ለአንድ የመንግስት ተቋም የተላከ መጥሪያ መጥሪያው በአግባቡ ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፉዎች ካልደረሰ በስተቀር መጥሪያው ለተቋሙ መዝገብ ቤት ገቢ በመሆኑ ብቻ መጥሪያው እንደደረሰ ተቆጥሮ ክርክሩ ተቋሙ በላለበት ላታይ የማይገባ አቶ አዲነ መንገሻ እና የጋሪ ማዘጋጃ ቤት VII የፍ/ሥ/ህ/ቁ 70/ሀ/፣78/2/፣96፣102
No summary available.
ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወላ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ አዲነ መንገሻ ቀረቡ ተጠሪ፡- የጋዘር ማዘጋጃ ቤት ተወካይ ዓ/ሕግ አሰግድ አድማሱ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት የተመለከተ ሲሆን የተጀመረው በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ ደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ይግባኝ ባይ ተጠሪ መልስ ሰጪ በመሆን ተከራክረዋል። አመልካች በቀረበው የሰበር አቤቱታ የሥር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪ በላለበት የተሰጠው ፍርድ ተነስቶ ወደ ክርክር እንዱገባ የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በሚል ያቀረበው ቅሬታ አጣርቶ ለመወሰን የቀረበ ጉዲይ ነው።
ለዚህ አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የንብረት ግምት የተመለከተ ሲሆን አመልካች የጋዘር ማዘጋጃ ቤት ባለሙያ ባልሆነ ግለሰብ የአትክልት ግምት ብር 14,772 መወሰኑ በሕጉ አግባብ ባለመሆኑ ለደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረቡ የሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ ያመለክታል። የሥር ፍርድ ቤትም የአመልካች ይግባኝ ያስቀርባል ያለው በመሆኑ ለተጠሪ መጥሪያ ልከዋል። ፍርድ ቤቱ በመ/ በ09/05/2005 ዓ.ም በተፃፈ የላከው መጥሪያ ለተጠሪ ጽ/ቤት መዝገብ ቤት ገቢ የተደረገ ሲሆን የመዝገብ ቤቱ ሰራተኛ የሆኑት ወ/ሮ ዘውዱቱ ፀጋዬ ፈርመው እንደተቀበለት እንዱሁም መተማመኛ ሰጥተው ከፍ/ቤቱ መዝገብ ተያይዟል። የሥር ፍርድ ቤትም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.70 /ሀ/ መሰረት ተጠሪ በላለበት ጉዲዩን የተመለከተው ሲሆን በባለሙያ ተሰራ የተባለው ግምት ውድቅ በማድረግ ተጠሪ ብር 128,700.00 ከወጪና ኪሳራ ጭምር እንዱከፍል ወስኗል።
አመልካች በክርክር ሂደት አወጣሁት ያለውን ወጪና ኪሳራ እንዱከፈለው ጉዲዩን ለወሰነው ፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። የአሁኑ ተጠሪ የመከላከያ መልሱ እንዱያቀርብ መጥሪያ የተላከለት ሲሆን በ25/06/2005 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ እንዱነሳላቸው አቤቱታ አቅርበው አመልካችም መልስ ሰጥቷል። የአሁኑ ተጠሪ ባቀረቡት አቤቱታ የጽ/ቤቱ ኃላፉ ለሥልጠና ሄደው እንደነበር፤
የኃላፉ ተወካዩም ቀበላዎች ለማስፊፊት ሥራ የሄደ በመሆኑ በላለበት የተሰጠው ፍርደ ሉነሳ እንደሚገባ ተከራክሯል። አመልካች በበኩላቸው ለተጠሪ ጽ/ቤት መዝገብ ቤት ገቢ የሆነውን መጥሪያ በጽ/ቤቱ የመዝገብ ቤት ሰራተኛ ተፈርሞ መተማመኛ የተሰጣቸው በመሆኑ ተጠሪ በላለበት የተሰጠው ፍርድ የሚነሳበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብሎል።
የሥር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ አንድ ተከሳሽ በላለበት የተሰጠው ፍርድ ሉነሳ የሚችለው በቂ ምክንያት መኖሩን ሲረጋገጥ ነው። የተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፉ ባይኖርም ላላ ሰው ተወክል መከራከር ይችል ነበር። የተጠሪ ጽ/ቤት የመዝገብ ቤት ሰራተኛ የሆኑት ወ/ሮ ዘውዱቱ ፀጋዬ መጥሪያው በ10/05/2005 ፈርመው ከተቀበለ በኋላ ፈቃድ የወጡት በ13/05/2005 ዓ.ም ነው። ጽ/ቤቱ ለሰራተኛዋ የዓመት ፈቃድ ስትወጣ ተተኪ ሰራተኛ መኖሩን ሳያረጋግጥ ፈቃድ እንደማይሰጥ ግልጽ ነው። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የሚያሳምን በቂ ምክንያት አልቀረበም በማለት የተጠሪ አቤቱታ ውድቅ በማድረግ ብይን ሰጥቷል።
የአሁኑ ተጠሪ የሥር ፍርድ ቤት ብይን በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙ ካከራከረ በኋላ መጥሪያው ለጋዘር ማዘጋጃ ቤት መዝገብ ቤት ገቢ መደረጉን አልተካደም። ጉዲዩ ተቋማዊ ይዘት ያለው በመሆኑ የጽ/ቤቱ ሰራተኛ የተቀበለችው ቢሆንም ለጽ/ቤቱ የሥራ ኃላፉ መጥሪያው አልደረሰም። መጥሪያው የተቀበለችው ሰራተኛ በልከር ውስጥ የቆለፈችው እና ለላልች ሰራተኞች ወይም የበላይ አመራር ካላደረሰች መ/ቤቱ በቸልተኝነት ወይም ህግን በመናቅ ትተዋል ለማለት አልተቻለም። የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩን በጥልቀት መርምሮ አስፈላጊ ከሆነ ተጠሪ በቂና ተመጣጣኝ ኪሳራ እንዱከፈል ተደርጎ ወደ ክርክር ሉገባ ይገባ ነበር። ተጠሪ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78/2/ መሰረት ወደ ክርክር ለመግባት ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ መደረጉ ተቀባይነት የለውም በማለት ሽሮታል። አመልካች የሥር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም። ይህ አቤቱታ የቀረበውም የሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ በመሆኑ ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት ቀርቦ የበኩለን መልስ አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘት፡- ከፍርድ ቤት ወጭ የተደረገው መጥሪያ ለተጠሪ ጽ/ቤት መድረሱ፤ በጽ/ቤቱ ማህተም የተረጋገጠ መተማመኛ አቅርቦ ሳለ ፍርድ ተሽሮ ተጠሪ ወደ ክርክር እንዱገባ መደረጉ አግባብነት የለውም የሚል ሲሆን በተጠሪ በኩል የቀረበው መልስ ዋና ፍሬ ነገሩ፡- ከፍ/ቤት የላከው መጥሪያ ለሚመለከተው ኃላፉ አለመድረሱ፤ ፍርድ ቤቱም ጉዲዩን ለመመልከት ሥልጣን እንዲልነበረው፤ መጥሪያው የሥነ ሥርዓት ሕጉ በደነገገው አግባብ አለመድረሱን መሰረት ተደርጎ ውሳኔው መሻሩ በሕጉ አግባብ ነው ሉጸና ይገባል የሚል መሆኑን ተረድተናል። የአመልካች የመልስ መልስም አቤቱታውን የሚደግፍ ነው።
ከሥር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በጽሐፍ ያደረጉት ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማዛመድ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመርነውም የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍ/ቤት የተላከው መጥሪያ ለተጠሪ በሕጉ አግባብ አልደረሰውም በማለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሻሩ በፍ/ሥ/ሥ/ሕጉ ስለመጥሪያ አደራረስ የተመለከቱት መሰረታዊ ድንጋጌዎች ያገናዘበ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የፍ/ቤት መጥሪያ ለተጠሪ ጽ/ቤት ገቢ መሆኑ የተካደ ጉዲይ አይደለም። ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክርክር መጥሪያው ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፉዎች እንዱቀርብ አልተደረገም። የሥራ ኃላፉዎቹ መጥሪያ መድረሱን ሳያውቁ ቀጠሮ አክብረው አልቀረቡም ልባል አይቻልም የሚል ክርክር አቅርበዋል። አመልካች መጥሪያ ማድረሱና ስለመድረሱም በተጠሪ ጽ/ቤት ክብ ማህተም የተረጋገጠ መተማመኛ ለፍ/ቤት ማቅረቡ መሰረት በማድረግ በላለበት የተሰጠው ፍርድ ለመሻር የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት የለም የሚል ክርክር ስለማቅረቡ ከሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ግልባጭ መረዲት ይቻላል። በመሰረቱ አንድ ተከሳሽ የፍርድ ቤት መጥሪያ ተልኮለት መጥሪያውም በአግባቡ ስለመድረሱ ሲረጋገጥ ጉዲዩ በላለበት የሚታይና የሚወሰን ስለመሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 70/ሀ/ ሥር ተመልክቷል። የፍ/ቤት መጥሪያ ለሚመለከተው ተከራካሪ ወገን የሚሰጥበት ሥርዓትም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 96 እና 102 ሥር ተደንግጓል። በልላ በኩል ከፍ/ቤት የተላከው መጥሪያ በሕጉ አግባብ ለሚመለከተው ተከራካሪ ወገን ካልደረሰ በላለበት የተሰጠው ውሳኔ የሚነሳበት ስርዓት መኖሩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 78/2/ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ነው። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ለጽ/ቤት መጥሪያ መድረሱ በማመን ነገር ግን መጥሪያው ተቀበለ የተባለት የመዝገብ ቤት ሰራተኛ መጥሪያ ስለመቀበላቸው ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፉዎች ባለማቅረባቸው ምክንያት ቀርበው ለመከራከር አለመቻላቸውን በመግለጽ ተከራክሯል። በሥር ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጡ ኩነቶች /facts/ የተጠሪ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፉዎች ትዕዛዙን ገቢ በሆነበት ጊዜ በልላ ቦታ ስልጠና እና ሥራ የነበሩ መሆኑን ነው። ከዚህ በተጨማሪ አመልካች መጥሪያው ለጽ/ቤቱ መዝገብ ቤት ገቢ አድርገው መተማመኛ ከመውሰዲቸው በቀር መጥሪያ ለመቀበል አግባብ ላለው ሰው መጥሪያውን ስለማደረሳቸው ያቀረቡት ክርክር የለም። የሥር ፍርድ ቤት በፍርድ ሐተታው እንደገለጸው መጥሪያውን የተቀበለችው ዘውዱቱ ፀጋዬ የተባለችው የተጠሪ መሥሪያ ቤት ሰራተኛ መሆኗ ከመገለጹ ውጭ ነገረ ፈጅ ወይም መዝገብ ቤት ሹም መሆኗ አልተረጋገጠም። ከሥር ፍርድ ቤት የውሳኔ ግልባጭ እንደተረዲነው መጥሪያው አግባብነት ያለው ሰራተኛ ተቀብልት ለመሥሪያ ቤቱ የሥራ ኃላፉዎች መቅረቡን የተረጋገጠ አለመሆኑን ነው። ከፍርድ ቤት የተላከው መጥሪያ ለሚመለከተው ተከራካሪ ወገን በሕጉ በተዘረጋው የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት መደረሱን ካልተረጋገጠ በስተቀር በላለበት የተሰጠው ፍርድ እንዱነሳ ተደርጎ መሰረታዊ የሆነውን መከራከር መብቱ ሉጠበቅለት ይገባል። የክ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ለተጠሪ የተላከው መጥሪያ በአግባቡ አልደረሰም በማለት የደረሰበት ድምዲሜው እና ለድምዲሜው መነሻ የሆኑ ፍሬ ነገሮች በማጣራት እና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣኑ መሰረት ያደረገ በመሆኑ በዚህ ችልት በድጋሜ የሚመረመርበት ሥርዓት አይኖርም። ምክንያቱም ሰበር ሰሚ ችልቱ በሕግ ተለይቶ የተሰጠው ሥልጣን መሰረታዊ የህግ አተረጓጏም ስህተት የተፈጸመባቸው የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ ጉዲዮች ብቻ መርምሮ መወሰን ስለመሆኑ ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 80/3//ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ነው። በመሆኑም የሥር የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመሻር ተጠሪ ወደ ክርክሩ እንዱገባ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈጸሙን አያሳይም። በዚህ ሁለ ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍረድ ቤት የደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ውሳኔ በመሻር የሰጠው ፍርድ እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ትዕዛዝ ጸንቷል።
ተጠሪ በላለበት የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ወደ ክርክር እንዱገባ መወሰኑ በሕጉ አግባብ ነው በማለት ወስነናል።
የዚህ ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.