አንድ ልጅ ሲወለድ ከልጇ እናት ጋር በጋብቻ ተሳስሮ የነበረው ሰው በህጉ ግምት መሰረት የልጁ አባት ስለመሆኑና ይህን የህጉን ግምት ማስተባበል የሚችለው እሡ ወይም በህግ የተፈቀደላቸው ሰዎች አባት አለመሆኑ እንዱወሰን የመካድ ክስ በማቅረብ ስለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 682፣741፣ የፍደራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 167
No summary available.
ሰኔ 5 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡-
ጉዲዩ የቀረበው የፍደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሐምል 27 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 23 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረበችውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።ጉዲዮ ከህጋዊ ጋብቻ የተወልድኩ የሟች ወልደሚካኤል ታረቀኝ ልጅ መሆኔ በፍርድ ተረጋግጦ ይወሰንልኝ በማለት የቀረበን ጥያቄን የሚመለከት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ /አመልካች/ተጠሪዎች ተከሳሽ /ተቃዋሚ/ ሆነው ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ግንቦት 15 ቀን 2003 ዓ.ም ፅፍ ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረበው የክስ ማመልከቻ ነው። ተጠሪ አባታቸው አቶ ወልደሚካኤል ታረቀኝና እናታቸው ወ/ሮ እቴነሽ ወ/ፃድቅ ሚያዝያ 18 ቀን 1971 ዓ.ም የጋብቻ ሥርዓታቸውን ፈፅመው በትዲር ተሣስረው አብረው እየኖሩ እያለ መጋቢት 7 ቀን 1972 ዓ.ም ተወልጃለሁ። ስለዚህ የአቶ ወልደ ሚካኤል ታረቀኝ ልጅ መሆኔ ይወሰንልኝ የሚል የዲኝነት ጥያቄ አቅርቧል።ተጠሪዎች በተከሳሽነት ቀርበው ሟችና የከሳሽ እናት ሚያዝያ 18 ቀን 1971 ዓ.ም አድርገውታል ተብል በቀረበው የጋብቻ ውል ሰነድ ላይ ያለው ፊርማ የሟች ፊርማ መሆኑን ስለምንክድ ይመርመርልን ።የአርሲ ነገላ ማዘጋጀ ቤት ከሳሽ የሟች ልጅ መሆናቸውን በመግለፅ የሰጠው የልደት ማስረጃ ተገቢነት የለውም።ከሳሽ በጋብቻ ውለ ስማቸው ያልተጠቀሱ ሰዎች በምስክርነት መቁጠሩ ተገቢ አይደለም።የኦርቶድክስ ቤቴክርስቲያን ስለከሳሽ ልደትና ጥምቀት የሰጠችው ማስረጃ ተገቢነት የለውም በማለት ከሳሽ/ተጠሪ/ የሟች ልጅ አለመሆኑንና ሟች ልጅ የላላቸው መሆኑን ገልፀው ያደረጉት ግልፅ ኑዛዜ የሚያሳይ እንደሆነ በማንሳት ተከራክረዋል።
የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ህጋዊ ጋብቻ የተወለደ የሟች ወ/ሚካኤል ታረቀኝ ልጅ መሆኑን ያስረደልኛል በማለት ወላጅ እናቱንና ወ/ሮ እቴነሽ የተባለ ሴት በምስክርነት አቅርቦ አሰምቷል ተጠሪዎች ምስክሮቻቸውን ባለማቅረባቸው ምስክር የማሰማት መብታቸውን በማለፍ፣የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረና ከመዘነ በኃላ በጋብቻ ውለ ላይ ያለው ፊርማ የሟች ወልደሚካኤል መሆኑን በፍረንሲክ ለማስመርመር በቂና አሳማኝ ምክንያት የለም። የኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ቤቴክርስቲያን ስለ ከሳሽ ልደት ፣ጥምቀት የሰጠው ማስረጃና የአርሲ ነገላ ማዘጋጃ ቤት የሰጠው የልደት ማስረጃ ተዓማኒነት ያላቸውና ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው ማስረጃዎች ናቸው።የከሳሽ እናትና አባት ከሚያዝያ 18 ቀን 1971 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 1978 በጋብቻ ተሳስረው መኖራቸውና ከሳሽ አባትና እናቱ በፀና ጋብቻ በነበሩበት ወቅት መጋቢት 2 ቀን 1972 ዓ.ም የተወለደ በመሆኑ የሟች ወልደሚካኤል ታረቀኝ ልጅ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል ።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት አመልካችዎች ይግባኝ ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ ተጠሪ /መልስ ሰጭ/ መልስ እንዱሰጡ ካደረገና የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የጋብቻ ውለ ሲፈረም ምስክር የነበሩ ሰዎች እንዱቀርቡ ትእዛዝ ሰጥቶ፣ምስክሮቹ በሞት የተለዩ በመሆኑ ስለተገለፀለት ለልች ጋብቻቸው ሥርዓት ላይ ነበሩ የተባለ ምስክሮች ቃልና የተጠሪን ወላጅ እናት የምስክርነት ቃል በድጋሚ ሰምቷል።ወ/ሮ ጥጋብነሽ ሙላቱ የተባለ ሴት ሟችና የተጠሪ ወላጅ እናት የጋብቻ ሥርዓት ሲፈፅሙ እንደነበሩና ተጠሪ ጋብቻው ከተፈፀመ በኃላ መወለደን እንደመሰከሩ ሁለተኛው ተጨማሪ ምስክር ሆነው የተሰጡት አቶ የማታው ወርቁ የሟች አክስትና የልጅ ልጅ መሆናቸውን ገልፀው ሟች የተጠሪን እናት በደብረብርሃን ከተማ እንዲገባቸውና ተጠሪን እንደወለደ የነገሯቸው መሆኑን ገልፀው መስክረዋል። የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡ ማስረጃዎችና በትዕዛዝ አስቀርቦ የሰማቸውን ተጨማሪ ማስረጃዎች ቃል ከመዘነ በኃላ የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ የሟች ወ/ሚካኤል ታረቀኝ ልጅ ነው በማለት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካቾች 12/07/2006 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ሟች ልጅ የላላቸው መሆኑን በፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 881 መሰረት ግልፅ ኑዛዜ አድርገዋል።የበታች ፍርድ ቤቶች በጋብቻ ውለ ላይ ያለው ፊርማ እንዱመረመር ያቀረብነውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግና ላልች አግባብነት የላለባቸውን ከኦርቶድክስ ቤቴክርስቲያን እና ላልች ማስረጃዎች በመቀበል የDNA /ዱኤንኤ/ ምርመራ ሳይደረግ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ እንዱሻርልን በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ ሰኔ 13 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ መልስ የሟች በጋብቻ የወለደው ልጅ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በማቅረብ ልጅነቱን ያስረዲ መሆኑን ገልፃ አመልካችዎች ያቀረቡት የፊርማና ዱኤንኤ ይመርመርልን ክርክር የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል።አመልካችዎች ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ ከዚህ በፉት ተስፊዬ ወልደሚካኤል የተባለ የሟች ልጅ መሆኑን ገልፆ የልጅነት ክስ አቅርቦ ይኽ ሰበር ችልት የሟች ልጅ ነው በማለት ወስኗል።ሟች በአንድ ከተማ ውስጥ ሁለት ሴቶችን አግብቶ በተመሣሣይ ጊዜ የሁለት ልጅ አባት የሚሆንበት አጋጣሚ የተጠሪን ጥያቄ እጅግ አጠራጣሪ የሚያደርገው በመሆኑ ዱ.ኤን.ኤ ሉመረመር ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ተጠሪ የሟች አቶ ወ/ሚካኤል ታረቀኝ ልጅ ነው ተብል የተሰጠው ውሣኔ ሕግን መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ለመያዝ ጉዲዩን ምርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ የተወለደው አባቱ አቶ ወልደሚካኤል ታረቀኝና እናቱ ወ/ሮ እቴነሽ ወ/ፃድቅ ሚያዚያ 18 ቀን 1971 ዓ.ም የጋብቻ ሥርዓታቸውን ፈፅመው በጋብቻ ተሣስረው በሚኖሩበት ወቅት መሆኑ ነው ተጠሪ ባቀረባቸው ማስረጃዎች የተረጋገጠ መሆኑ ለፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።የጋብቻ ሥርዓቱ ለሕዝብ ይፊ በሆነበት ፣የአካባቢው ነዋሪዎች በተጋበዙበትና በተሳተፊበት ሁኔታ የተከናወነ መሆኑን በተጠሪ እናትና አባት የሰርግ ሥርዓት ላይ የተገኙትና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረባቸው ምስክሮች አስረድተዋል።