ጋብቻ ሳይኖር እንደባልና ሚስት ለሚኖሩ ሰዎች የሚፈለገው ማስረጃ ወንደና ሴትየዋ የተጋቡ ሰዎችን ሁኔታ ሲያሳዩና ቤተዘመድቻቸውና ማህበረሰቡ እንደተጋቢ ሰዎች የሚኖሩ ናቸው ብለው የሚገምቷቸው መሆን ያለባቸው ስለመሆኑ፣ በአንድ ወንድና ሴት መካከል ለተወሰነ ጊዜ የፍቅር ግንኙነት መኖሩ ብቻ እንደባልና ሚስት የሚኖሩ ናቸው ሉያስብል የማይችል ስለመሆኑ ፣ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀፅ 97፣98፣99 እና 106/2/
No summary available.
መጋቢት 29 ቀን 2ዐ07 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- አቶ ጀቫኒ ላሮዛ - ጠበቃ ስንታየሁ ብርሃኑ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አዲነች ተስፊዬ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአንድ ወንድና በአንዱት ሴት መካከል በሕግ ጥበቃ ሉደርግለት የሚችል እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት አለ ለማለት የሚቻልበትን አግባብ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የተጠሪ የክስ ይዘትም ከአሁኑ አመልካች ጋር ከ1998 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም ወር 2003 ዓ/ም ድረስ እንደባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ቆይተው መስከረም ወር 2003 ዓ/ም ግንኙነቱ መቋረጡንና ልጅ ባይወልደም የተለያዩ የሚንቀሳቀሱም ሆነ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን በግንኙነቱ ጊዜ ያፈሩ መሆኑን ጠቅሰውና የንብረቶቹን አይነትና ብዛት ዘርዝረው አመልካች ንብረቶቹን እኩል እንዱያካፍሎቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለተጠሪ ክስ በሰጡት መልስም በኢትዩጵያ ውስጥ መኖር የጀመሩት ከጥር 1999 ዓ/ም ጀምሮ መሆኑን፣በዚህ ጊዜም ተጠሪ ይኖሩ የነበሩት በየካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 11/112 የቤት ቁጥር 539 እና 612 ውስጥ ሁኖ አመልካች ደግሞ በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 14/15 በቤት ቁጥር አዱስ ውስጥ መሆኑንና አብረው እንደባልና ሚስት ሁነው አለመኖራቸውን፣አመልካች በቱሪስት ቪዛ በ1998 ዓ/ም ወደ ኢትዩጵያ ገብተው ሐምል 21 ቀን 1998 ዓ/ም ተመልሰው መውጣታቸውን፣ነሐሴ 27 ቀን 1998 ዓ/ም ወደ ኢትዩጵያ ገብተው ደግሞ ጥቅምት 11 ቀን 1993 ለሶስተኛ ጊዜ ሲመጡ ያረፈት በሴንትራል ሸዋ፣በሀላዲይ፣በገነት ሆቴል፣በጊዩን ሆቴልች እና ለሶስት ወራት በአቶ ሽመልስ ወ/ስላሴ ቤት መሆኑን፣ ከተጠሪ ጋር ጓደኝነት የጀመሩት ታህሳስ 29 ቀን 1999 ዓ/ም ሁኖ የቆዩትም እስከ ሰኔ 18 ቀን 1999 ዓ/ም ድረስ መሆኑን፣ግንኙነታቸውም አልፍ አልፍ እንደነበርና ተጠሪ ሰኔ 18 ቀን 1999 ዓ/ም በኃላ ጣሉያን አገር አመልካች እንዱወስዶቸው ጠይቀው አመልካች ወስዶቸው ሳለ ከላላ ሰው ጋር ግንኙነት ፈጥረው ለመመለስ ባለመፈለጋቸው በመሀከላቸው ያለመግባባት በመፈጠሩ ግንኙነቱ መቋረጡንና ይህንም ሰኔ 18 ቀን 1999 ዓ/ም ኢትዩጵያ ከተመለሱ በኋላ ለጣሉያን ኢምባሲ አመልክተው ከዚያ በኋላ ነሐሴ 1999 ዓ/ም እስከ ሚያዚያ 2001 ዓ.ም ድረስ በፍቅር ጓደኝነት ከወ/ሮ መቅደስ አራጌ ጋር ለሁለት አመታት ከቆዩ በኋላ ከወ/ሮ እመቤት ጋሻው ጋር በፍቅር ጓደኝነት እየኖሩ እንደሚገኙ ዘርዝረው ከተጠሪ ጋር ከአምስት ወር በላይ በጓደኝነት ባልቆዩበት ሁኔታ በጣሉያን አገር እያለ ያፈሩት ገንዘብ በኢትዩጵያ ባንክ በኩል ተላልፍላቸው ኢትዩጵያ ውስጥ ያፈሩትን የማይንቀሳቀስና የሚንቀሳቀስ ንብረት ተጠሪ ሉካፈለ የሚችለበት የሕግ አግባብ የለም ሲለ ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ከ1999 ዓ/ም እስከ መስከረም 2003 ዓ/ም ድረስ እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት መኖሩ ተረጋግጧል የሚል ድምዲሜ ይዞ ንብረቶቹን በተመለከተም ግራ ቀኙ እኩል ሉካፈለ ይገባል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ተጨማሪ ማስረጃ ከሰማ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ በአመልካችና በተጠሪ መካከል እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት የለም ሲል የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙለ በሙለ ሽሮታል። ከዚህም በኋላ ተጠሪ ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኛቸውን አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ በግራ ቀኙ መካከል እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት መኖሩ ተረጋግጧል የሚል ድምዲሜ ይዞ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሽሮ የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የተጠሪ ምስክሮች ቃል እርስ በእርሱ የሚጋጭና ታዓማኒነት የላለው ከመሆኑም በላይ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው ግንኙነት እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት ነው ተብል የሚወሰድ አለመሆኑን እንደ ህጉ የማያስረዲ ሁኖ እያለና እንዱሁም የአመልካች ምስክሮች በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረውን ግንኙነት በተመለከተ የሰጡት የምስክርነት ቃል ያላግባብ ውድቅ መደረጉ ተገቢውን የማስረጃ ምዘና ስርዓት ያልተከተለ መሆኑን ዘርዝረው በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ በመደረጉ ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።እንዱሁም የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዋና መዛግብት እንዱመጡ ተደርገው የግራ ቀኙ ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል ይዘቱ ታይቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም በአመልካችና በተጠሪ መካከል እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት አለ ተብል መወሰኑ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ዋና ነጥብና ውጤቱ ምንድነው? የሚለው ተያያዥ ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ ተገኝቷል።
