የቅርብ አለቃውን ሰብአዊ ክብርና ሞራል የሚነካ የስድብና ማዋረድ የፈጸመ እና በስራ ቦታ የጠብ አጫሪነትን የፈጠረ ሰራተኛ የሥራ ውለ ያለማስጠንቀቂያ ሉቋረጥ የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ 377/96 አንቀፅ 32/1/ሀ አዋጅ 377/96 አንቀፅ 13/2/ እና 27
No summary available.
ግንቦት 28 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኸሉት ይመስል አመልካች፡- ኃብተሚካኤል ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማሕበር - ሥራ አስኪያጅ አቶ ተካልኝ ሁንዳ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ታመነ ታደሰ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሐምል 10 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዝገብ የካቲት 9 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ሥህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው የሰበታ ሀዋሳ ወረዲ ፍርድ ቤት ነው።
በወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሕግ አግባብ ውጭ የሥራ ውላ ተቋርጧል በማለት ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ አመልካች ሆነው ተከራክረዋል።
አመልካች በተከሳሽነት ቀርቦ ከሳሽ በጥቅምት 2 ቀን 2006 ዓ.ም አደም ገረመው ከሚባል ሰራተኛ ጋር በመደባደብ በሥራ ቦታ ሁከት የፈጠረ መሆኑንና ህዲር 25 ቀን 2006 ዓ.ም የድርጅቱን ሥራ አስኪያጅ አልታዘዝም ከማለቱም በላይ “ዝም በል አንተ አሽሻም ። አሽሽ አጭስህ መጥተሕ አፍህን አትክፈት። አእምሮ የሚያደነዝዝ አሽሽ ወስደህ ደንዝዘህ መጥተህ አታደንዝዘን” በማለት የተሳደበና ችግር የፈጠረ መሆኑ ከሥራ የተሰናበተ መሆኑን ገልፆ ተከራክሯል ። የወረዲው ፍርድ ቤት የከሳሽንና የተከሳሽን ምስክሮች ሰምቷል የከሳሽ አንደኛው ምስክር ከሳሽ ከቅርብ አለቃው ጋር መጣላቱን የመሰከረ መሆኑንና የተከሳሽ ምስክሮች ጥቅምት 7 ቀን 1986 ዓ.ም ከሳሽ የድርጅቱን አንድ ሰራተኛ የደበደበ መሆኑንና 25/03/2006 ዓ.ም ከሳሽ የቅርብ አለቃውን ሀሽሻም ሀሽሽ አጭሰህ መጥተህ ትናገረናለህ ጠብ እና ግርግር ያነሳ መሆኑን በማረጋገጥ እንደመሰክሩ የሥር ፍርድ ቤት በውሣኔው አስፍሮ ተጠሪ /ከሳሽ/ አለቃውን አልታዘዘም ማለቱንና መስደቡ የተረጋገጠ በመሆኑ የሥራ ውለ የተቋረጠው በሕግ አግባብ ነው በማለት የተጠሪ /ከሳሽን/ ክስ ውድቅ አድርጎታል ።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል ። የልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክረክር ከሰማ በኃላ አመልካች የተጠሪን የስራ ውል ያቋረጠው ተጠሪ አለቃውን ሰብዓዊ መብቱን በሚነካ መልኩ ስለሰደበው መሆኑ እንደተረጋገጠ ገልፆ አመልካች ተጠሪው ለፈፀመው ለዚህ ጥፊት ማስጠንቀቂያ መስጠት ሲገባው ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውለን ማቋረጡ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀፅ 4 ድንጋጌ መስፈርት የሚያሟላ አይደለም በማለት ስንብቱ ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈፀመ ነው ተብል አመልካች ብር 8,284.24 /ስምንት ሺ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ብር ከሃያ አራት ሳንቲም ) ለተጠሪ እንዱከፍል ውሣኔ ሰጥቷል ። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርቧል ። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የተጠሪ አድርጎት “ጠብና”አንባጓሮ ማንሣት ነው ተብል ሉያዝ አይገባም በማለት የልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል ።
