አንድ ሰራተኛ መብትና ጥቅሙን ሳይነካ ከአንድ የሥራ ቦታ ወደ ላላ የሥራ ቦታ ወይም የስራ መደብ በማዛወር ማሰራት የአሰሪው አስተዲደራዊ ሥልጣን ነው ሲባል ዝውውሩ ያለህጋዊ ምክንያትና በህብረት ስምምነቱ ከሰፈረው አሰራር ውጪ ይከናወናል ተብል ሉተረጎም የማይገባው ወ/ሪት ለሉት አያላው እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
No summary available.
የሰ/መ/ ሀምላ 21 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ተኸሉት ይመስል እንደሻው አዲነ ቀነአ ቂጣታ አመልካች፡- ዩሴፍ ተክላ ህንፃ ሥራ ተቋራጭ ጠበቃ ብሥራት መኮንን ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ወርቅነሽ ጌታቸው በራሳቸው እና ሞግዚት በሆነችላቸው እነ ሕፃን ረዱኤት ታምራት ከጠበቃ አቶ ፊንቱ አስፊው ጋር ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ።
?? ?? ??
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በሥራ ላይ በሚደርስ ጉዲት ለሚስትና በላልች ጥገኞች የሚከፈል የካሣ ገንዘብ ጥያቄ የይርጋ የጊዜ ገደብ የሚመለከት ነው ተጠሪ ባለቤቷ የሁለት ልጆች አባት የሆነው ታምራት ሀይላ አሰሪው በመደበው መኪና ከላልች ሰራተኞች ጋር ሲጓጓዝ መኪናው ተገልብጦ ሚያዝያ 23 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም ህይወቱ ያለመሆኑን ገልፆ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ለእርሷና ለህፃናቱ ካሣ እንዱከፈላቸው ውሣኔ እንዱሰጥላት ጥር 25 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ጠይቃለች ።
አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 162 ንሁስ አንቀፅ 4 የተደነገገው የስድስት ወር የይርጋ የጊዜ ገደብ አልፎል በማለት መቃወሚያ አቅርቧል ። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን መቃወሚያ በመቀበል ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ብይን ሰጥቷል ። ተጠሪ ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርባ፣ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ለጉዲዩ አግባብነት ያለው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 162 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ ነው ። ስለዚህ ክሱ የቀረበው በዚህ ድንጋጌ የተጠቀሰው የይርጋ የጊዜ ገደብ ከማለፈ በፉት በመሆኑ በይርጋ አይታገድም በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን ሽሮታል ።
አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው ይህንን የይግባኝ ሰሚውን ፍርድ ቤት ውሣኔ በመቃወም ሲሆን ተጠሪ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን ብይን የሕግ ስህተት የላለበት መሆኑን ገልፃ ተከራክራለች እኛም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ጉዲዩ በይርጋ አይታገድም በማለት የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 162 ንሁስ አንቀፅ /1/ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ የሰጠውን ብይን ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል ።
ጉዲዩን አንደመረመርነው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 162 ንሁስ አንቀፅ 4 የተደነገገው የስድስት ወር ይርጋ ተፈፃሚ የሚሆነው አሰሪው በሰራተኛው ላይ ወይም ሰራተኛው በአሰሪው ላይ ለሚያቀርበው የደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓት ሥራ ክፍያ፣በአል ቀናት ክፍያ ጥያቄና ለመሳሰለት የክፍያ ጥያቄዎች መሆኑን ከድንጋጌው አቀራረፅና ይዘት ለመረዲት ይቻላል በአዋጅ አንቀፅ 4 በይዘቱም ሆነ በአቀራረፅ ፣የሰራተኛው በስራ ላይ የደረሰበት የሞት አደጋ የሰራተኛው ባለቤትና ላልች ጥገኞች በአዋጁ አንቀጽ 110 መሰረት የሚያቀርቡትን የካሣ ክፍያ ጥያቄ በስድስት ወር የይርጋ የጊዜ ገደብ ለመገደብ ታስቦ የተደነገገ ድንጋጌ አይደለም ። ከዚህ አንፃር ሲታይ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጉዲዩ አግባብነት ያለው በአዋጅ አንቀፅ 162 ንዐስ አንቀፅ 1 የተደነገገው የይርጋ የጊዜ ገደብ ነው።ተጠሪ ክስ ያቀረበችው በአዋጁ አንቀጽ 162 ንዐስ አንቀጽ 1 የተደነገገው የይርጋ ጊዜ ገደብ ከማለፈ በፉት በመሆኑ የተጠሪ ክስ በይርጋ አይታገድም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል ።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ህዲር 25 ቀን 2007 ዓ.ም የሰ ጠውን ውሣኔ ፀንቷል ።
ተጠሪዎች ያቀረበት ክስ በይርጋ ቀሪ አይሆንም በማለት ወስነናል ።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ይቻቻለ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ።