በወጪና ኪሳራ ጉዲይ በተሰጠ ውሳኔ ላይ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 466
No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገብረሥላሴ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ ሸምሱ ሲርጋጋ አብረሃ መሰለ አመልካች፡- አቶ ክንፈ ወልደሰንበት - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የተዘጋ ነው የተባለን መንገድ በፍርድ ኃይል ለማስከፈት ከቀረበ ክስ ጋር ተያይዞ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንደቅደም ተከተላቸው ከ1ኛ እስከ 6ኛ ተከሳሾች በነበሩት የአሁኖቹ ከ1ኛ እስከ 6ኛ ተጠሪዎች ላይ በ11/10/2004 ዓ.ም ባቀረቡት ክስ ነው።
የአሁኑ 7ኛ ተጠሪ በከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ ወደ ጉዲዩ እንዱገባ የተደረገ ተከራካሪ ወገን ነው።ከሳሽ ያቀረቡት ክስ ይዘት ባጭሩ፡-ተከሳሾቹ ከይዞታቸው ውጪ በመውጣት አስር ሜትር ስፊት ያለውን መንገድ አጥረው በመያዝ በከሳሽ ላይ ችግር መፍጠራቸውን የሚገልጽ ሆኖ በክፍለ ከተማው ፕላን መሰረት የያዙትን አስር ሜትር መንገድ እንዱለቁ ይወሰን ዘንድ ዲኝነት የተጠየቀበት ነው።ተከሳሾቹ በበኩላቸው የመንገደ ስፊት አስር ሜትር ሳይሆን ስምንት ሜትር መሆኑን እና ከሕጋዊ ይዞታቸው በመውጣት አጥር በማጠር መንገድ ያላጣበቡ መሆኑን ገልጸው ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክረዋል።ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ ውሳኔ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ይግባኙ የቀረበለት ፍርድ ቤት ውሳኔውን ሽሮ የስር ፍርድ ቤት ጉዲዩ የሚመለከተውን የአሁኑን 7ኛ ተጠሪ ወደ ክርክሩ በማስገባት በጉዲዩ ላይ ውሳኔ እንዱሰጥ በመለሰው መሰረት ጣልቃ ገቡ በ26/04/2005 ዓ.ም. በሰጠው መልስ ከሳሽ በቂ መተላለፉያ መንገድ ያላቸው መሆኑን፣በፕላኑ ላይ ያለውን መንገድ ለመስራት በቂ የሆነ ዝግጅት የሚፈልግ እና በሂደት ላይ የሚገኝ መሆኑን፣ከሳሽ አቤቱታቸውን ማቅረብ የነበረባቸው ለአስተዲደሩ መሆኑን በመግለጽ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም ጉዲዩ ከሚመለከተው የክፍለ ከተማው የአስተዲደር ክፍል ተገቢው ተጣርቶ እንዱቀርብለት ካደረገ በኃላ ተከሳሾቹ ለውስጥ ለውስጥ መንገድ የተጠናውን አስር ሜትር አጣብበው ወደ ይዞታቸው ያጠሩ መሆኑን፣ይሁን እንጂ መንገደ የተጠናው ተከሳሾቹ ቦታውን በሕጋዊ መንገድ ከያዙ በኃላ እንደሆነ እና በካርታ ተከልል ከተሰጣቸው ይዞታ ውጪ የያዙት ቦታ እንደላለ ከሚመለከተው የአስተዲደሩ አካል ተጣርቶ በተላከው ደብዲቤ የተረጋገጠ መሆኑን፣በፀደቀው የክፍለ ከተማው ፕላን መሰረት የተጠናውን መንገድ ወደ ተግባር ለመለወጥ እንደወሰን ማስከበር፣የካሳ ክፍያ እና መሰል የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወን የሚገባቸው መሆኑን፣እንደነዚህ ዓይነት ተግባራትን ደግሞ አስተዲደሩ የሚያከናውነው በራሱ ዕቅድ እና የጊዜ ሰላዲ መሰረት እንጂ በግለሰቦች አነሳሽነት አለመሆኑን ገልጾ ክሱን ውድቅ በማድረግ እና ለተከሳሾቹ የወጪና ኪሳራ ዝርዝር የማቅረብ መብት በመጠበቅ ጭማሪ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት የከተማው ፍርድ ቤቶች ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች የቀረበላቸውን እንደቅደም ተከተለ ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ ዘግተው በማሰናበታቸው ሲሆን ለዚህ ችልት የቀረበው አቤቱታ ተመርምሮ ዲኝነት የተጠየቀበት መንገድ አላግባብ መዘጋቱ ተረጋግጧል ከተባለ በኃላ ተጠሪዎቹ ሉለቁ አይገባም መባለ፣እንዱሁም አመልካች በመንገደ መዘጋት ተጎጂ መሆናቸው ከታወቀ ተጠሪዎቹ የወጪና ኪሳራ ዝርዝር እንዱያቀርቡባቸው የመወሰኑን ተገቢነት ተጠሪዎቹ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት አንድ ግዳታ እንዱፈጸምለት የሚጠይቅ ሰው ለግዳታው መኖር ማስረጃ የማቅረብ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2001 (1) እንዱሁም በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 258 እስከ 261 ድንጋጌዎች ስር ተመልክቷል።