አመልካች የካቲት 24 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ የቅርብ ኃላፉውን አንድ ሰራተኛ ወደላላ ቦታ ሄድ እንዱሰራ ትዕዛዝ ሲሰጥ ትዕዛዙን ከመቃወም አልፈው የቅርብ አለቃውን አንተ ሀሽሻም በማለት የተሳደበና አምባጓሮ የፈጠረ፤ በዚህ ምክንያት የምርት ሥራው እንዱገታ ያደረገ መሆኑን በማስረጃ ተረጋግጧል ። ይህ የተጠሪ አድራጎት የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27/1/ረ መስፈርት አያሟላም በማለት የልዩ ዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት የሕግ ትርጉም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል ።ተጠሪ በበኩላ ሚያዚያ 6 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ መልስ እኔ አለቃዬን አልተሳደብኩም ። ሁከትም አልፈጠርኩም ። ስለዚህ ስንብቱ ህገ ወጥ ነው ተብል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል ። አመልካች ሚያዝያ 20 ቀን 2007 ዓ/ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራቀኙ ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አመልካች የተጠሪን የሥራ ውል ያቋረጠው ከሕግ አግባብ ውጭ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ የሕጉን ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም ? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ ተጠሪ ህዲር 25 ቀን 2006 ዓ.ም በሥራ ቦታ ያሳየውን ባህሪይና የፈፀመውን አድራጎት በተመለከተ ፍሬጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የወረዲው ፍርድ ቤትና የልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የደረሱበትን የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ምዘና ድምዲሜ መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል ። ህዲር 25 ቀን 2006 ዓ.ም ተጠሪና ላልች አራት ሰራተኞች ሥራ እየሰሩ እያለ የቅርብ አለቃቸው ከእነሡ መካከል አንድ ሰራተኛ ወደ ላላ የሥራ ክፍል እንዱሄድና ቀሪዎች አራቱ ቀሪውን ሥራ እንዱያከናውኑ ትዕዛዝ የሰጠ መሆኑ በዚህ ጊዜ ተጠሪ የቅርብ አለቃውን የሥራ ትእዛዝ ከመቃወም አልፍ ሀሽሻም ሀሽሽ አጭስህ መጥተህ ትናገረናለህ በማለት የተሳደበ መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑንና የተጠሪ ማስረጃ ይህንን በአመልካች ማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ጉዲይ ያላስተባበለ መሆኑን የወረዲው ፍ/ቤት በውሣኔው በግልፅ አስፍሮታል ።
