አንድ ሰራተኛ በአሰሪው የሚሰጠውን ትእዛዝ የመፈጸም ግዳታ ያለበት ስለመሆኑና ሳይፈጽም ቢቀር ካለማስጠንቀቂያ ከሥራ የሚያሰናብት በቂ ምክንያት ስለመሆኑ አዋጅ 377/1996 አንቀፅ 13/1/2/ እና /7/ እና 27/1/ ሸ/ 108789 ሴንቸሪ ጀኔራል ትሬዱንግ ኃ/የተ/የግል ማህበር እና አቶ ገስጥ ንጉሴ ሚያዚያ 10/ ቀን 2007 ዓ.ም 20 6. በየመስሪያ ቤቱ የሚቋቋሙ የዱሲፕሉን ኮሚቴዎች በህግ አግባብ የሚቋቋሙና የሰራተኛው ጥቅም ያለአግባብ እንዲይጎዲ ተገቢው መጣራት ተደርጎ እርምጃ እንዱወሰድ እገዛ የሚያደርጉ ናቸው ተብል የሚታመን ስለሆነ የዱሲፕሉን ኮሚቴ ውሳኔ ዋጋ ሉያጣ የሚገባው ተገቢው ማስረጃ ቀርቦ ህጋዊ ያለመሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 ንዐስ አንቀፅ 1/ሸ/ እና አንቀፅ 12/2/(7) III
No summary available.
ሚያዚያ 28 ቀን 2007 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- የኢትዮጵያ አካል ጉዲተኞች ብሓራዊ ማህበራት ኮንፋደሬሽን - ጠበቃ እሸቴ ጓንጉል - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ እመቤት ኤርሚያስ - ቀረቡ።
መዝገቡ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካች የስንብት እርምጃ ሕገ ወጥ ነው ተብል የተሰጠው ውሳኔ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመጽናቱ በውሳኔው ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 “ን” መሰረት ያደረገ የግል የስራ ክርክር ሁኖ አንድ ሰራተኛ በስራ ላይ የዱስፕሉን ጥፊት ፈፅሟል ተብል ከስራ ያለማስጠንቀቂያ የሚሰናበትበትን የሕግ አግባብ የሚመለከት ነው።
በስር ፍርድ ቤት የቀረበው የተጠሪ ክስ በአመልካች ማህበር ውስጥ በወር ብር 4,500.00 (አራት ሺህ አምስት መቶ) እየተከፈላቸው በሂሳብ ሰራተኝነት የስራ መደብ ከመስከረም 05 ቀን 1990 ዓ.ም ጀምሮ ሲያገለግለ ቆይተው አመልካች ማህበር የዱስፕሉን ጥፊት ፈጽመዋል በሚል ምክንያት በሕገ ወጥ መንገድ ከስራ ያሰናበታቸው መሆኑን ዘርዝረው ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ተብል የካሳ፣የስራ ስንብት፣የማስጠንቀቂያ ጊዜ እና ክፍያ ለዘገዬበት ክፍያ እንዱከፈላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን ያሳያል። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ተጠሪ የተለያዩ የዱስፕሉን ጥፊቶችን መፈፀማቸውን በመግለጽ ጥፊቶችም፡- ተጠሪ የስራ መደባቸው አካውንታት ሆኖ እያለ ከስራ ድርሻቸው ውጪ መጠኑ ብር 9000.00 (ዘጠኝ ሺህ ብር) የሆነ ገንዘብ ከአምስት ወራት በላይ በእጃቸው ላይ ያቆዩ መሆናቸውን፣ተጠሪ ይህን በእጃቸው ያቆዩትን ብር 9000.00 (ዘጠኝ ሺህ ብር) በስራ ላይ እንደዋለ በማስመሰል የተሳሳተ ሪፖርት ማቅረባቸውንና ይህንኑ በእጃቸው የቆየውን ገንዘብ ባንክ እንዱያስገቡ ሲታዘዙ ትዕዛዝ ያለመቀበላቸው፣የስራ አመራር ቦርድ ሳይፈቅድ የአመልካች ማህበር ተ/ዋና ስራ አስኪያጅ ለሆኑት አቶ ተሾመ ዳሬሳ በየወሩ ከሰኔ ወር 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 2005 ዓ.ም ድረስ ብር 430.00 በድምሩ ለአራት ወራት ብር 1720.00 (አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሃያ ብር) መክፈላቸው፣ለፋዳሬሽኑ አትክልተኛ ለአቶ መዝገቡ ገላው ሐምል ወር 2004 ዓ.