ለክርክሩ መነሻ የሆኑ እና በተከሳሽ እጅ የሚገኙ ንብረቶች እንዲይሸጡ፣ እንዲይለወጡና በማንኛውም መንገድ ለ3ኛ ወገን እንዲይተላለፍ በታገደበት ሁኔታና ተከሳሽ በንብረቶች ላይ ጉዲት እንደሚያደርስ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ተከሳሽን ተጨማሪ ዋስ አቅርብ ማለት አግባብነት የላለውና የስነ ስርዓት ህጉን ዓላማ ያላገናዘበ ስለመሆኑ፣ የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 151
No summary available.
ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፣- አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመስል አመልካች፡- ቴራ ኮንስትራክሽን ባለቤቱ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሚካኤል ነገሰ ደበበ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዮን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዮ በክርክር ባለው ጉዲይ ዋስ እንዱጠራ በተሰጠው ትዕዛዝ ተገቢነት የተመለከተ ነው። በሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ በመሆን እየተከራከሩ ነው። አመልካች በሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለክርክሩ መነሻ በሆኑ ማሽነሪዎች ሉያደርሰው ይችላል የተባለውን ጉዲት ለመከላከል ወይም ለማካካስ የብር 8 ሚሉዮን ዋስ እንዱጠራ የተሰጠው ትዕዛዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ የሚል አቤቱታ በማቅረቡ ምክንያት የዚህ ትዕዛዝ ሕጋዊነት ለመመርመር የቀረበ ጉዲይ ነው።
የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ ክፍለ ያሰፈረው ፍሬ ነገር ግራ ቀኙ እያከራከሩ ያለትን ማሽነሪዎች በአሁኑ ወቅት ሙለ በሙለ በአመልካች ይዞት ሥር ያለ ናቸው። ምንአልባት ተጠሪ እንደሰጋው የማሽነሪዎቹ የተለያዩ ወሳኝ አካላቶች ቢፈታቱ ወይም ከጥቅም ውጪ ቢሆኑ በእርግጥም በተጠሪ ላይ ከፍ ያለና የማይተካ ጉዲት ሉደርስ የሚችል በመሆኑ ማሽነሪዎችን በተመለከተ አመልካች ለብር 8 ሚሉዮን /ስምንት ሚሉዮን/ የሚበቃ ዋስ እንዱጠራ ወይም ገንዘቡን በሞዳል 85 እንዱያሲዝ ማዘዙን ያሳያል። የሥር ፍርድ ቤት ከዚህ በተጨማሪ ለክርክሩ መነሻ የሆኑ ማሽነሪዎች እንዲይሸጡ እንዲይለወጡ እንዱሁም በማናቸውም መንገድ ለላላ 3ኛ ወገን ሳይተላለፈ ታግደው እንዱቆዩ መታዘዙን የሥር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካች የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትዕዛዝ በመቃወም ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበው ይግባኝ ቅሬታ ተቀባይነት አላገኘም። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ትዕዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካችም የሰበር አቤቱታው መሰረታዊ ይዘት ማሽነሪዎቹ በታገደበት ሁኔታ ተጨማሪ ዋስትና እንዱጠራ መደረጉ ተደራራቢ ዋስትና መሆኑ፣ የተጠቀሰው ገንዘብ ማስያዝ እንደማይችል የጠቅላይ ፍርድ ቤት በትዕዛዝ ይግባኝ የለም በማለት ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ሉታረም ይገባል የሚል ነው። ተጠሪ ጥሪ ተደርጏለት ቀርቦ በሰጠው መልስ አመልካች ዋስ እንዱጠራ መታዘዙ ሉደርስ የሚችለው ጉዲት ለመከላከል አስፈላጊ መሆኑ፣ ገንዘብ የሚያስያዝ በቂ ሀብት ያለው ስለመሆኑ ትዕዛዙ ሉጸና የገባል በማለት ተከራክረዋል። የአመልካች የመልስ መልስ በዋናነት አቤቱታውን የሚያጠናክር ቢሆንም በሰበር ከተያዘው ጭብጥ በዘለለ በፍሬ ነገር ክርክር ሲነሱ የሚገባቸው ነጥቦች ያካተተ በመሆኑ ታልፎል።
ከሥር የጉዲይ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመላኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በጽሁፍ ያደረጉት ክርክር በሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ትዕዛዝ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር ለማዛመድ እንዱሁም ጉዲዮ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ጉዲዮን እንደሚከተለው መርምሮታል።
