ሰራተኛው በስራ ላይ በደረሰበት የሞት አደጋ ምክንያት የሰራተኛው ባለቤትና ላልች ጥገኞች የሚያቀርቡት የካሣ ክፍያ ጥያቄ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 162 ንዐስ አንቀፅ 1 108785 ዩሴፍ ተክላ ህንፃ ሥራ ተቋራጭ እና ወ/ሮ ወርቅነሽ ጌታቸው በራሳቸው እና ሞግዚት በሆኑላቸው /እነ ሕፃን ረዱኤት/ ሐምል 21 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም 54 13. አንድ ሰራተኛ በስራ መዘርዝሩ በግልጽ የተሰጠውን /የተቀመጠለትን/ ግዳታዎቹን አለመወጣቱ የስራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ሉያቋርጥ የሚችል ስለመሆኑ፡- V አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13(2) እና (7) አቶ እሸቱ አደፍርስ
No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 30 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል እንዲሻው አዲነ ቀነዓ ቂጣታ አመልካች፡- ሰላም ቦላ ሸማቾች ኃ.የተ.የህብረት ስራ ማህበር - የቀረበ የለም ከተባለ በኃላ ጠበቃ መለሰ ግርማይ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ እሸቱ አደፍርስ - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የግል ስራ ክርክር ሲሆን የተጀመረውም ተጠሪ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ ሰኔ 02 ቀን 2006 ዓ/ም ባቀረቡት ክስ መነሻ ነው። የክሱም ይዘት ባጭሩ፡-ተጠሪ በአመልካች ድርጅት ውስጥ ከ7/00/2003 ዓ/ም ጀምሮ በጉልበት ሰራተኝት የስራ መደብ ተቀጥረው በወር ብር 770.00 እየተከፈላቸው በመስራት ላይ እንዲለ የአሁኑ አመልካች ከስራ መደባቸው ውጪ የሆነ ስራ ተጠሪ እንዱሰሩ በማድረጉ ተጠሪ የአመልካችን ትዕዛዝ ከስራ መዘርዝራቸው ውጪ ነው በሚል በመቃወማቸው ምክንያት ከስራ ያሰናበታቸው መሆኑን ዘርዝረው ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ተብል የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈሎቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካቸ ለክሱ በሰጠው መልስም ተጠሪ የታዘዙት ከስራ መደባቸው ጋር ተያያዥነት ያለውንና በስራ መዘርዝሩ በተጠቀሰው አግባብ መሆኑን እንዱሁም በተደጋጋሚ በቅርብ አለቃቸው ሲታዘዙ ትዕዛዙን የማይቀበለ መሆኑን ጠቅሶ ስንብቱ ሕጋዊ ነው ሲል ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርን ከሰማ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ ከአሰሪው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ያለመፈጸማቸው አከራካሪ ያለመሆኑን፣ተጠሪ የሚፈፅሟቸው ተግባራት በስራ መዘርዝሩ በግልጽ መመልከታቸውን፣በዚህም መሰረት ተጠሪ ውሃ ያላቸውን ለስላሳ ጠርሙሶችን ከስቶር ወደ ባር፣ባድ ጠርሙሶችን ደግሞ ከባር ወደ ስቶር እንደሚመልሱ በስራ መዘርዝሩ ላይ ከመገለፁም በላይ በዚሁ ሰነድ ተራ ቁጥር 8 ስርም ከቅርብ አለቃቸው ሲታዘዙ ማንኛውንም የጉልበት ስራ ሉሰሩ እንደሚችለ መጠቀሱን ከሰነደ ይዘት መመልከቱንና ከዚህም ተጠሪ የታዘዙት ከስቶር ወደ ባር ውሃ ያለበትን ጠርሙስ ወስደው ከባር ወደ ስቶርም ውሃ ያለበትን ጠርሙስ እንዱመልሱ በመሆኑ ስራው የስራ ድርሻቸው የሆነው የጉልበት ስራ መሆኑን መረዲቱን ከአረጋገጠ በኋላ ይህ ተግባር የስራ ውልን ያለማስንጠቀቂያ ሉያቋርጥ ይችላል ወይስ አይችልም የሚለውን ጥያቄ በማንሳት በስራ መዘርዝሩ መሰረት ያለመስራት ስራተኛውን ያለማስጠንቀቂያ ለማሰናበት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት አይደለም በማለት ደምድሞ የአመልካችን እርምጃ ሕገ ወጥ ነው በማለት አመልካች ለተጠሪ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ብር 1540.00፣የካሳ ክፍያ ብር 4620.00፣የስራ ስንብት ክፍያ ብር 781.25፣የአመት ፈቃድ ክፍያ ብር 377.3 የገቢ ግብር ተቀንሶ እንዱከፈላቸውና የስራ ልምድ ምስክር ወረቀት እንዱሰጣቸው በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡-ተጠሪ በስራ መዘርዝራቸው መሰረት የታዘዙትን ስራ ለመስራት ፈቃደኛ ያለመሆናቸው ተረጋግጦ እያለ ተግባሩ ያለማስጠንቀቂያ ሉያሰናብት የሚችል አይደለም ተብል በበታች ፍርድ ቤቶች የተወሰነው የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 13(2) ድንጋጌን ያላገናዘበ ነው የሚል ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ በመሆኑ ተጠሪ ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል። እንደመረመርነውም ተጠሪ በስራ መዘርዝሩ መሰረት ስራቸውን ያለመስራታቸው ተረጋግጦ እያለ ተግባሩ ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውለን ሉያቋርጥ የሚችል አይደለም ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባ ሁኖ አግኝተናል።