ም ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) መክፈላቸው፣ለአመልካች ማህበር የሕዝብ ግንኙነት ሰራተኛ አቶ ደረሰ ታደሰ ከሰኔ ወር 2004 ዓ.ም እስከ መስከረም 2005 ዓ.ም ብር 130.00 በየወሩ በድምሩ 520.00 (አምስት መቶ ሃያ ብር) ጭማሪ በማድረግ መከፈላቸው፣በአመልካች የክልለ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች አስተባባሪዎች እጅ ብር 9000.00 (ዘጠኝ ሺህ ብር) የያዘ ሰደን ከሚያዝያ 19 ቀን 2004 ዓ.ም እስከ ህዲር 14 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ሳያወራረድ እንዱቆይ በቃል መፍቀዲቸው፣ተጠሪ በተለያዩ ግለሰቦች ክፍያ ሲፈፅሙ ተቀናሽ የሚደረግ ዊዝሆልዱንግ ታክስ 2 %) ከሐምል ወር 2003 ዓ.ም እስከ መስከረም ወር 2005 ዓ.ም ድረስ ብር 17,092.70 (አስራ ሰባት ሺህ ዘጠና ሁለት ብር ከሰባ ሳንቲም) በወቅቱ ለግብር አስገቢው መስሪያ ቤት ገቢ ያለማድረጋቸው፣ህዲር 04 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ከአስተደደርና ፊይናንስ ኃላፉ ቢሮ በኮምፒዩተር ላይ ተሰክቶ የነበረ 4GB የፍላሽ ዱስክ ያለ አመልካች ማህበር ፈቃድ መውሰዲቸው፣የቅጥር ውል ላልተፈፀመላቸውና ላልታደሰላቸው ሰራተኞች ደመወዝ መክፈላቸው፣ግዥዎች በእቅድ ከተያዘው በጀት በላይ እንዱፈፀሙ ማድረጋቸው፣ከፊይናንስ ውጪ ሰነድ ማዘጋጀታቸው፣ከአለም አቀፍ የሥራ ድርጅት የተገኘውን ብር 184,206.00 “ወርልድ ለርኒግ” ከተባለ ድርጅት የተገኘ በማስመሰል በጀት ምንጩን በማሳሳት መመዝገባቸው፣አመልካች ድርጅት ምንም እዲ ሳይኖርበት በስራ ማስኪያጃ 19,000.00 (አስራ ዘጠኝ ሺህ ብር) ከተለያዩ ወጪዎች ብር 162,000.00 (አንድ መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ) እዲ ያለበት መሆኑን አስመስለው መግለፃቸው፣ተጠሪ የአመልካችን ብር 500.00 እዲ እያለባቸው ለአንድ አመት ያህል ገቢ ያለማድረጋቸው ስለመሆናቸው ዘርዝሮ እና ከእነዚህ ጥፊቶች በዱስፕሉንና ኮሚቴ ውሳኔና በኦዱት ሪፖርት መረጋገጣቸውን ጠቅሶ የስራ ስንብቱ ሕጋዊ ነው በማለት ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል።
የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የፋዳሬሽን ተ/ዋና ስራ አስኪያጅና አትክልተኛ ደመወዝ እንዱጨመር ከሚመለከታቸው አካላት የደረሳቸውን የደመወዝ ዝርዝርና በአመልካች መስሪያ ቤት ይገኛል የተባለውን ሰነድ እንዱቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቶ ሰነደ ከቀረበለትና ከተጠሪ እጅ ያለውን ቀሪ ሁለ ከተመለከተ በኃላ ጉዲዩን መርምሮ ተጠሪ የፈፀሙት የዱስፕሉን ጥፊት የለም ወደ ሚለው ድምዲሜ ደርሶ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው በማለት የካሳ ክፍያ፣የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ፣ክፍያ ለዘገዬበት ክፍያና የሁለት አመት ፈቃድ እንዱከፍላቸው፣የስራ ስንብት ግን የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚና የተከፈላቸው በመሆኑ አይከፈላቸው ሲል ወስኗል።