በፍትሐብሕር ጉዲይ እያንዲንደ ተከራካሪ ወገን በክርክሩ ረቺ ላሆን የሚችለው በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት ክርክሩን ከላላኛው ተከራካሪ ወገን በተሻለ ሁኔታ አስረድቶ በተገኘ ጊዜ መሆኑም የሚታወቅ ጉዲይ ነው።በተያዘው ጉዲይ አመልካች ክስ የመሰረቱት ከ1ኛ እስከ 6ኛ ያለት ተጠሪዎች ከይዞታቸው ውጪ በመውጣት አስር ሜትር ስፊት ያለውን መንገድ አጥረው በመያዝ በከሳሽ ላይ ችግር መፍጠራቸውን በመግለጽ ነው።ይሁን እንጂ በጸደቀው የክፍለ ከተማው ማስተር ፕላን መሰረት አስር ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገደ የተጠናው ተጠሪዎቹ አሁን ይዘው የሚገኙትን ይዞታ በሕጋዊ መንገድ ከያዙ በኃላ መሆኑ እና ይዘው በሚገኙት የይዞታ መጠን ላይም በሚመለከተው አካል የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ የተሰጣቸው መሆኑ በክርክሩ ተረጋግጧል።ይህም ተጠሪዎቹ አስር ሜትር መንገደን አጥረው የያዙት ከሕጋዊ ይዞታቸው ውጪ በመውጣት ስለመሆኑ አመልካች በክሳቸው መሰረት ማስረዲት ያልቻለ መሆኑን ነው።ክስ ካስነሰው መንገድ ውጪ አመልካች በቂ የመተላለፉያ መንገድ ያላቸው መሆኑም በክርክሩ የተረጋገጠ ሲሆን አመልካች በዚህ ረገድ በሰበር አቤቱታቸው ያቀረቡት ግልጽ የማስተባበያ ክርክር የለም።በማስተር ፕላኑ መሰረት የውስጥ ለውስጥ መንገደ የጸደቀ ቢሆንም ተግባራዊ የማድረግ ስራው የስር ፍርድ ቤቶች እንደገለጹት በሚመለከተው የአስተዲደር አካል አማካይነት ዝግጅት ተደርጎበት እና አስፈላጊ የቅደመ ሁኔታ ስራዎች ከተከናወኑ በኃላ የሚፈጸም እንጂ ማስተር ፕላኑን መሰረት አድርገው ግለሰቦች የጸደቀው የውስጥ ለውሰጥ መንገድ ጉዲይ በሕግ አግባብ እንደተሰጠ በሚገመተው የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ በተረጋገጠው ሕጋዊ ይዞታቸው ውስጥ በሚገኝ ላልች ግለቦች ላይ በሚያቀርቡት የመንገድ ይከፈትልኝ ክርክር እልባት ማግኘት የሚችል ጉዲይ አይደለም።የተጠናው አስር ሜትር መንገድ በተጠሪዎቹ የተያዘ መሆኑ መረጋገጡ ደግሞ ብቻውን መንገደ ወዱያውኑ እንዱከፈት ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል አይደለም።በመሆኑም የአመልካቹን ክስ ውድቅ በማድረግ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
የወጪና ኪሳራ ጉዲይን በተመለከተ በልላ አኳኃን እንዱፈጸም በግልጽ ካልተደነገገ በቀር በክስ ምክንያት ስለሚከፈለው ስለማናቸውም ወጪና ኪሳራ የሚከፍለውን ወገን፣የወጪንና የኪሳራውን ልክ፣የሚከፈልበትን ሀብት ምንጭ፣የአከፊፈለን ሁኔታ እና ላላውንም ተገቢ መስል የታየውን ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ ፍርድ ቤቱ ትክክል መስል በሚገምተው ሁኔታ ላሰጥ የሚችል ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 462 ስር ተመልክቷል።ይህም የተከራካሪ ወገኖችን የክርክር አቋም፣የረቺ እና ተረቺ ወገኖችን ማንነት እና መሰል ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት ወጪና ኪሳራን የመወሰን ስልጣን በመሰረቱ ጉዲዩን ለሚወስነው ፍርድ ቤት የተሰጠ መሆኑን መገንዘብ የሚያስችል ነው።በወጪና ኪሳራ ጉዲይ በተሰጠ ውሳኔ ላይ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ስለመሆኑም በስነ ስርዓት ሕጉ ቁጥር 466 ስር ተመልክቷል።በተያዘው ጉዲይ አመልካች በክርክሩ ተረቺ ወገን መሆናቸው ተረጋግጧል።የተጠሪዎቹን የወጪና ኪሳራ ዝርዝር የማቅረብ መብት በመጠበቅ በስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ጭምር ተቀባይነት አግኝቷል።በመሆኑም በዚህ ረገድ በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በሕግ በተሰጣቸው ስልጣን መሰረት በአግባቡ የተሰጠ ነው ከሚባል በቀር ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ21/02/2006 ዓ.ም. ተሰጥቶ በከተማው ፍርድ ቤቶች ይግባኝ ሰሚ እና ሰበር ችልቶች እንደቅደም ተከተለ በመዝገብ በ17/04/2006 ዓ.ም. እና በመዝገብ በ27/05/2006 ዓ.ም. በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የውሳኔው ቅጂ ለስር ፍርድ ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ሰለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.