እንደመረመርነውም አመልካች ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ አጥብቆ የሚከራከረው ማሽነሪዎች ባለበት ሁኔታ በፍ/ቤት ትዕዛዝ የታገደ በመሆኑ በድጋሚ ዋስ እንዱጠሩ ወይም ገንዘቡ በሞዳል 85 እንዱያሲዝ መታዘዙ ድርብ ዋስትና እንዱጠራ የሚያስገድድ ትዕዛዝ መሆኑን ይገልፃል።
ተጠሪ በአንፃሩ ለክርክሩ መነሻ የሆኑትን ማሽነሪዎች በአመልካች እጅ የሚገኙ በመሆናቸው በመጨረሻ ረቺ መሆኑ በፍ/ቤት ቢወሰን ጉዲዩን ለማስፈፀም የሚያስችል ሀብት ከላለ የተጠሪ ክርክር መና የሚያስቀር በመሆኑ የፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ተገቢ መሆኑን ይከራከራል።
በመሰረቱ ከፍርድ በፉት ንብረት የሚከበርበት ወይም ዋስ የሚጠራበት ሥርዓት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
151 እና ተከታይ ድንጋጌዎች የተቀመጠ ሲሆን ተፈላጊው ዕቃ ወይም ንብረት ለማቅረብ የሚሰጠው ዋስትና ከተከሳሽ ድርጊት ጋር የተያያዙ ሁኔታዎች መፈፀማቸው ሲረጋገጥ ነው።
በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.151/1/ እንደተመለከተው ተከሳሽ /አመልካች/ ክሱን ለማሰናከል ማቀድ ወይም የተሰጠው ትዕዛዝ እንዲይፈፀም ዘዳ መፍጠሩ የሚመለከት በቃለ ማህላ የተደገፈ አቤቱታ ከቀረበ ፍ/ቤቱም በድንጋጌው የተዘረዘሩትን መሰረታዊ ነጥቦች አንደኛው አመልካች ንብረቱ በሙለ ወይም በከፉል ለማሸሽ ወይም ለማባከን ማቀደን ፣ሁለተኛ ከፍ/ቤቱ የዲኝነት ክልል ንብረቱ ለማሸሽ ማቀደን ሲረዲ ትዕዛዝ መስጠት እንደሚችል ተደንግጓል። በተያዘው ጉዲይ ለክርክሩ መነሻ የሆኑ ማሽነሪዎች እንዲይሸጡ፣ እንዲይለወጡ፣ እንዱሁም በማንኛውም መንገድ ለላላ 3ኛ ወገን እንዲይተላለፈ ታግደው እንዱቆዮ ክርክሩ እየተመለከተ ያለው ፍ/ቤት አዟል። የአሁኑ ተጠሪ በአመልካች እጅ ያለውን ንብረት ከማሳገድ በተጨማሪ ዋስ እንዱጠራ የተጠየቀበት ምክንያት ምንአልባት አመልካች የማሽነሪዎቹ የተለያዩ ወሳኝ አካላቶች ቢፈታቱ ወይም ከጥቅም ውጭ ቢሆኑ የሚል ስጋት በመኖሩ ነው። የሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተጠሪ የተነሳው ግምታዊ ስጋት ወደ እውነታ የተጠጋ ስለ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጠው ስለመሆኑ የሰጠው ትዕዛዝ አያሳይም። ለክርክሩ መነሻ የሆኑት ማሽነሪዎች በማናቸውም ሁኔታ ለ3ኛ ወገን እንዲይተላለፈ በታገደበት ሁኔታ ወይም ንብረቱ በተከበረበት ሁኔታ በተጠሪ ላይ ተጨማሪ ኪሳራ እንደሚደርስ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ አመልካች የብር ስምንት ሚሉዮን ዋስ እንዱጠራ ወይም በሞዳል 85 እንዱያሲዝ ማዘዙ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 151 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዘትና ዓላማ ያገናዘበ አይደለም ብለናል። በዚህ ሁለ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ዋስ እንዱጠራ የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ አተገባበር ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ተከታዮን ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ቁ. 138130 ጥር 22 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ/ይ/መ/ቁ.99240 መጋቢት 29 ቀን 2006 ዓ.ም የስምንት ሚሉዮን ዋስትና በተመለከተ የሰጠው ትዕዛዝ ክፍል ተሽሮአል።
አመልካች የብር ስምንት ሚሉዮን ዋስ እንዱጠራ ወይም በሞዳል 85 እንዱያሲይዝ አይገደድም ብለን ወስናል። ይፃፍ።
የሥር ፍርድ ቤት በላልች ጉዲዮች የሰጠው ትዕዛዝ አልተነካም።
የዚህ ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ ወደ መ/ቤት ይመለስ። በዚህ ፍ/ቤት የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
No topics extracted.