የፍትሐ ብሓር ክርክር በሂደት ላይ እያለ ከሰሽ ወይም ተከሳሽ በሞት ሲለይ የክርክሩ አካሄድ በምን አኳኃን መመራት እንዲለበት ልንከተለው ስለሚገቡ ሁኔታዎች የፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 48፣49 እና 50
No summary available.
ሀምላ 28 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መለሰ አመልካች፡- አቶ ለገሰ ዱባባ ተተኪ ሚስት ወ/ሮ ክቡ ደሜ ጠበቃ አብዱ ፈይሳ ቀርቡ ተጠሪ፡- ኢትዮጵያ ሜዱዬስ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ጠበቃ አቶ ሚሉዮን አለሙ ቀረቡ
ጉዲዩ ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ጋር የተያያዘ የጉዲት ካሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በወልመራ ወረዲ ፍርድ ቤት ተከሳሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ ላይ በ27/01/2006 ዓ/ም ባቀረቡት ክስ ነው። የክሱ ይዘት በአጭሩ ከ01/01/2000 ዓ/ም ጀምሮ በግሪን ሃውስ በብረት ስራ ተመድበው በቀን ደመወዝ ብር 20 እየተከፈላቸው በወር 600 እየሰሩ በጨመሩት 8 ሜ. ብረት ላይ የግሪን ሃውስ ላስቲክ እየሰሩ እያለ በ17/09/2005 ዓ/ም ብረቱን ወይም ላስቲኩን እንስተው ሁለት እግራቸው ሽባ ሆኖ ተሰብሮ መራመድ ያልቻለና የጀርባ አጥንታቸው ተሰብሮ ሽንትም ሆነ ሰገራ መቆጣጠር ያልቻለና ካሳና ሞራል ክፍያ እንዱሁም የተቋረጠባቸው ደመወዛቸውና ካሳ ከልዩ ልዩ ክፍያዎች ጋር ተጠሪ ሉከፍላቸው ሲገባ ፍቃደኛ ባለመሆኑ ውሃ እንኳን የሚገዙበት አጥተው አልጋ ላይ ሁለት ሰዎች ተሸክመው የሚያስተኟቸው እና የሚያነሷቸው መሆኑን እያወቀ ሃኪም ቤት ሳይወስዲቸው በመቅረቱ ተከሳሽ ድርጅት በአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 የተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 494/98 የስራ ስንብት ክፍያ ክፍያ ለዘገየበት የሦስት ወር ደመወዝ የጉዲት ካሳ የህክምና ወጪ ለወደፉት ህክምና ወጪ የሞራል ካሳ የተለያዩ ክፍያዎች በድምሩ 289,390 ብር ተከሳሽ ድርጅት እንዱከፈላቸው ክስ አቅርበዋል። የአሁኑ ተጠሪም በቀን 21/02/2006 ዓ/ም የተፃፈ መልስ ደግሞ ድርጅቱ አደጋ እንዲይደርስ አስፈላጊውን ጥንቃቄ የሚያስፈልጉ ቀበቶ የሰጠ እና ስልጠና በየወቅቱ እንደሰጠ ከሳሽ ተገቢውን ጥንቃቄ ሳያደርጉ ሆን ብል በራሱ ጉዲት ያደረሰ ስለሆነ ልጠየቅ አይገባም። ሃላፉነት አለ ካለ ደግሞ የጡረታ ተመዝጋቢ ስለሆኑ የተከፈለ መዋጮ ያለ ስለሆነ ተጠያቂ ሰራተኞች ጡረታ ኤጀንሲ ነው። አደጋው የደረሰው 2005 ዓ/ም ሳይሆን 2004 ዓ/ም ግንቦት 17 ቀን ነው። ጉዲት ከደረሰባቸው ቀን ጀምሮ የአንድ ዓመት ሙለ ደሞዛቸው የከፈላቸው መሆኑ የህክምና ወጪ የሸፈነ መሆኑ የዘገየ ክፍያ እንደላለ የዓመት እረፍት 24 ቀን አላቸው ግን 37 አይደለም። የህክምና ክፍያ በማስረጃ የተረጋገጠ አይደለም በማለት ክሳቸው ውድቅ ተዲርጎ በነፃ እንድሰናበት ብለዋል። ከሳሽም የመልስ መልስ የሰጡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙ ክርክር ከሰማና ማስረጃ መዝኖ አጣርቶ በከሳሽ የደረሰው ሙለ ዘላቂ የአካል ጉዲት የደረሰባቸው ተከሳሽ ሃለፉነት እንዲለበት በማረጋገጥ በድምሩ ብር 288,940 እንዱሁም የወጪና ኪሰራ ብር 500 እንዱከፈላቸው ውሳኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ በወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ቅሬታ በይግባኝ ለፉንፉኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ የግራ ቀኙ ወገኖች ክርክር ከሰማ በኃላ የወረዲ ውሳኔ አፅንቷል።
ተጠሪ አሁንም ቅሬታው ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርቦ ተቀባይነት ስላገኘ ከሰሽ መልስ እንዱሰጥበት ትዕዛዝ ተሰጥቶበት ነገር ግን በሞት ስለተለዩ ባለቤታቸው የሚሰነትታቸው አረጋግጠው ስለቀረቡ መልስ እንዱሰጡና የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዱፀናላቸው በመልሳቸው ገልፀዋል። በዚህ ሁኔታ ክርክሩ ከቀጠለ በኃላ ፍርድ ቤቱ የሟች ባለቤት ስለሆኑ ሉከፈላት የሚገባው ካሳ መሆን አለበት ወይ የሚለው ጭብጥ በመያዝ ጉዲት የደረሰባቸው መደበኛ ስራቸው እየሰሩ በዚህም አደጋ የሞቱ ስለሆነ ተጠሪ ሃላፉነት አለበት በማለት አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 110 በመጥቀስ ብቸኛ ጥገኛ ስለሆነች ለጥገኞች ከሚከፈላቸው 50% የወር ደመወዝ 600x12x5x50/100 =18,000 ብር ድርሻቸው ብቻ ነው።
ባለቤታቸው ስለሞቱ የስር ፍርድ ቤት የስራ ስንብት ክፍያ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 40 የመዘግየት ክፍያን በአንቀፅ 36 እና 38 መሰረት የእረፍት ክፍያ በአንቀፅ 77 ቀርቷል የተባለውን ደመወዝ ለወደፉቱ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ክፍያ በአንቀፅ 106 እና የሞራል ካሳን አስመልክቶ የሰጡት ውሳኔ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ እንደተደረገ ነው።
በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የተሰጠው ውሳኔ ቅሬታ ለሰበር በቀን 04/05/2007 ዓ/ም የተፃፈ አቅርበው ተቀባይነት ስለአገኛ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት በማድረግ ክርክር ተካሂዶል።
ባለቤታቸው ተተከተው ያቀረቡት አቤቱታ ባለቤቴ እየተከራከረ የነበረውን በሞት ምክንያት እንዲይቋረጥ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ.49 መሰረት ተክቼ የገባሁ ሲሆን የተጠየቀውን ወደ ጎን በመተው ማንም ተከራካሪ ባላነሳው በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.182 (2) በሚቃረን መልኩ የጥገኞች ነው በማለት የሞት ካሳ ክፍያ ላይ ፍርድ ሰጥቷል። በንብረት አስተዲዲሪነቴ ሥነ-ሥርዓቱ በሚፈቅደው መሰረት ተክቼ ነው የገበሁት ባለቤት ያልጠየቀውን ዲኝነት ጠይቄ የራሴ መብትና ጥቅም ለማስከበር አይደለም። የጥገኞች የሞት ካሳ አልነበረም የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ እንዱፀናልኝ ነበረ የጠየቅሁት በስር ፍርድ ቤት የነበረውን በመተው ክርክር ያልተከሄደበት ጉዲይ ራሱ ማንሳቱ ስህተት ነው። በማለት የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ እንዱሻር አመልክቷል።
በተጠሪ በኩል የቀረበ መልስ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.182 (2) የሚቃረን አይደለም ካመነበት ማናቸውም ላላ ማንሳት ይችላል። ጉዲት ከደረሰበት ግዜ ጀምሮ የአንድ ዓመት ደመወዝ የተከፈላቸው ስለሆነ ያልተከፈላቸው ክፍያ የለም የዘገየ ክፍያ የለም፣ የህክምና ወጪ ተሸፍኗል። የ100,000 ካሳ ክፍያ በፍ/ብ/ህ/ቁ.2116(3) መሰረት የለውም ብለን ተቃውሞ አቅርበናል። የአመልካች ባለቤት መሞቱ የክርክሩ ጭብጥ መቀየሩ ስህተት የለውም ለአመልካች የሚከፈለ ክፍያዎች ውስጥ መካተት ስለላለባቸው የሰበር ሰሚ ችልት ክፍያዎችን ውድቅ ማድረጉ በአግባቡ ነው።
በልላ በኩል ተጠሪ የመስቀለኛ ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ጥያቄያቸው በትዕዛዙ ተቀባይነት አላገኘም።
በሰበር አጣሪ እንዱመረመር የተያዘው ነጥብ በዚህ ጉዲይ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሟች ወራሾች ካለ ጠርቶ ሳያከራክር የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ለውጦ መወሰኑ ሥነ-ሥርዓታዊ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለ እና ላልች ተያያዥ ነጥቦችን ለመመርመር እንዱቀርብ የተደረገው ።
የክርክሩ አመጣጥ እና ይዘት ከላይ እንደተገለፀው ሲሆን ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ሥነሥርዓታዊ ግድፈት አለ ወይ የለም የሚለና ተያያዥ ጉዲዩች እንደሚከተለው ተመርምረዋል።