አመልካች ተጠሪን ከስራ ያሰናበተው ተጠሪ የሥራ ትዕዛዝ ባለመቀበለና የቅርብ አለቃውን ክብረ ነክ የሆነ ስድብ በመሳደቡ ምክንያት ነው በማለት የወረዲው ፍርድ ቤት የደረሰበትን የፍሬ ጉዲይ ማጣሪትና የማስረጃ ምዘና መደምደሚያ ሙለ በሙለ ትክክል ነው በማለት የልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተቀበለው መሆኑን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሀምላ 10 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ በአራተኛው ገፅ የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ይዘት ከተነተነ በኃላ ‹‹ በአጠቃላይ የመልስ ሰጭ ድርጅት ይግባኝ ባይን ከሥራ ያባረረው እሱ አለቃውን ሰብዓዊ ክብሩን መንካቱን በሚነካ መልኩ ስለሰደበው እንደሆነ ከመዝገቡ ውስጥ የምንረዲው ጉዲይ ነው በማለት በመጨረሻው ፓራግራፍ ካሰፈረው የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ምዘና መደምደሚያ ለመረዲት ይቻላል።
ከዚህ አንፃር ሲታይ ተጠሪ ህዲር 25 ቀን 2006 ዓ.ም በቅርብ አለቃው የተሰጠውን የሥራ ትዕዛዝ ከመቃወም አልፍ የቅርብ አለቃውን አንተ ሀሽሽ አጭሰህ መጥተህ አትናገረን “በማለት የተሣደበ መሆኑን ፍሬጉዲይ ያማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባላቸው የወረዲው ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልዩነት የላቸውም። የወረዲው ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተለያዩት ይኸ የተጠሪ አድርጎት አመልካች ህዲር 26 ቀን 2006 ዓ.ም ከተጠሪ ጋር ያለውን የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ በማቋረጥ ለወሰደው እርምጃ በቂና ህጋዊ ምክንያት ነው ወይስ አይደለም ? የሚለው የህግ ጥያቄ በሚመረምሩበትና መዝነው ውሣኔ በሰጠበት ጊዜ እንደሆነ ከውሣኔያቸው ለመረዲት ችለናል ።
ሰራተኛው ከሥራ ውል የተመለከተውን ሥራ ራሱ የመሥራትና የሥራ ውለና ደንቡ መሰረት በአሰሪው የሚሰጠውን ትዕዛዝ የመፈፀም ግዳታ ያለበት መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 13 ንዐስ አንቀፅ 1(1)እና ንዐስ አንፅ 2 ተደንግጓል ።ከዚህ በተጨማሪ አንድ ሰራተኛ እንደጥፊቱ ክብደት በስራው ቦታ አንባጓሮ ወይም ጠብ አጫሪነት ጥፊት በፈፀመ ጊዜ አሰሪው ሰራተኛውን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሲያሰናብተው የሚችል መሆኑን የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 ንዐስ አንቀፅ(1)ተደንግጓል። ተጠሪ የቅርብ አለቃው ከተጠሪ ጋር ከሚሰሩት አምስት ሰራተኞች አንድ ሰራተኛ ወደ ላላ ሥራ ክፍል ለማሰማራት የሰጠውን ትዕዛዝ የተቃወመና በአዋጅ አንቀፅ 13 ንዐስ አንቀጽ 2 አሰሪው በሥራ ውለና ደንቡ መሰረት የሰጠውን የሥራ ትዕዛዝ የመፈፀም ግዳታውን ያልተወጣ መሆኑን ና አሰሪው ላልች ሰራተኞች የሥራ ትዕዛዝና ስምሪት የመስጠት መብት በመጋፊት የቅርብ አለቃውን “አንተ ሀሽሻም ሀሽሽ አጭሰህ መጥተህ አትናገረን “በማለት የተሳደበ መሆኑ ተረጋግጧል።
አመልካች የቅርብ አለቃው ላይ የስድብና ማዋረድ ተግባር የፈፀመው በወንጀል ሕግ ማንም ሰው እንዲይዘውና እንዲይጠቀም ክልከላ የተደረገበትን ሀሽሽ አጭሰህ መጥተህ ነው የምትናገረን በማለት እንደሆነ ተረጋግጧል ። ተጠሪ በቅርብ አለቃው ላይ የፈፀመው የስድብና ማዋረድ ተግባር፣በህግ የተከለከለ ተግባር ፈጽመሀል በማለት ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡም የሚያወግዘውንና የሚጠየፈውን ተግባር የቅርብ አለቃው ፈጽሞ መጥቶ ሰራተኞችን እንደሚበጠብጥ አድርጎ ላልች ሰራተኞች እየሰሙ በመግለፅ እንደሆነና ይህም የተጠሪ አድርጎትና ተግባር የአሰሪው ወኪል የሆነውን የቅርብ አለቃውን ሰብዓዊ ክብር በሚነካ ሁኔታ ተጠሪ የስድብና ማዋረድ ተግባር የፈፀመና በዚህ ምክንያት የተጠሪ የቅርብ አለቃ ስሜት ውስጥ እንደገባና ለጠብና ለድብድብ እንዱነሳሳ ለማድረግ አስቦና መርጦ የተናገረው መሆኑን ከግራቀኙ ክርክርና ከሥር ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመረዲት ይችላል ።