የፍሬ ጉዲይ ክርክሩን በተመለከተ አመልካች አላግባብ ከስራ አስናብቶኛል በማለት ተጠሪ ላቀረቡት ክስ አመልካች በሰጠው መልስ ተጠሪው ከስራ ማሰናበቱን አምኖ ያሰናበተው ግን ተጠሪው እንደሚለት አላግባብ ሳይሆን የተጠሪ የቅርብ አለቃ በሰጣቸው ትዕዛዝ እና በስራ መዘርዝሩ መሰረት ተጠሪ የስራ ግዳታቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት መሆኑ በሚገባ ተረጋግጧል።
እንዱህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪው የተሰናበቱት በስራ መዘርዝሩ በተገለፀው አግባብ የስራ ግዳታቸውን ባለመወጣታቸው በመሆኑ ውጤቱ ከአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 13(2) እና (7) ድንጋጌዎች ይዘት እና መንፈስ እንዱሁም አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ መሰረታዊ አላማ መታየት ያለበት ነው። ተጠቃሹ አዋጅ መሰረታዊ አላማ ከያዛቸው ነገሮች ውስጥ የኢንደስትሪ ሰላምን በማስፈን ምርትና ምርታማነትን በማሳዲግ ለአገር ኢኮኖሚ እድገት አስተዋፅኦ ማድረግ መሆኑን የአዋጁ መግቢያ ያሳያል። ይህንኑ ለማሳካትም ሕጉ በአሰሪውም ሆነ በሰራተኛው ላይ ለይቶ ያስቀመጣቸው ግዳታዎች መኖራቸውን የአዋጁ አንቀጽ 12 እና 13 ድንጋጌዎች ያሳያለ።
በመሆኑም አሰሪውም ሆነ ሰራተኛው በሕጉ የተጣለባቸውን ግዳታ መወጣት ይጠበቅባቸዋል።
ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያለውና ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለውን ነጥብ በተመለከተ ስናይም አዋጁ ሰራተኛው በአሰሪው የተሰጠውን ሕጋዊ የስራ ትዕዛዝ በአግባቡ የመወጣት ግዳታ ያለበት መሆኑን በአንቀፅ 13(2) እና (7) ስር ከተቀመጡት ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
ላላው አዋጁ አካቶ ከያዛቸው ጉዲዮች መካከል የስራ ውል የሚቋርጥባቸው መንገድችና ምክንያቶች ይገኙበታል። የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ሉቋረጥ የሚችልባቸው ምክንያቶች በአዋጁ አንቀፅ 27(1) ስር በግልጽ ተቀምጠዋል። በዚህ ድንጋጌ ስር የተመለከቱት የስራ ውል ማቋረጫ ምክንያቶች ግን አንድ ሰራተኛ የስራ ግዳታውን ያለመወጣቱ ሲረጋገጥ የስራ ውለን ለማቋረጥ ማስጠንቀቂያ መስጠትን በቅድመ ሁኔታነት የሚያስቀምጡ አይደለም። ስለሆነም ግልጽ ደንብ ወይም መመሪያ መኖሩ በተረጋገጠበት ሁኔታ ሰራተኛው የስራ ግዳታውን ካልተወጣ አሰሪው ሰራተኛውን ያለማስጠንቀቂያ የማያሰናብትበት ምክንያት የለም። ከዚህ አንጻር ጉዲዩን ስንመለከተውም ተጠሪ በስራ መዘርዝራቸው በግልጽ የተቀመጠመውን ግዳታቸውን ያለመወጣታቸው ተረጋግጦ የተከናወነው ስንብት ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13(2) እና (7) ድንጋጌዎች እና ከአዋጁ መሰረታዊ አላማ አንፃር ሲታይ ህጋዊ ነው ከሚባል በስተቀር ሕገ ወጥ የሚባልበትን አግባብ አላገኘንም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን ከዚህ አንፃር መመልከት ሲገባቸው ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ መሰረታዊ አላማ በመውጣት የስራ ግዳታውን ያለመወጣቱ የተረጋገጠውን ተጠሪ መሰናበት የነበረበት በማስጠንቀቂያ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 03 ቀን 2006 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 20 ቀን 2007 ዓ/ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
ስንብቱም ህገወጥ ነው በማለት በስር ፍ/ቤቶች የሰጡት የውሳኔ ክፍል ተሽሮ ስንብቱ ሕጋዊ ነው ብለናል።
አመልካች ለተጠሪ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣የስራ ስንብት ክፍያና የካሳ ክፍያ ለመክፈል አይገደድም፣ የአመት ፈቃድ ክፍያ ብር 377.3 ግን ለተጠሪ ሉከፍል ይገባል፣የስራ ልምድ ምስክር ወረቀትም ላሰጥ ይገባል ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ይቻቻለ ብለናል።
No topics extracted.