አንድን ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከት ፍርድ ቤት በቀረበለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ላይ አግባብነት ያላቸው ምስክሮች ሳይሰሙ ወይም አግባብነት ያላቸው ሰነድች ሳይቀርቡ በመቃወሚያው ላይ ውሳኔ መስጠት የማይቻል በሚሆን ጊዜ ፍ/ቤቱ እነዚህ ማስረጃዎች እንዱቀርቡለት ትእዛዝ መስጠት የሚችል ስለመሆኑ፡የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244(1) እና 245(1) VI
No summary available.
መጋቢት 15 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ደበሬ ቡልቲ - ተወካይ ታከለ ደበሬ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዲንሹቴ ዋጋሪ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዲዩ በጋራ የእርሻ ይዞታ ላይ የተደረገ ውል የይፍረስልኝ ጥያቄን መሰረት አድርጎ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም ከሳሽ የነበሩት የአሁኗ ተጠሪ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን በወንጪ ወረዲ ፍርድ ቤት 1ኛ ተከሳሽ በነበሩት እና የዚህ ሰበር ክርክር ተካፊይ ባልተደረጉት ባለቤታቸው እና 2ኛ ተከሳሽ በነበሩት በአሁኑ አመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው። በ07/10/2005 ዓ.ም አዘጋጅተው ያቀረቡት ክስ ይዘትም ባጭሩ፡-በወንጪ ወረዲ በደጎዬ ጋለይ ቀበላ ውስጥ የሚገኘው እና አዋሳኞቹ በክሱ የተጠቀሰው ሁለት ጥማድ መሬት የከሳሽ እና የባለቤታቸው የ1ኛ ተከሳሽ የጋራ ይዞታ ሆኖ እያለ ከከሳሽ እውቅና ውጪ ተከሳሾቹ በ21/01/2004 ዓ.ም.የከሳሽን መብት የሚጋፊ የመሬት ቅያሪ ውል ማድረጋቸውን የሚገልጽ ሆኖ ውለ ፈራሽ ነው ተብል ውሳኔ እንዱሰጥላቸው ዲኝነት የተጠየቀበት ሲሆን 1ኛ ተከሳሽ በክሱ መሰረት ቢወሰን ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን በመግለጽ መልስ ሰጥተዋል።2ኛ ተከሳሽ በበኩላቸው በ25/10/2005 ዓ.ም.
በተጻፈ መልስ በተከሳሾቹ መካከል በ21/01/2004 ዓ.ም የተደረገው ውል የድንበር ግጭት ማስወገጃ ስምምነት እንጂ የመሬት ቅያሪ ውል አለመሆኑን፣ ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር የመሬት ቅያሪ ያደረጉት በ1994 ዓ.ም መሆኑን፣2ኛ ተከሳሽ በቅያሪ ባገኙት መሬት ላይ አንድ የሳር ቤት የሰሩበት እና በርካታ አትክልት ያለሙበት መሆኑን፣1ኛ ተከሳሽም በቅያሪ ባገኙት መሬት ላይ አንድ የሳር ቤት የሰሩበት መሆኑን እና የመሬት ቅያሪው ከተደረገ ከአስራ አንድ ዓመታት በኃላ የቀረበው ክስ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤቱም ክሱን እና በ21/01/2004 ዓ.ም በተደረገው ውል ላይ የነበሩትን ሶስት ምስክሮች አስቀርቦ ከሰማ በኃላ የ1ኛ ተከሳሽ ባለቤት ከሆኑት ከከሳሽ ስምምነት ውጪ ሁለቱ ተከሳሾች በ21/01/2004 ዓ.ም ያደረጉት ውል ሕጋዊ አለመሆኑን ገልጾ ለክሱ ምክንያት የሆነውን ሁለት ቀርጥ መሬት ከሳሽ ይጠቀሙበት በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት 2ኛ ተከሳሽ ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የስር ከሳሽ ክሱን ያቀረቡት ለክሱ መነሻ የሆነው የመሬት ለውጥ ውል መደረጉን ካወቁ ስድስት ወር ካለፈው በኃላ መሆኑን ገልጾ የወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔን በመሻር ክሱ በስድስት ወር ይርጋ የሚታገድ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።