አንድ አሰሪ ሰራተኛው ያቀረበውን የስራ መልቀቂያ ጥያቄ ተቀብል ሰራተኛውን ካሰናበተ በኋላ የተለያዩ የክፍያ ጥያቄዎች በሰራተኛው ሲቀርብለት ወደኋላ ተመልሶ የስራ ውል ማቋረጫ ምክንያት አግኝቻለሁ በማለት ላላ ደብዲቤ በመጻፍ ለሰራተኛው የሚገባውን ክፍያ አልፈፅምም ማለት አግባብነት የላለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27/1/ለ/፣25
No summary available.
ግንቦት 14 ቀን 2007 ዳኞች- አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- አቶ ካብራክ ተኮላ - ጠበቃ ጋር ቀረበ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርት ልጆስቲክስ - ነ/ፈ ቀረበ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ ነበሩ። አመልካች ባቀረቡት ክስ በተጠሪ ድርጅት ከታህሳስ 26/2000 - ጥር 29/2005 ዓ.ም ድረስ ለ5 አመት ከ1 ወር ስሰራ ቆይቼ ስራዬን በራሴ ፍቃድ ብለቅም፤ የስንብት፤ ለዘገየበት እና አበል አልተከፈለኝም በማለት እንዱከፈላቸው ጠይቀዋል። ተጠሪም በሰጠው መልስ አመልካች ያለደሞዝ የወሰደት እረፍት ከተጠናቀቀ ከህዲር 17/2005 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ሥራ ያልገቡ መሆኑን በመረዲቱ ከህዲር 17 /2005 ዓ/ም ጀምሮ ውላቸው መቋረጡን ፤ እና 5 አመት ያልሞላቸው በመሆኑ ያለማስጠንቀቂያ ስለሆነ ስንብት አይገባቸውም፤ ይገባቸዋል ከተባለም የማስጠንቀቂያ ግዜ 1 ወር ደሞዝና የቦንድ መግዣ ተቀንሶ ሉከፈላቸው ይገባል በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን ያየው ፍርድ ቤትም ተጠሪ የአመልካችን የስራ መልቀቅ ጥያቄ ከ29/6/2005 ጀምሮ ከተቀበለ እና ካሰናበታቸው በኋላ የስራ ውል ማቋረጫ ምክንያት መፈጸሙን አረጋግጫለሁ በማለት ላላ ደብዲቤ በመጻፍ ክፍያ አልፈጽምም የሚልበት ምክንያት አይኖርም በመሆኑም የ5 አመት ከ1 ወር የስንብት ክፍያ የቦንድ ተቀንሶ ተጠሪ ሉከፍል ይገባል በማለት ወስኗል። በቀጣይነት ጉዲዩን ያየው ፍርድ ቤትም ተጠሪ አመልካችን የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብል ቢያሰናብተውም፤ ድርጊቱ ስህተት ነው ብል ካመነበት ስህተቱን ለማረም ይችላል፤ አመልካችም ከህዲር 17 ቀን 2005 ጀምሮ በስራ ላይም አልተገኙም፤ በመሆኑም ተጠሪ ውል ማቋረጫ ምክንያት አግኝቻለው በማለት የስንብት አልከፍልም ማለቱ ባግባቡ ነው፤ በማለት የስር ውሳኔን ሽሮታል። የአመልካች አቤቱታም የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው። በመሆኑም አመልካች ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ቅሬታቸውን ሲገልጹ፤ ስራዬን የለቀቅኩት በጥር 29/2005 በጻፍኩት ደብዲቤ ሲሆን ተጠሪም የስንብት ደብዲቤ በሚያዝያ 11/2005 ሰጥቶኛል። ይሁን እንጂ በ17/03/2005 ነበር ወደ ስራ መመለስ የነበረብህ፤ ግንቦት 8/2005 ስህተት መፈፀሜን ተረዲሁ በማለት ጥር 29/2005 ያስገባውን ደብዲቤ አልቀበልም በማለት ከእረፍት በኋላ ወደስራ አልገባህም በማለት ከ ህዲር 17/2005 ጀምሮ ነው፤ መባለ አግባብ አይደለም። የተጠቀሰውም የሰበር ውሳኔ ከተያዘው ጉዲይ አይመሳሰልም። ሰራተኛውና አሰሪው የስራ ውላቸው ጸንቶ ባለበት የሚደረግ እርምት እንጂ፤ ከስራ በገዛ ፍቃደ ለለቀቀ ሰራተኛ ኪሉራንስ ተሰጥቶት ከ4 ወር በኋላ ስህተትን ማረም አይደለም። በመሆኑም በፍቃዳ ከተሰናበትኩ በኋላ ግንቦት 8/2005 የተጻፈውን፤
