በመርህ ደረጃ በህግ አግባብ የተቋቋመ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በህግ አግባብ በተቋቋመ የበላይ ፍ/ቤት በህጉ በተዘረጋው ስርዓት እስካልተለወጠ ድረስ የማይፈጸምበት ምክንያት የላለ ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 378፣372፣392
No summary available.
መጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ፀጋዬ ብርሃኑ - ወኪል ይርጋ ብርሃኔ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ መሰረት ተገኝ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የፍትሐብሕር ጉዲይ ፍርድ እና አፈጻጸሙን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ለአፈጻጸሙ መሰረት የሆነው ውሳኔ የተሰጠው ደግሞ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 128082 ነው። በዚህ መዝገብ የተሰጠው የውሳኔ ይዘት ዋናው ክርክር የጀመረው በአሁኑ አመልካች ከሳሽነት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚሁ ፍርድ ቤት የአመልካች ክስና የዲኝነት ይዘቱ በአራዲ ክፍለ ከተማ ወረዲ 5 የቤት ቁጥር 166 የሆነ የመንግስት ቤት ከአሁኗ ተጠሪ ተከራይተው ሲሰሩበት የነበረ መሆኑ በመመሪያው መሰረት ክፍለ ከተማው አምኖበት የኪራይ ውል በስማቸው አዙሮ ካበቃ በኋላ ቤቱን እንድትለቅ በማለት ሁከት የፈጠረባቸው መሆኑን ዘርዝረው ሁከቱ እንዱወገድላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት የጠየቁ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን ክሱን መጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤቱም የአራዲ ክፍለ ከተማውን በተከሳሽነት ፣ የአሁኗን ተጠሪ ደግሞ በጣልቃ ገብነት አከራክሮ ጉዲዩን መርምሮ ጣልቃ ገብ በመመሪያው መሰረት ልዩ ተጠቃሚ መሆናቸውን የማስረዲት ሸክም ያለባቸው መሆኑን፣ ይህን የሚያረጋግጥ ከሚመለከተው ህጋዊ ተቋም የተሰጠ ማስረጃ ስላላቀረቡ ቤቱንም የእድሳት ፈቃድ አውጥተው በማደስ እየሰሩ እያለ ለጣልቃ ገብ ይገባል በማለት ተረጋግተው እንዲይሰሩ ማድረጉ ሁከት ተግባር በመሆኑ ሁከቱ ሉቆም ይገባል በማለት የወሰነ ሲሆን በዚህ ውሳኔ የአሁኗ ተጠሪና ክፍለ ከተማው ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ጉዲዩን በመ/ በሆኑት የአሁኑን አመልካች በመልስ ሰጪነት ሰይሞ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ሙለ በሙለ ሽሮ ተፈጻሚነት ባለው የውሳኔው ክፍል በአራዲ ክፍለ ከተማ ወረዲ 5 የቤት ቁጥር 166 የሆነውን ክርክር የተነሳበትን ቤት ለወ/ሮ መሰረት ተገኝ ይመለስላቸው፣የተፈጠረ ሁከት የለም በማለት ወስኗል።
ይህንኑ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በመያዝና የፍርድ ባለመብት በመሆን የአሁኑ ተጠሪ በመ/ በሆነው አፈፃፀሙን የቀጠለ ሲሆን የአሁኑ አመልካችም በፍርድ ባለእዲነታቸው ቀርበው ፍርደን እንዱፈፅሙ ተጠይቀው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሉፈጸም አይችልም በማለት መዝገቡን የዘጋበትን ማስረጃ አፈጻጸሙን ለያዘው ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱን የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በችልቱ አፈጻጸሙ አይቀጥልም በማለት የገለፀ መሆኑ አፈጻጸሙን አያግድም በማለት በመ/ የተሰጠው ውሳኔ እንዱፈጸም ለአፈጻጸም መምሪያ ውሳኔውን በማያያዝ ትዕዛዙን አስተላልፍአል። በዚህ ትዕዛዝ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የሰጠው ውሳኔ የስር ፍርድ ቤት ያለ ስልጣኑ ሁከት ነው ተብል የተሰጠ ነው የሚል ሆኖ እያለ የሚፈጸም ውሳኔ አለ ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ በመደረጉ ተጠሪ ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ፍርድ ያረፈበት ንብረት ማዕድ ቤት እንጂ ስድስት ክፍል ቤቶች፣ ባህር ዛፍችና ጽድ ያለበት ቦታ አይደለም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