ተጠሪ በአመልካች ክስ ሲመሰርቱ በመካከላቸው ከ1998 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መስከረም ወር 2003 ዓ/ም ድረስ እንደባልና ሚስት አብረው መኖራቸውን የገለፁ ሲሆን አመልካች ደግሞ ከተጠሪ ጋር ከአምስት ወር በላይ በጓደኝነት ያለመኖራቸውን ጠቅሰው ግንኙነቱ የሕግ ጥበቃ የላለው መሆኑን በሚያስገነዝብ መልኩ መልሳቸውን ሰጥተው ግራ ቀኙ አለን ያሎቸውን ማስረጃዎችን አስቀርበው አሰምተዋል። የግራ ቀኙ ምስክሮች ቃል የሰጡት የምስክርነት ቃልም በአጭሩ እንደሚከተለው የተመዘገበው ነው።
ወ/ሪት ሳራ ተስፊዬ የተባለት የተጠሪ 1ኛ ምስክር የተጠሪ እህት መሆናቸውን ገልጸው አመልካችና ተጠሪ ከ1998 ዓ/ም ክረምት ወራት ጀምሮ እስከ 2003 ዓ/ም ድረስ ለአምስት አመታት ያህል በትዲር መቆየታቸውን፣ይህንኑ ሉያውቁ የቻለትም አመልካችና ተጠሪ ወደ ምስክሯ ቤት አብረው ሲሄደና አመልካችና ተጠሪ አብረው ሲኖሩ ስለነበር መሆኑን፣አመልካች ወደ ውጪ ይሄደ በነበሩበት ጊዜ ምስክሯ ይሄደ እንደነበርና አመልካች ውጪ ሂደውም ሁለት፣ሶስት ወራት ይቆዩ እንደነበር፣አመልካችና ተጠሪ ቤት ገዝተው እስከ ተጣለበት ጊዜ ድረስ አንድ ቤት ሲኖሩ እንደነበር፣አመልካችና ተጠሪ አብረው በሚኖሩበት ጊዜ ቤት፣መኪና እና የቤት ቀሳቁሶችን ገዝተው እንደነበር፣አመልካችና ተጠሪ ከክረምት 1998 ዓ/ም ጀምሮ በጓደኝነት መስሪያ ቤት መጥተው እንደተዋወቁ እንደሚያወቁና ለአምስት ተከታታይ አመታት ያለማቋረጥ መኖራቸውን፣ቤት፣መኪና እና የቤት ቁሳቁሶች ሲገዙ ምስክሯ እንዲልነበሩ ገልፀው መስክረዋል።ወ/ሮ እቴነሽ ተስፊዬ የተባለት ሁለተኛ የተጠሪ ምስክርም የተጠሪ እህት መሆናቸውን ገልጸው የሰጡት የምክርነት ቃል በይዘቱ ከ1ኛ ምስክር ቃል ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው።ወ/ሮ ዲግማዊት ደርቡ የተባለት የተጠሪ ሶስተኛ ምስክር የተጠሪ የአክስት ልጅ መሆናቸውን ገልጸው ከውጪ አገር ቆይተው በ1999 ዓ/ም ወደ ኢትዩጵያ ሲመጡ ተጠሪ ከጣሉያን አገር የመጣ የውጭ ሰው አግብተው እየኖሩ መሆኑን ወላጅ እናታቸው የነገሯቸው መሆኑን፣አመልካችና ተጠሪ በምስክሯ ወላጅ እናት ቤት በ2000 ዓ/ም እራት ሲጋበዙ አንድ ጊዜ መመልከታቸውንና አመልካችና ተጠሪ አንድ ላይ በአንድ ቤት ሲኖሩ እንደነበር ራሳቸው ተመልክተው የተረደት ሳይሆን ሰው ነግሯቸው ያወቁት ሁኔታ መሆኑን፣አመልካችና ተጠሪን እንደባልና ሚስት መኖራቸው ሉያውቁ የቻለት በቤተሰብ ሰርግም ሆነ ለቅሶ ወይም ልደትና ክርስትና ላይ እንደባልና ሚስት ሁነው በመሆኑ ምክንያት መሆኑን መስክረዋል። ወ/ሮ ሀረጓ በየነ የተባለት የተጠሪ 4ኛ ምስክር በበኩላቸው በግራ ቀኙ መካከል ዝምድና የላላቸው መሆኑን ገልጸው አመልካችንና ተጠሪን በ1999 ዓ/ም ክረምት ውስጥ አግኝተዋቸው