አንድ ተከራካሪ ወገን ላላ ተከራካሪ ግለሰብ ወደ ክርክር እንዱገባ በህጉ አግባብ መጠየቁ ተገቢ ቢሆንም ጉዲዩ መታየት ያለበት ከግለሰቡ መብት አንፃር ብቻ ሳይሆን ከፍትሐ ብሓር ሥነ- ሥርዓት ህጉ ዓላማና ግብ አንፃር ጭምር እነ አቶ ተስፊዬ ወርቁ /ሁለት ሰዎች/ እና እነ ወ/ሮ የምስራች ገ/መስቀል /አራት ሰዎች/
No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዝያ 16 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካቾች፡- 1ኛ አቶ ተስፊዬ ወርቁ ጠበቃ በረከት ቡሽራ - ቀረቡ 2ኛ ተስፊሽ ሪል እስቴት ኃ/የተ- የግል ማህበር ተጠሪዎች፡- 1ኛ ወ/ሮ የምስራች ገ/መስቀል 2ኛ ሰመረ ባህሩ ወ/ሩፊኤል - ቀረቡ 3ኛ መቅደስ ባህሩ ወ/ሩፊኤል 4ኛ ህፃን በረከት ባህሩ ወ/ሩፊኤል መዝገቡ መርምራን ተከተዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ ጉዲይ በሰበር ሰሚ ችልት ሉመረመር ይገባል ተብል የተያዘው ጭብጥ አንደኛ አመልካች በተከሰሱበት በንብረት ላይ ደረሰ በተባለው ጉዲይ ካሣ ጥያቄ ግንባታውን ፈፅመዋል የተባለው ብራይት የኮንስትራክሽን ድርጅት የክርክሩ ተካፊይ ላሆን ይገባ ነበር በማለት ያቀረቡት ጥያቄ የመታለፈ አግባብነት ከፍ/ህ/ቁ. 2136 አንፃር ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካቾች ተከሳሾች ተጠሪዎች ደግሞ ከሳሾች ነበሩ። ጉዲዩም በመኖሪያ ቤት ላይ በደረሰው ጉዲት ቤቱን በድጋሜ ለመገንባት የሚያስፈልግ የገንዘብ መጠን የተመለከተ ክርክር ነው። የአሁኑ ተጠሪዎች በሥር የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ ዋና ይዘቱ፡- በየካ ክፍለ ከተማ ቀበላ 09 የቀድሞ ወረዲ 17 ቀበላ 21 የቤት ቁጥር 711/2 የሆነ በካርታ በሟች አቶ ባህሩ ወ/ሩፊኤል ስም የተመዘገበው እና 1ኛ ተጠሪ የሟች ሚስት እንደሆኑ ከ2-3 ያለት ደግሞ የሟች ወራሾች መሆናቸው በመ/ቁ. 854/93 እና 206/93 ያረጋገጡበት ቤት የተከሳሾች ይዞታ ከከሳሾች ይዞታ ጋር ወሰንተኛ /ኩታ ገጠም/ በመሆኑ ተከሳሾች በቦታቸው ላይ ህንፃ ለመሥራት ላደረጉት ቁፊሮ መሬቱ ተንድ የከሳሾች ቤት መሰረቱ በመጋለጡ ያለድጋፍ በመንጠልጠለ እና ቤቱ ስለተሰነጣጠቀ ቤቱ ከመደርመሱ በፉት ተከሳሾች በራሳቸው የቀጠሩት አማካሪ መሃንድስ ባቀረበው ሐሳብ መሰረት ችግሩ ወደ ባሰ ደረጃ ሳይደርስ የመከላከያ ዕርምጃ እንዱወሰደ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የዱዛይንና ግንባታ ልማት ቢሮ አሳውቋል። ተከሳሾች በመሃንዱስ የቀረበው ምክረ ሐሳብ ባለመሥራታቸው ቤቱ መደርመሱ፣ ሳልኑ ደግሞ ያለድጋፍ መንጠልጠለ በአጠቃላይ ቤቱ ከጥቅም ውጭ በመሆኑ ከሳሾች ቤቱን መልቀቃቸው፤ የአዱስ አበባ አስተዲደር የዱዛይንና ግንባታ ልማት ቢሮ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በመጀመሪያ የድጋፍ ግንቡን ከሰሩ በኃላ ቀጥል የከሳሾች ቤት እንዱሰሩ የተሰጣቸው ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ አላደረጉም። በወንጀል ያቀረቡት ክስም ተቀባይነት አላገኘም። የፈረሰውን ቤት መልሶ ለመሥራት ብር 764,154.20 /ሰባት መቶ ስልሳ አራት ሺ አንድ መቶ ሃምሳ አራት ከሃያ ሳንቲም/ እንደሚያስፈልግ በቦታው ተገኝቶ ኢትዮ አማካሪ አርክቴክቶችና መሐዱሶች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለ ገለልተኛ ድርጅት ስለአረጋገጠ ይህንኑ ገንዘብ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ሕጋዊ ወለድ ጋር ተከሳሾች እንዱከፍለ እንዱወሰንላቸው ከሳሾች ቤቱ ተሰርቶ እስከሚገቡ በየወሩ ብር 8,000 የቤት ኪራይ እንዱወሰንላቸው ወጪና ኪሳራ የጠበቃ አበል ጭምር መጠየቃቸው የሚያሳይ ነው።
