አንድ የመንግስት ሰራተኛ በአሰሪው የመንግስት መ/ቤት ጥፊት በሆነ ምክንያት የስራ ውለ ተቋርጦ ቆይቶ በኋላ በፍርድ ሰራተኛው ወደ ስራው ሲመለስ ውለ ተቋርጦ በቆየበት ጊዜ ያለው ደሞዝ ጭምር ሉከፈለው የሚገባ ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የአ/ብ/ክ/መ/የመግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 171/2002 አንቀጽ 81/2/፣87/1 የፍትሐ ብሓር ሥነ- ሥርዓት 69
No summary available.
ሰኔ 9 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ት ክምክም እማኛው - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የደቡብ አቸፈር ወረዲ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት - ዐ/ሕግ ዘላለም ተስፊዬ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የስራ ቅጥር ውለ የተሰረዘው አላግባብ ነው ተብል ወደ ስራው እንዱመለስ የተወሰነ የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ ውዝፍ ደመወዝ ክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ክርክር ሲሆን የጉዲዩን አመጣጥ በተመለከተ፡-አመልካች በደቡብ አቸፈር ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ10/02/2004 ዓ.ም ተቀጥረው ሲያገለግለ ከቆዩ በኃላ በቅጥር ውድድሩ ጊዜ ያቀረቡት የስራ ልምድ ማስረጃ ለተቀጠሩበት ፕሳ-3 የስራ ደረጃ የሚጠየቀውን አግባብነት ያለው የስምንት ዓመት የስራ ልምድ መስፈርት የሚያሟላ አይደለም በሚል የክልለ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ በ04/12/2004 ዓ.ም. የአመልካችን ቅጥር መሰረዙን፣አመልካች በዚህ የስረዛ ውሳኔ ቅር ተሰኝተው ለክልለ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የአስተዲደር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝ ተቀባይነት ማጣቱን፣ ይግባኙ ቀጥል የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቅጥሩን የሰረዘው የክልለ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ መጥሪያ ደርሶት መልስ ባለማቅረቡ በላለበት ጉዲዩን መርምሮ ቅጥሩ ከተፈጸመ ከዘጠኝ ወራት በኃላ ቢሮው የቅጥር ፍርማሉቲ አልተሟላም በሚል ምክንያት ቅጥሩን በመሰረዝ የወሰደው እርምጃ ከክልለ አዋጅ ቁጥር 171/2002 ውጭ መሆኑን፣ አመልካች ያቀረቡት የስራ ልምድ ማስረጃ ሀሰተኛ ነው ያልተባለ በመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 23 የተመለከተው ድንጋጌም ለጉዲዩ አግባብነት የላለው መሆኑን ገልጾ ውሳኔውን በመሻር አመልካች ወደ ስራቸው እንዱመለሱ ውሳኔ መስጠቱን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
ይዘቱ ከላይ የተመለከተው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት አቤቱታቸውን ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ችልት ያቀረቡት አመልካቿ ሲሆኑ የአቤቱታቸው ይዘትም ቅጥሩ የተሰረዘው ከሕግ አግባብ ውጭ መሆኑ ተረጋግጦ ወደ ስራዬ እንድመለስ ተወስኖልኝ እያለ ቅጥሩ ከተሰረዘበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ስራ እንድመለስ ውሳኔ እስከተሰጠበት ጊዜ ድረስ ያለው ውዝፍ ደመወዝ እንዱከፈለኝ ሳይወሰን የታለፈው አላግባብ ነው የሚል ነው። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ አመልካች ለሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የአስተዲደር ፍርድ ቤት ይግባኝ ባቀረቡበት ጊዜ ያልተከፈላቸው ደመወዝ ጭምር እንዱከፈላቸው አለመጠየቃቸውን፣ ይግባኙ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሚቀርበውም በአስተዲደር ፍርድ ቤቱ የተሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ብቻ መሆኑን እና በዚህም ምክንያት ለአስተዲደር ፍርድ ቤት በቀረበው የይግባኝ ቅሬታ ላይ ዲኝነት ያልተጠየቀበትን ጉዲይ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችልትም ሆነ ሰበር ችልቱ ተቀብለው ውሳኔ ሉያሳርፈ የሚችለበት የሕግ አግባብ አለመኖሩን ገልጾ አቤቱታውን ባለመቀበል ውሳኔ ሰጥቷል።አመልካች ለዚህ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ለሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የአስተዲደር ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ቅጥራቸው ፀንቶ እንዱቀጥል ከመጠየቃቸውም በተጨማሪ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ይግባኝ ላይ በክርክር ላይ ለነበሩበት ጊዜ ያለው ደመወዝ ይከፈለኝ በማለት ጥያቄ አቅርበው እያለ ዲኝነት አልተጠየቀበትም ተብል የውዝፍ ደመወዝ ጥያቄው ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በክርክሩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው፡-
አመልካች ለክልለ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የአስተዲደር ፍርድ ቤት ይግባኝ ባቀረቡበት ጊዜ ያልተከፈላቸው ደመወዝ ጭምር እንዱከፈላቸው ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ የለም በማለት በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የተሰጠው ውሳኔ የመዝገቡን ግልባጭ መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም?
ቅጥራቸው ከተሰረዘበት ቀን ጀምሮ ወደስራቸው እንዱመለሱ ውሳኔ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ ያለው የአመልካች ደመወዝ ሉከፈላቸው የማይችልበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
የሚለ ነጥቦች መሆናቸውን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዚሁ ነጥቦች አንፃር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ ቀደም ሲል እንደተገለጸው ቅጥሩ አላግባብ ከተሰረዘበት ቀን ጀምሮ ወደ ስራ እንዱመለስ ውሳኔ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ ያለው ደመወዝ እንዱከፈለኝ ያቀረብኩትን ጥያቄ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያለፈብኝ አላግባብ ነው በማለት አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ሰበር ችልት ሳይቀበል የቀረው ደመወዙ ሉከፈል የማይችልበት ሕጋዊ ምክንያት መኖሩን መሰረት በማድረግ ሳይሆን ይልቁንም አመልካች ለክልለ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የአስተዲደር ፍርድ ቤት ይግባኝ ባቀረቡበት ጊዜ ያልተከፈላቸው ደመወዝ እንዱከፈላቸው ጭምር ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ የለም በማለት መሆኑን የውሳኔው ይዘት ያመለክታል። ይሁን እንጂ አመልካች ቅጥሩ የተሰረዘባቸው አላግባብ መሆኑን ገልጸው ወደ ስራቸው እንዱመለሱ እንዱወሰንላቸው ካቀረቡት ጥያቄ በተጨማሪ ቅጥራቸው ከተሰረዘበት ጊዜ ጀምሮ ያለው ደመወዝ እንዱከፈላቸው ጭምር ለክልለ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የአስተዲደር ፍርድ ቤት በ24/12/2004 ዓ.