በአንድ አሰሪ ድርጅት መተዲደሪያ ደንብና መመሪያ መሰረት በአንድ የሥራ መደብ ላይ የውጪ ሰው የሚቀጠረው መጀመሪያ ለቦታው የሚመጥን የውስጥ ሰራተኛ ካለ ለውስጥ ሰራተኛው እድል ከሰጠ ለኋላ ከሆነ አሰሪው ድርጅት ይኽን ደንብና መመሪያ ተላልፍ የውስጥ ዕድገት ማስታወቂያ ሣያወጣና ለሰራተኞች ዕድል ሳይሰጥ የውጪ ቅጥር ቢፈጸም ድርጊቱ ህገወጥ ተግባር ስለመሆኑና ቅጥሩ ሉሰረዝ የሚገባው ሲስተር ትዕግስት ፈቃድ እና የኤድስ መከላከያ ማህበራዊ አገልግልት ድርጅት
No summary available.
ግንቦት 14 ቀን 2007ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኸሉት ይመሰል አመልካች፡- ሲስተር ትዕግስት ፈቃድ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የኤድስ መከላከያ ማህበራዊ አገልግልት ድርጅት አልቀረበም
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዝገብ መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰበር ችልት በመዝገብ ህዲር 17 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበችውን የሰበር አቤቱታ አጣራቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የሥራ መደብ ሉሰጠኝ ይገባል በማለት የቀረበን ጥያቄ የሚመለከት ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በምዕራብ ኦሮሚያ አሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ነው። በአሰሪና ሰራተኛ ውሳኝ ቦርደ አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል ።
1- አመልካች በተከሳሽ (ተጠሪ) ድርጅት በአዱስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በነርስ ካውንስለር ሰባተኛ ደረጃ ተቀጥሬ በመሥራት ላይ እያለሁኝ የቤተሰብ ችግር ስላጋጠመኝ በራሴ አቤቱታ አቅራቢነት በደረጃ ሶስት የነርስ ካውንስለር የሥራ መደብ ወደ ነቀምት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተዛውሬና ተመድቤ በመሥራት ላይ እገኛለሁ ። ሆኖም ተከሳሽ እኔ በፉት ተቀጥሬበት የነበረው ሰባተኛ ደረጃ ነርስ ካውንስለር ለመመደብ መስፈርቱን የሚያሟላ የውስጥ ሰራተኛ የለም አግባብ ባልሆነ መንገድ የመሥሪያ ቤቱን መተዲደሪያ ደንብ በመጣስ ከአምስት ዓመት በፉት የሥራ ስንብት ክፍያና ላልች ጥቅማጥቅሞችን ከፍል ያሰናበታትን ሰራተኛ በመጥራት ያለምንም ውድድር በመቅጠር ደረጃ ሰባት ነርስ ካውንለር አድርጎ መድቧታል። ከሳሽ መስፈርቱ የሟማላ የውስጥ ሰራተኛ እያለሁ የውስጥ ሰራተኞች ተወዲድረው በእድገት በሚመደቡበት የሥራ መደብ ላይ የነቀምቴ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እኔን በቦታው ላይ መመደብ ሲገባው የውጭ ማስታወቂያ በማውጣት ቅጥር መፈፀሙ የድርጅቱን መተዲደሪያ ደንብ የሚጥስና የእኔን መብት የሚያጣብብ በመሆኑ፣ቅጥሩን በመሰረዝ እኔን በቦታው ላይ እንዱመድቡኝ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት የምዕራብ ኦሮሚያ አሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ክስ አቅርባለች።
