በጋብቻ ፍቺ ጊዜ ለፍችው ምንክያት የሆነው በደል ተፈጽሞባታል ተብል ለአንደኛው ወገን ካሣ የሚከፈለው እንዱከፍለው ዲኝነት ወ/ሮ ትርንጎ መስፍን እና IX ካሣውም የሚወሰነው ለፍትህ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 81/2/፣84 አቶ ሙለጌታ መኳንንት
No summary available.
ሰኔ 01 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ ትርንጎ መኮንን - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሙለጌታ መኳንንት - ታልፎል።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የባልና የሚስት የጋራ ሀብት ክፍፍልን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ ክርክር ሲጀመር ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች ሲሆኑ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ። በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ጋብቻ እንዱፈርስ በፍርድ ቤቱ ከተወሰነ በኋላ አመልካች ጥር 18 ቀን 2001 ዓ/ም ጽፈው ባቀረቡት የንብረት ዝርዝር በጉለላ ክፍለ ከተማ ቀበላ ዐ8/16 ክልል ውስጥ የሚገኝ ቁጥሩ 553/ለ/ የሆነና በተጠሪ ስም የተመዘገበ ቤት፣ በተጠሪ ስም የተመዘገበና የሰላዲ ቁጥሩ 3-205229 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ፣ በተጠሪ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቀመጠ ጥሬ ገንዘብ፣ የቤት ቁሳቁሶች /ሙለ ሶፊ፣ ኮንትሮል ቡፋ፣ ፍሪጅ፣ አንድ ዘመናዊ አልጋ፣ ባለቀለም ቴላቪዥን ከእነ ዳኩ/፣ 35 ግራም የአንገት ሃብል በተጠሪ እጅ የሚገኝና ከወላጆች በውርስ ያገኙት ብር 40,000.00 /አርባ ሺህ/ በተጠሪ እጅ የሚገኘው ንብረቶችን ዘርዝረው የጋራ የሆኑትን ቤት፣ መኪና፣ባንክ ውስጥ የሚገኝ ጥሬ ገንዘብና የቤት ቁሳቁሶችን እንዱያካፍሎቸው፣ የግል የሆኑትና 35 ግራም ወርቅና 40,000.00 ጥሬ ገንዘብ ደግሞ ተጠሪ እንዱመልስላቸው እና ካሳም እንዱከፈል ይወሰን ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስም ቤቱ የጋራ መሆኑን፣ መኪናውን አሰርተው ለጋራ እዲ መክፈያነት የሸጡ መሆኑን፣ ባንክ ውስጥ ያለው ገንዘብ 320.667 መሆኑን፣ የቤት ቁሳቁሶች በአመልካች እጅ እንደሚገኙ፣ 35 ግራም ወርቅና ብር 40,000.00 በተመለከተ ግን የሚያውቁት ነገር የላለ መሆኑን ዘርዝረው ተከራክረዋል። ፍርድ ቤቱም ስለመኪናው ተገቢውን አካል ጠይቆ ማስረጃ እንዱቀርብለት ከአደረገ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ ቤቱን በተመለከተ አመልካች ሰኔ 02 ቀን 2002 ዓ/ም በተደረገ ስምምነት አመልካች ልጆችን ይዛ እንድትጠቀምበት እና በኋላ ለልጆቻችን እንዱተላለፍ ተስማምተናል ቢለም ስምምነቱ የቴምበር ቀረጥ ያልተከፈለበትና ፈቃደኝነታቸውን የገለፁበት ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ግራቀኙ እኩል እንዱካፈለ፣ የቤት ቁሳቁሶችንም ግራ ቀኙ እኩል እንዱካፈለ በማለት የወሰነ ሲሆን መኪናው የግራ ቀኙ ጋብቻ ጸንቶ ባለበት ጊዜ የተሸጠና በልላ ሰው ስም የሚገኝ መሆኑ መረጋገጡን፣ የካሳ ጥያቄ ፍቺ ሲወሰን ያልቀረበ የዲኝነት ጥያቄ መሆኑን፣ ወርቅና የውርስ የተባለውን ጥሬ ገንዘብ በተመለከተ አመልካች ያቀረቡት ማስረጃ ያለመኖሩን ጠቅሶ በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል። የልጅ ቀለብን በተመለከተም ተጠሪ ሉቆርጡ የሚገባውን ቀድሞ ወስኖና ተጠሪ ስራ በማቋረጣቸው ምክንያት ቀለብ የመቁረጥ ግዳታ ቀሪ እንዱሆንላቸው ቢያመልክቱም ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም። አመልካች ቤቱ ግራ ቀኙ እኩል እንዱካፈለ በተወሰነውና መኪናውን፣ ወርቁንና የውርስ የተባለውን ጥሬ ገንዘብ በተመለከተ በተሰጠው የውሳኔ ክፍል ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ መኪናው ላይ ብቻ የቀረበውን ቅሬታ በመቀበል መኪናው በብር 70,000.00 /ሰባ ሺህ/ የተሸጠ መሆኑ ቢረጋገጥም ገንዘቡ ለትዲር ጥቅም እንዲልዋለ ተረጋግጧል። በሚል ምክንያት ተጠሪ ለአመልካች ብር 35,000.00 /ሰላሳ አምስት ሺህ/ እንዱተኩላቸው ሲል ወስኗል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- ቤቱ የጋራ ቢሆንም ሰኔ 02 ቀን 2002 ዓ/ም በተደረገ ስምምነት አመልካች እስከ ህይወታቸው ፍፃሜ ድረስ ተጠቅመው ከዚያ በኋላ ለጋራ ልጆቻችን እንዱተላለፍ ስምምነት ተደርጎ እያለ መታለፈ ያላግባብ ነው፣ ካሳውን በተመለከተም ተጠሪ በሴሰኝነት በወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ መባላቸው ተረጋግጦ እያለ በተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 84 መሰረት ካሳ እንዱከፈል የቀረበው ጥያቄ ውድቅ መደረጉ ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም በሁለቱም ነጥቦች ላይ በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ይዘት ተገቢነት በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ በሕግ አግባብ ተጠርተው ባለመቅረባቸው ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በመኖሪያ ቤቱና ካሳን አስመልክቶ በበታች ፍርድ ቤቶች በተሰጠው የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መኖር ያለመኖሩን በጭብጥነት ይዞ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካችና ተጠሪ በሕጋዊ ጋብቻ ተሳስረው ቆይተው ጋብቻው በፍቺው ውሳኔ ታህሳስ 24 ቀን 2001 ዓ/ም መፍረሱን፣ በጉለላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 08/16 ክልል ውስጥ የሚገኘውና ቁጥሩ 553/ለ የሆነና በተጠሪ ስም የተመዘገበ ቤት የጋብቻ ውጤት መሆኑ ተረጋግጦ የግራ ቀኙ ነው ተብል የተወሰነ ሲሆን አሁን አመልካች ቅሬታ የሚያቀርቡት ቤቱ የጋራ ቢሆንም ሰኔ 02 ቀን 2002 ዓ/ም በተደረገ ስምምነት አመልካች ቤቱን ልጆችን ይዘው እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ እንዱጠቀሙበትና በኋላም ለልጆች እንዱተላለፍ የተደረገ ሁኖ እያለና ተጠሪም በዚህ ረገድ ሰነደን በመካድ ያቀረበው ክርክር ሳይኖር በአመልካች በተጠሪ መካከል ክፍፍል እንዱደረግ ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው በማለት የሚከራከሩ መሆኑን፣ የበታች ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን ክርክር ያለፈት ስምምነቱ የቀረጥ ቴምብር ያልተከፈለበትና በነጻ ፈቃዲቸው የተደረገ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም በሚል ምክንያት መሆኑን ነው።
በመሰረቱ የተጋቢዎች የፍቺ ውጤቶች በስምምነት፣ በሽማግላዎች ወይም ባለሙያዎች ሉወሰን እንደሚችልና በዚህ አግባብ የተወሰነ የፍቺ ውጤት ተፈጻሚነት የሚኖረው ለፍርድ ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ሲያገኝ ስለመሆኑ የተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 ከአንቀጽ 77 እስከ 80 ድረስ ያለት ድንጋጌዎች ከአንቀጽ 83/3/ ድንጋጌ በጣምራነት ሲነበቡ የሚያስገነዝቡን ጉዲይ ነው። በተያዘው ጉዲይ ተጋቢዎቹ የክርክሩ ምክንያት የሆነውን መኖሪያ ቤት በተመለከተ ሰኔ 02 ቀን 2002 ዓ.ም ስምምነት ያደረጉ መሆኑን አመልካች ቢከራከሩም የፍቺ ውሳኔ በ24/04/2001 ዓ/ም ከተሰጠ በኋላ የተደረገና ስምምነቱ ፍርድ ቤት ቀርቦ ያልጸደቀ፣ ይህን የንብረት ክፍፍል ስምምነት አስመልክቶ በግልጽ ፈቃዲቸውን ሰጥተው ስለመስማማታቸው ያልተረጋገጠ መሆኑን የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ፍሬ ነገር ነው። ተጠሪም በስር ፍርድ ቤት የክፍፍል ጊዜ ቤቱ የጋራ መሆኑን ጠቅሰው ክፍፍል እንዱደረግ ዲኝነት የጠየቁበት ከመሆኑም በላይ በይግባኝ ደረጃም በቤቱ ላይ የተሰጠውን የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ክፍል ተገቢ ነው በማለት ሲከራከሩ የነበሩ መሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሳያል። ስለሆነም አመልካች አለ የሚለት ሰነድ በፍርድ ቤት ያልጸደቀና የግራ ቀኙን ፈቃዲቸው መኖሩ ያልተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች ቤቱን አስመልክተው የሚያቀርቡት ቅሬታ ተቀባይነት የሚያገኝበት የሕግ አግባብ አላገኘንም።
ላላው አመልካች አጥብቀው የሚራከሩት የካሳ ጥያቄ መታለፈ ያላግባብ ነው በሚል ነው።
የበታች ፍርድ ቤቶች ይህንኑ የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ያለፈት አመልካች የፍቺ ውሳኔ እንዱሰጣቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ ይህንኑ አልገለፁም በሚል ነው። በእርግጥም አመልካች የፍቺ ጥያቄ ሲያቀርቡ የካሳ ጥያቄ አላቀረቡም። ሆኖም ሕጉ የፍቺ ጥያቄ ሲቀርብ ለፍቺ ምክንያት የሆነውን ጉዲይ መግለፅ የላለባቸው መሆኑን በአንቀጽ 81/2/ ስር የተደነገገ ቢሆንም ካሳውን ግን በንብረት ክፍፍል ጊዜ ዲኝነት ሉያቀርቡ የሚችለ መሆኑን ይህንኑ ድንጋጌ ከአንቀጽ 84 ጋር አገናዝበን ስንመለከተው የምንረዲው ጉዲይ ነው። ይሁን እንጂ አመልካች ለፍቺ ምክንያት የሆነውን በደል ለፍቺ ምክንያትነት መጥቀስ በሕጉ ግዳታ ያልተጣለባቸው ቢሆንም ካሳ የሚወሰነው ለፍትህ አስፈላጊ ነው ብል ፍርድ ቤቱ ሲያምንበት መሆኑን አንቀጽ 84 በግልጽ ስለሚደነግግና የበታች ፍርድ ቤቶችም በዚህ ረገድ ካሳ መወሰኑ ለፍትህ አስፈላጊ መሆኑን ያላመኑበት መሆኑን በተለይ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በፍርደ ላይ የገለፀ ስለሆነ በዚህ ረገድ የተሰጠውን ውሳኔ ከአንቀፁ አቀራረፅና ይዘት አንጻር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሁኖ አልተገኘም። ሲጠቃለልም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 26 ቀን 2004 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 05 ቀን 2006 ዓ/ም ተሻሽል የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ አመልካች የራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.