አመልካች ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው። የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈል ተብል በተወሰነው የውሳኔ ክፍል ቀጥተኛ የይግባኝ አቤቱታ፣ተጠሪ ደግሞ በድርጅቱ ከአስራ አምስት አመት በላይ አገልግለው ለሰባት አመታት ለአገለገለት ጊዜ የፕሮቪደንት ፈንድ ተጠቃሚ መሆናቸው ለቀሪዎቹ አመታት የሥራ ስንብት ክፍያ እንዲገኙ መደረጉና የአመት ፈቃድም ሲተላለፍ የቆየ ሁኖ እያለ የሁለት አመት ብቻ ታስቦ እንዱከፈላቸው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው በሚል መስቀለኛ የይግባኝ አቤቱታ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኃላ ጉዲዩን መርምሮ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙለ በሙለ አጽንቶታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- ተጠሪ ስራቸውን ሲሰሩ ከአስራ አምስት በላይ የዱስፕሉን ግድፈት የፈፀሙ ስለመሆኑ በሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጦ እያለ ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ በስራቸው ላይ ጥፊት የፈፀሙ ስለመሆኑ በኦዱት ሪፖርትና በአመልካች መስሪያ ቤት የዱስፕሉን ኮሚቴ ተጣርቶ ተረጋግጦ ሳለ የሥር ፍርድ ቤቶች ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው በማለት የተለያዩ ክፍያዎች ለተጠሪ እንዱከፈለ የመወሰናቸውን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበውም ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል። እንዱሁም የስር ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ እንዱቀርብ ተደርጓል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን ከግራ ቀኙ ክርክር፣ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንጻር ጉዲዩ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አኳያ እንደሚከተለው መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ተጠሪን አሰናበትኩ የሚለው አስራ አምስት ያህል የዱስፕሉን ግድፈቶችን ተጠሪ ስለመፈጸማቸው ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ሲሆን ይህንኑ ለማስረዲትም የፋዳሬሽኑ የአስተዲደር ማኑዋል በሚያዘው መሰረት የተቋቋመው የዱስፕሉን ኮሚቴ የሰጠውን ውሳኔና የኦዱት ሪፖርት ሰነድ በማስረጃነት አቅርቧል። የፋዳራለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ሆነ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአመልካች በኩል የቀረቡትን እነዚህን የሰነድ ማስረጃዎች የማስረጃነት ዋጋ ሳይሰጡ አልፈዋል። የበታች ፍርድ ቤቶች የዱስፕሉን ኮሚቴውን የውሳኔ ሰነድ ያልተቀበለት ተጠሪ ሰነደን ባለማመን ፍርድ ቤት ክስ ማቅረባቸውን በመጥቀስ ሲሆን የኦዱት ሪፖርቱን ደግሞ የስራ ስንብቱ ከተደረገ በኃላ የተጠቃለለ በመሆኑ የተጠሪ የዱስፕሉን ግድፈት መኖሩ ታውቆ ስንብቱ ተደርጓል በማለት የሚያስችል አይደለም የሚለውን አብይ ምክንያት ከአሰፈሩ በኃላ በተጨማሪነት የኦዱት ሪፖርቱ ከቀድሞ ሰራተኛ ያልተሰራ ስራ መኖሩን ገልጾ በተተኪ ሰራተኛ ሉሰራ እንደሚገባ መገለጹ ከሂሳብ አሰራር ጉድለት ጋር ተያያዥ የሆኑትን ሰራተኛ ማንነት የማይገልጽና የማያብራራ ነው፣ኦዱት ሪፖርቱ በተራ ቁጥር 4.8፣4.3 እና 4.9 የተዘረዘሩት ካልሆነ በስተቀር ቀሪዎቹ የኦዱት ሪፖርት ይዘቶች ከቀረቡት መከራከሪያ ነጥቦች ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ተያያዥነት የላላቸው ናቸው፣የኦዱት ሪፖርት ተራ ቁጥር 5 ስር የሂሳብ ሰራተኛዋ የብቃት ችግር ያለባቸው መሆኑን መግለጹም ለስንብቱ ምክንያት የተባለው የዱስፕሉን ጉድለት በመሆኑ አግባብነት የላለው ነው የሚለትንና የደመወዝ ጭማሪ አከፊፈል በተመለከተ ደግሞ ተጠሪ በሚመለከተው አካል ተፈቅድ የፈፀሙት መሆኑን አረጋግጠዋል የሚለ ምክንያቶችን አስፍሮ ነው።
በመሰረቱ አንድን ፍሬ-ነገር ለማስረዲት በተከራካሪ ወገኖች ተቆጥሮ የቀረበ የሰነድ ማስረጃ በህጉ ተቀባይነት የለውም (inadmissible) ወይም ከተያዘው ፍሬ-ነገር ጭብጥ ጋር አግባብነት የለውም እስካልተባለ ድረስ ሰነደ በማስረጃነት ተመርምሮ እንዱሁም ከላልች ማስረጃ አይነቶች ጋርም በአንድነት ታይቶና ተመዝኖ የሚገባው ዋጋ ሉሰጠው ይገባል። ምክንያቱም በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 138 ስር እንደተመለከተው በህግ አግባብ የተቆጠረው ማስረጃ በዝምታ የሚታለፍበት ወይም ከሕግ ውጪ የማስረጃነት ዋጋ ሳይሰጥ ውድቅ የሚሆንበት አግባብ የለምና። የሥር ፍርድ ቤት ይህንኑ በፍትሐብሄር ስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከተውን የማስረጃ አቀራረብና አቀባበል ደንብ ያለፈው በአመልካች በኩል የቀረበው የዱስፕሉን ኮሚቴ ውሳኔ የሰነድ ማስረጃ በተጠሪ እምነት ያላገኘና ፍርድ ቤት ክስ ያቀረበበት ጉዲይ ነው በሚል ነው። ይሁን እንጂ አመልካች ያቀረበው ይኼው ሰነድ የፋዳሬሽኑ የአስተዲደር ማኑዋል በሚያዘው መሰረት በተቋቋመው ኮሚቴ ተጠሪ ተገቢውን ምላሽ እንዱሰጡበት ተደርጎና ተገቢነት አላቸው የሚሎቸው ማስረጃዎች ቀርበው በተጠሪ ተፈጸሙ የተባለትን ጥፊቶች መኖራቸውን፣ተጠሪም በዱስፕሉን ኮሚቴው ጥፊቶችን ማመናቸውን በማረጋገጥ የተሰጠ መሆኑን የሰነደ ይዘት በግልፅ ያሳያል ። ይህ ማስረጃ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ማስረጃ ሲሆን የማስረጃነት ዋጋ ሉያጣ የሚችለው ተጠሪ በፍርድ ቤት ክስ በማቅረባቸው ወይም ሰነደን ባለማመናቸው ሳይሆን ሰነደ በፋዳሬሽኑ የአስተዲደር ማኑዋል መሰረት ባልተቋቋመ የዱስፕሉን ኮሚቴ የተዘጋጀ፣ወይም ዱስፕሉን ኮሚቴው ከሕግ ውጪ ማስረጃውን በመስማትና በመመዘን ያልተገባ ድምዲሜ ይዞ የሰጠው ውሳኔ መሆኑን ተጠሪ በፍርድ ቤት ላይ በሚያቀርቡት ክርክርና ማስረጃ የአመልካችን ማስረጃ ሲያስተባብለ እንጂ እንዱሁ በደፈናው ማስረጃውን አላመኑም፣ፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል በሚል ምክንያት አይደለም። በየመስሪያ ቤቱ የሚቋቋሙ የዱስፕሉን ኮሚቴዎች በሕግ አግባብ የሚቋቋሙና የሰራተኛው ጥቅም ያላግባብ እንዲይጎዲ ተገቢው መጣራት ተደርጎ እርምጃ እንዱወሰድ እገዛ የሚያደርጉ ናቸው ተብል የሚታመን ሲሆን የዱስፕሉን ኮሚቴ ውሳኔ በማስረጃነት ዋጋ ሉያጣ የሚገባው ተገቢው ማስረጃ ቀርቦ ሕጋዊ ያለመሆኑ ሲረጋገጥ ነው። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካች መስሪያ ቤት ያቀረበውን የዱስፕሉን ኮሚቴ የውሳኔ ሰነድ የማስረጃነት ዋጋ ያሳጡት ተጠሪ ተገቢውን ማስረጃ አቅርበው ሰነደ ሕገ ወጥ መሆኑን ሳያስረደና ይህንኑ ለማስረዲትም በሕግ አግባብ የቆጠሩት ማስረጃዎች ሳይኖር ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤትን ዋና መዝገብ አስቀርበን ከጠቅላላ የግራ ቀኙ የክርክር ሂደት ተገንዝበናል።