የስር ከሳሽ በዚህ የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውሳኔ ባለመስማማት በተራቸው ያቀረቡትን ይግባኝ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዘግቶ ያሰናበተው ሲሆን ጉዲዩን በመጨረሻ የተመለከተው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ችልት በበኩለ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የስር ተከሳሾች ሁለት ጥማድ መሬት የተቀያየሩ መሆኑ እና የመሬት ቅያሪ ውለ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1723 “ም” ሆነ በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 መሰረት ስልጣን ባለው አካል ያልተመዘገበ መሆኑ በግራ ቀኙ ያልተካደ መሆኑን፣የስር ከሳሽ በ21/01/2004 ዓ.ም. የተደረገውን ውል ካወቁበት ጊዜ ጀምሮ ክስ እስካቀረቡበት ቀን ድረስ ስድስት ወር ያለፈው ስለመሆኑ የስር 2ኛ ተከሳሽ ያቀረቡት ማስረጃ አለመኖሩን፣የመሬት ቅያሪ ውል የይፍረስልኝ ክስ በይርጋ ቀሪ የሚሆንበትን የይርጋ ዘመን የሚያመለክት በክልለ የቤተሰብ ሕግም ሆነ በክልለ የገጠር መሬት አስተዲደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 130/1999 እና ደንብ ቁጥር 151/2005 ውስጥ የተካተተ ድንጋጌ አለመኖሩን ገልጾ የሁለቱን የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመሻር እና በአንጻሩ የወረዲ ፍርድ ቤት ውሳኔን በማጽናት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችልት ያቀረቡት ይዘቱ ከላይ የተመለከተው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዲይ የክልለ ሰበር ችልት ክሱ በይርጋ አይታገድም በማለት የሁለቱን ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ከሻረ በኃላ በፍሬ ጉዲዩ ረገድ በአሁኑ አመልካች የቀረበውን ክርክር አጣርቶ ይወስን ዘንድ ጉዲዩን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሳይመልስ በፍሬ ጉዲዩ ረገድ ጭምር ውሳኔ የመስጠቱን አግባብነት ከፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 341 ድንጋጌ አንጻር ተጠሪዋ ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በክርክሩ እልባት ማግኘት የሚገባው የስር ፍርድ ቤቶች በአንድ ወይም በልላ አግባብ ውሳኔ የሰጡት ለጉዲዩ አወሳሰን አስፈላጊ የሆኑ ፍሬ ነገሮች በአግባቡ እንዱጣሩ ካደረጉ በኃላ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ነጥብ መሆኑን በመገንዘብ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከዚሁ ጭብጥ አንጻር መርምረናል።
በዚህም መሰረት ተጠሪዋ በወረዲው ፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡት ባለቤታቸው 1ኛ ተከሳሽ ከአመልካቿ እውቅና ውጪ ከአሁኑ አመልካች ጋር ያደረጉት የሁለት ጥማድ የእርሻ መሬት ቅያሪ ውል በፍርድ ኃይል እንዱፈርስላቸው በመጠየቅ ሲሆን አመልካች በበኩላቸው ከይርጋ መቃወሚያ በተጨማሪ መሬቱን የተለዋወጡት በ1994 ዓ.ም መሆኑን፣ በ2004 ዓ.ም የተደረገው የድንበር ስምምነት እንጂ የመሬት ቅያሪ ውል አለመሆኑን፣ሁለቱም ወገኖች በ1994 ዓ.ም በተደረገው ለውጥ መሰረት በእጃቸው በገባው መሬት ላይ የሳር ቤት መስራታቸውን እና አመልካች በተጨማሪም በመሬቱ ላይ ቋሚ አትክልቶችን ማልማታቸውን በመግለጽ ተከራክረዋል።