል በፍ/ህ/ቁ.298 ተመልክቷል። በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ ጉዲይ ደግሞ ለክርክር መነሻ ላሆን ስለማይችል ክሱ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 244/2//ረ/ መሰረት በዕርቅ እልባት አግኝቶ ያደረ ነው ። በማለት ክሱ በብይን ውድቅ አድርጎታል።
የአሁኑ ተጠሪዎች የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ ወ/ሮ ሄለን ያዕቆብ ዕርቅ የፈፀሙት በ06/01/07 ዓ.ም ሲሆን ሞግዚት ሆነው የተሾሙት ደግሞ በ30/02/97 ዓ.ም ነው። ይህ የሚያሳየው ደግሞ በሞግዚትነት ስልጣን ከመውሰዲቸው በፉት እርቁን መፈፀማቸው ነው።
የተጠሪዎች እናት በፍ/ህ/ቁ.205 በህግ ሞግዚቶች እንደሆኑ ይሁን እንጂ የተጠሪዎች የውርስ ሀብቱ አስመልክተው ዕርቅ ለማድረግ የቤተዘመድ ጉባኤ የሰጣቸው ስልጣን የለም። የቤተዘመድ ጉባኤ ሥልጣን ቢሰጣቸው እንኳን ከብር 300 በላይ ከህፃናቱ ጥቅም ጋር በተያያዘ ክርክር ውስጥ ከገባ በሽምግልና መስማማት እንደማይችለ በፍ/ሕ/ቁ.301 በአስገዲጅነት መልኩ ተቀምጠዋል።
ወ/ሮ ሄለን ያዕቆብ የፈፀሙት ስምምነት መጠኑ ብር 25‚000.00 ነው ይህ የሚያሳየው ደግሞ ወ/ሮ ሄለን ያዕቆብ ከስልጣናቸው ውጭ የተጠሪዎች የውርስ ሁብት ስምምነት እንደፈጽሙ ነው።
ወ/ሮ ሄለን ያዕቆብ ፈጽሙት የተባለው የሽምግልና ስምምነት ከሥልጣናቸው ውጭ በቤተዘመድ ጉባኤ ባልተፈቀደላቸው ነው። ባልተሰጣቸው ስልጣን ለፈጸሙት ስምምነት ደግሞ ውጭ ተጠሪዎች / ህፃናት / ስምምነቱ ይፍረስልን ብለው አስቀድመው የሚጠይቁበት ምክንያት የለም።
ስምምነቱ በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠው የህፃናት መብት የሚጋፈ ፈራሽ ነው። ስምምነቱ ፈራሽ ነው። ከተባለ ደግሞ ህፃናቱ ስምምነቱ ይፍረስልን የሚለበት ምክንያት የለም። በመሆኑም የስር ፍርድ ቤት በዋናው ጉዲይ አከራክሮ ውሳኔ ይስጥበት በማለት ብይኑ ለመሻር በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.341 በነጥብ ለሥር ፍ/ቤት መልሶታል። የአሁኑ አመልካቾች ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረቡት ይግባኝ አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
ጉዲዩ ለሰበር ይቅረብ በመባለ በዚህ ችልት ግራ ቀኙ በጽሐፍ ክርክር አድርጓል። አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ያነሱዋችው ዋና ዋና ፍሬ ነገሮች የተጠሪዎች እናት ሕጋዊ ሞግዚት ናቸው ሰምምነቱም እንዱፈርስ ጥያቄ አልቀረበም ተጠሪዎች በሸማግላዎች ግምት መሰረት ድርሻቸውን ወስደዋል የሚል ይዘት አለው። ተጠሪዎች በበኩላቸው በግራ ቀኙ የዕርቅ ስምምነት ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም አለመጠናቀቁ የእርቅ ሰምምነቱም የህፃናት መብትና ጥቅም የሚጎዲ ስለመሆኑ የተጠሪዎች ሞግዚት ዕርቅ ለማድረግ የቤተሰብ ጉባኤ ፍቃድ አልሰጣቸውም ተጠሪዎች የጠየቁት ሀብት ያልተከፊፈለ የውርሰ ሀብት መሆኑ በፍ/ህ/ቁ 205 መሰረት ከወላጆቹ አንደ በማይኖርበት ወይም ችልታ ባጣበት ወቅት የማሳደግ፣ የማሰተማር፣ የመንከባከብና የማሰተዲደር ስልጣን እንጂ ንብረት የማሰተላለፍ ሀላፉነት እንደማይሰጠው በመጥቀሰ መልሰ አቅርበዋል የአመልካቾች የመልሰ መልሰም የሰበር አቤቱታው የሚያጠናከር ነው።
ከሥር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በጽሐፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ውሳኔ አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ለማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። መዝገቡን እንደመረመረውም በዚህ ችልት ዕልባት የሚያስፈለገው ጭብጥ የሥር ፍርድ ቤቶች በተጠሪዎች ሞግዚት ተደረገ የተባለው የዕርቅ ስምምነት ከመሾማቸው በፉት የተደረገ በመሆኑ ተጠሪዎችን የሚያስገድደ አይደለም በማለት መወሰናቸው በሕጉ አግባብ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
ከክርክር ሂደቱ መረዲት እንደተቻለው አመልካቾች ከተጠሪዎች ሞግዚትነት ጋር ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት መስከረም 6 ቀን 1997 ዓ.ም ዕርቅ ስምምነት አድርገው በሽማግላዎች ግምት መሰረት 25.00.00 ብር እንደወሰደ እና ላላ እንደማይጠይቁ መግለፃቸው፤ተጠሪ የሞግዚትነት ስልጣን የወሰደትም ጥቅምት 30 ቀን 1997 ዓ.ም ስለመሆኑ ነው። አመልካቾች ተጠሪዎች ሞግዚት ያደረጉ ስምምነት ለህግና ሞራል የማይቃረን መሆኑን ተረጋግጦ በሚመለከተው አካል ቀርቦ መመዝገቡን ይከራከራለ ተጠሪዎች በበኩላቸው ሞግዚቱ እንደገና ሞግዚቶቻቸው በቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ያልጸደቀ በመሆኑ አደረጉት የተባለው ዕርቅ እንደማያስገድዲቸውና የሥር ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ስለመሆኑ መከራከራቸው የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። በሥር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠው የተጠሪዎች ሞግዚት የሞግዚትነት ሥልጣን ከማግኘታቸው በፉት ከአመልካች ጋር ዕርቅ ማድረጋቸው ነው። በተጠሪዎች ሞግዚት የተደረገው ስምምነትም ለቤተዘመድ ምክር ጉባኤ አቅርቦ ስለመጽደቁም በአመልካቾቹ የቀረበ ክርክር የለም። አመልካቾች ከሥር ፍርድ ቤት ጀምሮ አጥብቀው የሚከራከሩት በተጠሪዎች ሞግዚት የተደረገው ስምምነት ለህግና ለሞራል የሚቃረን አይደለም በሚል ነው። ከዚህ በተጨማሪ የዕርቅ ስምምነቱ እንዱፈርስ ክስ እንዲልቀረበ አመልካቾች በሰበር አቤቱታቸው ያቀረቡት ቅሬታ ያመለክታል። በመሰረቱ የልጅ አስተዲደግ እና ንብረት አስተዲደር ባልና ሚስት በጋብቻ ተሳስረው በሚኖርበት ጊዜ በጋራ እንደሚያከናውኑት በማንኛውም ምክንያት ከወላጆች አንደ ተግባሩን ማከናወን ካልቻለ ላላኛው ኃላፉነቱን እንደሚሸከም ከፍ/ህ/ቁ.204 እና 205 ጭምር ጥምርንባብ የምንረዲው ነው።
ሞግዚት አካለ መጠን ያልደረሰው ልጅ ሀብት በማስተዲደር ሥልጣን እንዲለው ከፍ/ህ/ቁ. 280 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ንባብ መረዲት ይቻላል። ሞግዚቱ የልጅን ሀብት በሚያስተዲድሩበት ጊዜ እና ሁኔታ በፍ/ህ/ጉ የተመለከቱትን መሰረታዊ ድንጋጌዎች ባስከበረ መልኩ መሆን እንዲለበት ከድንጋጌዎቹ አጠቃላይ ይዘት አላማና መንፈስ የምንገነዘበው ነው። አካለመጠን ያልደረሰው ልጅ የውርስ ሀብት ያገኘ እንደሆነ ሞግዚቱ ከቤተዘመድ ምክር አባልች መካከል ምስክሮች ባለበት ንብረቱም የዋጋ ግምት መግለጫ ሉዘጋጅለት እንደሚገባ ልጅ ከውርስ ሀብት የሚደርሰው መጠን ጉድለት እንዲይኖርበት ሞግዚቱ ጥንቃቄ ማድረግ እንዲለበት ልጅን ወክል እንደሚቀበል፤
ለአውራሽ ዕዲ የማይበቃ ካልሆነ በቀር አካለመጠን ላልደረሰ ልጅ በውርስ የደረሰው ሀብቱ የቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ካልተፈቀደለት በቀር ሞግዚቱ ለመተው እንደማይችል ከፍ/ህ/ቁ. 282/1/ ፤/2/ እና 298/1/ እና /2/ ጥምር ንባብ መረዲት ይቻላል። ከላይ የተመለከተናቸው ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘትና አላማ መረዲት እንደተቻለው ሕግ አውጭው የህፃናት መብት በተመለከተ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረጉን የሚያሳይ መሆኑን ነው ከዚህ ጋር በተያያዘም ሞግዚቱ የልጅን መብትና ጥቅም በተመለከተ የሚያደርገው ሕጋዊ ግንኙነት የቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ፍቃድ የሚጠይቅ ስለመሆኑ ነው። የፍ/ህ/ቁ.301 ድንጋጌ ሙለ ይዘቱ ሞግዚቱ ክርክር የሚደረግበት ጥቅም ከሦስት መቶ የኢትዮጵያ ብር ያነሰ ካልሆነ በቀር አካለ መጠን ያልደረሰው ልጅ ጥቅሞች በሚመለከት ነገር ከቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ካልተፈቀደለት ምንም ግልግል ለመፈፀም አይችልም።
