የአንድ ድርጅት ሰራተኛ በሰራው ጥፊት ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውለ ቢቋረጥም ያልወሰደው የዓመት እረፍት ካለ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ሉከፈል የሚገባው ስለመሆኑና የፕሮቪደንት ፈንድም በከፈለው ልክ የማግኘት መብት ያለው ዲሽን ባንክ እና እነ ተፈሪ አሳልፈው /ሦስት ሰዎች/ II
No summary available.
/ መጋቢት 30 ቀን 2007 ዓ/ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፊ አህመድ ተኽሉት ይመሰል አመልካች፡- ወ/ሪት ሸዊት ኃይለ - VC - ስላልሰራ ማረጋገጥ አልተቻለም።
ተጠሪ፡- መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራዝ - ነ/ፈጅ ደረጀ ከበደ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
አዋጅ ቁጥር 377/96 “ን” መሰረት አድርጎ የቀረበ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በደጉዓ ተምቤን ወረዲ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በተጠሪ ድርጅት ውስጥ በካሼር የስራ መደብ ላይ በወር ብር 1744.00 እየከፈላቸው ከሰኔ 27 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሀምላ 25 ቀን 2005 ድረስ ቀጥሮ ሲያሰራቸው እንደቆዩና ከህግ ውጪ የስራ ውለ ያለማስጠንቀቂያ በአሰሪው ድርጅት የተቋረጠ መሆኑን ገልጸው የተለያዩ ክፍያዎች እንዱከፈሎቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለክሱ በሰጠው መልስም፡- የስራ ውለ የተቋረጠው አመልካች ታህሳስ 17 ቀን 2005 ዓ/ም ባቀረቡት መልቀቂያ መሰረት መሆኑን ጠቅሶ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመመርመር አመልካች ታህሳስ 17 ቀን 2005 ዓ/ም ባስገቡት የስራ ውል መነሻ ግንኙነቱ መቋረጡን ገልጾ ስንብቱ ሕጋዊ ነው በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ የአሁኗ ተጠሪ ለምስራቅ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ተቀባይነት አላገኙም። ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታቸውን አቅርበውም ችልቱ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ስንብቱ በአመልካች ጥያቄ መሰረት የተደረገ በመሆኑ ሕጋዊ ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በድምጽ ብልጫ አጽንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካች ታህሳስ 17 ቀን 2005 ዓ/ም ስራውን ለመልቀቅ ለተጠሪ ድርጅት መልቀቂያ አስገብተው ቆይ ተብለው ለሰባት ወራት ያህል ስራ እንዱሰሩ ከተደረገ በኋላ የስራ ውለን ከሰባት ወራት በፉት በቀረበ ማመልከቻ መነሻ ተቋርጧል ተብል ስንብት መደረጉና ሁለም ክፍያዎች ውድቅ መደረጋቸው ያላግባብ ነው የሚል ነው።አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርቦ ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምሮታል። እንደመረመረውም ተጠሪ ከአመልካች ጋር የነበረውን የስራ ውል ያቋረጠው በአመልካች የስራ መልቀቂያ ጥያቄ ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በአመልካችና በተጠሪ መካከል በ17/04/2005 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ የስራ መልቀቂያ እንዱሰጣቸው ለተጠሪ ጥያቄ አቅርበው ተጠሪም የአመልካችን ጥያቄ አቆይቶ አመልካች ለሰባት ወራት ምድብ ስራቸው ላይ እየተገኙ ስራውን እንዱሰሩና ግዳታቸውን እንዱወጡ ሲያደርግ ቆይቶ ከነሐሴ ወር 2005 ዓ/ም ጀምሮ የአመልካች የወር ደመወዝ ሳይያዝና ስማቸው ከአቴንዲንስ ተሰርዞ በአመልካች የስራ መደብ ላይ ላላ ገንዘብ ያዥን በመመደብ አመልካች በ17/04/2005 ዓ/ም ያስገቡትን የስራ መልቀቂያ በመጥቀስ የስራ ውለን ያቋረጠ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ የስራ ውል ሁለት ወገኖች አንደ አሰሪ ላላኛዉ ሰራተኛ ሆነው በአሰሪው ቁጥጥር እያደረገ ሰራተኛው ለሚሰራለት የጉልበት ወይም የዕወቅት ስራ ደሞዝ የሚከፍልበት የስራ ግንኙነት የሚፈጥር ስምምነት ስለመሆኑ ከአዋጅ ቁጥር 377/96 በአንቀጽ 4/1/ ስር ከተደነገገው ድንጋጌ ይዘት የምንረዲው ጉዲይ ነው። በዚህ የህጉ የትርጉም ይዘት መሰረት ከሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች አንደ በሕጉ መሰረት አሰሪ ነው ተብል የሚወሰድ ሲሆን ይህ ወገን ለሚያገኘው አገልግልት ተገቢውን ደሞዝ የሚከፍልና አገልግልቱም በእርሱ ቁጥጥር የሚመራ መሆኑ፣ሰራተኛ ደግሞ በአሰሪው ቁጥጥር መሰረት አገልግልት የሚሰጥ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። የስራ ውለ መኖሩ ደግሞ በማናቸውም አይነት ሉረጋገጥ የሚችል ነው። በሕጉ አግባብ የተመሰረተ የስራ ውል ደግሞ የሚቋረጥባቸው መንገድች ስለመኖራቸው ሕጉ ያስቀመጠው ጉዲይ ነው። በአዋጅ ቁጥር 377/96 የስራ ውል ስለሚቋረጥበት ምክንያቶችና ሁኔታዎችን በአንቀጽ 23 ስር ተመልክተዋል። እነዚህም በሰራተኛው አነሳሽነት የሚደረግ፣ በሕግ በተደነገገው መሰረት፣በህብረት ስምምነት መሰረት እና በተዋዋይ ወገኖች ስምምነት የሚደረግ የውል ማቋረጥ ሲሆኑ ዝርዝር ምክንያቶቻቸውና ሁኔታዎችንም ህጉ አስቀምጧል። በአሰሪው አነሳሽነት የሚደረግ የስራ ውል መቋረጥ እንደየሁኔታው በማስጠንቀቂያ ወይም ያለማሰጠንቀቂያ ላደረግ የሚችል ሆኖ የምክንያቶቹ ዝርዝር እና አፈጻጸሙ በአዋጁ አንቀጽ 26 እስከ 30 ባለት ድንጋጌዎች ስር በግልጽ ተቀምጧል። ላላው በህጉ በዝርዝር የተቀመጠው የስራ ውል ማቋረጥ ስርዓት በሰራተኛው አነሳሽነት የሚደረገው ሲሆን ይህም በአሰሪው አነሳሽነት ላደረግ እንደሚችለው በማስጠንቀቂያ እና ያለማሰጠንቀቂያ ውለን ሰራተኛው የሚያቋርጥበት መንገድ ስለመኖሩና ውለን ለማቋረጥ የሚቻልባቸው ሁኔታዎቹና ምክንያቶቹን ዘርዝሮ የያዘ ነው። እነዚህ ሁኔታዎችና ምክንያቶቹ በአዋጁ ከአንቀጽ 31 እስከ 33 ድንጋጌዎች ስር በግልጽ ተደንግገው ይገኛለ።
እንግዱህ ሕጉ የስራ ውለ ሉቋረጥ የሚችልባቸውን መንገድች በዝርዝር ከአስቀመጠ በግራ ቀኙ መካከል ክርክር ሲነሳም ውለ የተቋረጠበትን መንገድ ሕጋዊ መሆን ያለመሆኑ ተለይቶ ዲኝነት መሰጠት ያለበት በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ነው።
በተያዘው ጉዲይ በአመልካችና በተጠሪ ከሰኔ 27 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ ህጋዊ የስራ ውል መኖሩ ግራ ቀኙን ያላከራከረ ሲሆን ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው ጉዲይ ይኼው ውል የተቋረጠው በማን አነሳሽነት ነው? የሚለው ነው። ተጠሪ አመልካች ታህሳስ 17 ቀን 2005 ዓ/ም ያስገቡትን የስራ መልቀቂያ መሰረት አድርጎ የስራ ውለን ማቋረጡን ያልካደው ሲሆን አመልካችም ታህሳስ 17 ቀን 2005 ዓ/ም የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን ሳይክደ መልቀቂያው ሳይሰጣቸው ቆይቶ የስራ ግዳታቸውን እየተወጡ እስከ ሰኔ ወር 2005 ዓ/ም ድረስ ያለው ደመወዝም እየተከፈላቸው ስራቸውን ሲሰሩ የቆዩ መሆኑን ገልጸው የስራ መልቀቂያ ጥያቄአቸው በተጠሪ ምክንያት ተግባራዊ ያለመሆኑን