ተከሳሾች የመጀመሪያ ደረጃ መቃሚያ፤ በፍሬ ጉዲዩ መልስ እና የተከሳሽ ከሳሽነት ይዘው ቀርበዋል። የመጀመሪያው መቃወሚያ ሥራውን የሚሰራው ብራይት ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ ማህበር በመሆኑ በክሱ ገብቶ እንዱከራከር የሚል ሲሆን በፍሬ ጉዲዩ ከሳሾች ክስ ያቀረቡት ቤቱን አንገዛም ስላልናቸው ከቅን ልቦና ውጭ በለቀቁት ጎርፍ መሆኑን፣ የወንጀል ክስም ማቅረባቸው ተጠሪዎች ከቤቱ ውስጥ እየኖሩ ነው። በአካባቢው የተመሳሳይ ቤት ኪራይ ከ1000-2000 ብር ብቻ ነው። በተከሳሽ ከሳሽነት ቤቱ ለአደጋ የተጋለጠው ከሳሽ በለቀቁት ፈሳሽ መሆኑን በከሳሽ በተፈፀመው ድርጊት ምክንያት የቤቱ መሰረት ሲፈርስ አንድ ሰራተኛ መሞቱ፣ መከላከያ ግንብ ለመገንባት፤ ለድንጋይ ለጠጠር፣ ለአናጢ፣ ሚስማር በድምሩ 200,000 እንዱከፍለ እንዱወሰንባቸው የተከሳሽ ከሳሽነት አቅርበዋል።
ከሳሾች ለቀረበው የተከሳሽ ከሳሽነት መልስ ያቀረቡ ሲሆን የከሳሾች ቤት ሙለ በሙለ ከጥቅም ውጪ መሆኑ በባለሙያ መረጋገጡ፤ ጉዲት የደረሰውም በተከሳሾች ጥፊት መሆኑን የወንጀል ክስም ውድቅ መደረጉ ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም የግራቀኙ የቃል ክርክር አዲምጧል። ተገቢ ነው ያለውን ጭብጥ (ቤቱ በማን ጥፊት ፈረሰ? ተከሳሾች ኃላፉ ሉሆኑ ይገባል? ኃላፉነት አለባቸው ከተባለ መጠኑ ምን ያክል ነው?) በመመስረት የግራ ቀኙ ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ ቤቱ ሉፈርስ የቻለው የተከሳሾች የግንባታ ሥራውን ለማከናወን ባደረጉት ቁፊሮ በፍ/ህ/ቁ.1210 የተጣለባቸው ግዳታ ወደ ጎን በመተው እና አስፈላጊ ጥንቃቄ ባለማድረጋቸው በፈጸሙት ጥፊት እንደሆነ ፍ/ቤቱ መገንዘቡን፤
ተከሳሾች ቤቱን ሉፈርስ የቻለው በአንደኛ ከሳሽ ጥፊት ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። የተከሳሽ ከሳሽነትን በተመለከተም ተከሳሾች ወጪ አውጥተው የድጋፍ ግንብ መሥራታቸውን ገልፀዋል ይህ የሚያመለክተው ደግሞ የከሳሽ ተከሳሾች ቤቱ ለአደጋ የተጋለጠው እነሱ በፈጸሙት ጥፊት መሆኑን እምነው መቀበላቸው ነው። በዚህ አግባብ የፈጸሙት ክፍያ የመጠየቅ መብት የላቸውም። ቤቱ መልሶ ለመሥራት የሚያስፈልገው ወጪ ብር 764,154.20 መሆኑን ኢትዮ አማካሪ አርክቴክቶችና መሐንዱሶች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተባለ ገለልተኛ አካል ገምቶ አቅርበዋል። የግምቱ መጠን የተጋነነ ነው የሚለው መከራከሪያ በብይን ውድቅ ተደርጓል። በመሆኑም በገለልተኛ አካል ተገምቶ የቀረበው ብር 764,154.20 ይክፈለ በማለት ወስኗል። የቤት ኪራይ በተመለከተ በራሳቸው ቤት ስለሚኖሩ አልተቀበለውም ።
የአሁኑ አመልካቾች ይህንን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም። ፍርድ ቤቱ ቤቱ የፈረሰው በአመልካቾች ጥፊት መሆኑ የክርክሩ ተካፊይ ላሆን ይገባ ነበር የተባለው የስራ ተቋራጭ ከሰው ከሚጠይቁ በስተቀር አሁን ጉዲዩን ወደ ሥር ፍ/ቤት የሚመለስበት የህግ ምክንያት እንደላለ፣ የካሳ መጠኑም በገለልተኛ ባለሙያ ተገምቶ የቀረበ ነው የሚነቀፍ አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ አጽንቷል። የአሁኑ አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይህንን ውሳኔ ለማስለወጥ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል።
ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ይቅረብ በመባለ ግራ ቀኙ በጽሐፍ ተከራክሯል። አመልካቾች በሰበር አቤቱታቸው ካነሱዋቸው መሰረታዊ ነጥቦች፡- ህንፃው ገና ያልተገነባ በመሆኑ የኃላፉነት መሰረቱ በአግባቡ ያልታየ መሆኑን፤ የስራ ተቋራጩ ጣልቃ እንዱገባ የቀረበው ጥያቄ መታለፈ ተገቢ አለመሆኑን፤ የካሳው አወሳሰን ሥርዓትና መጠን አወሳሰን የተጋነነ ስለመሆኑ የሚገልጽ ነው።
ተጠሪዎች የበኩላቸውን መልስ አቅርበዋል ። ዋና ፍሬ ነገሩ ቤቱ እየተገነባ ያለው በአመልካቾች መሆኑን ቤቱን በሙለ ለመገንባት ግዳታ ገብቷል። ቤቱ የፈረሰው በቁፊሮ ላይ ነው የህንፃ ተቋራጩ መሥራቱን አያሳይም። የተከሳሽነት ከሳሽ ያቀረቡት በራሳቸው ስለሚሰሩት ነው።
በአስተዲደሩ የድጋፍ ግንብ እንዱሰሩ ታዘው ነበር። የወንጀል ክስም ውድቅ ተደርጓል። የካሳው ዘዳና መጠን አሁን ቤት ለመሥራት የሚያስፈልገውን ወጭ ታሳቢ ያደረገ ነው። ቤቱ ለመሥራት ግዳታ ገብቷል የሚል ነው። የአመልካች የመልስ መልስም የሰበር አቤቱታቸው የሚያጠናክር ነው።
ከሥር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክር፤ ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማዛመድ እንዱሁም ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ብቻ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል። እንደመረመርነውም ግራ ቀኙ እያከራከረ ያለው የጉዲት ካሳ ጥያቄ በተመለከተ ግንባታ ለማከናወን የሥራ ተቋራጭ የነበረው ብራይት ኮንትራክሽን የክርክሩ ተካፊይ ላሆን ይገባ ነበር የሚል ክርክር በአመልካች ቀርቧል። ተጠሪ በበኩላቸው አመልካቾች ግንባታው በራሳቸው የሚያከናውኑት በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤትም ጉዲዩን አጣርቶ በመወሰኑ አመልካች መክሰሳችን በአግባቡ ነው የሚል ክርክር አቅርበዋል።
ከሥር ፍርድ ቤት የክርክር ሂደት ለመረዲት አንደተቻለው አመልካቾች የተጠሪዎች ቤት ላይ የመከለከያ ግንብ እንዱገነቡ፤ ጉዲት ከደረሰ በኃላም ቤቱን ሙለ በሙለ እንዱገነቡ በአዱስ አበባ አስተዲደር ዱዛይንና ግንባታ ልማት ቢሮ መታዘዛቸው፤ አመልካቾችም ቤቱን ለመገንባት ግዳታ መግባታቸው የተካደ ጉዲይ አይደለም። የሥር ፍርድ ቤቶች ፍሬ ነገር በማጣራት እና ማስረጃ በመመዘን ሥልጣናቸው የተጠሪዎች ቤት ሉፈርስ የቻለው በአመልካቾች ጥፊት ስለመሆኑ አረጋግጠዋል። የሥር ፍርድ ቤቶች የፍሬ ነገር ማጣራት እና ማስረጃ ምዘና ውጤት ይህ ሰበር ሰሚ ችልት እንዲለ የሚቀበለው ነው። ምክንያቱም የሰበር ሰሚ ችልቱ በሕግ ተለይቶ የተሰጠው ሥልጣን የመጨረሻ ውሳኔ በተሰጠባቸው ጉዲዮች መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመ መሆን ያለመሆኑን መመርመር ብቻ ስለመሆኑ ከሕገ መንግስቱ አንቀጽ 80(3)(ሀ) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ነው። ከላይ እንደተመለከተው የሥር ፍርድ ቤቶች