በማለት ደንግጓል። ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የተጠሪዎች ሞግዚት ለዕርቅ ስምምነት አድርጉ የተባለው በቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ከመሾማቸው በፉት ስለመሆኑ አላከራከረም። በአመልካቾች እና በተጠሪዎች ወኪል ተደረገ የተባለው የገንዘብ መጠንም ከ25‚000.000 ብር ያላነሰ ነው።
በአንጻሩ ሕግ አውጭው ሞግዚቱ ስለ ህፃኑ የሚያደርገው ግልግል ከ300.00 ብር በላይ ከሆነ የቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ይሁንታ እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን ከላይ የተመለከተው ድንጋጌ ያመለክታል። በተያያዘው ጉዲዩ የተጠሪዎችም ሞግዚት ዕርቅ ለማድረግ ቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ፊቃድ ስለማግኝታቸው አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤቱ ያቀረቡት ነገር የለም። ይህ ከሆነ ደግሞ የህፃናቱ መብትና ጥቅም በሚጎዲ መልኩ ሞግዚቱ ከ3ኛ ወገን በሕጉ ከተፈቀደው ውጭ የመስማማት ሥልጣን አልተሰጠውም የተጠሪዎች ሞግዚት በሕግ ከተሰጣቸው ሥልጣን ውጭ የተደረገ የቤተዘመደ ምክር ጉባኤ ፍቃድ ሲያገኙ ተጠሪዎች ከአውራሻቸው የሚያገኙት የውርስ ሀብት ድርሻ በተመለከተ ያደረጉት ስምምነት በሕግ ፉት ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ተጠሪዎችም በሞግዚታቸው የተደረገው ዕርቅ መጀመሪያ እንዱያፈርሱ የሚገደድበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። አመልካች ከዚህ ጉዲይ ጋር ተመሳሳይነት አለው በማለት የጠቀሱት አስገዲጅ የሰበር ውሳኔ
በክርክሩ ይዘት ባህሪ እና ለውሳኔ የተያዘው ጭብጥ ከዚህ ጉዲይ ጋር የሚዛመድ ሆኖ አልተገኘም። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥር ወረዲ እና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሻር ግራ ቀኙ በፍሬ ጉዲዩ እንዱከራከሩ የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስሕተት የተፈፀመበት አይደለም ብለናል። በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በ
በ23/03/2006 የሥር የወረዲና የዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመሻር የሰጠው ፍርድ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ. 96934 በ10/06/2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ጽንቷል።
የተጠሪዎች ሞግዚት ከአመልካች ጋር አደረጉት የተባለው ስምምነት የሞግዚትነት ሥልጣን ሳይሰጣቸው እና በቤተዘመድ ምክር ጉባኤ ፍቃድ ያላገኘ በመሆኑ በሕግ ፉት የሚጸና አይደለም ተብል በሥር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መወሰኑ በአግባቡ ነው በማለት ወስነናል።
የዚህ ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
በዚህ ፍ/ቤት 03 ሰኔ 2006 ዓ.ም የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል ይፃፍ።
መዝገቡ ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ ወደ መ/ቤት ይመለስ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.