በልላ በኩል በ21/01/2004 ዓ.ም በተደረገው ውል ላይ የነበሩት ምስክሮች ውለ የመሬት ቅያሪ ውል መሆኑን እና የተደረገውም በአንድ ጥማድ መሬት ላይ መሆኑን በመግለጽ የመሰከሩ ሲሆን የወረዲው ፍርድ ቤት ውሳኔ የሰጠው ደግሞ ተጠሪዋ በሁለቱ ጥማድ እንዱጠቀሙ በማለት ከመሆኑም በላይ የተጠሪዋ ባለቤት በቅያሪ አግኝተዋል ስለተባለው መሬት በውሳኔው ላይ ያሰፈረው ነገር አለመኖሩን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።የመሬት ቅያሪው የተደረገው በ1994 ዓ.ም ስለመሆኑ እና ከዚህ ጊዜ ጀምሮ መሬቱ የሚገኘው በአመልካች እጅ ስለመሆኑ የወረዲው መሬት አስተዲደር እና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በቁጥር WLBEN/525/06 በ25/02/2006 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዲቤ የገለጸ ስለመሆኑ አመልካች በሰበር አቤቱታቸው ላይ የገለጹትን ፍሬ ነገር ተጠሪዋ በመልሳቸው በዝምታ ከማለፍ በቀር ማስተባበያ ያልሰጡበት ከመሆኑም በላይ የወረዲው መሬት አስተዲደር እና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ቁጥሩ እና ቀኑ ከላይ በተጠቀሰው ደብዲቤ ሰጠ ስለተባለው መግለጫ ሁለም የስር ፍርድ ቤቶች በውሳኔያቸው ላይ የገለጹት ነገር የለም።
በመሰረቱ ማንኛውም ፍርድ ቤት ባለጉዲዮችን ማከራከር የሚገባው የተለያዩበት የሕግ ወይም የፍሬ ነገር አግባብ ምን እንደሆነ አረጋግጦ ለጉዲዩ ትክክለኛ ጭብጥ በመያዝ ስለመሆኑ፣የነገር ጭብጥ የሚመሰረተው አንደኛው ተከራካሪ ወገን ያመነውን የሕግ ወይም የነገር አግባብ ላላኛው ተከራካሪ ወገን በማስተባበል የካደ በሆነ ጊዜ ስለመሆኑ፣ፍርድ ቤቱ ጭብጥን ለመመስረት የሚችለውም ከግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር እና ማስረጃ እንዱሁም በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 241 መሰረት በሚደረግ ምርመራ በተከራካካሪ ወገኖች የሚሰጠውን መልስ መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ የጭብጥ አመሰራረትን በሚደነግጉ ከቁጥር 246 እስከ 248 በተመለከቱት የስነ ስርዓት ሕጉ ድንገጌዎች እንዱሁም ፍርድ ቤቱ ውሳኔ በሚሰጥበት ጊዜ በክርክሩ የተያዘው ጭብጥ ምን እንደሆነ እና ጭብጡ በአንድ ወይም በልላ አግባብ የተወሰነበትን ምክንያት በውሳኔው ላይ መግለጽ ያለበት ስለመሆኑ የፍርድ አጻጻፍን በሚመለከተው በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 182(1) ስር በአስገዲጅነት ተደንግጎ ይገኛል።
በልላ በኩል ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የሚመለከተው ፍርድ ቤት ማስረጃ ተቀብል ከመመርመሩ ወይም ምስክሮችን ከመስማቱ አስቀድሞ በመጀመሪያ ደረጃ የመቃወሚያ ነጥቦች ላይ ውሳኔ መስጠት ያለበት ቢሆንም ለመቃወሚያ ክርክሩ አወሳሰን አግባብነት ያላቸው ምስክሮች ሳይሰሙ እና አግባብነት ያላቸው ሰነድች ሳይቀርቡ በመቃወሚያው ላይ ውሳኔ ለመስጠት የማይቻል በሆነ ጊዜ ግን ፍርድ ቤቱ በመቃወሚያ ነጥቦች ላይ ውሳኔ ከመስጠቱ በፉት ተገቢ መስል የሚገምተው ማስረጃ እንዱቀርብለት ትዕዛዝ የሚሰጥ ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 244(1) እና 245(1) ድንጋጌዎች ያመለክታለ።በተያዘው ጉዲይም አግባብነት ያለውን የይርጋ ዘመን ከመለየት በተጨማሪ ይርጋው መቆጠር የሚጀምርበትን ጊዜ ለይቶ ለማወቅ የሚቻለው የመሬት ለውጡ የተደረገው መቼ ነው? የሚለው የክርክር ነጥብ በማስረጃ ተጣርቶ ከታወቀ በኃላ ነው።