በካሳ ጉዲይ ካሳ የጠየቀው ወገን ገንዘቡን በማስረጃ ባላረጋገጠበት ሁኔታ ላላኛው ተከሳሽ ወገን ዝም በማለቱ ብቻ እንዲመነ ተቆጥሮ የሚሰጥ ውሣኔ ተገቢ ያለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 83
No summary available.
ቀን 29/11/2007 ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብርሃም መሰለ አመልካቾች፡- 1ኛ. አቶ መላኩ ካሳዬ 2ኛ. አቶ ደነቀው ደሳለው 3ኛ. አቶ ጋሻው ፀሐይነው ጠበቃ አቶ አላና ፈፊ 4ኛ. አቶ ሳንጃው አየለ 5ኛ. ወ/ሮ የሮም ካሳዬ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ሱሲ አሉ ጠበቃ አቶ ኤቢሳ ሶቦቅሳ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የእርሻ መሬትን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በኦሮሚያ ክልል አመያ ወረዲ ፍ/ቤት ነው። የአሁኑ ተጠሪ በዚህ ፍ/ቤት አመልካች ላይ ያቀረቡት ክስ ይዘት ከባለቤቴ እቶ ሸለማ አንገሣ ጋር በፍቺ ምክንያት በፍ/ቤት መዝገብ ተወስኖልኝ በ6/12/2003 እጄ ገብቶ የይዞታ ምስክር ወረቀት ያለኝን 5.5 ሄክታር መሬት የማሣ ኮድ ቁ.
2020፣2022፣2025 እና 2029 የሚታወቀውን ይዞታ መሬቴን አመልካቾች በጉልበት ይዘውብኛል የማሳ ኮድ 2025 የሆነውን መሬት 2004 ለ 2005 ዓ.ም የምርት ዘመን ለራሳቸው አርሰውታል የዚህ የምርት ዘመን ውጤት 32 ኩንታል ጤፍ ብር 30,000 ከፍለውኝ መሬቱ እንዱለቁልኝ የሚል ነው።
የአሁን አመልካች በበኩላቸው ተጠሪ ክስ የመሰረተችበትን መሬት ይዛው አታውቅም የተፈጠረ ሁከት የለም የሷ አይደለም የእሷ ቢሆን የመሬቱን አዋሳኝ አልጠቀሰችም።
የምርት ውጤት መጠየቁ ስህተት ነው ከባለቤቷ በውሳኔ የተከፈላት መሬት 4.5 ሄክታር ነው ድርሻዋ 2.5 መሆኑን ውሳኔው እና አፈፃፀሙ ተመልክቶ እያለ ያቀረበችው አቤቱታ ተገቢ አይደለም ብለው ተከራክረዋል። ተጠሪ ካሳ እንድትከፍል ተደርጋ ከተራ ቁ.1-4 የተጠቀሱ አመልካቾች ቀደም ሲል ከሰጡት መልስ ጋር በተመሣሣይ መልስ ማቅረባቸው በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ተመልክቷል። 5ኛ አመልካች ወደ ክርክሩ የገቡት በጣልቃ ገብነት ተጠሪ ክሱ የመሰረቱት የጣልቃ ገብን ይዞታ በመጨመር መሆኑን ገልፀው ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ ተጠሪ የፍ/ቤቱ ውሳኔን ሽፊን በማድረግ ያልተወሰነላትንና ያልተፈፀመላት ፍ/ቤት የወሰነላት በማስመሰል እጅ ገብቶ ያላዘዘችበትን መሬት ጨምራበት ላልች ሰዎች የፈጠሩትን ሁከት አመልካቾች (የስር ተከሳሾች) እንደፈፀሙ አስመስላ ማቅረቡ ተቀባይነት የለውም የተፈጠረ ሁከት የለም በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ለደቡብ ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኃላ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት አዋሳኙን ጠቅሳ ክስ የመሰረተችበት በኮድ 0220፣2022፣2025 እና 2029 የሚታወቀው መሬት ተጠሪ ከባለቤታቸው ጋር በመ/ቁ.12615 በሆነው መዝገብ በነበራቸው ክርክር የመሬት ስፊት 4.5 ሄክታር ነው ተብል መሬቱን