ተጠሪ አመልካችን ለምስክሯ ባለቤቴ ነው ብላ ያስተዋወቻቸውና አመልካችም ይህንኑ የተጠሪዋን ንግግር ይሰማና አመልካችም ጆቫኒ እባላለሁ ብል የመለሰላቸው መሆኑን እንዱሁም ቀኑን፣ወሩንና አመተ ምህረቱን በማያስታውሱት ጊዜ አመልካችና ከላልች ሴቶች ጋር ሲመለከቷቸው እንደነበር ገልጸው የመሰከሩ ናቸው። አቶ ተፈራ ሲሳይ የተባለው የተጠሪ አምስተኛ ምስክር በበኩላቸው በግራ ቀኙ መካከል ዝድምና የላላቸው መሆኑን ገልፀው አመልካችና ተጠሪ መኪና ለመከራየት ወደ ምስክሩ በ1999 ዓ/ም መሄዲቸውን መኪና ተከራይተው መሄዲቸውን፣ከዚያ በኋላም በሚያዚያ ወር 2002 ዓ/ም መኪናቸውን በብር 80,000.00 ሽጠው ቴሮስ መኪና በብር 172,0000.00 የገዙ መሆኑን እንደሚያውቁ፣አመልካችና ተጠሪ በሚመጡበት ጊዜ እንደባልና ሚስት ሁነው እንደሚረዶቸው የመሰከሩ ናቸው።ወ/ሮ አስናቀች ደስታ የተባለት የተጠሪ ስድስተኛ ምስክር ደግሞ ከግራ ቀኙ ዝምድና የላላቸው መሆኑን ገልጸው ተጠሪ የጓደኛቸው እህት መሆናቸውንና እርሳቸውም ከተጠሪ ጋር ጥቂት ጊዜ አብረው የሰሩ መሆኑን፣ጽጌ የተባለችው የተጠሪ እህት ተጠሪ ከውጭ ሀገር ዜጋ ጋር ተዋውቃ አብራ መኖርም የጀመሩ መሆኑን ለምስክሯ የነገረቻቸው መሆኑን፣ከዚህ በኋላ 1999 ዓ/ም ገና አልፍ በሳምንቱ ፅጌ ቤት በእንግድነት ሂደው ለመጀመሪያ ጊዜ አመልካችና ከተጠሪ ጋር መጥተው እንደተመለከቷቸውና ከዚያ በኋላ ወንድሟ ተስፊዬ ሲያገባ አመልካችና ተጠሪ አብረው በሰርጉ ላይ በ2000 ዓ/ም መጥተው እንደነበር በሳምንቱ በሙሽሪት ቤት መልስ ላይ ተገናኝተው እንደነበር፣አመልካችና ተጠሪ ቤት እንዲላቸው የሰሙ መሆኑንና አመልካችና ተጠሪ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲመጡ ባልና ሚስት ተብለው መሆኑን እንደሚያውቁ መስክረዋል።ወ/ት ሸዋእመቤት ተስፊዬ የተባለት የተጠሪ 7ኛ ምስክር የተጠሪ እህት መሆናቸውን ገልጸው የሰጡት የምስክርነት ቃልም በይዘቱ ከተጠሪ 1ኛ እና 2ኛ ምስክሮች ቃል ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው።
የአሁኑ አመልካች አለኝ ያሎቸው ምስክሮች የሰጡት የምስክርነት ቃል ሲታይም እንደሚከተለው የተመዘገበው ነው።
አቶ ማርቆስ የተባለው የአመልካች 1ኛ ምስክር ከግራ ቀኙ መካከል ዝምድና የላላቸው መሆኑን ገልጸው አመልካችንና ተጠሪን ከ1999 ዓ/ም ጀምሮ ጎረቤቶቻቸው ሁነው እንደሚያውቋቸው ጠቅሰው ለተወሰኑ ወራት ብቻ ተጠሪን ከአመልካች ጋር ከአዩ በኋላ ከአመልካች ጋር መቅደስ የሚባለ ሴት ከ2000 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚያዩ እና ወደ እርሳቸው ቤትም እኚህ ሴት ሲሄደ የነበሩ መሆኑን፣አመልካች በራሳቸው ስም በሚታወቅ ቤት ሲኖሩ ምስክሩ ደግሞ ከወንድማቸው ቤት ከአመልካች ጋር በጉርብትና ይኖሩ እንደነበር እንዱሁም አመልካችና ተጠሪ በ2000 ዓ/ም መጀመሪያ አከባቢ አንድ ሲመለከቷቸው የነበሩ ከመሆኑ ውጪ አመልካችን ከወ/ሮ መቅደስ እና ከወ/ሮ እመቤት ጋር ሲመለከቷቸው እንደነበር የመሰከሩ ናቸው።