የኦዱት ሪፖርቱን በተመለከተም ኦዱት የተደረገው እ.ኤ.አ ከጃንዋሪ 1/2011 እስከ ኦክቶበር 31/2012 ድረስ ያለው የአመልካች ማህበር ዝርዝር ሂሳብ ሁኖ ሪፖርቱ በተጠቀሱት 22 ወራት ውስጥ የታዬውን የሂሳብ አያያዝ ችግር ከዝርዝር ከማስቀመጡ በፉት የ2012 በቀድሞዋ የሂሳብ ሰራተኛ ያልተሰራ መሆኑ፣በተተኪው ሰራተኛ ሉሰራ የሚገባ እና ይህም የተጀመረ መሆኑን በመግቢያው ላይ ያሰፈረ መሆኑን ሰነደ ያሳያል። የኦዱት ሪፖርቱ የተጠቃለለው በእርግጥ ጥር 14 ቀን 2005 ዓ.ም ስለመሆኑ ሰነደ የሚገልጽ ሲሆን ስንብቱ የተከናወነው ደግሞ ጥር 10 ቀን 2005 ዓ.ም መሆኑን የስንብት ደብዲቤው ያሳያል። ይሁን እንጂ ኦዱት በተደረገበት ጊዜ የሂሳብ ስራው የሚመለከተው ተጠሪን ስለመሆኑ አመልካች በክሱ የጠቀሰ ሲሆን ተጠሪም ቢሆኑ የኦዱት ስራው ራሳቸውን የሚመለከት ሁኖ በውጤቱ ግን ተጠያቂ ያላደረጋቸው መሆኑን ጠቅሰው አመልካች አለኝ የሚለው ይሄው የሰነድ ማስረጃ በፍርድ ቤት እገዛ እንዱቀርብላቸው በማስረጃ ዝርዝር መግለጫቸው ላይ የጠቀሱ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት ዋና መዝገብ ውስጥ ያለት ሰነድች የሚያሳዩት ሐቅ ሲሆን የስንብት ደብዲቤው መሰረት ያደረገው የዱስፕሉን ኮሚቴውን ውሳኔ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሲታይ በዚህ ውሳኔ መሰረት ተጠሪ በ17 የዱስፕሉን ክሶች ተከሰው በ15ቱ ጥፊተኛ ሁነው የዱስፕሉን ኮሚቴ ማግኘቱን፣ጥፊቶቹም ከባድ መሆናቸውን ጭምር የሚገልጽ ነው። እንዱህ ከሆነ ተጠሪ በአመልካች መስሪያ ቤት ላይ ክስ ያቀረቡት መጋቢት 09 ቀን 2005 ዓ.ም እንደመሆኑ መጠን አመልካች ስንብቱ ሕጋዊ ነው የሚልባቸውን ምክንያቶች በዱስፕሉን ኮሚቴው ውሳኔና ይህንኑ የሚደግፊትን ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ላልች የሰነድ ማስረጃዎችን በማስረጃነት ቢያቀርብ ከስንብቱ በኃላ የተገኘ ማስረጃ ነው ተብል የማስረጃነት ዋጋ የሚያጣበት የማስረጃ አቀራረብና አቀባበል ደንብ የለም። አንድ ማስረጃ ለአንድ ጉዲይ ላቀርብ አይገባም ተብል ውድቅ መደረግ ያለበት ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ሁኖ ሲገኝ ወይም በሕጉ ለማስረጃነት እንዱቀርብ ተለይቶ የተቀመጠ የማስረጃ አይነት መኖሩ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
ከዚህ አንጻር ጉዲዩን ስንመለከተው የበታች ፍርድ ቤቶች የተጠሪን የዱስፕሉን ኮሚቴ ውሳኔን እና የኦዱት ሪፖርት ማስረጃዎችን ውድቅ ያደረጉት ተገቢውን የማስረጃ አቀራረብና አቀራረብ ስርዓት ተከትል ያለመሆኑን ተገንዝበናል። እነዚህ ማስረጃዎች የማስረጃነት ዋጋ አላቸው ከተባለ ደግሞ በማስረጃዎቹ የተረጋገጡት የዱስፕሉን ጥፊቶች ከባድ መሆናቸውንና የተደጋገሙ መሆኑን የሚገልፁና ተጠሪ ስራቸውን በአግባቡ የማይወጡ የነበሩ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።
