አንድ ወንድና ሴት ሲጋቡ በጋብቻ ውላቸው ንብረትን በተመለከተ ካደረጉት ስምምነት ላይ “ከወለደች የግል የለባትም ” ፣ “ ሀብትሽ ሀብቴ ነው “ ተብል የተፈጸመው የውል ሀረግ ካለና ልጅ ከወለደ ከጋብቻ በፉት የነበራቸውን የግል ንብረት የጋራ ለማድረግ እንደተስማሙ የሚቆጠር ወ/ሮ ልዩሴት ሥዩም እና አቶ ሸዋፈራ ንጉሴ
No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዚያ 12 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሮ ልዩሴት ሥዩም ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሽዋፈራ ንጉሴ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የባልና ሚስት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በበረኸት ወረዲ ፍርድ ቤት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው አመልካች የነበሩት የአሁኑ አመልካች ከአሁኑ ተጠሪ ጋር የመሰረቱት ጋብቻ በፍቺ ውሳኔ ይፍረስልኝ እና የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ መነሻ ነው። አመልካች ባቀረቡት አቤቱታ ከተጠሪ ጋር በጋብቻ ተሳስረው የቆዩና አንድ ልጅ የወለደ ቢሆንም ጋብቻው ውስጥ ተግባብተው መኖር ያልቻለ መሆኑን ጠቅሰው ጋብቻው ፈርሶ የጋራ ንብረት ያካፍለኝ በማለት የንብረቶቹን አይነት እና ብዛት ዘርዝረው ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስም ከአመልካች ጋር በጋብቻ ተሳስረው መኖራቸውንና ልጅ መውለዲቸውን ሳይክደ የጋራ ንብረትን በተመለከተ በአመልካች ተዘርዝረው ከቀረቡት ውስጥ መኖሪያ ቤቱንና ካዝናው ከጋብቻ በፉት የተፈሩ መሆናቸውን ገልጸው የግላ ናቸው ያለ ሲሆን ላልችን የጋራ መሆናቸውን አምነው መልሳቸውን ሰጥተዋል።ከዚህም በኋላ የአሁኗ አመልካች ተጠሪ የግላ ናቸው በማለት የጠቀሷቸው ንብረቶች ግራ ቀኙ ሐምል 23 ቀን 1997 ዓ/ም ባደረጉት የጋብቻ ውል ሀብትሽ በሃብቴና ከወለደች የግል የለባትም በማለት መስማማታቸውን ገልጸው ንብረቶች የጋራ ናቸው ሲለ ተከራከሩ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ የጋብቻ ውለ ይዘት አመልካች "ከወለደች የግል የለባትም" የሚል ሐረግ መያዙ ንብረቶቹን የጋራ ሉያደርግ የማይችል መሆኑን ጠቅሰው ተከራክረዋል። የወረዲው ፍርድ ቤትም የክፍለን ማዘጋጃ ቤት ጠይቆ አከራካሪው ቤት በ1995 ዓ/ም መሰራቱን ያረጋገጠ ሲሆን የጋብቻ ውለን ይዘትና መንፈስ ለመረዲት ደግሞ በውለ ያለትን የግራ ቀኙን ምስክሮች ሰምቷል። ከዚህም በኋላ ጉዲዩን መርምሮ ከተሰሙት ሶስቱ ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል ከጋብቻ በፉት የተፈራውን ንብረት የማይመለከት መሆኑን የሚያሳይ ስለመሆኑ ጠቅሶ በጋብቻ ውለ ላይ አመልካች "ከወለደች የግል የለባትም" የሚለው ሐረግ ቤቱ ከጋብቻ በፉት የተፈራ የተጠሪ የግል ንብረት በመሆኑ ለአመልካች ተጠሪ የሚያካፍልበት ምክንያት የለም ሲል በዚህ ንብረት ላይ የቀረበውን የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል። ካዝናውንና ላልች ንብረቶችን የጋራ ናቸው በማለት ግራ ቀኙ እኩል እንዱካፈለ የወሰነ ሲሆን የልጅ ቀለብን በተመለከተም ተጠሪ በየወሩ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) እንዱከፍል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱም ጉዲዩን መርምሮ የወረዲው ፍርድ ቤት በቤቱ ላይ የሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍ ያለመሆኑን ምክንያቱን ዘርዝሮ ያጸናው ሲሆን የልጁን ቀለብ በተመለከተ ግን መጠኑ ያነሰ መሆኑን ገልፆ ተጠሪ በየወሩ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) እንዱከፍል ሲል ወስኗል።ከዚህም በኋላ አመልካች ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታቸውን አቅርበው ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ግራ ቀኙ ባደረጉት የጋብቻ ውል "ሀብትሽ ሀብቴ ነው አመልካች ከወለደች የግል የለባትም" ተብል የተቀመጠው ሐረግ ከጋብቻው በፉት የተፈራውን የተጠሪን ንብረት የጋራ ለማድረግ ታስቦ የገባ ሁኖ እያለ በውለ ላይ ያለው ይኼው ሐረግ ከጋብቻ በኋላ የሚገኘውን ንብረት የጋራ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ ነው ተብል በስር ፍርድ ቤቶች መተርጎሙ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረት የጋራ ስለመሆኑ ሕጉ ጥበቃ ያደረገውን መብት ያላገናዘበ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበውም ግራ ቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የንብረት ክፍፍለን በተመለከተ በ18/08/95 ዓ.ም በተደረገ የፍቺ ስምምነት አንጻር ሉፈጸም የሚገባው እንጂ ዲግም ዲኝነት የሚጠየቅበት አይደለም ተብል መወሰኑ ተገቢ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካችና ተጠሪ ሐምል 23 ቀን 1997 ዓ/ም ባደረጉት የጋብቻ ውል "ሀብትሽ ሀብቴ ነው አመልካች ከወለደች የግል የለባትም" የሚል ሐረግ አስገብተው ስምምነት መደረጉን፣ ጋብቻው በዚህ እለት ተፈጽሞም አመልካችና ተጠሪ አንድ ላይ ሲኖሩ አመልካች አንድ ልጅ ለተጠሪ የወለደችላቸው መሆኑን፣ ተጠሪ ቤቱን ከጋብቻ በፉት ያፈሩት መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ መሆኑን፣አሁን ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው ጉዲይም የጋብቻ ውለ ላይ " ከወለደች የግል የለባትም" ተብል የተቀመጠው ሐረግ አመልካች ለተጠሪ ልጅ ሰለወለደላቸው ከጋብቻ በፉት የተፈሩ ንብረቶችን የጋራ የማድረግ ውጤት ያለው መሆን ያለመሆኑን ነው።
በመሰረቱ ባልና ሚስት ጋብቻቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜ በየግል የነበሯቸው ንብረቶች ወይም ከጋብቻ በኃላ በውርስ ወይም በስጦታ በየግላቸው የሚያገኟቸው ንብረቶች በጋብቻ ዘመንም የግል ሆነው እንደሚቀሩ የክልለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 79/95 አንቀጽ 68(1) በግልጽ ያሳያል። ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ በሕጉ ጥበቃ የሚደረግለት ንብረቶቹ በጋብቻ ውል የጋራ እንደሆኑ ስምምነት ከላለ ብቻ ነው። አመልካችና ተጠሪ ሐምል 23 ቀን 1997 ዓ.ም የተደረገው የጋብቻ ውል ስምምነት "ሀብትሽ ሀብቴ ነው ልጅ ከወለደች የግል የለባትም" የሚል ሐረግ የያዘ ነው።