ከዚህ በተጨማሪ የተጠሪ ወላጅ እናት ለመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና ለፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት የምስክርነት ቃልና ላልች ደጋፉ የሰነድ ማስረጃዎች የተጠሪ ወላጅ እናትና አባት ሚያዚያ 18 ቀን 1971 ዓ.ም የጋብቻ ሥርዓታቸውን ፈፅመው እስከ 1978 ዓ.ም ድረስ በጋብቻ ተሣስረው እንደኖሩ ተጠሪ መጋቢት 12 ቀን 1972 ዓ.ም የተወለደ መሆኑና እናቱና አባቱ የሚከተለት የተዋህድ ኦርቶድክስ ክርስትና ሀይማኖት ቀኖና በሚያዘው መሰረት በአርባ ቀኑ የጥምቀት ሥርዓት የተከናወነበት መሆኑ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።የተጠሪ እናትና አባት የጋብቻ ውል ሲዋዋለ ምስክር የነበሩት ሰዎችን በሕይወት የላለ በመሆናቸው የምስክርነት ቃላቸውን ለመቀበል ያልተቻለ ቢሆንም በጋብቻ ሥርዓት ላይ የነበሩ ሰዎችም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰማ በመሆኑ አመልካችዎች በጋብቻ ውለ ላይ ያለው ፊርማ የሟች መሆኑ በፍርንሲክ አልተረጋገጠም በማለት ያቀረቡት ክርክር የሕግ ድጋፍ ያለው ሆኖ አላገኘነውም ።
ተጠሪ የተወለደው አባቱና እናቱ በጋብቻ ተሣስረው በሚኖሩበት ጊዜ ውስጥ መሆኑ ከተረጋገጠ፣የተጠሪ አባት ተጠሪ ሲወለድ ከተጠሪ እናት ጋር በጋብቻ ተሣስሮ ሲኖሩ የነበሩት አቶ ወልደሚካኤል ታረቀኝ ናቸው ብል ሕግ ግምት የሚወስድ መሆኑን ከፍትሐ ብሓር ሕጉ አንቀፅ 741 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ለመረዲት ይቻላል። ይህ ከሆነ ተጠሪ የሟች ልጅ ነው የሚለውን የህጉን ግምት ለማስተባበል የሚቻለው ሟች በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 881 መሰረት ባደረገው ግልፅ ኑዛዝ እኔ ከአብራኬ የወጣ ልጅ የለኝም በማለት ያደረገውን ግልጽ ኑዛዜ ሣይሆን፣በወቅቱ ሥራ ላይ በነበረው የፍትሐ ብሓር ሕግ 682 እና ተከታይ ድንጋጌዎች እና በተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 167 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት የመካድ ክስ በማቅረብ ተጠሪ የሟች ወ/ሚካኤል ታረቀኝ ልጅ አለመሆኑን በፍርድ በማስወሰን ነው ። ከዚህ አንፃር ሲታይ ተጠሪ የሟች ልጅ አለመሆኑ እንዱወሰንለት ሟች ወይም የመካድ ክስ እንዱያቀርቡ በሕግ የተፈቀደላቸው የሟች የቅርብ ዘመድች ለፍርድ ቤት አቅርበው የተወሰነ ውሣኔ በላለበት ሁኔታ ተጠሪ የሟች ልጅ መሆኑን በሕግ ግምት የተረጋገጠው ልጅነት ከአብራኬ የወጣ ልጅ የለኝም ብል የኑዛዜ ቃል ተናዝዞ በመሞቱ ብቻ የሚስተባበል አይደለም።
ከዚህ አንፃር ሲታይ ይኽ የአመልካችዎች መከራከሪያ የህግ ድጋፍ የላለው በመሆኑና አንድ ሰው በኑዛዜ የሚፈፅማቸው ተግባራት በፍትሐ ብሓር ሕግ ቁጥር 909 የተደነገጉ በመሆናቸው የአመልካችዎችን መከራከሪያ አልተቀበልነውም።
አመልካዎች በዚህ ሰበር ችልት ባቀረቡት የመልስ መልስ በመዝገብ አቶ ተስፊዬ ወልዳሚካኤል የተባለ ሰው የተሰጠን ውሣኔ በማንሣት ተከራክረዋል።
አመልካችዎች በሥር ፍርድ ቤትና በይግባኝ ይህንን ፍሬ ነገር መከራከሪያ አድርገው ያላቀረቡትና በማስረጃ ያላረጋገጡት አዱስ የፍሬ ነገር ክርክር በመሆኑ የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 329/1/ መሰረት አልተቀበልነውም። በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ የሟች ወልደሚካኤል ታረቀኝ በህጋዊ ጋብቻ የተወለደ ልጅ ነው በማለት አግባብነት ያለውን የቤተሰብ ሕግ ድንጋጌ የሕግ ግምት መሰረት በማድረግ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ሥህተት የለበትም በማለት ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.