በላለሁበት የተሰጠ ውሳኔ /ትእዛዝ/ ይነሳልኝ በማለት የቀረበ አቤቱታው ውሳኔው/ትእዛዙ ከተሰጠ በ30 ቀን ውስጥ በቃለ መሀላ ለሬጅስትራር የቀረበ ሆኖ እያለ አቤቱታው ለችልት የቀረበው ከ30 ቀን በኋላ መሆኑ በህግ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ /ይርጋ/ አላሟላም ሉያስብል የማይችል ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 78/1/
No summary available.
ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- የረር ኮንስትራክሽን ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - ጠበቃ ጌታቸው ለማ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ተስፊዬ ባልቻ - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ አንድ ተከሳሽ በክርክሩ ላይ ቀርቦ መልስ ሳይሰጥ ወይም ተገቢውን መከራከሪያ ሳያቀርብ በመቅረቱ በላለበት አንድ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ በተሰጠበት ጊዜ ውሳኔው ወይም ትዕዛዙ እንዱነሳለት አቤቱታ ሉያቀርብ የሚችልበትን የጊዜ ገደብ የሚመለከት ክርክር ነው።
የጉዲዩን አመጣጥ በተመለከተ፡-ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የስራ ክርክር ችልት ተከሳሽ በነበረው የአሁን አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካች የጽሁፍ መልሱን እንዱያቀርብ በተያዘለት የ30/07/2005 ዓ.ም ቀነ ቀጠሮ መልሱን ባለማቅረቡ መልስ የመስጠት መብቱ የታለፈ መሆኑን፣ ክሱን ለመስማት አስቀድሞ በተያዘው የ17/08/2005 ዓ.ም ቀነ ቀጠሮ በአመልካች በኩል የቀረበው ሰው ተገቢ ተወካይ ባለመሆኑ ፍርድ ቤት ለመከራከር የውክልና ስልጣን የተሰጠው የአመልካች ተወካይ እንዱቀርብ ትዕዛዝ በመስጠት ለ01/09/2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን፣ በዚህ ቀነ ቀጠሮም የአመልካች ተወካይ ባለመቅረቡ ፍርድ ቤቱ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 70 (ሀ) መሰረት አመልካች በላለበት ክሱን ከሰማ በኃላ የተጠሪውን ምስክሮች ለመስማት ለ19/10/2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን፣በዚህ ቀነ ቀጠሮ የአመልካች ተወካይ አመልካች በላለበት የተሰጠበት ትዕዛዝ ተነስቶ ወደ ጉዲዩ ገብቶ ለመከራከር እንዱፈቀድለት በ30/09/2005 ዓ.ም የተጻፈ እና በሬጅስትራር ጽ/ቤት ቃለ መሀላ ስለመፈጸሙ በዚሁ ዕለት ምልክት የተደረገበትን ማመልከቻ ይዞ እንደቀረበ በችልት መመዝገቡን፣ፍርድ ቤቱም የተጠሪው ምስክሮች እንዱመለሱ አድርጎ በቃለ መሀላ አቤቱታው ላይ የተጠሪውን የጽሁፍ አስተያየት ከተቀበለ በኃላ አቤቱታውን መርምሮ አመልካች የቃለመሀላ አቤቱታውን ያዘጋጀው እና በሬጅስትራር ጽ/ቤትም ቀርቦ የመሀላ ቃል የፈጸመው በ30/09/2005 ዓ.ም ቢሆንም የቃለ መሀላ አቤቱታውን ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው ግን በ19/10/2005 ዓ.ም. መሆኑን እና ይህም ጉዲዩ አመልካቹ በላለበት እንዱታይ ትዕዛዝ ከተሰጠበት ከ01/09/2005 ዓ.ም ጀምሮ ሲቆጠር የአንድ ወር ጊዜ ያለፈው መሆኑን ገልጾ የቀረበውን የቃለመሀላ አቤቱታ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 78 (1) መሰረት በ01/11/2005 ዓ.ም በዋለው ችልት በትዕዛዝ ውድቅ በማድረግ የተጠሪውን ምስክሮች ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካች አቤቱታውን ለዚህ ችልት ያቀረበው ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የስር ፍርድ ቤት ትዕዛዝን በማጽናቱ ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ አመልካች በላለበት የተሰጠበት ትዕዛዝ እንዱነሳለት ትዕዛዙ በተሰጠ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አላመለከተም ተብል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ትዕዛዝ በሬጅስትራሩ ፉት የተመዘገበውን ማስረጃ መሰረት ያደረገ መሆን አለመሆኑን ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታው የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ እና ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመባቸው መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት አንድ ተከሳሽ በክርክሩ ላይ ቀርቦ መልስ ሳይሰጥ ወይም ተገቢውን መከራከሪያ ሳያቀርብ በመቅረቱ በላለበት አንድ ውሳኔ ወይም ትእዛዝ የተሰጠ ሲሆን ውሳኔው ወይም ትእዛዙ መሰጠቱን በተረዲው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ትዕዛዙ ወይም ውሳኔው እንዱነሳለት ሉያመለክት እንደሚችል በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 78 (1) ስር ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዲይ ጉዲዩ አመልካች በላለበት እንዱታይ ትዕዛዝ የተሰጠው በ01/09/2005 ዓ.ም ሲሆን አመልካቹ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ የተሰጠበት ትዕዛዝ እንዱነሳለት የቃለ መሀላ አቤቱታ ያዘጋጀውም ሆነ በሬጅስትራር ጽ/ቤት ቀርቦ በተወካዩ አማካይነት የመሀላ ቃል የፈጸመው በ30/09/2005 ዓ.ም መሆኑ የተረጋገጠ እና የስር ፍርድ ቤትም የተቀበለው ጉዲይ ነው። ፍርድ ቤቱ ጥያቄው በቁጥር 78 (1) ድንጋጌ መሰረት በአንድ ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ የቀረበ አይደለም ከሚል ድምዲሜ ላይ የደረሰው አመልካች አቤቱታውን ያዘጋጀውም ሆነ በሬጅስትራር ጽ/ቤት ቀርቦ በተወካዩ አማካይነት የመሀላ ቃል የፈጸመው በ30/09/2005 ዓ.ም ቢሆንም አቤቱታውን ለፍርድ ቤቱ (ለችልቱ) ያቀረበው ግን በ19/10/2005 ዓ.ም መሆኑን እና ከአንድ ወር የጊዜ ገደብ በኃላ የቀረበው አቤቱታ ሉስተናገድ የማይገባው መሆኑን በመግለጽ ነው። አመልካች በበኩለ የሚከራከረው በአቤቱታው ላይ በ30/09/2005 ዓ.ም በሬጅስትራር ጽ/ቤት ቀርቦ በተወካዩ አማካይነት መሀላ ከፈጸመ እና ቀኑን ጭምር የሚገልጽ ምልክት ካስደረገበት በኃላ የቃለ መሀላ አቤቱታውን ለችልቱ ያቀረበው በዚያኑ ዕለት መሆኑን እና የችልቱ ዲኛ የቃለ መሀላ አቤቱታውን ከተቀበለ እና ከመሩበት በኃላ በዕለቱ ስራ በዝቶባቸው ስለነበረ በ19/10/2005 ዓ.ም.
ለሆነው ቀጠሮ እንዱቀርቡ ነግረው ያሰናበቷቸው መሆኑን በመግለጽ ነው።የቃለ መሀላ አቤቱታው ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ ለችልት እንዱቀርብ በቃለ መሀላ አቤቱታው ላይ በዲኛው በጽሁፍ የተመራበት እና የተፈረመበት መሆኑን እና የተመራበትን ቀን ግን ያልተገለጸበት መሆኑን አመልካች አቅርቦ በአጣሪው ችልት ካያያዘው የቃለመሀላው ቅጂ እና ቀርቦ በተያያዘው ዋናው መዝገብ ውስጥ ከሚገኘው የቃለመሀላው ቅጂ መገንዘብ ተችሎል።በመሰረቱ እያከራከረ ያለው የቃለ መሀላ አቤቱታው ለችልት የቀረበው መቼ ነው? የሚለው የጊዜ ጉዲይ ሲሆን የችልቱ ዲኛ የቃለመሀላ አቤቱታውን ተቀብለው ከመዝገቡ ጋር ተያይዞ እንዱቀርብ የመሩበትን ቀን በመሩበት ጽሁፍ ላይ ካልገለጹ ቃለመሀላው ለችልቱ ዲኛ የቀረበው በ19/10/2005 ዓ.ም መሆኑን ማረጋገጥ የሚቻልበት አግባብ አይኖርም። ይልቁንም አመልካች የቃለመሀላ አቤቱታውን በሬጅስትራር ጽ/ቤት ቀርቦ መሀላ የፈጸመው በ30/09/2005 ዓ.ም መሆኑ የተረጋገጠ እስከሆነ ድረስ አመልካች የቃለመሀላ አቤቱታውን ለችልቱ አቅርቧል ተብል ሉወሰድ የሚገባው ቀን ግንቦት 30 ቀን 2005 ዓ.ም ነው። ጉዲዩ አመልካች በላለበት እንዱታይ ትዕዛዝ የተሰጠው በ01/09/2005 ዓ.ም ሲሆን አመልካቹ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ የተሰጠበት ትዕዛዝ እንዱነሳለት የቃለ መሀላ አቤቱታውን ያዘጋጀውም ሆነ በሬጅስትራር ጽ/ቤት ቀርቦ በተወካዩ አማካይነት የመሀላ ቃል የፈጸመው እና ለችልቱም ያቀረበው በ30/09/2005 ዓ.ም. መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ አቤቱታው የቀረበው በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 78 (1) ስር የተመለከተው የአንድ ወር ጊዜ ከማለፈ በፉት በመሆኑ አመልካች አቤቱታውን ያቀረበው የጊዜ ገደቡ ካለፈ በኃላ ነው ልባል የሚችል ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ21/09/2006 ዓ.ም.
በውሳኔ የጸናው ትዕዛዝ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሮአል።
አመልካች የቃለ መሀላ አቤቱታውን ያቀረበው በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 78 (1) ስር የተመለከተው የአንድ ወር ጊዜ ከማለፈ በፉት ነው በማለት ወስነናል።
አመልካች በክርክሩ ሉሰማ በተያዘው ቀጠሮ ቀርቦ መከራከሪያውን ያላሰማው ወይም መልስ ያልሰጠው በቂ በሆነ ምክንያት መሆን አለመሆኑን በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 78 (2) መሰረት መርምሮ ተገቢውን ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዱመለስ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 341 (1) መሰረት ወስነናል።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ በውሳኔው መሰረት ተገቢውን መፈጸም ያስችለው ዘንድ ለፈዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣እንዱያውቀው ደግሞ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.