አቶ አሉ ሰይድ የተባለት የአመልካች ምስክር ደግሞ ግራ ቀኙን ያወቁበትን ጊዜ ለይተው አመልካችና ተጠሪ ከ1999 ዓ/ም ጀምሮ በጓደኝነት እንደሚኖሩ የሚያውቁ መሆኑን፣ይህንኑ ሉያውቁ የቻለትም ወደ ጣሉያን አገር ሲሄደ ምስክሩ በአመልካች ቤት ውስጥ የጥበቃ ስራ ሲሰሩ ስለነበሩ መሆኑን፣የጥበቃ ስራውን የሰሩትም እስከ 2001 ዓ/ም ሁኖ አመልካች በሰኔ ወር 1999 ዓ/ም ከጣሉያን አገር ከተመለሱ በኋላ ከተጠሪ ጋር ያላዩዋቸው መሆኑንና አመልካችና ተጠሪ በነበሩበት ጊዜ ተጠሪ ወደ አመልካች ቤት መጥተው የሚሄደ መሆኑንና ብዙ ጊዜ ተጠሪ በአመልካች ቤት ውስጥ ያልኖሩ መሆኑን እንዱሁም አመልካችን ከወ/ሮ መቅደስ ጋር ምስክሩ እንደሚያያቸው እና በ2001 ዓ/ም ግን ምስክሩ ከጥበቃ ስራ ስለለቀቁ የሚያውቁት ነገር ያለመኖሩን ገልጸው የመሰከሩ ናቸው።ወ/ሪት ተሰረ አሰግደው የተባለት የአመልካች ምሰክር ደግሞ ከግራ ቀኙ ጋር ዝምድና የላላቸው መሆኑን ጠቅሰው ግራ ቀኙን ከመስከረም ወር 2001 ዓ/ም ጀምሮ በቤት ሰራተኛነት በአመልካች ቤት ገብተው ስለነበር እንደሚያውቋቸው ገልጸው አመልካችና ተጠሪ አብረው ሁነው ከደላላው ቤት ምስክሯን ማስመጣታቸውን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ተጠሪ ከአመልካች ቤት ውስጥ ያልነበሩ፣የማይመጡ የነበረ መሆኑን፣ ምስክሯ በአመልካች ቤት እስከ መስከረም ወር 2004 ዓ/ም ድረስ እንደቆዩ፣በዚህ ጊዜ ውስጥም መቅደስ የሚባለ ሴት ከአመልካች ጋር ይኖሩ እንደነበርና እኚህ ሴትም ከአመልካች ጋር ምስክሯ እስከ ቆዩበት ጊዜ እንዲልቆዩና እመቤት የተባለ ሴት ከአመልካች ጋር እንደነበሩ የመሰከሩ ናቸው። ወ/ሮ እመቤት ጋሻው የተባለት የአመልካች 4ኛ ምስክር በበኩላቸው የአመልካች የፍቅር ጓደኛ መሆናቸውን ገልጸው አመልካችን ከመጋቢት ወር 2002 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚያውቋቸውና ከአመልካች ጋር አብረው የማይኖሩ ቢሆንም በሳምንት ሶስት ቀንና እረፍት በሚሆንበት ጊዜ ከቤቱ ሄደው እንደሚያድሩ፣ስራ በልላቸውና ስራ ባቆሙ ጊዜም ሁለት ወር የሚሆን ከአመልካች ቤት ሂደው እንደሚቆዩና በዚህ ጊዜ ተዘሩ የምትባል የቤት ሰራተኛ እንደነበረችና የአሁኗ ተጠሪ ወደ ቤቱ መጥተው እንደማያውቁ እንዱሁም ከአመልካች ጋር ጓደኝነት ከጀመሩ ጊዜ ጀምሮ ግንኙነቱ ቀጥል ያለ መሆኑን የመሰከሩ ናቸው።አቶ ግዛቸው አምዳ የተባለው የአመልካች አምስተኛ ምስክር ደግሞ ከግራ ቀኙ ጋር ዝምድና የላላቸው መሆኑን ጠቅሰው አመልካችና ተጠሪ ከሐምል ወር 1999 ዓ/ም ጀምሮ በጉርብትና እንደሚያውቋቸውና ተጠሪን ደግሞ ከ1999 ዓ/ም መጨረሻ ጀምሮ እስከ ጥር ወር 2000 ዓ/ም ድረስ ብቻ እንደሚያውቋቸው ገልጸው በዚህ ጊዜ ውስጥም ተጠሪን ሁለት ጊዜ ብቻ ያገኟቸው መሆኑን፣ ከአመልካች ጋር ከጥር ወር 2000 ዓ/ም በኋላ የሚያገኟቸው ወ/ሮ መቅደስን ስለመሆኑና እሳቸውም ቢሆን ከ2002 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 2003 ዓ/ም ድረስ አልፍ አልፍ እንደሚመለከቱ ገልፀው መስክረዋል። ዋና ሳጅን እልፍነሽ ግርማ የተባለት የአመልካች 6ኛ ምስክር ደግሞ አመልካች ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ቤት ተከራይተው በነበሩበት ጊዜ ተጠሪን እስከ ሰኔ ወር 1999 ዓ/ም የተመለከቷቸው መሆኑን በግንቦት ወር 1999 ዓ/ም አመልካች ተጠሪን ወደ ጣሉያን አገር ይዘው ሂደው ከሁለት ወር ቆይታ በኋላ አመልካች መምጣቱን