አንድ በሹፋርነት የተቀጠረ ሰራተኛ አሰሪው ጋር በተያያዘ ሁኔታ ጥንቃቄ ማድረግ ከሚገባው ነገር አንደ መኪናውን የሚያሽከረክርበት አግባብ ከአካባቢው አየር ሁኔታና ከመልከዓ ምድሩ ጋር ባገናዘበ መልኩ መሆን ያለበት ስለመሆኑና ይህንን ሳያደርግ ቀርቶ አደጋና ጉዲት ቢደርስ ከባድ ቸልተኝነት እንዲደረሰ ተቆጥሮ የስራ ውለ ያለማስጠንቀቂያ ሉቋረጥ የሚችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 13/3/፣27/1/ሸ/ IV
No summary available.
ግንቦት 28 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ፒ.ኤስ አይ ኢትዩጵያ - ጠበቃ አላምነህ ስንሻው ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ እሸቱ ካሳ - የቀረበ የለም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ሐምል 24 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም በተፃፈ ክስ በአመልካች ድርጅት በሹፋርነት ተቀጥረው እየሰሩ ባለበት ሁኔታ ያላግባብ ከስራ መሰናበታቸውን ገልፀው ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ አመልካችም በተከሣሽነቱ ቀርቦ በሰጠው መልስ ተጠሪ የድርጅቱን መኪና ባግባቡ የመንዲት ኃላፉነታቸውን ባለመወጣት ግንቦት 05 ቀን 2006 ዓ.ም ሰው ገጭቶ ጉዲት ማድረሱንና ከዚህ በኋላም ሰኔ 08 ቀን 2006 ዓ/ም ከደሴ ወደ መቐላ በሚሄድበት ጊዜ በግድየለሽነት በማሸከርከር በመኪናው ላይ ጉዲት ከማድረሱም በላይ በተሽከርካሪው ውስጥ በነበሩት የድርጅቱ ሰራተኞች ላይ ቀላል የመቁሰል አደጋ ማድረሱንና ይህም በክፍለ የትራፉክ ፖሉስ መረጋገጡንና አመልካችም ተገቢውን ኮሚቴ አቋቁሞ በማጣራት ከአረጋገጠ በኋላ ስንብቱን ያከናወነ መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የደሴ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ግንቦት 05 ቀን 2006 ዓ/ም ደረሰ የተባለው አደጋ በሰላሳ የስራ ቀናት ውስጥ የስራ ስንብት ማከናወኛ ምክንያት ያልሆነ በመሆኑ በይርጋ እንዱሚታገድ፣ ሰኔ 08 ቀን 2006 ዓ/ም ደረሰ የተባለው አደጋ ደግሞ በተጠሪ በኩል ቸልተኝነት በመኖሩ የደረሰ ነው ቢባልም በከባድ ቸልተኝነት የደረሰ ነው ልባል የሚችል ያለመሆኑን ጠቅሶ የአመልካችን የስንብት እርምጃ ሕገወጥ መሆኑን በመደምደም ተጠሪ የአምስት ወር ከስድስት ቀናት ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎቸው ወደ ስራ እንዱመለሱ በማለት ወስኗል። የአሁኑ አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለደቡብ ወል መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙለ በሙለ አፅንቶታል።
አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ መጋቢት 24 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል።
ይዘቱም ባጭሩ፡- የተጠሪ ድርጊት በሕጉ አግባብ ሲጣራ ቆይቶ ተጠሪ ከባድ ቸልተኝነት ያለባቸው መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ለተፈፀመው እርምጃ ድርጊቱ በይርጋ የታገደ ነው መባለ አሰሪ የሰራተኛውን ጥፊት በትክክል አወቀ ልባል የሚችልበትን አግባብና በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ሸ/1/ ስር ስለ ከባድ ቸልተኝነት የተመለከተውን የህጉን ድንጋጌ ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ሰኔ 08 ቀን 2006 ዓ.ም ደረሰ ለተባለ አደጋ የተጠሪ ቸልተኝነት ከባድ ልባል የሚችል አይደለም ተብል የስንብቱ እርምጃ ሕገወጥ ነው መባለ ባግባቡ መሆን አለመሆኑን በጭብጥነት ሉመረመር የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በአመልካች ድርጅት በሹፋርነት ተቀጥረው እየሰሩ ባለበት ወቅት ግንቦት 05 ቀን 2006 ዓ.ም መንገደኛ በነበረው ሰው ላይ ጉዲት አድርሰዋል፣ሰኔ 08 ቀን 2006 ዓ.ም ደግሞ የአመልካች ድርጅት ሰራተኞችን ከደሴ ወደ መቐላ ለስራ ይዞ በመሄድ ላይ እያለ መንገደ ጠመዝማዛና የአየሩ ሁኔታም ዝናብማ ሁኖ እያለ ከጥንቃቄ ጉድለት መኪናውን እንዱወድቅ በማድረግ በመኪናው ላይ ጉዲት አድርሷል፣በሰራተኞች ላይም ቀላል የመቁሰል አደጋ አድርሷል ተብል ስንብቱ የተከናወነ መሆኑንና የስር ፍርድ ቤቶች ግንቦት 05 ቀን 2006 ዓ.ም ተፈጸመ የተባለው ጥፊት በሰላሳ ቀን የይርጋ ጊዜ መታገደን፣የሰኔ 08 ቀን 2006 ዓ.ም ጥፊት ግን በወቅቱ ዝናባማ የአየር ሁኔታ በነበረበትና መንገደ እርጥበታማና ቁልቁለታማ በሆነበት አካባቢ የተፈፀመ ቢሆንም በተጠሪ በኩል ቸልተኝነት ነበር ከሚባል በስተቀር በአዋጁ በተመለከተው አግባብ ከባድ ቸልተኝነት ነበር ልባል የሚችል አይደለም በሚል ምክንያት የበታች ፍርድ ቤቶች የወሰኑ መሆኑን ነው። በመሆኑም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ የተጠሪ አድራጎት በከባድ ቸልተኝነት ስር ሉወድቅ ይችላልን?