ጠቅሰው ተከራክረዋል። ከዚህ መረዲት የሚቻለው የተጠሪ የስራ ስንብት የተከናወነው አመልካች የስራ መልቀቂያ ከአስገቡ ከሰባት ወራት በኋላ መሆኑንና መልቀቂያው ለሰባት ወራት የቆየው በአመልካች ፍላጎት ስላለመሆኑ ነው። በልላ አገላለጽ አመልካች መልቀቂያውን ያነሱ ስላለመሆናቸው በተጠሪ በኩል የተረጋገጠ ነገር የለም። የአመልካች የስራ መደብ ላይ ተገቢው ሰራተኛ ባለመገኘቱ ሰራተኛ እስከሚገኝ ድረስ አመልካች በስራቸው ላይ እንዱቆዩ የተደረጉ ስለመሆኑና ስራተኛው ሲገኝ መልቀቂያው የሚሰጣቸው ሰለመሆኑ በተጠሪ በኩል የቀረበ ግልጽ ክርክርና ማስረጃ ያለመኖሩን ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል። አመልካች የስራ መልቀቂያ ከአስገቡ በኋላ ለረዥም ወራት እንደ ሰራተኛነታቸው በሕጉ የተጣለባቸውን የስራ ግዳታ ሲወጡ መቆታቸውና ተጠሪም ለአመልካች ስራ እየሰጠና ደመወዝም እስከ ሰኔ ወር 2005 ዓ/ም ድረስ እየከፈለ መቆየቱ ሲታይ ግራ ቀኙ በነጻ ፍላጎታቸው የቀደመውን የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት እንዱቀጥል የተስማሙ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በዚህ አግባብ እንዱቀጥል የተደረገ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ደግሞ በተግባር ቀሪ በሆነው የስራ መልቀቂያ ጥያቄ በሕጉ የተቀመጠውን ስርዓት ሳይከተል ሉቋረጥ የሚችልበት አግባብ የለም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች ጉዲዩን ከዚህ አንፃር መመልከት ሲገባቸው አመልካች ስራውን የለቀቁት በራሳቸው ተነሳሽነት ነው በሚል የሰጡት ውሳኔ የስራ ውል አመሰራረት፣ውለ የሚቋረጥባቸውን ሁኔታዎችና ምክንያቶችን እንዱሁም በሕጉ የተቀመጡትን ስርዓቶችን ያላገናዘበ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በደጉዓ ተምቤን ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ ህዲር 23 ቀን 2006 ዓ/ም ተሰጥቶ በምስራቃዊ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 01 ቀን 2006 ዓ/ም፣በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ግንቦት 23 ቀን 2006 ዓ/ም በአብላጭ ደምጽ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ አመልካችን ያሰናበተው በራሱ ተነሳሽነት እና ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ነው ብለናል። በዚህም ምክንያት ተጠሪ ለአመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 39 እና 40(2) መሰረት የስራ ስንብት ክፍያ፣ በአንቀጽ 43(4(ሀ)) መሰረት የካሳ ክፍያ፣ በአንቀጽ 35(1(ለ)) መሰረት የማስንጠቀቂያ ጊዜ ክፍያ እና በአንቀጽ 38 መሰረት ክፍያ ለዘገዬበት ክፍያ የሁለት ወር ደመወዝ እንዱከፍል ብለናል።
ላልች ክፍያዎች ማለትም ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ እስከዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የተጠየቁት የትርፍ ሰዓት እና ህዝባዊ ባዕላት ክፍያዎች ግን በስር ፍርድ ቤት በማስረጃ ያልተጣሩ በመሆኑ የወረዲው ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮና በማስረጃ አጣርቶ ተገቢውን ሉወሰን ይገባል በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።ይፃፍ።
ብር 518.00 የዲኝነት ገንዘብ አመልካች ለተጠሪ ሉተኩ አይገባም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.