ም አዘጋጅተው ባቀረቡት የይግባኝ ማመልከቻ በተራ ቁጥር ስምንት ላይ ጠቅሰው መጠየቃቸውን እና ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በ19/02/2005 ዓ.ም አዘጋጅተው ባቀረቡት የይግባኝ ማመልከቻ በተራ ቁጥር አስራ ሁለት ላይም ተመሳሳይ ዲኝነት መጠየቃቸውን በመግለጽ ለዚህ ችልት ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ላይ ላቀረቡት ክርክር ተጠሪው በመልሱ የሰጠው ግልጽ ማስተባበያ ካለመኖሩም በላይ በአጣሪው ችልት በኩል ከዚህ መዝገብ ጋር እንዱያያዙ የተደረጉት ለአስተዲደር ፍርድ ቤቱ እና ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችልት የቀረቡት የሁለቱ የይግባኝ ማመልከቻዎች ይዘትም የአመልካቿን የክርክር ነጥብ የሚያረጋግጥ መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም አመልካች ለክልለ የሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የአስተዲደር ፍርድ ቤት ይግባኝ ባቀረቡበት ጊዜ ያልተከፈላቸው ደመወዝ እንዱከፈላቸው ጭምር ያቀረቡት የዲኝነት ጥያቄ የለም በማለት በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የተሰጠው ውሳኔ የመዝገቡን ግልባጭ መሰረት ያደረገ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ ከላይ በመጀመሪያው ጭብጥ ትችት ላይ እንደተገለጸው አመልካች ቅጥሩ የተሰረዘባቸው አላግባብ መሆኑን ገልጸው ወደ ስራቸው እንዱመለሱ እንዱወሰንላቸው ካቀረቡት ጥያቄ በተጨማሪ ቅጥራቸው ከተሰረዘበት ጊዜ ጀምሮ ያለው ደመወዝ እንዱከፈላቸው ጭምር በአስተዲደር ፍርድ ቤትም ሆነ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችልት ዲኝነት መጠየቃቸው የተረጋገጠ ሲሆን የአስተዲደር ፍርድ ቤት ውሳኔን ሽሮ ቅጥሩ የተሰረዘው አላግባብ መሆኑን በመግለጽ አመልካች ወደ ስራቸው እንዱመለሱ ውሳኔ የሰጠው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች ቅጥራቸው ከተሰረዘበት ጊዜ ጀምሮ ያለው ደመወዝ እንዱከፈላቸው ጥያቄ አቅርበው የነበረ ስለመሆኑም ሆነ ጥያቄውን አቅርበው ነበረ ከተባለም ውሳኔ ሳያሳርፍበት የቀረው በምን ምክንያት እንደሆነ በውሳኔው ላይ የገለጸው ነገር አለመኖሩን ከውሳኔው ይዘት ተገንዝበናል።ተጠሪ በዚህ ሰበር ችልት በሰጠው መልስ የስራ ቅጥሩ የተሰረዘበት ሰራተኛ በፍርድ ቤት ወደ ስራው እንዱመለስ ቢወሰንለት ቅጥሩ ከተሰረዘበት ጊዜ ጀምሮ ያለው ደመወዝ ሉከፈለው የሚገባ ስለመሆኑ በተሻሻለው የአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 171/2002 ላይ የተደነገገ ነገር አለመኖሩ ሕግ አውጭው የዚህ ዓይነቱ ውዝፍ ደመወዝ እንዲይከፈል መፈለጉን የሚያሳይ ነው በማለት ተከራክሯል። እንደተባለው ቅጥሩ ለተሰረዘበት እና በፍርድ ቤት ውሳኔ ወደ ስራው እንዱመለስ ለተወሰነለት ሰራተኛ ውዝፍ ደመወዝ ሉከፈል የሚገባ ስለመሆኑ በአዋጁ በግልጽ የተቀመጠ ፈቃጅ ድንጋጌ የላለ ሲሆን በአንጻሩ የዚህ ዓይነቱ ደመወዝ ሉከፈል የማይገባው ስለመሆኑም በአዋጁ በግልጽ የተቀመጠ ከልካይ ድንጋጌም የለም።