ለምስክሯ ከነገሯቸው በኋላ ምስክሯ አመልካችን ተጠሪ ደህና መሆናቸውን ሲጠይቁ አመልካች ከተጠሪ ጋር ተጣልተው እንደተለያዩ አመልካች ለምስክሯ የነገሯቸው መሆኑን፣ምስክሯ ከተጠሪ ጋር አንድ ቀበላ ይኖሩ ስለነበርም ከአመልካች ጋር ለማስታረቅ በሚፈልጉበት ጊዜ ተጠሪ ከአመልካች ጋር መታረቅ የማይፈልጉ መሆኑን ለምስክሯ እንደነገሯቸው፣ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አመልካችና ተጠሪ ተገኛኝተው እንደማያውቁና ከ1999 ዓ/ም ጀምሮ አመልካች መቅደስ ከምትባል ሴት ጋር ተዋውቀው ወደ ምስክሯ ቤት ይዘው ሂደው እንደነበርና መቅደስ ጋር ደግሞ አመልካች በግምት ለሁለት አመታት ያህል አብረው የቆዩ መሆኑንና ከመቅደስ ጋር ከተለያዩ በኋላ ደግሞ እመቤት የሚባለ ሴት ጋር በጓደኝነት እየኖሩ እንደሚገኙ መስክረዋል።አቶ ወንደወሰን ተሰማ የተባለት የአመልካች ሰባተኛ ምስክር በበኩላቸው ከግራ ቀኙ ጋር ዝምድና የላላቸው መሆኑን ጠቅሰው በአከባቢው የጥበቃ ኃላፉ ሁነው ሲሰሩ አመልካችንና ተጠሪን ከ1999 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚያውቋቸው፣ተጠሪ አመልካች ወደ ገዙት ቤት 1999 ዓ/ም መጨረሻ አካባቢ ከተጠሪ ጋር አልፍ አልፍ ሲመጡ እንደነበር፣ተጠሪ እስከ መስከረም 2000 ዓ/ም ድረስ ያዩአቸው እንደነበርና ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ተጠሪ ከአመልካች ጋር እንዲላያቸውና አመልካች ከላልች ሴቶች ጋር ይታዩ የነበረ መሆኑን የመሰከሩ ናቸው።የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተጨማሪ ማስረጃነት የሰማቸው ምስክሮች ቃልም በይዘቱ ከላይ የተጠቀሱት የአመልካች ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል የሚደግፍ መሆኑን መዝገቡ የሚያሳይ መሆኑን ተገንዝበናል።እንግዱህ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች እነዚህ ከሆኑ ከሕጉ አገናዝቦ ግንኙነቱ በሕጉ ጥበቃ ላደረግለት የሚችል መሆን ያለመሆኑን መመልከት አስፈላጊ ነው።
በመሰረቱ የተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 98፣ 99 እና 1ዐ6 በአንድ ወንድና በአንዱት ሴት መሃከል እንደ ባልና ሚስት አብሮ የመኖር ሁኔታ አለ የሚባለው መቼ እንደሆነና የግንኙነቱ መኖር በምን አይነት መንገድ ማስረዲት እንደሚቻል ያመላክታል።የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 106/2/ ድንጋጌ ሲታይም ጋብቻ ሳይኖር እንደባልና ሚስት ለሚኖሩ ሰዎች የሚፈለገው ማስረጃ ወንደና ሴትየዋ የተጋቡ ሰዎችን ሁኔታ ሲያሳዩና ቤተዘመድቻቸውና ማህበረሰቡ እንደተጋቡ ሰዎች የሚኖሩ ናቸው ብለው የሚገምቷቸው መሆኑን ማሳየት እንደአለበት ያመለክታል።