ተጠሪ ከባድ የዱስፕሉን ግድፈቶች ሲፈጽሙ የነበረ ከሆነና ጥፊቶችም ተደጋጋሚ መሆናቸው ግልጽ ከሆነና አመልካች በተጠሪ የስራ ግዳታቸውን በአግባቡ ባለመወጣት ስራው በአግባቡ ያልተሰራለት፣በገንዘብ ጥቅሙ ጉዲት የደረሰበት መሆኑ ከተረጋገጠ በአመልካች ማህበር የገንዘብ ጥቅም ላይ ጉዲት ያለመደረሱን የማስረዲት ግዳታ የተጠሪ ነው። በዚህ ጉዲይ ግን ተጠሪ የአመልካች የሰነድ ማስረጃዎች የተጠሪን ጥፊት የሚያረጋግጡ አይደለም ከማለት ውጪ ይህንኑ የሚያስረዲ ማስረጃ ያለማቅረባቸውን የሥር ፍርድ ቤትን ዋና መዝገብ በማስቀረብ ከክርክሩ ሂደት ለመገንዘብ ችለናል። ተጠሪ የፈፀሙት ጥፊት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 ንዐስ አንቀጽ 1/ሸ/ የሚሸፈንና የተጠሪን የሥራ ውል ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ የሚያስችል በቂ ምክንያት ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች በተጠሪ የተፈፀመ ጥፊት የለም በማለት ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው ሲለ የሰጡት ውሣኔ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/1/ሸ/ እና አንቀጽ 12(2) (7) ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘት፣መንፈስ አላማ ያላገናዘበ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከዚህ አንፃር ሲታይ አመልካች የተጠሪን የሥራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ ማቋረጡ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27(1(ሸ)) እና 12(2)(7) ድንጋጌዎች መሰረት ሕጋዊ እንጂ ሕገ ወጥ ተግባር ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች የተጠሪን የሥራ ውል ያቋረጠው ከሕግ ውጭ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስለአገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ህዲር 19 ቀን 2006 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 30 ቀን 2006 ዓ.ም ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
የአመልካች እርምጃ ሕጋዊ ነው፣አመልካች ለተጠሪ ካሳም ሆነ የሥራ ስንብት ክፍያ፣የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያ ሉከፍል አይገባም ብለናል።
የዓመት እረፍት የ57 ቀናት ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ብር 8,550.00 (ስምንት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ብር) እና ይህንኑ ክፍያም ያላግባብ ያዘገዬ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ መሰረት የአንድ ወር ደመወዝ ብር 4,500.00 (አራት ሺህ አምስት መቶ) ይክፈል ብለናል።
ለክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ት እ ዛ ዝ ጥቅምት 26 ቀን 2007 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው እግድ ተነስቷል። ይፃፍ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.