ይልቁንም ከዱሲፕሉን ጉዲዮች ጋር በተያያዘ ሁኔታ የመንግስት ሰራተኛው የተላለፈበት ውሳኔ በይግባኝ ከተሻሻለለት ወይም ከተሰረዘለት ውሳኔው ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ ሳይከፈለው የቀረው ደመወዝ ታስቦ ያለወለድ የሚከፈለው ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 81 (2) ስር የተመለከተው ድንጋጌ የሰራተኛው የስራ ውል ተቋርጦ የቆየው የሰራተኛው ባልሆነ እና ይልቁንም የመንግስት መስሪያ ቤት በሆነ ጥፊት ምክንያት መሆኑ በፍርድ ተረጋግጦ ሰራተኛው ወደ ስራው እንዱመለስ ሲወሰን የስራ ውለ ተቋርጦ በቆየበት ጊዜ ያለው ደመወዝ ጭምር ሉከፈለው የሚገባ ስለመሆኑ በአዋጁ ተቀባይነት ያገኘ መርህ መሆኑን መገንዘብ የሚያስችል ነው። በአዋጁ መሰረት የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ የደመወዝ ጭማሪ ወይም ላላ ጥቅም የተሰረዘበት የመንግስት ሰራተኛ በማታለል ወይም በማጭበርበር ያገኘው ካልሆነ በቀር የስረዛው እርምጃ እስከተወሰደበት ጊዜ ድረስ የተከፈለውን ደመወዝ እና ጥቅማጥቅሞች እንዱመልስ የማይጠየቅ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 87 (1) የተመለከተው ድንጋጌም ይህንኑ የሚያጠናክር ነው።ቅጥሩ የተሰረዘበት ሰራተኛ ወደስራው እንዱመለስ በፍርድ ቤት ሲወሰን ውዝፍ ደመወዙ ጭምር እንዱከፈል ሕግ አውጭው አለመፈለጉን አዋጁ ያመለክታል በማለት በደፈናው ከመከራከር በቀር የዚህ ዓይነት ትርጉም የሚሰጠው ወይም የዚህ ዓይነት ግምት ለመውሰድ የሚያስችለው የአዋጁ ድንጋጌ የትኛው እንደሆነ ተጠሪው በግልጽ ለይቶ ያቀረበው ክርክር የለም።በመሆኑም ቅጥራቸው ከተሰረዘበት ቀን ጀምሮ ወደስራቸው እንዱመለሱ ውሳኔ እስከተሰጠበት ቀን ድረስ ያለው የአመልካች ደመወዝ ሉከፈላቸው የማይችልበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
ሲጠቃለል ከላይ በዝርዝር በተገለጹት ምክንያቶች ቅጥራቸው ከተሰረዘበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ስራቸው እስኪመለሱ ደረስ ያለው ደመወዝ እንዱከፈላቸው አመልካች ያቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄ በዝምታ በማለፍ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የተሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ለክልለ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የአስተዲደር ፍርድ ቤትም ሆነ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ባቀረቡት የይግባኝ ማመልከቻ ላይ ቅጥራቸው ከተሰረዘበት ጊዜ ጀምሮ ያለው ደመወዝ እንዱከፈላቸው ጭምር የዲኝነት ጥያቄ አቅርበዋል በማለት ወስነናል።
የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ በ05/06/2005 ዓ.ም. የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሎል።
በተራ ቁጥር ሶስት ከተጠቀሰው ውሳኔ ውስጥ ቅጥራቸው የተሰረዘው አላግባብ በመሆኑ አመልካች ወደስራ ሉመለሱ ይገባል በማለት የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ፀንቷል።
በተራ ቁጥር ሶስት ከተጠቀሰው ውሳኔ ውስጥ ቅጥራቸው ከተሰረዘበት ቀን ጀምሮ ያለው ደመወዝ እንዱከፈላቸው አመልካች ያቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄ በዝምታ በማለፍ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
ቅጥራቸው ከተሰረዘበት ከ04/12/2004 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ስራቸው እንዱመለሱ እስከተወሰነበት 05/06/2005 ዓ.ም. ድረስ ያለው የአመልካች ደመወዝ ያለወለድ ሉከፈላቸው ይገባል በማለት ወስነናል።
የውሳኔው ግልባጭ በውሳኔው መሰረት ማስፈጸም ያስችለው ዘንድ ለክልለ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ የአስተዲደር ፍርድ ቤት፣ እንዱያውቁት ደግሞ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና አመልካች ለሚሰሩበት የመንግስት መስሪያ ቤት ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.