በመሆኑም በጉዲዩ ላይ የሚቀርበው ማስረጃ ጋብቻ መፈፀሙን እንዱያረጋገጥ የማይጠበቅ ሲሆን ሕጉ ለይቶ ያስቀመጠው የማስረጃ አይነት ስለላለ በማናቸውም ማስረጃዎች ስለግንኙነቱ ማስረዲት ይቻላል። በጉዲዩ ላይ የሚቀርቡ ማስረጃዎች ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት አብሮ መኖርን የሚያሳዩ፣ሕጋዊ ውጤቱ የሚኖረው ሶስት አመትና ከዚያ በላይ አብሮ መኖሩ ሲረጋገጥ መሆኑና ምስክሮች የሚያረጋግጡት ሶስት አመትና ከዚያ በላይ አብሮ መኖራችንና በትዲር መልክ አብሮ መኖርን ስለመሆኑ ሕጉ ያሳያል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች እና ተጠሪ የነበራቸው ግንኙነት ከሕጉ ይዘትና መንፈስ ሲታይ በተጠሪ ምስክሮች ቃል አመልካችና ተጠሪ ጋብቻ ሳይፈጽሙ እንደባልና ሚስት አብሮ መኖርን የማያሳዩ፣ በሕጉ ግንኙነቱ ሕጋዊ ውጤቱ የሚኖረው ሶስት አመትና ከዚያ በላይ አብሮ መኖሩ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የተመለከተውን የተጠሪ ምስክሮች ጊዜውን በትክክል ለይተው ያልመሰከሩ እና አመልካችና ተጠሪ በትዲር መልክ አብሮ መኖርንም ያላረጋገጡ መሆኑን ከአመልካች ምስክሮች ጋር ተዲምሮ ሲታይ የምንገነዘበው ጉዲይ ሁኖ አግኝተናል።ህጉ ጋብቻ ሳይኖር እንደባልና ሚስት ለሚኖሩ ሰዎች የሚፈለገው ማስረጃ ወንደና ሴትዩዋ የተጋቡ ሰዎችን ሁኔታ ሲያሳዩና ቤተዘመድቻቸውና ማህበረሰቡ እንደተጋቡ ሰዎች የሚኖሩ ናቸው ብለው የሚገምቷቸው መሆኑን ማሳየት እንደአለበት የሚያመላክት ሲሆን አመልካችና ተጠሪ ይኖሩበት ነበር በተባለ አከባቢ ያለት የአመልካች ምስክሮች ቃል አመልካችና ተጠሪ ለተወሰነ ጊዜ ግንኙነት እንደነበራቸው፣አመልካች ከላልች ሴቶች ጋር አንድ ላይ ይኖሩ እንደነበር፣ተጠሪ ከላልች ሴቶች ጋር የቀጠለው የአመልካች ግንኙነት እያለ ከአመልካች ግንኙነት ያልነበራቸው መሆኑን ጭምር የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። በመሆኑም የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተጠሪ ምስክሮች ቃል በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረው ግንኙነት በትዲር መልክ ቀጣይነት የነበረው መሆኑን ባልመሰከሩበትና በአንፃሩ የአመልካች ምስክሮች ስለጉዲዩ የሰጡት የምስክርነት ቃል የአመልካችና የተጠሪ ግንኙነት በትዲር መልክ ሳይሆን ጊዜያዊ የፍቅር ግንኙነት የነበረ መሆኑን በአረጋገጡበት አግባብ የተጠሪ ምስክሮች የተጠሪ ቤተዘመድ በመሆናቸው ብቻ አይታመኑም ሉባለ የሚችለበት አግባብ የለም በማለት የሰጠው ውሳኔ ተገቢውን የማስረጃ ምዘና መርህ መሰረት ያላደረገና በተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 97፣98፣99 እና 106(2) ድንጋጌወች መሰረታዊ አላማ፣ይዘትና መንፈስ ውጪ ሁኖ አግኝተናል።
ሲጠቃለልም ስንመለከተው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 09 ቀን 2005 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ህዲር 30 ቀን 2006 ዓ/ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)መሰረት ተሽሯል።
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 128087 ሰኔ 28 ቀን 2005 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በአመልካችና በተጠሪ መካከል እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።