2- ተከሳሽ (ተጠሪ በበኩለ ከሳሽ በሶስተኛ ደረጃ ነርስ ካውንስለር የሥራ መድብ ተመድባ የምትሰራ ሰራተኛ ናት ከሳሽ አራት ደረጃዎችን በመዝለል ደረጃ ሰባት ነርስ ካውንስለር ሥራ መደብ ላይ መመደብ አለብኝ በማለት ያቀረበችው ክስ የህግ ስህተት የለውም ። ከሳሽ ለደረጃ ሰባት የሚመጥን የሙያ ብቃት ስነምግባርና የሥራ አፈፃፀም የላትም ። ባለው የሥራ መደብ ፤ሥራውን ለመሥራት የሚችል ሰራተኛ በዕድገት ወይም በቅጥር የመመደብ መብት ያለው አሰሪው (ድርጅቱ) እንጅ ሰራተኛው አይደለም ። ከሳሽ ያለምንም ውድድር የሥራ መደቡ እንዱሰጣት ያቀረበችው ክስ ተገቢ ባለመሆኑ ውድቅ ይደረግልኝ በማለት ተከራክሯል።
3- የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ የግራቀኙን ክርክር ከመረመረ በኃላ ከሳሽ በአዱስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ፣ተመድባ ስትሰራ የነበረ መሆኑ በተከሳሽ አልተካደም ከሳሽ ወደ ወለጋ ቅርንጫፍ የተዛወረችውና በደረጃ ሶስት የሥራ መደብ ላይ ተመድባ ለመሥራት የተስማማችው በቤተሰብ ችግር ምክንያት መሆኑ ተረጋግጧል ።
ተከሳሽ ከሳሽ በዱሲፒሉን ችግር ምክንያት ወደ ደረጃ ሶስት ብቅ ብላ የተመደበች ስለመሆኑ ያቀረበው ማስረጃ የለም።ስለዚህ ተከሳሽ ደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ተመድባ ስትሰራ የነበረችውን ተከሳሽን ሣያሳውቅ ከውጭ ላላ ሰው የቀጠረው ከሳሽ ቦታውን እንዲታገኘ ለማድረግ በማስብ በክፊ ልቦና ነው። ስለዚህ ተከሳሽ ከሳሽን በደረጃ ሰባት የሥራ መደብ መድቦ የደመውዝን ልዩነት አስቦ ሉከፍል ይገባል በማለት በድምፅ ብልጫ ውሣኔ ሰጥቷል።
4- የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ መልስ ሰጭ (አመልካች) ያለውድድር በደረጃ ሰባት የሥራ መደብ እንድትመደብ የሰጠው ውሳኔ የመሥሪያ ቤቱን የሥራ አመዲደብ መመሪያ መሰረት ያላደረገ ነው በማለት ቦርደ የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል ።
አመልካች ይግባኝ ሰሚው ችልት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርባለች ። የክልለ የሰበር ችልት የአመልካችን የሰበር አቤቱታ አልተቀበለውም ።
5- አመልካች ህዲር 18 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የድርጅቱ መተዲደሪያ ደንብ በአንድ የሥራ መደብ ላይ የውጭ ሰው የሚቀጠረው በመጀመሪያ ለቦታው የሚመጥን የውስጥ ሰራተኛ ካለ እድል ከሰጠ በኃላ መሆን እንዲለበት በግልፅ ያስቀምጣል ። አመልካች በደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ተመድቤ አዱስ አበባ ቅርንጫፍ ስሰራ እንደነበር ተረጋግጧል ።
ይህ ሆኖ እያለ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት አመልካች በደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ልትመደብ አይገባትም በማለት የሰጡት ውሳኔ የድርጅቱን መተዲደሪያ ደንብ ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክታለች ። ተጠሪ መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አመልካች ያለውድድር በቀጥታ ለመመደብ ጥያቄ ያቀረበችበት ደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ለመወዲደር የሚስፈልገው የትምህርት ደረጃ አድቫንስድ ዱፕልማ ሲሆን አመልካች ያላት ድፕልማ በመሆኑ ለቦታው ለመወዲደር አትችልም አመልካች አዱስ አበባ ቅርንጫፍ ደረጃ ሰባት ተመድባ የነበረው በድሮው መዋቅር ነው። ስለዚህ ያለምንም ውድድር በደረጃ ሰባት እንድትመደብ የተሰጠውን ውሣኔ መሻሩ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል። አመልካች ሚያዚያ 8/ቀን 2007 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ በነርስ ሙያ ዱፕልማና ዱግሪ የትምህርት መርሃ ግብር እንጂ አድቫንስድ ዱፕልማ የሚባል የትምህርት መረሃ ግብር የለም በነርስ በአድቫንስ ዱፕልማ የተመረቀ ባለሙያ የለም ። ተጠሪ ዕውነትነት የላላቸውን መስፈርቶች በማንሣት የቀረበው ክርክር ተቀባይነት ሉኖረው አይገባም በማለት ተከራክራለች።
6- ከሥር የክርክሩ አመጣጥና ለዚህ ሰበር ችልት ግራቀኙ በፅሐፍ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት አመልካች በድርጅቱ መተዲደሪያ ደንብ መሰረት መስፈርቱን የማሟላው ሰራተኛ ሣልወዲደር የደረጃ እድገት ሣይሰጠኝ ተጠሪ ቅጥር በመፈፀም የሥራ መደቡን ማስያዙ ሕገ ወጥ ስለሆነ ቅጥሩ ተሰርዞ እኔ በቦታው ላይ እንድመደብ በማለት ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም ? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መርምረናል ።
7- ጉዲዩን እንደመረመርነው በተጠሪ ድርጅት ውስጥ ክፍት የሥራ መደብ ሲኖር ድርጅቱ ላላ ሰራተኛ ከመቅጠሩ በፉት መስፈርቱን የሚያሟለ የድርጅቱ ሰራተኞች ካለ ተወዲድረው በእድገት በቦታው ላይ እንዱመደቡ እድል መስጠት ያለበት መሆኑ በድርጅቱ መተዲደሪያ ደንብና የሰው ሀይል አመዲደብ መመሪያ በግልፅ የተደነገገ በመሆኑን አመልካችና ተጠሪ የሚተማመኑበት ነጥብ ነው። አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩበት ጭብጥ አመልካች ተጠሪ የመተዲደሪያ ደንቡንና መመሪያውን በመጣስ ለደረጃ ሰባት የሚያስፈልገውን መስፈርት የማሟላ ሰራተኛ እኔ እያለሁ ለእኔ እድል ሣይሰጠኝ ከውጭ ሰራተኛ በመቅጠር የስራ መደቡን ማስያዙ ህገወጥ ነው በማለት ያቀረበችውን ክስ ተጠሪ ሙለ በሙለ በመካድ በነቀምት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የነበረውን ደረጃ ሰባት የስራ መደብ በቅጥር ሰው ያሟላሁት ካለኝ ሰራተኞች ለሥራ መደቡ የሚያስፈልገውን መስፈርት የሚያሟላ ሰራተኛ ስለላለኝ ነው። አመልካችም ለደረጃ ሰባት የሚያስፈልገውን መስፈርት አታሟላም የሚል ክርክር በማቅረቡ ነው። ይህም የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 246 በሚደነግገው መሰረት ፣ተጠሪ ደረጃ ሰባት የሥራ መደብ በውጭ ቅጥር ያሟላው የሥራ መደቡ የሚያስፈልገውን መስፈርት የሚያሟለ ሰራተኞች እንዱወዲደሩ እድል ከሰጠ በኋላ መስፈርቱን የሚያሟላ ሰራተኛ ባለማግኘቱ ነው ወይስ አይደለም ? የሚለው አከራካሪ ነጥብ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል ።
8- ተጠሪ በደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ላይ የውጭ ቅጥር በመፈፀም በሥራ መደቡ ላይ ሰራተኛ ከመመደቡ በፉት የድርጅቱ መተዲደሪያ ደንብና የሰው ሀይል ምደባ አፈፃፀም መመሪያ በሚደነግጉት መሰረት በሥራ መደቡ የሚያስፈልገውን የትምህርት ዝግጅት፣የሥራ ልምድና ላልች መስፈርቶች የሚያሟለ ሰራተኞች ማስረጃውን በማቅረብ እንዱወዲደሩ እና እንዱመዘገቡ የእድገት ማስታወቂያ ያላወጣና መስፈርቱን የሚያሟለ ሰራተኞች እንዱወዲደሩ እድል ያልሰጠ መሆኑን የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ከሰጠው ውሣኔ ተረድተናል ። ከዚህ አንፃር ተጠሪ አመልካችና ላልች የድርጅት ሰራተኞች ለደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ለመወዲደር የሚያስችላቸውን ማስረጃ በማቅረብ እንዱወዲደሩ የውስጥ የእድገት ማስታወቂያ ሣያወጣና መስፈርቱን ለሚያሟለ ሰራተኞች እድለን ሣይሰጥ ፣ሰራተኛ በመቅጠር በደረጃ ሰባት ላይ መመደቡ የድርጅቱን መተዲደሪያ ደንብና የሰው ሀይል አመዲደብ መመሪያ መሰረታዊ መርህ የሚጥስና ህጋዊ ዕውቅና ሉሰጠው የማይገባው ተግባር ሆኖ አግኝተነዋል ።
9- ተጠሪ የራሱ የሆነ የሥራ መዋቅር ፣አደረጃጀትና የሥራ መደብ ያለው ድርጅት መሆኑ አያከራክርም። ከዚህ አንፃር ሲታይ ተጠሪ በተለያዩ አካባቢዎች በራሱ የሆኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ያለት መሆኑንና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹም ያላቸው ተመሳሳይ የሥራ መደቦች የሚያስፈልገው የትምህርት ዝግጅት፣የሥራ ልምድና ላልች መስፈርቶች ተመሣሣይነት ያላቸው እንደማይሆኑና በተመሣሣይ የሥራ መደብ ተመድበው ለሚሰሩ ሰራተኞች የሚከፈለው ደመወዝና ላልች ሁኔታዎች ተመሣሣይነት ያላቸው እንደሚሆኑ ከተጠሪ ድርጅታዊ ተፈጥሮአዊ ባህሪና መተዲደሪያ ደንብ ለመረዲት ይቻላል። ከዚህ አንፃር በአዱስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደረጃ ሰባት ነርስ ካውንስለር የሥራ መደብ ላይ ለመመደብ የሚያስፈልገው መስፈርትና በነቀምት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደረጃ ሰባት ነርስ ካውንስለር የሥራ መደብ የሚያስፈልገውን መስፈርት አንድ አይነትና ተመሣሣይ መስፈርቶች መሆናቸውን በመካድ ተጠሪ ያቀረበው ክርክር የለም። አመልካች በአዱስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደረጃ ሰባት የሥራ መደብ መስፈርት በሟሟላት ተመድባ ስትሰራ እንደነበር ተረጋግጧል። ተጠሪ አዱስ አበባ የነበራትን ደረጃና ደሞወዟን በመቀነስ ወደ ነቀምት ቅርንጫፍ የተዛወረችው በነበረባት የቤተሰብ ችግር ምክንያት አመልካች ጥያቄ በማቅረቧ ምክንያት መሆኑ ተረጋግጧል። ከዚህ አንፃር በአዱስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተመድባ ስትሰራበትና ደመወዝ ስትበላበት ለነበረው ደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ለመወዲደር የሚያስፈልገውን መስፈርት አታሟላም በማለት የሚያቀርበው ክርክር የሕግ መሰረት ያለው መከራከሪያ ሆኖ አላገኘነውም ። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ ለአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ያላቀረበውን አዱስ የፍሬ ጉዲይ መከራከሪያ በዚህ ሰበር ችልት በማንሣት ለደረጃ ሰባት የሚያስፈልገው የነርስ አድቫንስድ ዱፕልማ ነው የሚልና መዋቅሩ ስለተለወጠ መስፈርቱም ተለውጧል በማለት ያቀረባቸው መከራከሪያዎች በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 329 ንዐስ አንቀፅ/1/ የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት ያለው መከራከሪያ ሆኖ አግኝተነዋል ። ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች ተጠሪ የነቀምት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለው ደረጃ ሰባት ክፍት የሥራ መደብ ለመወዲደር አትችልም በማለት ያቀረበው ክርክር ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
10- አመልካች በተጠሪ ድርጅት ደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ላይ ተመድባ በአዱስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስትሰራ የነበሩ መሆኑንና አመልካች ይህንን የሥራ መደብ ለቅቃ በነቀምት ጽ/ቤት በደረጃ ሶስት የሥራ መደብ የተመደበችው በራሷ ጥያቄ አቅራቢነት መሆኑ ፣ተጠሪ በነቀምት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ላለው ከፍት ቦታ ለመወዲደር የሚያስችላት ቢሆንም ፣ከላልች ሰራተኞች ጋር ሣትወዲደር የሥራ መደቡን ለማግኘት የሚያስችላት አይደለም ። ከዚህ አንፃር የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ አመልካች ከላልች ሰራተኞች ጋር በደረጃ ሰባት የሥራ መደብ የመወዲደር እድል እንዱሰጣት ውሣኔ መስጠት ሲገባው አመልካች ያለምንም ውድድር ደረጃ ሰባት ላይ እንድትመደብ የሰጠው ውሳኔ የተጠሪን መተዲደሪያ ደንብና የሰው ሀይል አመዲደብ መመሪያ ያልተከተለ በመሆኑ ነው።
በልላ በኩል የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት አሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ አመልካች ደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ላይ ያለምንም ውድድር እንድትመደብ የሰጠውን ውሣኔ መሻራቸው ተገቢ ቢሆንም ፣ተጠሪ አመልካችና ላልች ሰራተኞችን በማወዲደር የውስጥ እድገት ማስታወቂያ ሣያወጣና ለሰራተኞች እድል ሣይሰጥ የውጭ ቅጥር መፈፀሙ ህገወጥ ተግባር በመሆኑ ፣ተጠሪ የፈፀመው ቅጥር ተሰርዞ አመልካችንና ላልች ሰራተኞችን በማወዲደር በደረጃ ሰባት የሥራ መደብ በእድገት እንዱመደብ ውሣኔ ሣይሰጡ ማለፊቸው አመልካች ያቀረበችውን ግልፅ የዲኝነት ጥያቄና የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 182 ንዐስ አንቀፅ 2 ያላገናዘበና በከፉል መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የምዕራብ ኦሮሚያ የአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
ተጠሪ የውስጥ እድገት ማስታወቂያ ሣያወጣና አመልካችና ላልች ሰራተኞች ተወዲድረው በደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ለማደግና ለመመደብ የሚያስችላቸውን እድል ሣይሰጥ የውጭ ቅጥር በመፈፀም ደረጃ ሰባት የሥራ መደብ ላይ መመደቡ ሕገወጥ ተግባር በመሆኑ ተጠሪ በደረጃ ሰባት ላይ የፈፀመው ቅጥር ሉሰረዝ ይገባዋል በማለት ወስነናል።
አመልካች በደረጃ ሰባት የስራ መደብ ለመወዲደር የሚያስፈልጉ መስፈርቶችን የምታሟላ በመሆኑ ፣ተጠሪ አመልካችንና ለልች መስፈርቱን የሚያሟለ ሰራተኞችን በማወዲደር የውስጥ እድገት ላሰጥ ይገባዋል በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለያራሳቸው ይቻለ ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.