ከሁለቱም ለጉዲዩ ኃላፉ ማን ነው? የሚለው በሥር ፍርድ ቤት ከተደረገው ክርክር እና የቀረበው ማስረጃ መሰረት በማድረግ አመልካቾች ቤቱን በማፍረስ ረገድ ጥፊት መፈጸማቸው ከድምዲሜ ላይ ደርሰዋል። የአሁኑ ተጠሪዎችም ቤቱን አፍርሰዋል ባለት ግለሰብ ላይ ክስ አቅርበው ፍርድ ቤቱም የግራቀኙ ክርክር ማስረጃ በመመዘን ኃላፉ መሆናቸው ካረጋገጠ ግንባታው ለመሥራት ውል ገባ የተባለው የስራ ተቋራጭ የክርክሩ ተካፊይ ካልሆነ ልንጠይቅ አይገባም የሚለው ክርክር ተገቢነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። የአሁኑ አመልካቾች ድርጊት የተፈጸመው በሥራ ተቋራጭ ነው የሚለ ከሆነም ለተጠሪዎች ተገቢ ተብል የተወሰነው ካሣ ከፍለው በሥራ ተቋራጩ ላይ ክስ ለማቅረብ የሚከለከለበት የህግ ምክንያት አይኖርም።
የአመልካቾች የስራ ተቋራጭ የክርክሩ ተካፊይ ይሁን ጥያቄ በፋዳራል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ ተደርጓል። የጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍርድ ሐተታው ጉዲዩ አሁን ባለበት ደረጃ ወደ ሥር ፍ/ቤት መመለሱ ተገቢነት እንደላለው ገልጸዋል። አንድ ተከራካሪ ወገን ላላ ተከራከሪ ግለሰብ ወደ ክርክሩ እንዱገባ በሕጉ አግባብ መጠየቁ ተገቢ ቢሆንም ጉዲዩ መታየት ያለበት ከግለሰቡ መብት አንጻር ብቻ ሳይሆን ከፍትሐብሄር ስነሥርዓት ሕግ ዓላማ ግብ ጭምር ነው።
የፍትሐብሄር ሥነ ሥርዓት ሕግ ዓላማና ግብ የፍትሐብሕር ጉዲዮች ፍትሐዊ ኢኮኖሚያዊ ቀልጣፊ በሆነ ሁኔታ ውሳኔ እንዱያገኙ/ economic and efficient resolution of dies puts/ ማድረግ ስለመሆኑ ከአጠቃላይ የህጉ ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ነው። በተያዘው ጉዲይ በተጠሪዎች የቀረበው የቤታችን ፈረሰብን ጥያቄ እንደገና በሥር ፍርድ ቤት ክርክር ቀርቦ እንዱወሰን ማድረግ ጉዲዮች ከበቂ ጊዜ በላይ እንዱጓተቱ በማድረግ በተከራካሪዎች ጊዜ፤ ወጪና ጉልበት ከፍተኛ ጉዲት ማድረስ ይሆናል። በልላ በኩል አመልካቾች የሥራ ተቀራጩን ለመጠየቅ የሚከለክል የህግ አግባብ በላለበት ሁኔታ ጉዲዩን በአዱስ ክርክር እንዱመራ መጠየቅ ከላይ የተመለከተው የፍትሐብሕር ህግ ዓለማና ግብ የሚያሳካ ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤቶች የአመልካቾች የሥራ ተቋራጭ የክርክሩ ተካፊይ ይሁንልን ጥያቄ ውድቅ ማደረጋቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት መፈፀማቸውን የሚያሳይ ሆኖ አልተገኘም። በዚህ መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 88156 በ30/03/2006 ዓ/ም የሰጠው ፍርድ ጸንቷል።
አመልካቾች የተጠሪዎች ቤት መልሶ ለመሥራት የሚያሰፈልገውን ብር 764,154.20 ውሳኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ገንዘብ ተከፍል እስካለቀ ድረስ ከሚታሰብ 9% ህጋዊ ወለድ ጋር በአንድነትና በነጠላ ይክፈለ መባለ በአግባቡ ነው በማለት ወስነናል።
የዚህ ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ ግራቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
በዚህ ፍ/ቤት የካቲት 12 ቀን 2006 ዓ/ም የተሰጠው የዕግድ ትእዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.