በመሰረቱ አንድ ፍርድ መፈፀም ያለበት እንደ ፍርደ መሆኑን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 ድንጋጌ መረዲት የምንችለው ጉዲይ ሲሆን ደረጃውን ጠብቆ በቀረበው የአፈፃፀም ጉዲይ ላይ በአፈፃፀሙ ምክንያት የሆነውን የፍርድ ይዘት አድማስ በማስፊት ወይም በማጥበብ ፍርድን ለማስፈፀም የሚያስችል የህግ አግባብ የላለ መሆኑን ስለፍትሐብሕር ጉዲይ አፈጻጸም ከተደነገጉትና የፍትሐብሕር ስነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ጉዲይ ነው። በአንድ የፍትሐብሕር ጉዲይ ፍርድ የሚሰጠው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 182 እና 183 በተደነገገው አግባብ ሲሆን በዚህ አኳኃን የተሰጠን ፍርድ በማስፈፀም ረገድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 378 እና 372 መሰረት ሥልጣን ያላቸው የአፈፃፀም ችልቶች ስለ ፍርድ አፈፃፀም የተዘረጉትን ሥርዓቶችን በመከተል እንደ ፍርደ ከመፈፀም በቀር የአንድ ፍርድ ይዘትን በመመልከት የፍርደን ይዘት አድማስ በማጥበብም ሆን በማስፊት ረገድ ፍርድን የመተርጎም ሥልጣን ያልተሰጣቸው መሆኑም ግልፅ ነው። ድንጋጌዎች በግልፅ የሚያስገነዝቡት አቢይ ነጥብ የፍርድ አፈፃፀም ስርዓት ፍርድ ቤት የሰጠው ፍርድ በእራሱ አማካኝነት ወደ ተግባር ወይም ውጤት የሚለውጥበት ሥርዓት መሆኑን ነው። በልላ አገላለፅ የድንጋጌዎች አቀራረፅ፣ ይዘትና መንፈስ በጥንቃቄ ሲታይም የፍርድ አፈጻጸም ስለፍርድ አፈጻፀም የተደነገጉትን ድንጋጌዎች በመከተል ፍርድን በተግባር መተርጎም እንደመሆኑ መጠን የአፈጻጸም ሥርዓቱ ህጉን መሰረት ማድረግ ያለበትና የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉን መሰረታዊ ዓላማ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በአነስተኛ ወጪ፣ጊዜና ጉልበት በተፊጠነና ፍትሒዊ በሆነ መንገድ እንዱፈፀም በሚያስችል አግባብ ሕግ አውጪ ያስቀመጣቸው መሆኑን የምንረዲው ጉዲይ ነው።
በመሆኑም በሕግ አግባብ የተቋቋመ ፍርድ ቤት አከራክሮ መወሰን ብቻ ሳይሆን የወሰነው ውሳኔ ውጤት ባለው መልኩ ወደ ተግባር መለወጡን ጭምር ማረጋገጥ አቢይ ሐላፉነትና ተግባሩ በመሆኑ ይህንኑ በሕግ የተሰጠውን ስልጣን ተግባራዊ ሲያደርግ ግን ሕጉንና ሕጉን ብቻ መሰረት ማድረግ አለበት። የአፈጻጸም ጉዲይ ደግሞ የሚመራበትን አግባብ ሕጉ ዘርግቷል። በሕጉ ከተዘረጉት ስርዓቶች አንደ ደግሞ አፈጻጸሙ ሉመራ የሚገባው እንደዋናው ፍርድና ተገቢ ሁኖ ሲገኝም ፍርደን ለማስፈፀም በሚያስችል አግባብ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና 392 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝቡን ጉዲይ ነው።
ስለሆነም በሕግ አግባብ የተቋቋመ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በሕጉ አግባብ በተቋቋመ የበላይ ፍርድ ቤት በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት እስካልተለወጠ ድረስ የማይፈፀምበት አግባብ የለም። ከላይ እንደተጠቀሰው በመርህ ደረጃ የተሰጡት የፍርድ ቤት ውሣኔዎች እንደፍርደ ተፈፃሚነት እንዱያገኙ ማድረግ ህጉ የግድ የሚለው ጉዲይ ሲሆን አልፍ አልፍ ሉፈፀም የማይቻል ፍርድ ሉኖር እንደሚቻል ከፍታሐብሓር ሥነ ሥርዓት ህጋችን መገንዘብ ይቻላል።
እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ሲያጋጥም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 392(1) መሰረት አፈፃፀሙን የያዘው ፍርድ ቤት ሉፈፀም የሚቻል ውሣኔ ስለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ ማረጋገጥ እንዲለበት ያመለክታል። ፍርደ የማይፈፀምበት ህጋዊ ምክንያት ካለ ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.392(2) መሰረት ይሄንኑ በማመልከት ሉፈፀም የማይቻል ስለመሆኑ ትዕዛዝ መስጠት እንደሚቻል ያስገነዝባል።
ከዚህ አንጻር የተያዘው ጉዲይ ስንመለከት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የነበረው ዋና ክርክር በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሁከት ይወገድ ተብል ከተወሰነ በኃላ ጉዲዩ በይግባኝ ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርድ ቤቱም ጉዲዩን በመ/ በሆኑት የአሁኑን አመልካች በመልስ ሰጪነት፣ የአሁኗን ተጠሪ እና ክፍለ ከተማውን ደግሞ በይግባኝ ባይነት ሰይሞ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኃላ ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ሙለ በሙለ ሽሮ ተፈፃሚነት ባለው የውሳኔው ክፍል ደግሞ በአራዲ ክፍለ ከተማ 5 የቤት ቁጥር 166 የሆነውን ክርክር የተነሳበት ቤት ለወ/ሮ መሰረት ተገኝ ይመለስላቸው፣ የተፈጠረ ሁከት የለም በማለት በግልጽ ወስኗል ። ይህ ውሳኔ በግለጽ የሚያሳየው ቤቱ ለተጠሪ እንዱመለስላቸው እንጂ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ያለስልጣኑ የታየ ነው በሚል የተደመደመ ያለመሆኑን ነው። ውሳኔው በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት ስለመለወጡ በአመልካችም በኩል የቀረበ ክርክር የለም እንዱሁም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ራሱ አፈጻጸሙን የማይመራ መሆኑን ጠቅሶ አመልካችን ከማሰናበቱ በስተቀር በመ/ የሰጠው ውሳኔ የማይፈፀም መሆኑን ገልፆ አፈጻጸሙን ማቆሙን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አለማቅረቡን የክርክሩ ሂደት በግልጽ ያሳይል ። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ትዕዛዝ ለአፈጻጸም መነሻ ከሆነውና በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ከተሰጠው ዋና ውሳኔ ይዘት እና ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 378 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ጋር የተጣጣመ ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም ። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 04 ቀን 2006 ዓ/ም በተሰጠው ትዕዛዝ የፀናው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንቷል።
ተጠሪ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ሉፈጸምላቸው ይገባል ተብል አፈጻጸሙ ለአፈፃጸም መምሪያ መመራቱ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ሰኔ 02 ቀን 2006 ዓ/ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ለሚመለከታቸው አካላት ይፃፍ ብለናል።
No topics extracted.