ሟች ከተጠሪ ድርጅት ሰራተኛ እንደነበረ እና መደበኛ ስራተኛው እየሰሩ እንዲለ በደረሰባቸው አደጋ ምክንያት ዘላቂ ሙለ አካል ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑ በፍሬ ነገር የማጠራት ስልጣን ባለባቸው ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ነው። ተጠሪ ለጉዲቱ ሃላፉነት እንዲለበት የተለየዩ ክፍያዎች እንደተወሰነ ነው።
ጉዲዩ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ከደረሰ በኃላ ከሳሽ የነበሩት መልስ ሳይሰጡ በመሞታቸው ነው ባለቤታቸው ተክተው በክርክሩ መልስ ሰጥተውበታል።
በክርክሩ ሂዲት እያለ ከሳሽ ወይ ተከሳሽ በሞት ብለይ የክርክሩ አካሄድ በምን አኳኃን እንደሚመራ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 48,49,50 ተመልክቷል። ፍ/ብ/ሕ/ስ/ስ/ቁ 48(1) ክርክሩ እንዱቀጥል የሚያስችለው መብት የሚያቋርጥ ከሆነ የከሳሽ ወይ የተከሳሽ መሞት ክርክሩ እንዱቆም አያደረገውም እንዱሁም አንቀፅ 49 50 የሟች መብት የሚታለፈው ከሆነ የሟች ከሳሽ ተከሳሽ ንብረት አስተዲደር ተተክቶ ክሩክሩ እንዲሚቀጥል ተደንግጓል።
ስለዚህ ከዚህ የሥነ -ሥርዓት ድንጋጌ የምንረዲው የተጀመረው ክርክር የሚቋረጠው የሚተላለፍ መብት ከላላ የሚተላለፍ ከሆነ ደግሞ ክርክሩ እንደሚቀጥል ነው ከዚህ ውጭ አዱስ ጭብጥ ተመስርቶ ክርክር ይዘት የሚለውጥበት ምክንያት የለም ክርክር የሚቀጥል ከሆነ በቀረበው ቅሬታ መሰረት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የተፈፀመ ስህተት አለ የለም የሚለው ነው መጣራት የሚኖርበት ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በአሁኑ ተጠሪ የቀረበው አቤቱታ ሀላፉነት የለብኝም የተለያዩ ክፍያዎች በአግባቡ አልተወሰነም በማለት ነው መልስ ሰጪ የነበሩት መልስ እንዱሰጥበት ትዕዛዝ በተሰጠበት ሂዲት በሞት መለየታቸው በስር ፍርድ ቤቶች የነበረው ጭብጥ ተለውጦ ጉዲዩ የጥገኞች ክስ የሚመለከት ሆኖ ተገኝቷል በማለትና የተቀሩት የተለያዩ ክፍያዎች ውድቅ በማድረግ ውስኗል ይሁን እንጂ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ቅሬታ የተነሳባቸው የተፈፀመ የህግ ስህተት አለ የለም ብል መወሰን ሲገባው ከባለ ዋና ጉዲዩ (ሟች) መብት የሚተላለፍ ወይ የማይተለለፍ መሆናቸው አረጋግጦ የሚተላለፍ መብቶች አለ ከተባለ በተጀመረው ክርክር መርምሮ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ. 48፣49፣50፣ በሚፈቅደው መሰረት ማጣራት ሲገባው በስር ፍርድ ቤት ክርክር ባልተነሳበትና ባልተካሄደበት ፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.182(2) በሚቃረን መልኩ ሰለሞት ክፍያ መሰረት አድርጎ የተሰጠ ውሳኔ ሥነ-ሥርዓቱ በሚፈቅደው ያልተከተለ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህታት የተፈፀመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ሰጥተናል።
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 05/01/2007 ዓ/ም የተሰጠ ውሳኔ በወ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 348 (1) መሰረት ሽረናል።
በጉዲዩ ከተጠሪ ላላ የሚገቡ ወራሾች ካለ በማስገበት የከፍተኛ እና ወረዲ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ ቅሬታ የቀረበበት ላይ መሰረት በማድረግ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖሩን ወይም አለመኖሩን መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.
348 (1) መሰረት ጉዲዩ ለኦሮሚያ ብ/ክ/መ/ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት እንዱመለስ ወስነናል። በዚሁ ውሳኔ እንዱፈፀም ግልባጭ ይላክለት።