የተጠሪን ደብዲቤ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተቀብልት፤ አመልካች ከህዲር 17/2005 በኋላ ወደስራ ያለመግባቱ ተረጋግጦ እርማት መደረጉ ባግባቡ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤት መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ጠይቋል።
በዚህም መሰረት ችልቱም አመልካች የሥራ መልቀቂያ ለተጠሪ ሚያዝያ 11/2005 ዓ.ም ከሰጠው በኋላ፤ እንደገና ያለደሞዝ የወሰድከው ዕረፍት የተጠናቀቀው በ17/3/2005 ሆኖ ወደሥራ አልገባህም በማለት ከዚሁ ግዜ ጀምሮ የስራ ውለን ማቋረጡ፤ እና ጥር 17/2005 ክሉራንስ እንዱያዞር ከመፍቀደ አኳያ ስንብቱ ህጋዊ ነው መባለን በጭብጥነት በመያዝ የግራቀኙ በጽሁፍ መልስና የመልስ መልስ እንዱቀባበለ በማድረግ አከራክረዋል።
ተጠሪ በሰበር መልሱ የሚከራከረው፡- አመልካች እረፍታቸውን ጨርሰው ካልተመለሱ ማስታወቂያ በማውጣት ጥሪ በማድረግ ካልመጡ ውል ማቋረጡ የተሻለ ይሆን ነበር፤ ይህ ያለመደረጉ ምንም መብት አይፈጠርላቸውም እንጂ፤ ላላው ኪሉራንስ የተሰጣቸው አስተዲደሩ ስራ ላይ ነበሩ በሚል እምነት ነው፤ አመልካች ወደ ስራ መመለስ ከነበረባቸው 17/3/05 ጀምሮ እስከ ጥር 30/2005 ድረስ ወደስራ አልተመለሱም፤ በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 27/1/ ለ መሰረት ከ5 ቀን በላይ ስለቀሩ መሰናበታቸው ባግባቡ ነው፤ በመሆኑም ተጠሪ የፈጸመውን ስህተት ባወቀበት ጊዜ ማረሙና አመልካችን ማሰናበቱ አግባብነት ያለው በመሆኑ ስንብቱ ህጋዊ ነው መባለ የሚነቀፍ ባለመሆኑ ሉጸና ይገባል በማለት ይከራከራል። አመልካች በበኩለ፡- ከተጠሪ ጋር በአዋጅ 377/96 አንቀጽ 25 መሰረት በስምምነት የስራ ውላችንን ካቋረጥን በኋላ እና ተጠሪ ጥያቄዬን ተቀብል፤ ክሉራንስ አዞሬ እንድወጣ ከፈቀደና ውለ ከተቋረጠ ወድያ የሚታረም ነገር አይኖርም በማለት የስር ክርክሩን በማጠናከር የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ሉሻር ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ባጠቃላይ የክርክሩ አመጣጥ ከላይ የተገለጸውን ይመስላል። እኛም የግራቀኙን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌ አንጻር መዝገቡን መርምረናል።