የሚለው ነው።
በመሰረቱ አንድ ሰራተኛ ለስራው የተሰጡትን መሣሪያዎችና እቃዎች ሁለ በጥንቃቄ የመጠበቅ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 13/3/ ስር የተመለከተ ሲሆን በአሰሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ ስራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸውም ንብረት ላይ ሆነ ብል ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዲት ማድረስ ሰራተኛውን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 27/1/ሸ/ ድንጋጌ ያሣያል። ሆኖም ከባድ ቸልተኝነት የሚለውን ቃል መለኪያ በተመለከተ ሕጉ በግልጽ አያሣይም። ይሁን እንጂ ቸልተኝነት የጥንቃቄ ጉድለት እንደመሆኑ መጠን የጥንቃቄ ዓይነትና ደረጃ እንደየድርጊቱና አድራጊው የስራ ድርሻ አኳያ በመመልከት ምላሽ ለማግኘት እንደሚገባ ይህ ችልት በሰ/መ/ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በመሆኑም የተጠሪ የጥፊት ደረጃ "ከባድ ቸልተኝነትን" ሉያቋቁም የሚችል መሆን አለመሆኑን ከስራቸው ባህርይ አንፃር መመልከቱ የግድ የሚል ነው። ተጠሪ ስራቸው ሹፋር ሲሆኑ ከስራቸው በተያያዘ ሁኔታ ጥንቃቄ ማድረግ ከሚገባቸው ነገሮች አንደ መኪናውን የሚያሽከረክሩበትን አግባብ ከአከባቢው አየር ሁኔታ እና ከመልክዓ ምድሩ ጋር በአገናዘበ መልኩ መሆን ያለበት መሆኑን የሚመለከት ነው።በመሆኑም በዝናባማ የአየር ሁኔታና ጠመዝማዛና ቁልቁለታማ በሆነ መንገድ በዝግታና በጥንቃቄ ተሽከርካሪን ማሽከርከር ከአንድ አሽከርካሪ የሚጠበቅ ሙያዊ ግዳታ ነው። ይሁን እንጂ በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ መኪናውን ዝናባማ በሆነ የአየር ሁኔታ ውስጥ በጠመዝማዛና ቁልቁለታማ በሆነ መንገድ ላይ ተጠሪ ማርሹን በተመጣጣነ ማርሽ አስሮ ባለማሽከርከሩ አደጋው መደረሱ በክፍለ ፖሉስና አመልካች ባቀረባቸው ላልች ማስረጃዎች የተረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ተጠሪ ማስተባበያ ማስረጃ ያላቀረበበት ጉዲይ ስለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል። ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶችም ተጠሪ ሲያሽከረክሩት የነበረው መኪና በተጠቀሰው የአየር ሁኔታና መልክዓ ምድር ላይ ሲሽከረከር ተጠሪ ተገቢውን ማርሽ አስሮ ሲሽከረክር ነበር በማለት የደመደሙት ፍሬ ነገር ያለመኖሩን የውሳኔያቸው ይዘት ያስገነዝባል።
ተጠሪ መኪናውን ሲያሽከረክሩ የነበረበት ሁኔታ ከላይ የተገለጸው ነው ከተባለ ደግሞ ትክክለኛ አእምሮ ባለው ሰውና በተጠሪ የግል ሁኔታ መመዘኛ መሰረት ከባድ ቸልተኝነትን ሉያሣይ የሚችል አይደለም ልባል የሚችልበትን አግባብ አላገኘንም፡፤። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች የተጠሪ ጥፊት ከባድ ቸልተኝነት አይደለም ማለታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ሁኖ ስለተገኘ የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በደሴ ከተማ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.10762 ታህሳስ 06 ቀን 2007 ዓ.ም ተሰጥቶ በደቡብ ወል መስተዲደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.19554 የካቲት 19/ 2007 ዓ.ም፣ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 03-10681 መጋቢት 18 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ተጠሪን ያሰናበተው በሕጉ አግባብ ነው ብለናል።
በዚህ ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.