አንድ ሰራተኛ መብትና ጥቅሙን ሳይነካ ከአንድ የሥራ ቦታ ወደ ላላ የሥራ ቦታ ወይም የስራ መደብ በማዛወር ማሰራት የአሰሪው አስተዲደራዊ ሥልጣን ነው ሲባል ዝውውሩ ያለህጋዊ ምክንያትና በህብረት ስምምነቱ ከሰፈረው አሰራር ውጪ ይከናወናል ተብል ሉተረጎም የማይገባው ወ/ሪት ለሉት አያላው እና የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
No summary available.
የሰ/መ/ ሚያዚያ 26 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሪት ለሉት አያላው ማሞ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዩጵያ መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ ማህላት ዓለሙ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ከሰራተኛ የስራ መደብና ቦታ ዝውውር ጋር ተያይዞ የተነሳውን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአመልካች የክስ ይዘትም፡- የተጠሪ ድርጅት አመልካች የኢንዱስትሪ ሰላም አላግባብ ንትርክ እየፈጠሩ መረባሻቸውን ሳያረጋግጥ በ26/08/2005 ዓ/ም በፃፈው የአመልካችን የግል ታሪክ በሚያጎድፍ ደብዲቤ ከኦዱት ወደ ማርኬቲንግ ክፍል ያላግባብ በማዘዋወር እርምጃ መውሰደን ጠቅሰው የተወሰደው እርምጃ እንዱነሳና ወደ ኦዱት ክፍል እንዱመለሱ እንዱሁም የዝውውሩ ደብዲቤ እንዱሰረዝላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም፡- አመልካች ከኦዱት ሰራተኞች ጋር ባላቸው አለመግባባት የተነሳ የኢንዱስትሪ እና የስራ ቦታ ሰላም ለመጠበቅ ሲባል የአመልካች የስራ ደረጃ እና ደመወዝ ሳይነካ ዝውውሩ መፈፀሙንና ክሱ ከተመሰረተ በኋላም የአመልካችን ደመወዝ ብር 10,759.00 ማድረጉን ገልፆ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
ጉዲዩ በዚህ መልክ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ጉዲዩን በመመርመር የሥራ መደብ ዝውውሩ ሕጋዊ ነው፣ የዝውውር ደብዲቤም ሉሰረዝ አይገባም በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸው ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- አመልካች ለኢንዱስትሪ ሰላም የፈጠሩት ችግር ስለመኖሩ ሳይረጋገጥ እና በስራው ላይ ያስከተለት ችግር መኖሩ በተጠሪዎች ምስክሮች ባልተነገረበት ሁኔታ ዝውውሩ ህጋዊ ነው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክርና ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነውን ውሳኔ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር እንደሚከተለው መርምሮታል። ጉዲዩ ለዚህ ችልት ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ ዝውውሩ ሕጋዊ ነው ተብል የመወሰኑን አግባብነት አመልካች ከአቀረበው ክርክር ይዘትና ከሕጉ ጋር አገናዝቦ ለማየት ይቻል ዘንድ ነው። በመሆኑም ጉዲዩን ከዚሁ ጭብጥ አንጻር ብቻ እንደሚከተለው ተመልክተናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁን አመልካች ሥራዬን በአግባቡ እየተወጣሁ እያለ አሰሪው ወደ ላላ የሥራ መደብ ተዛውረሻል በማለት ደብዲቤ ጽፍልኛል፣ ዝውውሩ ከፍላጎቴና ከህብረት ስምምነቱ ውጪ የተደረገ ከመሆኑም በላይ በግል ማህደሬ ላይ ከፍተኛ ችግር የሚያስከትል ነው በማለት ገልጸው ተከራከረው ተጠሪ ዝውውሩ የተደረገበትን ምክንያቶችን ዘርዝሮ በሕግ ከተሰጠው ስልጣን የመነጨ መሆኑንም ጭምር ጠቅሶ መከራከሩን ነው። የግራ ቀኙን ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የተጠሪ ምስክሮች ቃል አመልካች ከሰራተኞች ጋር ብልም ከሃላፉዎች ጋር ግጭት የሚፈጥሩ፣የሚሰጣቸውን ስራውም በአግባቡ የማይሰሩ ስለመሆኑ፣የስራ ባልደረቦቻቸው አብረዋቸው ለመስራት የማይመርጧቸው ሰው እንደሆኑ፣ ስራቸውን በአግባቡ ስለማይሰሩ የጊዜ ብክነት፣ አላስፈላጊ ውጪና ያልተቃና ስራ መከሰቱን መመስከራቸውን፣ የአመልካች ምስክር ደግሞ አመልካች በስተመጨረሻ የኦዱት ስራ የሰሩባቸው ሶስት ቅርንጫፍች አስመልክቶ የተፈጠረ ችግር ሳይኖር ስራውን ከአመልካች ጋር መስራታቸውን ገልጸው መመስከራቸውን በውሳኔ ላይ ከአሰፈረ በኋላ የአመልካች ምስክር የሰጡት የምስክርነት ቃል አመልካች አለባቸው የተባለትን ከስራው ጋር የተያያዙ በርካታ ችግሮችን ፈጽሞ የላለባቸው ስለመሆኑ አስረድተዋል ለማለት የሚያስችል አይደለም፣ አመልካች ስራው ላይ ያሳያለ የተባለት ባህርይ በስራ ቅልጥፍና፣ በውጤታማነትና በኢንዱስትሪ ሰላም ላይ አለታዊ ተእፅኖ የሚፈጥሩ በመሆናቸው ተጠሪ ድርጅት የአመልካችን ደመወዝ፣ የስራ ደረጃና ላላች ጥቅማጥቅሞችን ሳይነካ የፈፀመው የሥራ መደብ ዝውውር ሕጋዊ ነው በማለት ደምድሟል።
ከተጠሪ የሥር ክርክርም ሆነ በዚህ ሰበር ደረጃ ከሰጠው መልስ መገንዘብ የተቻለው ደግሞ በአንድ በኩል ዝውውሩ የተፈጸመው በአመልካች ጥያቄ መነሻ መሆኑን ጠቅሶ የተሻለ ደመወዝ አመልካች እንዱያገኙ ማድረጉን፣ በልላ በኩል ደግሞ የአመልካችን ተገቢ ያልሆነ ባህርይ መነሻ በማድረግ ለኢንደስትሪና ለስራ ቦታ ሰላም የተደረገ ነው በማለት የሚከራከር መሆኑን ነው።
በመሰረቱ አንድ አሰሪ አንድን ሰራተኛ ከአንድ የስራ መደብ ወደ ላላ የስራ መደብ የማዛወር አስተዲደራዊ ስልጣኑ ነው ተብል የሚታመነው አሰሪው ስራንና ሰራተኛን ለማገናኘት የሚችልበት አግባብ ነው በሚል ምክንያት ሆኖ ዝውውሩም ተቀባይነት የሚያገኘው የሰራተኛውን መብትና ጥቅም በማይነካ መልኩና ተመሳሳይ ወደሆነው የስራ መደብ ተከናውኖ ሲገኝ እንጂ ይህንኑ በሚቃረን መልኩ ላሆን እንደማይገባ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት አግባብነት ያላቸውን የአዋጅ ቁጥር 377/1996 ድንጋጌዎችን በመመርመር በሰ/መ/ እና በላልች በርካታ መዛግብት በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ የፍርድ ቤትን የሚያስገድድ የህግ ትርጉም የሰጠበት ጉዲይ ነው።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ አመልካችን ከኦዱት ክፍል ወደ ማርኬቲንግ የስራ መደብ ያዛወራቸው መሆኑን ሳይክድ አዱሱ የስራ መደብ አመልካች ቀድሞ ይሰሩበት ከነበረው የስራ መደብ ጋር ተመሳሳይ የሆነና የአመልካችን መብትና ጥቅም በማይነካ መልኩ መከናወኑንና ለዝውውሩ አብይ ምክንያትም የአመልካች ባህርይ ሁኖ ለኢንዱስትሪ ሰላም ሲባል አመልካች እንዱዛወሩ ከተደረገበት የስራ ቦታ በጡረታ የወጣ ሰራተኛ አመልካች እንዱተኩ ለማድረግ ሲባል መከናወኑን ጠቅሷል።