በመሆኑም ከተያዘው ጭብጥ አንጻር የክርክሩን አጠቃላይ ሂደትና የስር ውሳኔዎችን እንዲየነው አመልካች በራሳቸው ፍቃድ የስራ መልቀቂያ በመጠየቅ ተጠሪም በጥያቄው መሰረት እንዱፈጸም ፈቅድና አመልካችን ካሰናበተ በኋላ፤ ያለማስጠንቀቂያ የሚያሰናብት ምክንያት አገኘሁ በማለት አስፈላጊውን ክፍያ አልከፍልም በማለቱ ነው። እንግዱህ ተጠሪ የሚለው አመልካች እረፍት በ17/2/2005 ወስደው ወደስራ መመለስ የነበረባቸው በ17/3/2005 ሆኖ ሳለ በቦታው ተገኝተው ስራ ባለመጀመራቸው እና በስህተት በጥር 30/2005 የቀረበውን የአመልካች መልቀቂያ ጥያቄ ተቀብለን ሚያዝያ 11/2005 እንዱፈጸም ብናደርግም ስህተት መሆኑን በመረዲታችን ከህዲር 17/2005 ጀምሮ ማሰናበታችን ባግባቡ ነው የሰበር ሰሚው አሰሪው ስህተቱን ማረም የሚችል መሆኑን ወስኗል በማለት ተከራክረዋል። በዚሁ መሰረት ጉዲዩን ያየው ፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን የስራ መልቀቂያ ተቀብል ካሰናበተው በኋላ ላላ ምክንያት አገኘሁ በማለት ድጋሜ ደብዲቤ መጻፍ ተገቢነት የለውም በማለት የስንብት ክፍያ ለአመልካች እንዱከፈላቸው ቢወስንም፤ የከፍተኛው ፍርድ ቤትም ጉዲዩን ካየው በኋላ ተጠሪ ስህተቱን ማረም ይችላል ሲል የአመልካች ስንብት ባግባቡ ነው በማለት የስር ውሳኔን ሽሮታል።
በዚህም መሰረት ተጠሪ ሉያርሙት የሚችለት ስህተት የትኛውን አይነት ስህተት ነው የሚለውን ስናይ የሰበር ውሳኔ ቁ. 45889 ከተያዘው ጉዲይ የማይገናኝ በመሆኑ መከራከሪያ ላሆን አይገባም። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ የአመልካችን የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብልና ለአግባብነቱም ምላሽ ሰጥቶ ካሰናበታቸው እና የክፍያ ጥያቄ ሲቀርብለት ከወራት በኋላ ወደኋላ ተመልሶ ስህተት መፈጸሜን ተረዲሁ ማለቱ ባለቀ ጉዲይ ስህተት ማፈላለግ ካልሆነ በቀር፤ ተጠሪን የመሰለ ድርጅት አስተዲደራዊ ስራውን ባግባቡ ባለመወጣት በፈጸመው ጉዲይ የአዋጁን ቁ 377/96 አንቀጽ 27/1//ለ/ን ጠቅሶ ለመከራከር መሞከሩ አግባብነት የለውም። ምክንያቱም ተጠሪ እረፍት የሰጠውን ሰራተኛ በተባለው መመለሻ ጊዜ ካልገባ ምን ላደረግ እንደሚገባ ሳያውቅ የአመልካችን መልቀቂያ ያስተናግዲል ተብልም የሚታሰብ አይሆንም። ባጠቃላይ የመጀመሪያው ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን ጥያቄ በፍሬ ነገር ደረጃ በማረጋገጥ ክፍያ እንዱከፈላቸው የወሰነው ውሳኔ በከፍተኛው ፍርድ ቤት አግባብነት የላለው አሰሪ ስህተቱን ማረም ይችላል ተብል የተወሰነው አስገዲጅ ውሣኔ ተጠቅሶ መሻሩ ሉታረም የሚገባው ነው ብለናል።
በመጨረሻም የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከስንብት በኋላ የተሰጠውን የውል ማቋረጫ ምክንያት በመቀበል ተጠሪ ስህተቱን ማረም ይችላል በማለት የስር ውሳኔን መሻሩ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ.139381 በቀን 13/12/06 ዓ/ም የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ. ህዲር 16/2006 የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለአመልካች የስንብት ክፍያ ብር 7,540.50 ይከፈላቸው በማለት የወሰነው ጸንቷል።
የግራቀኙ የወጪ ኪሳራቸውን ይቻቻለ ብለናል።
No topics extracted.