ይህንን የተጠሪ አድርጎት በአዋጅ ቁጥር 32 ንዐስ አንቀጽ 1(ሀ) ድንጋጌ ጋር በማነፃፃር ስንመለከተው “አሰሪው የሰራተኛውን ሰብዓዊ ክብርና ሞራልን የሚነካ ወይም በወንጀለኛ መቅጫ ህግ መሰረት የሚያስቀጣ ላላ አድርጎት የፈፀመ እንደሆነ ሰራተኛው የሥራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ የሥራ ውለን ለማቋረጥ እንደሚችል ይደነግጋል 10. በዚህ መዝገብ እየታየ ያለው ጉዲይ ከላይ የተጠቀሰው ድንጋጌ የተገለፁት ተግባራት በአሰሪው ሣይሆን በሰራተኛው የተፈፀመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ተጠሪ የቅርብ አለቃው የሰጠውን የሥራ ትዕዛዝ አልፈፅምም ከማለት አልፍ አንተ ሀሽሻም ሀሽሽ አጭሰህ መጥተህ አትናገረን በማለት የቅርብ አለቃውን የሰደበና ያዋረደ መሆኑን በዚህ ምክንያት ከቅርብ አለቃው ጋር ጠብ የተፈጠረ መሆኑ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ያሳያል ከዚህ አንፃር በአዋጅ ቁጥር 32 ንዐስ አንቀፅ 1(ሀ) የተገለፀ ሁኔታ ሰራተኛው የቅርብ አለቃውን ሰብዓዊ ክብርና ሞራል የሚነካ የስድብና የማዋረድ ተግባር በመፈፀሙ ወይም ላላ ህገወጥ ተግባር በመፈፀሙ ምክንያት በሥራ ቦታ በሰራተኛውና በቅርብ የሥራ ሀላፉው መካከል ጠብ የተነሳ መሆኑ ከተረጋገጠ አሰሪው በአዋጅ ቁጥር 27 ንዐስ አንቀጽ 1(ረ) በተደነገገው መሰረት የሥራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ እንደሚችል የአዋጁን አንቀጽ 13 ንዐስ አንቀጽ 2፣የአዋጅ አንቀጽ 32(2) ሀ ከሚደነግገው በሚቃረን ሁኔታ ሰራተኛው የቅርብ የሥራ ሀላፉውን ሰብዓዊ ክብርና ሞራል የሚነካ ተግባር መፈፀም ሉያስከትል የሚችለውን ህጋዊ ውጤትና የአዋጁን አንቀፅ 27 ንዐስ አንቀፅ 1(ረ) ድንጋጌ ይዘትና መሰረታዊ ዓላማ በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል። በመሆኑም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት ተጠሪ በቅርብ አለቃው የተሰጠውን የሥራ ትዕዛዝ ከመቃወም አልፍ የቅርብ የሥራ ሃላፉውን አንተ ሀሽሻም ሀሽሽ አጭሰህ መጥተህ እኛን አትናገረን በማለት በመሳደቡና ከቅርብ አለቃው ጋር መጣላቱ የሥራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚያስችል በቂና ህጋዊ ምክንያት አይደለም በማለት የሰጡት የሕግ ትርጉምና ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፉንፉኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሸሯል።
የሰበታ ሀዋሳ ወረዲ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
አመልካች የተጠሪን የሥራ ውል የቋረጠው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 13 ንዐስ አንቀፅ 2 እና በአንቀፅ 27 ንዐስ አንቀፅ 1(ረ) መሰረት በመሆኑ የሥራ ስንብቱ በሕግ አግባብ የተከናወነ ነው በማለት ወስነናል ።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጡትን ወጭና ኪሳራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.