እኩል እንዱካፈለ ተወስኗል። ይህን ውሳኔ መሰረት በማድረግ በአፈፃፀም በ/መ/ቁ. 12837 ተጠሪ ውሳኔው እንዱፈፀምላቸው በስር ፍ/ቤቱ ጠይቀው በውሳኔው መሰረት በማስፈፀም ውጤቱን ለፍ/ቤቱ እንዱያሳውቁ በፍ/ቤቱ የታዘዙ የቀበላው አስተዲደር የሚመለከታቸው አካላት በአዋሳኝ ተጠቅሶ ውሳኔ የተሰጠበትን መሬት ለተጠሪ እና ለባለቤታቸው እኩል ለማካፈል ሲለኩት ውሳኔው ላይ እንደተመለከተው 4.5 ሄክታር መሬት ሳይሆን 11 ሄክታር መሬት መሆኑን ለፍ/ቤቱ አሳውቀው እንዱካፍለ በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት ለተጠሪ 5.5 ሄክታር መሬት አካፍለው ለክተው ለፍ/ቤቱ ሪፖርት በማድረግ የአፈፃፀሙን መዝገብ የዘጋው መሆኑን ከስር ፍ/ቤት መዝገብ እንዲረጋገጠ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ገልፆ በውሳኔ ላይ የተጠቀሰው ይዞታ መሬት አዋሳኝ እና ኮድ ቁጥሩ ባልተቀየረበት ውሳኔው ላይ ከተመለከተው ስፊት በላይ ስለሆነ በማለት የተጠሪ አቤቱታ ውድቅ መደረጉ በአግባቡ አይደለም የአሁኑ አመልካቾች የፈጠሩት ሁከት ይቁም። በማሣ ኮድ 2029 ከሆነው የተጠሪ ይዞታ መሬት ተጠሪ ያጣችውን የአንድ ዓመት ምርት ብር 30,000 ከ1-6ኛ ያለት (የስር መልስ ሰጭዎች) ይክፈለ በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሮታል።
በዚህ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሣኔ የአሁን አመልካች ቅሬታቸውን ለማሳረም ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት በይግባኝ በመቀጠልም የሰበር አቤቱታቸውም ለሰበር ሰሚው ችልት ቢያቀርቡም ከፍ/ቤቱ የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
በዚህ ውሳኔ ተፈፀመ ያለትን መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመጥቀስ እንዱታረምላቸው አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበዋል።
የአመልካቾች አቤቱታ በሰበር ሰሚ ችልት ላታይ ይገባል የተባለው ለተጠሪ የተወሰነው 2.5 ሄክታር ነው ተብል የተፈፀመው 5.5 ሄክታር ድርሻ አለኝ በሚል መነሻ ከእጁ ያልገባ ይዞታ ላይ አመልካቾች ሁከት ፈጥረዋል መባላቸውንና ካሳ እንዱከፍለ መወሰኑ ተገቢ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ነው።
ግራ ቀኙ የፅሐፍ ክርክር አድርገዋል።
ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እና ጉዲዩ በሰበር ችልት ሉመረመር ይገባል ተብል ከተያዘው ጭብጥ ጋር መርምረናል።
እንደመረመርነውም ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ይዞታ መሬት በአዋሳኝ ተጠቅሶ እና በኮድ ቁጥር ተለይቶ (ተጠቅሶ) ተጠሪ ከባለቤታቸው ጋር ቀደም ሲል በነበራቸው የጋብቻ ፍቺ ውጤት ክርክር የመሬቱ ይዘት 4.5 ሄክታር መሆኑ ተገልፆ ተጠሪ ከባለቤታቸው ጋር እኩል እንዱካፈለ በፍ/ቤት ውሳኔ አግኝቷል። ይህን ውሳኔ ተከትል ተጠሪ እንዱፈፀምላቸው የአፈፃፀም ፊይል ፍርድ ቤት አስከፍተው በውሳኔው መሰረት ለማስፈፀም የተላኩ የአስተዲደር አካላት በውሳኔ ተለይቶ የተመለከተውን መሬት ሲለኩ ስፊቱ በውሳኔው ላይ የተጠቀሰው 