ሆኖም ተጠሪ ድርጅት ለዝውውሩ ምክንያት ያደረጋቸው እነዚህ ምክንያቶች ባንድ በኩል ከአመልካች ባህርይ ጋር እንደተያያዙ፣ በልላ በኩል ደግሞ በአመልካች ጥያቄ መነሻና በጡረታ የተገለለ ሰራተኛን የሥራ መደብ እንዱሸፈኑ ለማድረግ ታሰቦ የተደረገ መሆኑን የሚገልጹ በመሆናቸው ይዘታቸው ሲታይ እርስ በራሳቸው የሚቃረኑ ምክንያቶች መሆናቸውን የሚያስገነዝብ መሆኑን ተመልክተናል። አንድ ሰራተኛ በባህርይ ችግር ለኢንዱስትሪ ሰላም አስቸጋሪነቱ ከተረጋገጠ በሕጉ አግባብ ተገቢው ማስጠንቀቂያ እንዱሰጠው ተደርጎ እንዱታረም ማድረግ የሚቻልበት አግባብ መኖሩ የሚታወቅ ሲሆን በባህርይ ችግር ተዛወረ የተባለን ሰራተኛ ደግሞ የስራ መደቡ ክፍት በመሆኑ እንዱዛወር ተደርጓል በሚል የሚቀርብ ክርክር ዝውውሩ ስራንና ሰራተኛን ለማገናኘት የተደረገ ነው ብል ለመደምደም የማያስችል ነው። ተጠሪ አመልካችን በየጊዜው የሚያዛውራቸው ስለመሆኑ በክርክሩ ሂደት መገለጹም ሲታይ ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። ስራንና ሰራተኛን ለማገናኘት ሲባል ባልተደረገ የሥራ ውል ደግሞ የስራ ውል የሚሻሻልበት አግባብ ያለመኖሩን ከአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 15 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
በመሆኑም ተጠሪ የስራ መደቡ ዝውውሩ ሕጋዊ ነው ብል የሚያቀርባቸው ምክንያቶች እርስ በራሳቸው የሚቃረኑ በመሆናቸው ተጠሪ ዝውውሩ በህጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ያከናወነው ነው በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ሉሰጠው የሚገባ ሆኖ አልተገኘም።
ዝውውሩ ሕጋዊ መሆኑን ያሳያለ የተባለት የተጠሪ ምክንያቶች እርስ በርሳቸው የሚቃረኑ ናቸው ከተባለ የአሰሪው የዝውውሩ እርምጃ የአስተዲዲሪነት ሥልጣኑን በዘፈቀደ ለማከናወን መነሳቱን ያሳያል ከሚባል በስተቀር የዝውውሩን ህጋዊነት በምንም መመዘኛ አያሳዩም።
ስለሆነም አንድን ሰራተኛ መብትና ጥቅሙን ሳይነካ ከአንድ የስራ ቦታ ወደ ላላ የሥራ ቦታ ወይም የስራ መደብ በማዛወር ማሰራት የአሰሪው አስተዲደራዊ ሥልጣን (Administrative prerogative) ነው ሲባል ዝውውሩ ያለ ሕጋዊ ምክንያትና በሕብረት ስምምነቱ ከሰፈረው አሰራር ውጪ ይከናወናል ተብል ሉተረጎም የማይገባው ስለመሆኑ ከአሰሪና ሰራተኛ ሕጉ አጠቃላይ መሰረታዊ አላማና ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/፣77113 እና በላልች በርካታ መዛግብት ከሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ይዘትና መንፈስ የምንረዲው ሁኖ ስለአገኘን ተጠሪ አመልካችን ያዛወረበት ሁኔታ ሕገ ወጥ ነው ተብል መሰረዝ ሲገባው በስር ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ማግኘቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሁኖ አግኝተናል። ተጠሪ ያከናወነው ዝውውር ሕገ ወጥ ነው ከተባለም የአመልካችን ባህርይ በተመለከተ በዝውውር ደብዲቤው የገለፀበት አግባብ ከአመልካች የግል ማህደር ጋር ሉኖር የማይገባ በመሆኑ ሉሰረዝ የሚገባው ሁኖ አግኝተናል። በእነዚህ ሁለ ምክንያቶች ተከታዩን ወስናል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 09 ቀን 2006 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ነሐሴ 07 ቀን 2006 ዓ/ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
የአመልካች ዝውውር ሕገ ወጥ ነው፣ ሉሰረዝ ይገባል ብለናል። አመልካች ይሰሩበት ከነበረው የኦዱት የስራ መደብ ወደ ማርኬቲንግ የስራ መደብ ሉዛወሩ አይገባም፣ የዝወውሩ ደብዲቤም ሙለ በሙለ ሉሰረዝ ይገባል ከአመልካች ማህደር ሉያያዝ አይገባም ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት በተደረገው የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.