ተጠሪ ከአመልካች ጋር በዚህ መልኩ ያደረጉት የጋብቻ ውል ስምምነት ውጤቱ ከጋብቻ በኋላ የሚፈሩትን ንብረቶች የጋራ የሚያደርግ ነው ይበለ እንጂ የውለ ይዘትና መንፈስ እንደ አመልካች ክርክር ነው እንዲይባል የቤተሰብ ሕጉ ባልና ሚስት ንብረታቸውንና የግል ግንኙነታችን በተመለከተ የሚያደርጓቸው ስምምነቶች በህጉ በአስገዲጅነት የተቀመጡ ድንጋጌዎችን በሚፃረር መልኩ ላሆን አይገባም ተብል በሕጉ ከተቀመጠው ድንጋጌ ጋር አብሮ የማይሄድ ነው። ሕጉ በጋብቻ ውስጥ የተፈራ ንብረትን በተመለከተ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ነው በሚል በአስገዲጅ መልኩ ደንግጓልና። በመሆኑም በሕጉ ጥበቃ በተደረገው መብት ላይ የጋብቻ ውል ስምምነት ሕጉን በሚፃረር መልኩ ማድረግ በሕጉ የሚፈቀድ አይደለም። ከዚህ አንጻር የውል ስምምነቱ በግልፅ በጋብቻ በፉት በተፈሩት ንብረቶች ላይ መደረጉን የሚያሳይ መሆኑን ከግራ ቀኙ ስምምነት ይዘት፣ የቤተሰብ ሕጉ በጋብቻ ጊዜ ስለሚፈሩ ንብረቶች ከአደረገው ጥብቃና ከውል ሕግ የአተረጓጎም ደንቦች መንፈስ የምንረዲው ነጥብ ነው። የጋብቻ ውል ስምምነት ይዘት ትርጉም አከራካሪ ከሆነ ስምምነቱ የግራቀኙን የንብረትን መብት የሚገዛ እንደመሆኑ መጠን ከውል አይነቶች አንደ ልባል የሚችል ስለሆነና አተረጓጎምን በተመለከተ ልንከተለው የሚገባ ደንብ በቤተሰብ ሕጉ በግልፅ የተቀመጠ ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1677/1/ ድንጋጌ መሰረት በጠቅላላ ውል ስለውልች አተረጓጎም የተቀመጡትን ደንቦች ማለትም ከፍ/ሕ/ቁጥር 1731 እና ተከታዩቹን ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ የግራቀኙ ሐሳብና ፍላጏት ምን እንደነበር መመርመር የግድ የሚል ነው።
በመሰረቱ በውል ውስጥ የተጠቀሱት ቃላትና ድንጋጌዎች ግልጽ ባልሆኑ ጊዜ ከፍ/ሕ/ቁጥር 1732፣ 1735-1738 ድረስ ባለት ድንጋጌዎች ስር በሰፈሩት ደንቦች መሰረት መተርጎም የተፈቀደ ነው። በዚህም መሰረት ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያላቸው ደንቦች በፍ/ሕ/ቁጥር 1734 እና 1736 ሲሆኑ ተዋዋዩች ውላቸውን ከመዋዋላቸው አስቀድሞ ወይም ከተዋዋለ በኃላ የነበሩበትን ሁኔታዎች የፈጸሙትን ተግባር በማመዛዘንና ሐሳባቸው ምን እንደነበር ለማወቅ መሞከር እና የውልችን ቃልች አንደን ከአንደ ጋር እያዛመደ በመመልከት ለውለ ጉዲይ አግባብ ያለውን ትርጉም በመስጠት አዎንታዊ ውጤት እንዱኖረው ማድረግ ተገቢ ስለመሆኑ ተጠቃሽ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። በያዝነው ጉዲይ አመልካችና ተጠሪ በ23/11/1997 ዓ.ም አደረግን የሚለት የጋብቻ ውል ቤቱ ከጋብቻ በፉት የተፈራ የተጠሪ የግል ንብረት መሆኑን ተጠሪ እያወቁ አመልካች ጋር ሲጋቡ ግን "ሀብትሽ ሀብቴ ነው ልጅ ከወለደች የግል የለባትም" በማለት ስምምነት ማድረጋቸው አስቀድሞም ከጋብቻ በፉት የተፈራ ንብረት የግል ስለመሆኑ በህግ የተጠበቀላቸውን መብት በመተው አመልካች ልጅ እስከወለደላቸው ድረስ የተጠሪን የግል ንብረት የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት ለማድረግ አምነው ልጅ ከማግኘት በመነጨው ፍላጏት የግል ንብረታቸውን የጋራ ለማድረግ ተስማምተዋል ከሚባል በስተቀር ላላ ትርጉም ሉሰጠው የሚገባው ሆኖ አልተገኘም። በልላ አገላለፅ በጋብቻ ውለ አመልካች ልጅ ከወለደች የግል የለባትም ተብል የተቀመጠው ሐረግ ሀብትሽ ሀብቴ ነው ከሚለው ሐረግ ጋር ተሳስሮ ሲታይ ግራቀኙ የነበራቸው ሀሳብ አመልካች ልጅ በመውለድ ሁኔታ ላይ የተገደበ ሁኖ ልጅ ከወለደ ግን ከጋብቻ በፉት የተፈራ የተጠሪ የግል ሀብት የግላቸው ሁኖ የሚቀር ንብረት ስለመሆኑ የሚያሳይ ሳይሆን የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት ስለመሆኑ መስማማታቸውን የሚያሳይ ነው። "ሐብትሽ ሀብቴ ነው" የሚለው የአማርኛ ሐረግም የሚታወቀው ተጋቢዎች በግል የነበራቸውን ሀብት የጋራ ለማድረግ በማሰብ የሚጠቀሙበት ስለመሆኑ ከነባራዊ ሁኔታ የምንረዲው ጉዲይ ነው። "ከወለደች የግል የለባትም" የሚለው ሐረግ በጋብቻ ጊዜ የሚፈራውን ንብረት የጋራ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ ነው እንዲይባል በጋብቻ ወቅት የሚፈሩ ንብረቶቹን ሕጉ የጋራ ስለመሆናቸው በአስገዲጅ ሁኔታ የደገገ በመሆኑ የጋብቻ ውል ሲደረግ ይኼው በሕጉ አስቀድሞ በአስገዲጅ ሁኔታ ጥበቃ ያገኘ ጉዲይ በስምምነት ውስጥ የሚካተትበት አግባብና በህግ ጥበቃ የሚያገኝበት ምክንያት አይኖርም።ተጠሪ ከጋብቻ በፉት ያፈሯቸው ንብረቶች የግላቸው ሁነው የሚቀጥለ መሆኑም በሕጉ የተደገገ በመሆኑ ይህንኑ በህግ ጥበቃ ያገኘ መብት መኖሩን እያወቁና ውጤቱን እየተረደ የጋብቻ ውል ስምምነቱ ሲደረግ "ሀብትሽ ሀብቴ ነው" "ከወለደች የግል የለባትም" የሚለትን ሐረጋትን በስምምነቱ እንዱገቡ ያደርጋለ ተብል አይታሰብም።
ሲጠቃለልም ስምምነቱ መኖሩ ግራ ቀኙን ያላከራከረና ይዘቱም አንደ ሀረግ ከአንደ ጋር ተሳስሮ ሲታይ ከጋብቻ በፉት የተፈሩ ንብረቶችን የጋራ የሚያደርግ መሆኑን የሚያሳይ ሁኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ስምምነቱ በጋብቻ ውስጥ ለተፈራ ንብረት ተፈፃሚነት ያለው እንጂ ከጋብቻ በፉት ለተገኘ ንብረት አይደለም በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
አከራካሪውን ቤት አስመልክቶ በበረኸት ወረዲ ፍ/ር/ቤት በመ//05 ጥቅምት 25 ቀን 2006 ዓ/ም ተሰጥቶ በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/1 ጥር 09 ቀን 2006 ዓ/ም፣በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 030-4591 የካቲት 19 ቀን 2006 ዓ/ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት “በድምፅ ብልጫ” ተሽሯል።
አመልካችና ተጠሪ ሐምል 23 ቀን 1997 ዓ/ም ባደረጉት የጋብቻ ውል አመልካች "ከወለደች የግል የለባትም" በማለት ያስቀመጡት የውለ ሐረግ በውለ ሀብትሽ ሀብቴ ነው ተብል ከተቀመጠው የውለ ሀረግ ጋር ተሳስሮ ሲታይ አመልካች ለተጠሪ ልጅ ከወለደ ከጋብቻ በፉት በነበረው የተጠሪ የግል ንብረት ላይ የጋራ ባለሃብት እንዱሆኑ በማስብ ያስቀመጡት ነው በማለት አመልካችና ተጠሪ ክርክር የተነሳበትን ቤት እኩል ሉካፈለ ይገባል፣ ክፍፍለም በክልለ የቤተሰብ ሕግ በተቀመጠው ስርዓት ላሆን ይገባል በማለት ወስነናል። በላልች ንብረቶች በወረዲው ፍርድ ቤት፣ ስለ ልጅ ቀለብ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጡ ውሳኔዎች አልተነኩም።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.