የክልለ ሰበር ችልት ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት በሁለቱ የስር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን ውሳኔ ያልተቀበለው ከሆነም ውሳኔውን ሽሮ በፍሬ ጉዲይ ረገድ የቀረበለትን ይግባኝ መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩን ለደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መመለስ የሚገባው ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 341 ድንጋጌ የሚያመለክት ሆኖ እያለ አመልካች በፍሬ ጉዲይ ክርክሩ ረገድ ያላቸውን የይግባኝ መብት በሚያጣብብ ሁኔታ በፍሬ ጉዲዩ ረገድ ጭምር ጉዲዩን አጠቃል ውሳኔ መስጠቱ በስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከተውን የክርክር አመራር ስርዓት መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም።የዚህ ሰበር ክርክር ተካፊይ ያልተደረጉት ከአመልካች ጋር ውለን አድርገዋል የተባለት የስር 1ኛ ተከሳሽም የክርክሩ ውጤት በቀጥታ የሚመለከታቸው በመሆኑ በቀጣይ የክርክር ሂደት የክርክሩ አካል መደረግ የሚገባቸው መሆኑን ተገንዝበናል።
ሲጠቃለል ለክርክሩ አወሳሰን አስፈላጊ የሆኑ ፍሬ ነገሮች በተገቢው ስነ ስርዓታዊ አግባብ እንዱጣሩ ሳይደረግ የስር ፍርድ ቤቶች በአንድ ወይም በልላ አግባብ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የተሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ቅያሪው የተደረገው አመልካች እንደሚለት በ1994 ዓ.ም. ነው ወይስ ተጠሪ እንደሚለት በ21/01/2004 ዓ.ም. በተደረገው ውል ነው? ከይርጋ አቆጣጠር አንጻር ተጠሪ የለውጥ ውል መደረጉን ያወቁት ወይም አውቀዋል ሉባለ የሚችለት መቼ ነው? የቅያሪውን ጊዜ አስመልክቶ በማስረጃ በሚረጋገጠው እና ለጉዲዩ አግባብነት ባለው ሕግ መሰረት ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው ወይስ አይደለም? የመሬት ቅያሪ ውለ በሚመለከተው አካል የተመዘገበ እና ዕውቅና የተሰጠው ነው ወይስ አይደለም? አመልካች እና የተጠሪ ባለቤት የተቀያየሩትን መሬት በይዞታቸው ስር አድርገው የቆዩት ለምን ያህል ጊዜ ነው? በተለዋወጡት መሬት ላይ አመልካች ቤት መስራታቸው እና ቋሚ አትክልቶችን ማፍራታቸው የሚረጋገጥ ከሆነ ይህ ሁኔታ በጉዲዩ አወሳሰን ላይ የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት አለ ወይስ የለም? በ21/01/2004 ዓ.ም. የተደረገው ውል ሙለ ይዘት ምንድነው?
ቅያሪው የተደረገው በ1994 ዓ.ም. መሆኑ የሚረጋገጥ ከሆነ በ21/01/2004 ዓ.ም.
የተደረገው ውል ዓላማ ምንድ ነው? የቅያሪ ውለ ሉፈርስ ይገባል የሚባል ከሆነ የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት ምንድን ነው? የሚለትን እና ከእነዚሁ የሚመነጩ ተያያዥ ነጥቦችን እንደየአግባብነቱ በግራ ቀኙም ሆነ ጉዲዩ ከሚመለከታቸው አካላት በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በሚቀርቡ ማስረጃዎች በማጣራት እና የስር 1ኛ ተከሳሽ አቶ ታከለ ደበሬ የክርክሩ ተካፊይ ሆነው እንዱቀጥለ በማድረግ ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዲዩ ለወንጪ ወረዲ ፍርድ ቤት እንዱመለስ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት ወስነናል።
በዚሁ መሰረት መፈጸም ያስችለው ዘንድ የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለወንጪ ወረዲ ፍርድ ቤት እንዱሁም እንዱያውቁት ለደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.