4.5 ሄክታር ሳይሆን 11 ሄክታር መሆኑንና ለፍ/ቤቱ ገልፀው 11 ሄክታር መሬት ለተጠሪ እና ለባለቤታቸው እኩል እንዱካፈል በተሰጠ ትዕዛዝ መሰረት ለተጠሪ 5.5 ሄክታር መሬት በድርሻ የተሰጣቸው መሆኑ ከስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተመልክቷል። በአንፃሩ የአሁን አመልካቾች ለክርክር ምክንያት የሆንው ይዞታ መሬት ሕጋዊ ይዞታ መሬታቸው መሆኑን የሚያስረዲ የተሻለ ማስረጃ አቅርበው አልተከራከሩም ለክርክር ምክንያት የሆነው መሬት በአዋሳኝ እና በኮድ ቁጥር ተለይቶ ይዞታው የተጠሪ እና የባለቤታቸው ነው እኩል ይካፈለ ተብል ውሳኔ የተሰጠ በመሆኑ ውሳኔው ላይ የተመለከተው እና እንዱፈፀም በተደረገው መሬት ላይ የይዞታ መብት አለን የሚለ ከሆነ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ ላይ በተመለከቱ አግባብነት ባላቸው ድጋጌዎች መሰረት አመልካቾች መብታቸውን ጠብቀው ሳይከራከሩ በውሳኔው ላይ የተመለከተው የመሬት ሰፊት እና በአፈፃፀም የተከፈለው የመሬት ስፊት ልዩነት አለው በሚል ያደረጉት ክርክር ተገቢነት ያለው አይደለም። አመልካች ይህን ይዞታ መሬት አልያዝንም ወይም በሕጋዊ መንገድ ያገኘነው ነው ብለው ያቀረቡት መከራከሪያም የለም።
ስለዚህ በተጠሪ ይዞታ ላይ የአሁን አመልካች ሁከት መፍጠራቸውን ገልፆ የክልለ ከፍ/ፍ/ቤት እና ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጡት ውሳኔ በአግባቡ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት የሚቻል አይደለም ብለናል፡፤
ላላው በወረዲ ፍ/ቤት ላይ በማሣ ኮድ 2025 በሚል በተጠቀሰው በከፍ/ፍ/ቤት መዝገብ ውሳኔ ላይ ደግሞ በማሣ ኮድ 2029 በሚል በተጠቀሰው ይዞታ መሬት ላይ 2004 -2005 ዓ.ም የምርት ዘመን ተጠሪ ያጡት ምርት ብር 30,000 አመልካቾች ይክፈለ ተብል የተወሰነውን በተመለከተ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 83 የካሳ ጉዲይ ካልሆነ እና ካልተካደ በስተቀር በክሱ የተጠየቀው ገንዘብ እንዱተመን ይጣራል በሚል ከተመለከተው የሕግ ድንጋጌ መረዲት የሚቻለው በካሣ ጉዲይ ላላኛው ተከራካሪ ወገን ዝም ማለቱ እንደታመነ ተቆጥሮ በካሣ ጉዲይ ላይ ውሳኔ የሚያሰጥ ባለመሆኑ የስር ፍ/ቤቶችም ይህን ሥነ-ሥርዓታዊ ድንጋጌ በማለፍ የአሁን አመልካቾች በካሳው ጉዲይ ክደው አልተከራከሩም እንዲመኑ ይቆጠራል በማለት ተጠሪው ገንዘቡን በማስረጃ ባላረጋገጡበት ሁኔታ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካቾች የተጠቀሰውን የካሳ ገንዘብ ሉከፍለ አይገባም። ብለናል።
የክልለ ከፍ/ቤት በፍ/መ/ቁ/ 32269 በቀን 8/12/2006፣ የክልለ ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ቁ. 196121 እና በመ/ቁ. 20370 በቀን 8/07/07 በዋለው ችልት የሰጡት ውሳኔ ከዚህ በላይ በተራ ቁ. 1 ከተጠቀሰው የውሳኔ ክፍል ውጭ ያለው አከራካሪው ይዞታ መሬት የአሁኑ አመልካቾች ሁከት ድርጊት ፈፅመዋል ብለው የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ሰበር ችልት በተደረገው ወጪ ግራ ቀኙ ያወጡት ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.